Sunday, March 31, 2013

የኢህአዴግ እብሪትና ትዕቢት አገርንና ህዝብን የሚያጠፋ ነው”


የኢህአዴግ እብሪትና ትዕቢት አገርንና ህዝብን የሚያጠፋ ነው”

አቶ ግርማ በቀለ 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ

የዛሬው እንግዳችን አቶ ግርማ በቀለ ይባላሉ ፡፡ አቶ ግርማ በቀለ በቅርቡ የትብብር ሠነድ የተፈራረሙት 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ እና የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት /ኦህዴህ/የተባለ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡-  ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች አሁን በምን እንቅስቃሴ ላይ ናቸው?
Ato Girma Bekele opposition politician based in Ethiopia
አቶ ግርማ በቀለ 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ
አቶ ግርማ፡- የፔቲሽን ፊርማው ወደ ትብብር ሠነድ ከተሸጋገረ በኃላ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ የቀጣይ 6 ወራት ተግባር እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ትብብሩን ለሚቀጥለው 6 ወራት የሚመራ ቋሚ አስተባባሪ ኮሚቴ ለማስመረጥ በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ እስከ አሁን ድረስ ስንቀሳቀስ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ ከውስጥም ከውጪም የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቋቋም እዚህ ደርሰናል፡፡ አሁን የደረስንበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ትብብሩ ስስ ነው፤ ትንሽ ቆይተው አለመግባብት ይፈጥራሉ፤ሁሉም አብረው አይዘልቁም የሚሉ ወገኖች አሉና እርስዎ ምን ይላሉ?
አቶ ግርማ፡- የማራቶን ውድድር አብረው የጀመሩ ሁሉ አይጨርሱም፡፡ እጅግ ውስብስብና ፈታኝ በሆነ ሠላማዊ ትግል አብሮ የጀመረ ሁሉ አብሮ ይጨርሰሳል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ትግሉ እየጠራና እየገፋ በሄደ ቁጥር እየተራገፈና እየተንጠባጠበ ሊቀር ይችላል፡፡ እስከ አሁን በይፋ ለቅቄአለሁ ብሎ በይፋ መግለጫ የሰጠ ፓርቲ ባይኖርም በተግባር ግን እስአሁን አምስት ድርጅቶች ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል፡፡ ነገ ሌላ ሊቀጥል ይችላል፡፡ 15 ወይም 20 ፓርቲ ነጥሮ ቢወጣ አያስገርምም ቁምነገሩ ቁጥሩ ላይ አይደለም ዋናው ቁም ነገር ፓርቲዎቹ ሕዝብና አገር የሚፈልገውን ተግባር እያከናወኑ ናቸው ወይ? የሚለው ነው፡፡ ከህዝብ የሚጠበቀው አመራሩን በቅርብ መከታተለና መቆጣጠር ነው፡፡ ድክመቶችንና ችግሮቹን ብቻ እየነቀሱ በማውጣት መተቸት ሳይሆን እኔንም ያገባኛል ብሎ ከትግሉ መቀላቀል ያስፈልጋል፡፡

ሳዑዲና ዓባይ ምን አገናኛቸው?


ሳዑዲና ዓባይ ምን አገናኛቸው?

Source:-  Fitih le Ethiopia
በዘሪሁን አበበ ይግዛው
ሳዑዲ ዓረቢያንና አፍሪካን (ዓባይን) የከፈለውን ቀይ ባህርን ስናስብ እንዴት ሳዑዲ ዓረቢያ ከዓባይ ጋር ልትያያዝ የምትችለው ብለን ላናስብ እንችላለን፡፡ ምንም ዓይነት መቀራረብም ሆነ ጉርብትና የላቸውም፡፡ የሰውየውን መልዕክት አዘል ንግግር ስናስብ ደግሞ ሳዑዲ ዓረቢያ ለግብፅና ለሱዳን ጠበቃ ለመቆም የተናገረችው ሊመስለን ይችላል፡፡ ይህንንም ከተለያዩ መላምቶችና ምክንያቶች ብለን ከምናስባቸው ጉዳዮች እየተነሳን ልናትት እንችላለን፡፡Abay fallsሆኖም ግን የዓባይ ውኃ ፖለቲካን ጠለቅ ብለን ስንመረምር የምናገኘው እውነት ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድም በሌላም መልኩ በዓባይ ውኃ ፖለቲካ ውስጥ እጇን ለማስገባት መፈለጓን እንረዳለን፡፡ ይህንም ከኢትዮጵያው ባሮ (ጋምቤላ) በተከዜ አትባራ (ፖርት ሱዳን) እስከ ቶሽካ ፕሮጀክቶች እንደሚከተለው እንቃኛለን፡፡
ሳዑዲ ስታር የማንና ለማን ነው?

Ethiopia: EPRDF, no identity and no vision


FOR  IMMEDIATE  RELEASE
March 28 2013
For the past twenty one years, the Tigray People Liberation Front (TPLF) that has no mandate to rule Ethiopia hasGinbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy actually ruled Ethiopia with iron fist dashing on the  Trojan horse,  the  EPRDF ( Ethiopian People Revolutionary Democratic Front).  The EPRDF, a political front; composed of a hodgepodge of ethnically assembled organizations, is a hollow group of ethnic demagogues created by its late leader to materialize his lifelong dream of dividing Ethiopia along ethnic lines. Ironically, the EPRDF that blatantly boasts to have averted the disintegration of Ethiopia, firmly stood up to the dreams of its creator and augmented the fragmentation of Ethiopia, the very country it calls home.
On Saturday March 23, 2013, the EPRDF started its 9th and possibly what could be its last congress with an embarrassing; and to the vast majority of Ethiopians with a pointless theme of – “The Thoughts of Meles”.  In fact, if there is one good cause served by the 9th EPRDF congress, it should be that, the Trojan horse EPRDF proved to the Ethiopian people that it is a party in existence with a borrowed identity that rules over a nation of ninety million people with a dead vision of a deceased man. The EPRDF is a party that lives in the past, failed to cease the moment and has no vision for the future.
The four-day congress that ended on Tuesday c

Saturday, March 30, 2013

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ


የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት  የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡNews, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy. የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።

Thursday, March 21, 2013

ህጻናት እየራባቸው መማር አቅቷቸዋል!


ህጻናት እየራባቸው መማር አቅቷቸዋል!

"ምሳ ያላቸው ሲበሉ እኔ የቤት ስራ እሰራለሁ"
students in addis


ህጻናት እየራባቸው ትምህርት መማር እንዳቃታቸው ሸገር አዲስ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው መምህራንና ተማሪዎች ተናገሩ። ሸገር ያነጋገራቸው ተማሪዎች በየተራ እንደተናገሩት በምግብ ችግር ትምህርታቸውን መከታተልና ክፍል ውስጥ ትኩረት ማድረግ ተስኗቸዋል።
“ሌሎች ምሳ ያላቸው ምሳ ሲበሉ እኔ የቤት ስራ እሰራለሁ። ወይም ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ” በማለት አንድ ተማሪ ሲናገር፣ ሌላኛው ምሳ የሚባል ነገር እንደማያውቅ ገልጿል። በርሃብ ምክንያት ትምህርታቸውን በወጉ መከታተል ያልቻሉ ተማሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው መምህራኑ ሲናገሩ ሸገር አስደምጧል። በሰሙት ዜና ረፍት ያጡ በርካታ ወገኖች ስልክ በመደወል ተማሪዎቹ በትምህርት ቤታቸው ውስጥ የምሳ አገልግሎት እንዲያገኙ የበኩላቸውን ለማድረግ ሲነጋገሩና ቃል ሲገቡ ለመስማት ተችሏል።

ህወሓት ስለምን ሰልፉን ለመከልከል ፈለገ?


ህወሓት ስለምን ሰልፉን ለመከልከል ፈለገ?

ግራዚያኒ የሚቆመውን መታሰቢያ ሃውልት በመቃወም በአዲስ አበባ ከሚደረገው ሰልፍ ጋር በተያያዘ ህውሓት ያደርጋል ብየ የወሰድኳቸውን ግምቶችን ውጨ በ”ምን ያደርግ ይሆን?” ስሜት ስጠባበቅ ነበር። ዛሬ ጊዜው ደርሶ የሆነውን ሰማን። ስለ እውነት ለመናገር የህወሃት መራሹ መንግስት ሰልፉን ሳያስተጓጉል ቢፈቅድ ኖሮ ብዙ ጊዜ ህወሓት ተለክፎበታል የምለውን የበታችነት ስነ-ልቦና ልክፍት ትክክለኛነት ራሴን ለመጠየቅ እጀምር ነበር። ሰማያዊፓርቲ ከሌሎች ከባለራዕይ ወጣቶች እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር የጠራውን ሰልፍ የህወሃትን ስነ-ልቦና በእጂጉ የሚያደማ እንደሆነ ግልጽ ነበር ለኔ። የተቃውሞ ሰልፉ ከፖለቲካዊ ፋይዳው ይልቅ ስነ-ልቦናዊ ፋይዳው የህወሃትን ሂሊና
qeylebash
 እንደሚበጫቀጭው ግልጽ ነበር ለኔ። ይሄ ጉዳይ በ”ባለራዕዮ” መሪ “ራዕይ” ላይ የተቃጣ ጥቃትም ሊሆን ይችላል- ለሕወሓት (በትክክል ወይንም በስህትተ)። ሰልፉ እንድምታው በደንብ ከተጤነ ህወሓትን እንደፖለቲካ ቡድን የሚያሳንስ ስልፍ ነበር። እኛ (ከህወሓት ወገን ያልሆነው) በየካትቲ ወር በሶስት ቀን አዲስ አበባ ላይ ብቻ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተሰውተውብናል- ዛሬ ለተቃውሞ በተወጣበት ግለሰብ ምክንያት– በዋነኛነት ምክንያቱ የልግዛ አልገዛም ቢሆንም። ህወሓት ደሞ ጀግና ነኝ እያለ ወደ ላይ የሚዘልበት ጉዳይ በ17 ዓመት ከደርግ መንግስት ጋር ባደረኩት ትግል 60 000 የትግራይ ልጆች ሰውቻለሁ እያለ ነው።

Saturday, March 16, 2013

በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ



ቴዎድሮስ አረጋ
ቁጥራቸው በግምት ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የኢትዮጵያ መንግስት ያለዓግባብ አስሮ እያንገላታቸው የሚገኙትን የሃይማኖት መሪዎቻቸውንና እንዲሁም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በአስቸኳይ እንዲፈታ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ከቀትር ሰዓት በኋላ እዚህ ስቶክሆልም ከተማ በሚከኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፊትለፊት አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩ ሙስሊም ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን እንግልት፡ዝርፊያ እና ህገወጥ ብርበራ በአስቸኳይ እንዲቆም የጠየቁ ሲሆን መንግስት በዩኒቨርሲቲና በሌሎችም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በመማር ላይ በሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውን ላይ እያደረሰ ያለውን ማዋከብና ማስፈራራት ከትምህርታቸው እያፈናቀለ ያለውን አፓርታዳዊ ተግባር እንዲያቆም ጠይቀዋል።
በእለቱ የእስልምና እና የክርስትና መሪዎች በየተራ ንግግር ያሰሙ ሲሆን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በእስልምናና በኦርቶዶክ ቤ/ክ ሃይማኖቶች ላይ እያደረገ ያለውን ጣልቃ ገብነት በማውገዝ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳስበዋል። ከዚህ በተጨማሪም የተቋውሞ ሰልፈኞቹ የጸረአሸባሪነት ህግ ከለላ በማድረግ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች፡የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ በአንድ ድምጽ ጠይቀዋል።

በሚዲያ መረሳት ያስፈራል



“ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”
the meeting


“ከምድር በታች ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰሩትን በቀን ለ10 ደቂቃ እናያቸዋልን። ልብ የሚነካ ነው። የብርሃን ማነስ አይናቸውን እንደጎዳቸው ያስታውቃሉ … ሴቶችን በተገኘው ሰበብ ያስሯቸዋል። ምክንያት ፈልገው እስር ቤት ይከቷቸዋል። ከዚያም ይደፍሯቸዋል። በርካታ የተደፈሩ እህቶች አሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግሥት ያሰማራቸው ሚሊሻዎች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት እንደፈጸሙ ተነግሮናል” ይህ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ፣ ችግሩ ባለበት ቦታ ተገኝቶ የነበረው ስዊድናዊ የፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ማርቲን ካርል ሻቢዬ ቃል ነው።
ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት መስማት ይጨንቃል። ሰዎች በሲቃ የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ለጆሮ  የተለመደ ነው። ከመሬት በታች የጨለማ ክፍል አለ። በዚህ መታጎሪያ ውስጥ ሆነው ስቃይ የሚፈራረቅባቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ማዕከላዊ ብዙ ጉድ ያለበት ሲኦል ነው። የሰው ልጆች በግፍ ማቅቀውበታል። እየማቀቁበትም ነው። ለውጥ እስከሌለ ድረስ የሚቆም አይመስልም። በመሃላ የሚነገርለት ውርስና ይቀጥላል የሚባለው የመለስ ራዕይ አንዱ ክፍል ይህ ነው።
መጋቢት 3፤2005 (3/12/2013) በኖርዌይ ኦስሎ የሥነጽሁፍ ቤት (ሊትሬቸር ሀውስ) በተዘጋጀ የመወያያ መድረክ ላይ ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር። መድረኩን ያዘጋጀው ደግሞ NOAS በሚል ስያሜ የሚታወቀው የስደተኞች ተሟጋች ድርጅት ነው። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አን-ማግሬት ኦስቴና ሁለቱን እንግዶች ካስተዋወቁ በኋላ መድረኩን እየመሩ ውይይቱ ተካሄደ። በዚህ ውይይት ላይ ሁለቱ ጋዜጠኞች እየተፈራረቁ የደረሰባቸውንና በትክክል ያዩትን አስታወቁ።

በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች



የጋምቤላ “አኬልዳማ” እየተደረሰ ነው
crime scene 1



በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊት ከጨፈጨፋቸው ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ ለማጣራት ከአሜሪካ መንግስት የተላኩት የፎረንሲክ (ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉ) ባለሙያዎችን ጋምቤላ ገብተው የማጣራት ሥራ ጀምረዋል። “የጋምቤላ አኬልዳማ” እየተዘጋጀ እንደሆነም ተሰማ።
የጎልጉል የጋምቤላ መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጋምቤላ የደረሱት የአሜሪካ ዜጎች የሄዱበትን ጉዳይ ለማከናወን ከክልሉና ከመከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ዘንድ እክል ገጥሟቸው ነበር።
(ፎቶው የማሳያ ነው)
የፎረንሲክ ባለሙያዎቹ የዜጋቸውን አሟሟት መንስኤና የጉዳት መጠን ለማጣራት ጋምቤላ እንደደረሱ አስከሬኑ በስውር የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ እንደሚፈልጉ፣ አስከሬኑ ላይ የዲኤንኤ ምርመራ በማካሄድ የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ፣ የጉዳቱን መጠንና በምን ያህል ጥይት እንደተደበደበ ለማጣራት፣ ከዚያም በላይ ለምርመራ ስራቸው ይረዳቸው ዘንድ የሚፈልጉትን መረጃ ለመሰብሰብ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ መሄድ እንደሚፈልጉ ጠይቀው እንደነበር ለክልሉ መንግስት ቅርብ የሆኑ ለጎልጉል ገልጸዋል።
ጥያቄውን መቀበል የተሳናቸው የመከላከያና የክልሉ ባለስልጣናት አስከሬኑ መመርመር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን፣ ከተቀበረ የቆየ በመሆኑ ለማውጣት አስቸጋሪ እንደሆነና እንደማይቻል ለመርማሪዎቹ ገልጸው ነበር። “ስራው የኛ ነው” ያሉት መርማሪዎቹ አስከሬኑ በየትኛውም ደረጃ ላይ ቢገኝም ማየት እንደሚፈልጉ፣ ይህ አቋም እንደማይቀየር መሆኑን አመልክተው አስከሬኑ የተቀበረበት ቦታ ደርሰው የሚፈልጉትን ምርመራ ማድረጋቸው ታውቋል። አከራካሪ የነበረውና ግድያው የተፈጸመበት ቦታ የመጓዙ ጉዳይ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጭ፣ የቀረበው መልስ አስገራሚ እንደነበር ይገልጻሉ።
“ቦታው ላይ ደም የለም፣ ማንንም አታገኙም፣ ምን ያደርግላችኋል?” የሚሉ መከራከሪያዎችን ባለሥልጣናቱ  ቢያቀርቡም ተቀባይነት ማግኘት አልቻሉም። አጣሪዎቹ ወደ ስፍራው ከመሄዳቸው በፊት ካድሬዎች ሽማግሌዎችንና ያካባቢው ነዋሪዎችን በማባበል የቅስቀሳና ፊልም የማዘጋጀት ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የጎልጉል ምንጮች አመልክተዋል።

Tuesday, March 5, 2013

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!


ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)
ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡

ከኬኒያው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ምን እንማራለን?


በታምሩ ገዳ (tamgeda@gmail.com)

East Arican Kenya election 2013
ለውጥ ፈላጊ ኬንያዊያን መራጮች ደምጽ ለመሰጠት ተራቸውን ሲጠባበቁ
ህዝባዊ  ምርጫዎች  በመጡ ቁጥር ስልጣኑን እነማን ይርከባሉ? ምርጫው ምን አዲስ  ነገር ይፈጥርልን ይሆን? ምርጫው ሰላም ወይም  አለመረጋጋት … ወዘተ ይቀሰቀስ ይሆን? የሚሉ መሰል  ጥያቄዎች በበርካታ መራጮች  አይምሮ ውስጥ መመላለሱ የተለመደ ነው፡፡
ከአምስት አመት (2007\2008 እ ኤ አ) በፊት ተካሄዶ  በነበረው  ፕሬዜዳንታዊ  ምርጫ ሳቢያ  ከ1300 በላይ ዜጎቿን ያጣች ፡ከ600ሺህ በላይ ዜጎቿ የተፈናቀሉባት  እና   በቤሊዮኖች  የአሜሪካ ዶላሮች  የሚገመቱ ንብረቶች  የወደሙባት  ጎረቤት አገር  ኬኒያ  በያዝነው  የፈረንጆቹ መጋቢት 4 2013 እኤአ ፕሬዜዳንታዊ  ምርጫ አድርጋለች፡፡ ከአንድ  ሳምንት በፊት በጋዜጠኞች አዘጋጅነት  ስምንት እጩ ፕሬዜዳንታዊ  ተመራጮች  ባደረጉት  3 ሰአት  የፈጀ የመጀመሪያው ዙር  ክርክር  በ34  ራዲዮኖች  እና  ስምንት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች  በቀጥታ ተተላልፋል፡፡ ይህ ከትምህርት  ፖሊሲ  አንስቶ  እስከ የዘር ማጥፋት  ወንጀል  ክስ  ድረስ  ያካተተው  ክርክር  ከ40ሚሊዮን  በላይ የሚገመተው  የኬኒያ  ህዝብን  ቀልብ ከመሳብ አልፎ አለማቀፋዊ  ትኩርትን  መሳቡ አልቀረም፡፡

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል



“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” -- እነ ስብሃት ነጋ
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” -- እነ አባይ ወልዱና አዜብ
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም« መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?»ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን«  የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል። (ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል - ያለን መረጃ እየሩሳሌም አርአያ ካቀረበችው ዘገባ እጅጉን የተለየ ነው። እንደኛ እምነት ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከአልሞትኩም ባይ ተጋዳይነት አልፎ በነ አዜብና በረከት የሚመራውን አዲስ እና እየተጠናከረ ያለውን ጉልበተኛ ቡድን የሚፈታተን ምንም አይነት ኃይል የለውም።)
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
February 27, 2013

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ



የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው
fisherman


የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ



የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (http://www.goolgule.com/)
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።
Gambella
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።

Friday, March 1, 2013

ሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

 
“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ
 
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር!

 
ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ
tigist gebre
“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ” አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው “አቧራው ጨሰ” የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። “ህጻን እናሳድጋለን” እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት የህጻናትን ደም የሚጠጡ “አንቱ” የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር …
በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም። ቀሪው ተግባር “ሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል ወይም ክፈይ” የሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።