Friday, May 31, 2013
ጥቁር ለባሾችን እናመሰግናለን! (ሰማያዊ ፖርቲ)
ሰማያዊ ፖርቲ ከግንቦት 15 እስከ 17 ጥቁር አልባሳት በመልበስ እንዲሁም ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊትለፊት የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወስ ነው፡፡ በነዚህ ቀናት ጥቁር አልባሳት በመልበስ ፓርቲው ላደረገው ጥሪ ህዝቡ ያደረገው ተሣትፎ የሚደነቅ ነው፡፡
በመሆኑም ይህ የህዝብ ተሣትፎ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን በመጪው እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በሚካሄደው ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሠልፍ ጥቁር አልባሳት መልበስ አስገዳጅ ያለመሆኑ እና ማንኛውም አልባስት መልበስ የሚቻል መሆኑን እየገለጽን በዕለቱ የተቃውሞውን ሠልፍ ደማቅ ለማድረግ ከሠልፉ ዓላማ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን የተለያዩ መፈክሮችና መልዕክት አስተላላፊ ነገሮች በቡድንና በተናጥል በመስራት እና በማዘጋጀት በዕለቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሃላፊቱን እንዲወጣ ፓርቲው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
Thursday, May 30, 2013
የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን (SMNE) በኅብረት ስራ ጀመሩ! ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ
በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተየአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።
(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወር ጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።
Wednesday, May 29, 2013
ኢህአዴግ የሚያሸንፈው መቼ ነው?
- ጌታቸው ሽፈራው
መቼም ይህን ጥያቄ ስጠይቅ የግንቦት 20ን ‹‹ድል››፣ የ2002ና የባለፈውን ሚያዚያ 2005 ዓ/ም የቀበሌ፣ የወረዳ……ምርጫም ጨምሮ በመከራከሪያነት በማንሳት ምን ነካው ኢህአዴግ እኮ እያሸነፈ ነው የሚሉ አይጠፋም፡፡ ለእኔ ማሸነፍ ማለት የህዝብን ልብና አዕምሮ (hearts and minds) መያዝ ሲቻል ነው፡፡ በሀይልማ ከሆነ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ በአጠቃላይ ቀኝ ገዥዎቹ አፍሪካውያንን በወታደራዊ ሀይልና በሌሎች አቅሞቻቸው በመብለጣቸው እስከ መቶ አመት ድረስ ገዝተዋል፡፡ በኤሲያን ደቡብ አሜሪካ ደግሞ ከ200 እስከ 800 አመትም የተገዙ ህዝቦች ነበሩ፡፡ ለጊዜው አሸናፊ የመሰሉት ቅኝ ገዥዎች የእነዚህን ህዝቦች ልብ መግዛት ባለመቻላቸው ጊዜ ጠብቀውም ቢሆን ተሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ ኢህአዴግ አሸነፍኩት የሚለውን የመንግስቱ ሀይለማሪያም ደርግ ጨምሮ ህዝባቸውን በሀይል ጨምድደው የኖሩ ስርዓቶች የኋላ ኋላ ተሸንፈዋል፡፡ እነዚህ አካላት የተሸነፉት ህዝብን በሀይል እንጂ በሀሳብ ማሳመን ባለመቻላቸው ነው፡፡ ሰውን በሆዱ አሊያም በግድ ለዘላለም መግዛት አይቻልም፡፡ አንድም የሚፈልገው ነገር በየጊዜው ስለሚጨምር ይህን በየጊዜው የሚጨምርን ነገር ማሟላት አይቻልም፡፡ ማሟላት ቢቻል እንኳ ሰው የመጨረሻ ፍላጎቱ ነጻነት ነውና ዳቦ ጠግቦም ሆነ ሳይጠግብ ነጻነቱን መጠየቁን አያቆምም፡፡
ማንዴላ በመጨረሻዋ የፍርድ ቀን ለዘረኞች ያለው
ሉሉ ከበደ
ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ስር ያዋላት የትግራይ ዱር አራዊት ቡድን ዛሬ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየጫነ ያለውን የአፓርታይድ አይነት ስራት እነ ኒልሰን ማንዴላ ከደቡብ አፍሪካ ምድር ከስሩ መንግለው ለመጣል እጅግ ብዙ መስዋእትነትና ምእተ አመት የሚጠጋ ጊዜ ነበር የወሰደባቸው።

ምእራቡም ሆነ ምስራቁ አለም ለአፍሪካውያኑ የነጻነት ትግል ፈጥኖ እውቅናና ድጋፍ አለመስጠቱና በተለይ ምእራቡ ከነጮቹ ጋር ተመሳጥሮ በተዘዋዋሪ እነሱን መደገፉ ትግሉ ረጅም ጊዜ እንዲወስድና የነጻነቱም ቀን እንዲርቅ ቢያደርገውም፤ በትግሉ መሪዎች ፍጹም ቆራጥነትና ለሞት መዘጋጀት እንዲሁም በህዝቡ አንድነትና ጽናት አፓርታይድ ተወግዶ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ መሪ መሾምና መሻር ችሏል በነጻነት።
የኢትዮጵያ ትንሣኤ! (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ: ፕሬዚደንት ንኩሩማ ሃዉልት
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (ኦ ኤ ዩ) የአፍሪካ ሕብረት (ኤ ዩ በየአፍሪካ አንድነትን የተካው) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ የወርቅ ኢዩቤልዩውን በማክበር ላይ ነው፡፡ በሜይ 1963 አፍሪካ አንድነት ሲመሰረት፤የጋናው ፕሬዜዳንት ክዋሚ ንኩርማ የመዝጊያ ንግግሩን የደመደመበት በተለይ በእድገት ላይ ያለችውንና ተቀኚ የነበሩትን የአፍሪካ ሃገራት ወደ ነጻነት ለመራችው ኢትዮጵያ ለክብሯ በመረጠውና ባዘጋጀው ግጥሙ ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አስመልክቶ ንኩሩማ ሲናገር: ‹‹ግርማዊ ሆይ! በጓደኞቼና በራሴ ስም የሚቀረኝ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ በተለይም ለግረማዊነትዎ ያለኝን አክብሮት በመግለጽ በዚህች ታሪካዊ ሃገር ባደረግነው ቆይታ የተቸረንን አቀባበልና መስተንግዶ ሳላመሰግን ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ንኩሩማህ ዘወትር ባነበብኩት ጊዜ ትውስታ የሚያጭርብኝን ይህን የግጥሙን ስንኝ አሰማ፡፡ የራሱ የንኩሩማህ ቃላት እነዚህ ናቸው፡፡
Tuesday, May 28, 2013
ይህ በደል እና ግፍ አይመለከተኝም ብሎ የቀረ ቀረበት!!! (አቶ ይድነቃቸው ከበደ)
1ኛ.ኢትዮጵያ ሀገራችን የብዙ ሺህ ዓመት አኩሪ ታሪክ ያላት እና የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገርባት ፣ህዝቦ የቋንቋ ልዩነት ሳይገድበው አንዱ ከሌላው የተዋለደ፤ እጅግ ውብ እና ማራኪ ቋንቋ ፣ብህል ፣ልምድ፣ ወግ ፣አለባበስ እና አመጋገብ ወዘተ… የሚታይባት ድንቅ ሃገራችን ናት፡፡ ይሁን እንጂ የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ለዚያውም በ21ኛ ክፍለ ዘመን አንድ ከሚያደርገን ኢትዮጵያዊነት በላይ የምንናገረው ቋንቋ እና የተወለድንበት አካባቢ መሠረት ያደረገ ጠባብ ጎሰኝነት ጎልበት እንዲኖረው ለማድረግ እየሞከረነው፡፡ ከዚህም በላይ በጎሣ መከፋፋሉ ሲያስቆጨን ይበስ ብሎ እናተ ከዚህ ቦታ ለቃችሁ ሂዱ! ይህ የእናንተ ቦታ አይደለም በማለት ዜጎችን ማፈናቀል፣ መግደል ፣ሀብት ንበረት ማውደሙ እና ዘረኝነትን ማስፋፋቱ ያላስቆጨው ያላንገበገበው ማነው ? ይህን ቁጭቱን እና በደሉን መግለፅ የማይፈልግ ማነው?
የኢህአዴግ የታሪክ ሽሚያ አሁንም ቀጥሏል፡፡ (አቶ ጌታቸው ሸፈራው)
የኢህአዴግ የታሪክ ሽሚያ አሁንም ቀጥሏል፡፡ (አቶ ጌታቸው ሸፈራው)


መቼስ ቢሆን አቶ መለስ በጊዜው ባይኖሩም ጣሊያን ኤርትራን ቆርጦ ባስቀረበት ጦርነት የመሪያችን አያት ከጣሊያኖች ጎን ሆነው መዋጋታቸው ከብሄር ጥያቄው በተሻለ ከአቶ መለስ ታሪክ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኖረዋልና በአድዋ ጉዳይ መጽሐፍ ቢጻፍበት የሚያስገርም አይሆንም፡፡ የአቶ አስረስ የልጅ ልጅ ደግሞ ይችውን ኤርትራን ‹‹የኤርትራ ህዝብ ከየት ወደ የት?›› በሚል ‹‹የአብዮታዊ ዴሞክራሲ›› መጽሐፍ አጋዥነት ዳግም ከኢትዮጵያ እንድትለይ አድርገዋል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ‹‹ሌጋሲ›› ማለት! ያውም አቶ ኃይለማሪያም አስቀጥለዋለሁ እንደሚሉት የ‹‹ባዳ›› ሳይሆን የአያት!
አሁንም የኢህዴግ የታሪክ ሽሚያ ቀጥሏል፡፡ የአባይ ግድብ የኢህአዴግ ግድብ አይደለም፡፡ እነ አቶ ተመስገን ዘውዴ ለግድቡ ግንባታ 300 ሺህ ብር በላይ የሰጡት ግድቡ ፖለቲካ ድንበር የማይለየው የኢትዮጵያውያን ግድብ በመሆኑ ነው፡፡ ኢህአዴጎችማ ይህ ግድብ ከመገደቡ 20 አመት (ከዚያም አለፍ ብሎ) ጀምረው ሁለት ሶስት ግድብ የሚያስገድብ ገንዘብ ሲዘርፉ ኖረዋል፡፡ በየ አስር አመቱ በሙስና ስም የሚመዘዘው ካርድ ዋናው ምክንያቱ ሙስና አይሁን እንጅ ስርዓቱ ውስጥ ያለውን የሙስና ናሙና ግን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ እናም ያለፉትን ባልስቴራ በወርቅ የተቀየረባቸው፣ ኢትዮጵያውያን በቁም የተዘረፉበትና ታጋይ ባለሀብት የሆኑበትን 22 ድፍን የሙስና አመታት ለማድመቅ የአባይን ወንዝ ውሃ በግንቦት 20 ቀን አቅጣጫውን እንዲቀይር ተደርጓል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አንድም ስራው ሳያልቅ ለግንቦት 20 በቶሎ እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ ‹‹ባለሙያ›› ተብየዎቹ ይህን ትዕዛዝ አንቀበልም የማለት ሞራል የላቸውም፡፡ እናም እንደማንም እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ አሊያም ከወርና ሁለት ወር በፊት ውሃውን ማስቀየስ እየተቻለ ለግንቦት 20 አቆዩት ተብለው ቁጭ ብለው ሰንብተዋል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም ‹‹የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ››ም ለግንቦት 20 ተብሎ ዘግይቷል፡፡ አሊያም ሳያልቅ ተመርቋል፡፡ ዋናው ትዕዛዙ ከላይ መምጣቱ ነው፡፡ እነዚህ እንግዲህ የግንቦት 20 ፍሬዎች መሆናቸው ነው፡፡ በተለይ የስፖርት አካዳሚው ከፖለቲካው ሸሽቶ በስፖርት የተደበቀውን ወጣት ለመያዝ ያስችላል ተብሎ ነው፡፡ በቀጣይነት በርካቱ ታሪኮች እየተጎተቱ ለግንቦት 20 ማድመቂያዎችና የኢህአዴግ ታሪኮች ተደርገው መቅረባቸው የማይቀር ነው፡፡ ጉዱ ገና እኮ ነው የ30ዎቹንም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ግንቦት 20 ላይ እንመርቃለን እንዳይሉ? ምን ይህ ብቻ ወይዘሮ አዜብ አሊያም ሌላ የአቶ መለስ ቀርብ የነበረ ሰው ‹‹አቶ መለስ የዘመን መለወጫ በዓልን ከግንቦት 20 ጋር ለማድረግ አላማ ነበራቸው›› ብሎ ቢያወራ ‹‹ሌጋሲውን›› ለማስቀጠል የማይደክመው ኢህአዴግ የዘመን መለወጫንም አራት ወር ወደኋላ ጎትቶ ግንቦት 20 ሊያደርገው ይችላል፡፡ እንዲያውም የአቶ መለስን ስብዕና የሚያገንን ፖለቲካዊም ሆነ ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ዶክመንተሪ ተሰርቶለት! ዋናው ይህ ሁሉ ታሪክ ፈራሽ መሆኑ ነው፡፡
አይ ሰው ፈራሹ! አይ ታሪክ ፈራሹ! አይ ኢህአዴግ ፈራሹ!
አባይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መደበቂያ አይሆንም!
አባይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መደበቂያ አይሆንም!
- በስዊትዘርላንድ የሚገኙ የሲቪክ ተቋማት፣ የፖለቲካ ሃይሎችና፣ የዴሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች ግብረ ሃይል የጋራ አቋም መግለጫ
በኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በስልጣን ላይ ያለው ራሱን ወያኔ /ኢህአዴግ ብሎ የሚጠራው ገዢ አምባገነናዊ ቡድን በነዚህ አመታት የፈጸማቸውን እንዲሁም አሁንም እየፈጸማቸው ላሉት ግፎች መደበቂያ ይሆነው ዘንድ አፍራሽ ቀያሽ በሆነው መሃንዲሱ ሟቹ መለስ ዜናዊ አማካይነት የህዝቡን ቀልብ ይስብልኛል ያለውን የአባይ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ከዛሬ ሁለት ዓመት ቀደም ብሎ በሚያዚያ ወር 2003 ማወጁ ይታወሳል፣ በመሰረቱ ግድቡ ጥልቅ ጥናት ያልተደረገበት፣ ከበስተጀርባው ውስብስብና ያልተፈተሹ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና፣ ዲፕሎማሲያዊ ችግሮችን አግተልትሎ የያዘና ይልቁንም በወቅቱ በቱኒዚያ በግብጽና ሌሎች በዓረቡ አለም አካባቢዎች የተነሳውን ህዝባዊ ቁጣና ማእበል እንዳይዛመት ብሎም የህዝብን ቀልብ ለመስረቅ ተብሎ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ አስቀድሞ ያውቀዋል። በመሆኑም የተጠቀሱት አንኳር ችግሮች እንደተጠበቁ ሆነው መሰረታዊ የሆኑትን የህዝቦችን ጥያቄ ሳይመልሱ በአባይ ስም ህዝብን እያጭበረበሩ መኖር አይቻልም።
Monday, May 27, 2013
በኢትዮጵያ የሀይማኖቶች ትስስር እና የህዝቦችዋ አንድነት
በኢትዮጵያ የሀይማኖቶች ትስስር እና የህዝቦችዋ አንድነት
በአቶ መንሱር ሙሐመድ ኑሩ
ታሪክ እንደሚያስረዳን ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለማችን ረጂም ዕድሜ ካስቆተሩ ሀገሮች አንድዋ መሆንዋን ነው፡ ኢትዮጵያ በዚህ ረጂም እድመዋ በጊዜው ከነበሩ ሀገሮች ጋር በንግድ እና በዲፕሎማሲ ከነበራት ግኑኝነት በተጨማሪ ለዐለማችን በርካታ የስልጣኔ መሰረት ከሆኑት ሀገሮች አንድዋ ነች፡ ከነዚህም ስጦታዎች አንዱ እና ዋናው ለዛሬይቱ ዐለማችን ትልቅ ምሳሌነቱ የማያጠያይቅ እና በሀገራቸው በአምባ ገነኖች ጭቆና ምክንያት መኖርላቃታቸው ህዝቦች በዐለም አቀፍ ሕግ መሰረት የጥገኝነት መብት ያስገኘና ከሰው ልጆች መብት መካከል አንዱ የዛሬ 1435 አመታት በፊት ኢትዮጵያ በዐለም ለመጀመሪያ ጊዜ በእምነታቸው ምክንያት ለተጨቆኑ ህዝቦች የሰጠችው የጥገኝነት መብት ነበር፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)
ጥንቃቄ! እባካችሁ ባንተባበር እንኳ አንጠላለፍ!
ጥንቃቄ! እባካችሁ ባንተባበር እንኳ አንጠላለፍ!
አርያ ጌታቸው
ሰማየዊ ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ የሆነ ትኩረትን ሽፋንን በተለያዩ ሚዲያዎች አግኝቱዋል ፡፡ እነዚህን ሽፋኖች ያገኘበትን ምክንያትን ግን አንዳንድ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች “ድርጅቱ የአፍሪካ ህብረትን ስብሰባ ተጥቅሞ በጠራው ሰልፍና እንደማይፈቀድላቸው እያወቁ ለሚዲያ ፍጆታ በማዋላቸው ነው” የሚል እንድምታ በመያዝ የሰልፉን ቀን መራዘምና መተላለፍ እንደ ፖለቲካ ክስረት ቆጥረውታል፡፡ ይህንን ለማስረዳት ፓርቲው ባለፉት አራት ወራት ያደረጋቸውን ጉልህ እንቅስቃሴዎች እና የሚዲያውን ትኩረት ያገኘባቸው ኩነቶች በወፍ በረር ለማየት እንሞክር፡፡

1. የካቲት 3 ቀን 2005 ዓም. በብሔራዊ ትያትር ቤት “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” በሚለው የ ፕ/ር መስፍን መጽሃፍ ዙሪያ ሀገሪቷ ውስጥ ያሉ እውቅ ምሁራንን ጋብዞ ያወያየው (አዳራሹ ሞልቶ ሰዎች መመለሳቸውን እንዳትዘነጉ) ከረጅም ጊዜ በሁዋላ እንዲህ አይነት ትልቅ ህዝባዊ ውይይት ሲደረግ የመጀመሪያው ነው፡፡
2. መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ፡፡ በጊዜው አባላቱና ደጋፊዎቹ ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት አመራሮቹ ቀድመው ቦታው ላይ በመገኘት የሰልፉን ሂደት ለማሰማመር ደፋ ቀና ሲሉ 6 የሰማያዊ ስራ አስፈጻሚ አባላት(ሊቀመንበሩን ጨምሮ) እና ታዋቂ ግለሰቦችን የፓርቲው አባላትን ጨምሮ 34 ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸው ከ 24 ሰዓት በኋላም ፈቷቸዋል፡፡ ይህ ሰላማዊ ሰልፍም አንድነት ፓርቲ ወ/ሪት ብርቱካን ታስራ በነበረበት ወቅት ከተደረገው ሰልፍ በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ)
3. ፓርቲው በዋቢ ሸበሌ ሊያደርገው የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ እና የኢህአዴግን ውንብድናን ያጋለጠበት ቪዲዮና የሶሻል ሚዲያዎች ሽፋን፡፡
4. በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው የተመለሱ ዜጎችን ሁኔታ ለመመልከት የተጓዙት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ይዘውት የተመለሱት ማስረጃ እና በወቅቱ የፓርቲው አመራሮች ለሰኣታት በክልሉ የታጠቁ ኋይሎች መታሰራቸው፡፡
እንዲሁም ፓርቲው በየጊዜው በጽ/ቤቱ የሚያደርጋቸው ውይይቶችና እንቅስቃሴዎች ማለትም ከየካቲት – ግንቦት ባሉት አራት ወራቶች በብዙ ሰዎች እና ሚዲያዎች አይን እንዲገባ አድርጎታል፡፡በነዚህ ሂደቶች ውስጥ አነጋጋሪ ከነበሩት አንኳር ሀሳቦች ውስጥ፤ በአብዛኛው በወጣቶችና በሴቶች ዙርያ መመስረቱ፣ የበርካታ አንጋፋ ምሁራን ይሁንታ ድጋፍ ከጀርባ መኖሩ በተለይ (እንደ ፕ/ር መስፍን፣ ፕ/ር በፍቀዱ፣ ዶ/ር ያዕቆብ፣ ዶ/ር ዳኛቸው፣ ፕ/ር ገብሩ እና አርቲስት ደበበ …)፣ የአመራሮቹ ቁርጠኝነትና በሚኖሩት ማናቸውም ፕሮግራሞች ላይ ግምባር ላይ መገኘታቸውና ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ወደኋላ አለማለታቸው… የመሳሰሉት አንኳር ነጥቦች ጋር የሰሞኑ በግንቦት 17 ቀን የጠሩት ታላቅ ሰልፍ የድርጅቱን ጅማሮ (ጅማሮ ያልኩት ፓርቲው ከተመሰረተ 1አመት ከ6 ወር ብቻ እንደሆነው ለማመልከት ነው) በማየት በሀገር ውስጥ ያለውን የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለወደፊቱም ተስፋ በማድረግ ጭምር ነው፡፡
ፓርቲው በግንቦት 17 ለጠራው ሰልፍ ያስቀመጠው ምክንያት ፓርቲው ከዚህ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ ለመንግስት አቅርቦ መልስ የተነፈጋቸውን ጥያቄዎች
1. ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን እንዲቆም
2. የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ
3. የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ
4. መንግስት የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን መቆጣጠር አለመቻሉ
ከላይ ያሉትን ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ መፈለግ የሚል ነበር፡፡ ይህንንም ሰልፍ ለማድረግ ከመንግስት ምንም እንኳ ፈቃድ ባያስፈልገውም ማሳወቅ ይጠበቅበት ነበር፡፡ ህጉም በሚያዘው መሰረት ከ48 ሰዓት በፊት ቢያስገቡም የመስተዳድሩ ሃላፊዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በእማኞች ፊት ደብዳቤውን ጠረጴዛ ላይ ትተውት የሰልፉን ዝግጅት ቀጠሉ፡፡ እዚህ ላይ “ማሳወቅ” የሚለው ጉደይ የገባው ዜጎች ተቃውሟቸውን በሚገልጹበት ወቅት ከተቃራኒ ወገን ጥቃት እንዳይደርስባቸው እና ሰልፉ ወዳልታሰበ ረብሻ እንዳያመራ ጥበቃ ወይም ከለላ ለማግኘት እንዲሁም የትራፊክ ስርዓቱን ለማስተካከከል ለመሳሰሉት ጥንቃቄዎች ሲባል ብቻ እንጂ ሰልፍ ማድረግ በራሱ ፈቃድ አያስፈልገውም፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ መስተዳድሩ ያቀረበው ምክንያት እውነትም ይሁን ውሽት የህግ ክፍተቱን በጠቀም ወይም ህጉን ከለላ በማድረግ ሰልፉን ያራዘመበት መንገድ ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አንድ ፖቲካ ተቋም ሊያከብረው የሚገባ ሂደት ከመሆኑም በላይ ፓርቲው መንግስትን ትልቅ ጫና ውስጥ በመክተት ሌሎች ፓርቲዎች የአዳራሽ ውስጥ ስብሰባ ተከለከልን በሚሉበት ወቅት እንዲሁም ፓርቲው ለመስተዳድሩ ያቀረበውን ደብዳቤ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑት አካላቶች፤ የሰላማዊ ሰልፉን ሂደት በመቀበል ደብዳቤ መጻፋቸው (አቤ ቶክቻው እንዳለው ሳይገግሙ) ፓርቲው በመንግስት አካላት ላየ ፈጥሮት የነበረውን ጫና በገሀድ ያሳያል፡፡
ይህ ማለት ግን በራሱ እንደስኬት ሊቆጠር የሚገባው ነው ብዬም አላምንም እንደውም ፓርቲው የበለጠ ትልቅ ውጥረት ውስጥ የሚገባበትና ሀላፊነትን የሚሸከምበት ጊዜ ነው የሚሆነው፡፡ ኢህአዴግ የ 1997 እና 1998 የነበሩትን የሰላማዊ ትግል እና የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪዎች እንዴት አድርጎ እንዳጨናገፋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ኢህአዴግ በባህሪው ብዙ ተለዋዋጭ ስልት የሌለው የዛሬ 20 ዓመትም ዛሬም ባለበት የሚሄድ ድርጅት እንደመሆኑ የፊታችን ግንቦት 25 የሚካሄደው ሰልፍ ላይ ምን አይነት እክል ሊፈጥር ይችላል? የሰማያዊ ፓርቲ ዝግጅትስ ምን ይመስላል? የሚለውን በተግባር በሳምት ጊዜ ውስጥ የሚታይ ይሆናል፡፡
ጥንቃቄ! እባካችሁ ባንተባበር እንኳ አንጠላለፍ!!
ፓርቲው ይህንን ሰልፍ ሲጠራ ከጎኑ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሺቪክ ማኅበራት አብረውት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም በውጭ ከሚገኙ እንደነ አኢጋን በአቶ ኦባንግ የሚመራው፣ የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ካውንስል፣ በኖርዌይ የሚገኘው አዲስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የመሳሰሉ ተቋማት ካልሆኑ በተለይ ሀገር ቤት ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ አለመፈለጋቸው መንገዱ ገና ረጅም መሆኑን ያሳያል፡፡ ሆኖም የየራሳቸው ምክንያት አላቸው ብንል እንኳ ከሰልፉ መራዘም በኋላ ዝምታቸውን በመስበር አንዳንድ ግለሰቦች ነገሩ “የከሸፈ” መሆኑን ለማብሰር ሲሯሯጡ ትንሽ እንኳ ትዝብት ውስጥ እንወድቃለን አለማለታቸው ያሳዝናል፡፡
እባካችሁ ባንተባበር እንኳ አንጠላለፍ !! ይህ ሰልፍ ቁጥሩ ይብዛም ይነስም ከተሳካ አይነጥላችንን የምንገፍበት ነውና ጥቅሙ ለሰማያዊ ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ ትግል እንምናለን ለሚሉ ሀገር ውስጥ ላሉ ፓርቲዎች በሙሉ ስለሆነ ከተቻለ ባለው ጊዜ መተባበር ካልተቻለ እጅን መሰብሰብ እላለሁ!!
ሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል!!!
ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ድርጊቶች፣ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙና የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ለመንግስት አካላት በተለያዩ ጊዚያት ጥሪ ቢያቀርብም ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ጥሪውን ከፍ ባለ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለማሰማት በወሰነው መሰረት ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጥቁር ልብስ በመልበስ እንዲሁም ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ተቃውሞውን ለመግለጽ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚሁም መሰረት ዜጎች በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስ መንግስት በሚፈፅማቸው ሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሳይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አባላቶቻችን ላይ ወከባና እስር ደርሶባቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጋፋት የተፈፀሙ ድርጊቶችን እንቃወማለን፤ የታሰሩትም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ግንቦት 17 ቀን ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊደረግ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ.ም ለሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ ሰልፉ የሚደረግ መሆኑን የማሳወቂያ ደብዳቤ ፓርቲው ቢያደርስም የቢሮው ኃላፊና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤአችንን አንቀበልም ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነቱን ሕገ ወጥ አሰራር በማውገዝ ሰልፉን ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በመግለጫ ለሕዝብና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል፡፡ በመጨረሻም የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ በአዋጁ መሰረት የሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀንና ቦታ እንዲለወጥ በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ሁለታችንም አካላት ባደረግነው ድርድር ሰልፉ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲሆንና የሰልፉ መነሻ ቦታ የፓርቲው ፅ/ቤት መድረሻ ቦታ ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ወይም ጥቁር አንበሳ ዋናው ፖስታ ቤት ፊለፊት እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚሁም መሰረት፡-
1ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተጠቀሱት ጥያቄዎች እንደተጠበቁ መሆናቸውንና የግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም ዋና ዋና ጥያቄዎች መሆናቸውን፣
2ኛ. ለረጅም ጊዜ ያለ ህግ ተነፍገን የቆየነውን ሃሳባችንን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብት በትግላችን ያረጋገጥን በመሆኑ ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍበትና በሰልፉ ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ማሳሰብ ይቻል ዘንድ ሁላችንም የዜግነት ድርሻችንን እንድንወጣና ለሰልፉ መሳካት በምንችለው አቅም ሁሉ አስተዋፅኦ እንድናደርግ ጥሪ የምናቀርብ መሆኑ፣
3ኛ. ሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ሰላማዊ ታቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትና ዜጎች ላደረጋችሁልን ድጋፍ ፓርቲው ምስጋናውን ማቅረብ የሚፈልግ መሆኑንና የፓርቲያችንን ጥሪ ለህዝቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲዳረስ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች ያደረጉት አስተዋፅዖ እጅግ የሚያስደንቅና የሚያስመሰግን መሆኑን ፣
እየገለፅን አሁንም ፓርቲው ያነሳቸው ጥያቄዎች መመለስ አላባቸው ብሎ የሚያምን የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበርና ዜጎች በሰልፉ እንዲሳተፉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
እየገለፅን አሁንም ፓርቲው ያነሳቸው ጥያቄዎች መመለስ አላባቸው ብሎ የሚያምን የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበርና ዜጎች በሰልፉ እንዲሳተፉ ፓርቲያችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም አዲስ አበባ

Saturday, May 25, 2013
የቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያን የዜጎችን መፈናቀል አወገዙ
የቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያን የዜጎችን መፈናቀል አወገዙ
ብሄርን መሰረት ያደረጉ መፈናቀሎችንና ሀይማኖትን መሰረት ያደረጉ ሰብአዊ ግፎችን ለመዋጋትም ቃል ገቡ
በቶሮንቶና አካባቢዋ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያ በተለያየ ስፍራ የሚደረገውን ብሄርን መሰረት ያደረገ መፈናቀልና ሀይማኖትን የዘመረኮዘ የሰብአዊ መብት ገፈፋ በጽኑእ አወገዙ።

ባለፈው እሁድ ሜይ 19 ቀን ብሉር መንገድ ላይ በሚገኘው በትሪኒቲ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን አዳራሽ፤ በሁለቱ ዋና ዋና ሀይማኖት መሪዎች አስተባባሪነት በተደረገው ስብሰባ ላይ፤ ተሰብሳቢዎቹ በያዝነው ግንቦት ወር ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግና ጉዳዩን ለአለም መንግስታት ለማሳወቅም ወስነዋል።
በዚህ፤ ከአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ጀምሮ በሕዝብ እንደራሴነትና በተለያዩ ሀላፊነት ኢትዮጵያን ሲያገለግሉ የቆዩት ሀጂ መሀመድ ሰይድ በምክትል ሊቀመንበርነት፤ እንዲሁም በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ቃል አቀባይ፤ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ፤ በሊ/መንበርነት የሚመሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮችን የያዘው ስብስብ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ የስብስቡ ምክትል ሊ/መ ሀጂ መሀመድ ከህመማቸው እንዲፈወሱ ጸሎት በማድረግ ተጀምሮ፤ ሶስት ሰዓታት ያህል በመምከር፤ በወቅቱ አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳቦችን አሳልፏል።
Friday, May 24, 2013
ሰበር ዜና፣ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ እውቅና ተሰጠው!
ፓርቲው “በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ ለመፈለግ…” በሚል ባስተላለፈው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ያነሳናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ” ሲል አሳስቧል።
Friday, May 10, 2013
ሲጠበቅ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ ዛሬ ተካሄደ
ሲጠበቅ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ ዛሬ ተካሄደ
- ክራንቻ፣ ከደቡብ አፍሪካ
በዛሬው ዕለት የተደረገውን ሰልፍ ለማደናቀፍ የወያኔ መንግስት ጭፍሮች ለዲፕሎማቶች እና ለፖሊስ የሰጡት የሀሰት ውንጀላ በትላንትናው ዕለት ውድቅ ተደርጎ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል።
ተቃዋሚ ሀይሎች የሚያደርጉትን የሰላማዊ ሰለፍ እጅግ የፈራው ወያኔ ሰልፉን የጠሩት አሸባሪዎች ናቸው፣ ከዚህ በፊትም ቴዎድሮስ የሚባለውን የኢትዮጵያ ባለስልጣን በደርባን ርዕሰ ከተማ የጠለፋ ሙከራ ሊያካሂዱበት ነበር የሚልና መሰል የሀሰት ውንጀላዎችን በመደርደር ቢሟገትም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል የደቡብ አፍሪካን ዲሞክራሲያዊ ህገ-መንግስት የሚጻረር ስህተት ላለመፈጸም ሲል የሰላማዊ ሰልፉን ፈቃድ በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰጥቷል።
በመሆኑን ዛሬ አርብ ሜይ 10፣ 2013 ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በጆሀንስበርግ የተሰበሰበው ህዝብ ወደ ፕሪቶሪያ ጉዞውን በማድረግ የስብሰባው ስፍራ ተገኝቶ መልዕክቱን በቃልና በደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ልዑክ እና ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቃል-አቀባይ፣ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ደረጀ አማካኝነት አስረክቧል።
ሌላው በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የተፈጠረ አስገራሚ ነገር ቢኖር፣ የኦጋዴን ተቃዋሚ ሀይሎች በስፍራው በመገኘት “ከወያኔ እንጂ ከኢትዮጵያ ህዝብ የመገንጠል ሀሳብ የለብንም… ወያኔ ይወገድ!” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከ ኦጋዴን ወገኖቻችን መካከል አንዲት እህታችን ይዛ የነበረው መፈክር የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነበር። እንዲህ ይነበባል፣
Abune Petros in our heart
Abune Petros in our heart
On July 29th. 1936 Abune Petros was executed by the Italian fascist that were trying to colonize our country for his refusal to submit. On May 2nd. 2013 the monument that was built to commemorate our Holy Father was removed by the order of the TPLF party that is currently ruling our country. Our Holy Father died for the first time. The murder by a firing squad was an honor and showed his deep love for his people and country. The fascist killed his body but he made his home in every Ethiopian soul for ever and ever. We all carry Abune Petros in our heart. ‘Abune Petros Adebabaye’, ‘Abune Petros Hawelt’ is not just a location but the symbol of our pride and the true meaning of sacrifice for a higher cause.

The order to Kill Abune Petros was given by the fascist Viceroy Graziani but the trigger was pulled by solders from the Northern Ethiopia that were faithfully serving the fascist invader. The order to remove our monument to our beloved father was given by the TPLF party but the backhoe and flatbed truck was driven by modern day Banda’s.
Thursday, May 9, 2013
የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች መሆናቸው ያብቃ!
የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች
(May 3፣ 2013)
አቶ እሰክንድር ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ በሽብርተኛነት የፈጠራ ክስ ውንጀላ በረጅም እሰራት የሚማቅቁትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በቀጣይነት ለማሰቃየት በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰደውን እርምጃ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣በጥብቅ ያወግዛል።

በመላው ዓለም የነፃ ፕሬስ መብት በሚከበርበት ቀን ዋዜማ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ በእውቅ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች ላይ ካሁን በፊት የበታች ፍርድ ቤት ጥሎባቸው የነበረውን ፍርደ ገምድል ብይን እንዲጸናና የስቃይ ዘመናቸው እንዲቀጥል መፍረዱ አገዛዙ ነፃ ፕሬስንና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት ለ21 ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በዚያው አጥፊ ጎዳና እየቀጠለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። የሀገሪቱ የፍትህ አካላትም ይህንኑ እኩይ ተግባር ለማሳካት ሙሉ በሙሉ የአገዛዙ የፖለቲካ መሳሪያ እንደሆኑ መቀጠላቸውን የሚያመለክት ነው።
Wednesday, May 8, 2013
ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ
“በአስመሳይ ስደተኞች ላይ በቂ መረጃ አለ”
ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ
“ክፉን በክፉ መመከት ባያስደስትም ወቅቱ ያስገድደናል” ሲሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል ተናገሩ። አገዛዙን ሸሽተው በተለያዩ አገራት ከለላ አግኝተው በስደት የሚኖሩም ሆኑ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አስጠንቅቀዋል።
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህግ አውጪዎች፣ የጀርመን የኢሚግሬሽን ሃላፊዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች፣ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ሃላፊዎችና ተዛማጅ ሃላፊነት ካላቸው የህግ ክፍሎች፣ በካናዳ በተለያዩ ደረጃ ካሉ ባለስልጣናትና ወትዋቾች (አክቲቪስቶች)፣ በስዊድን አንዲሁም በእንግሊዝ በተመሳሳይ ግንኙነት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አገራቱ የስደት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ለስደት ዳረገን ከሚሉት መንግሥት ጋር በቅርብ እየሰሩ ስላሉ አስመሳይ ስደተኞች አስገራሚ መረጃዎች መሰብሰባቸውን አውቃለሁ” ብለዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)