Monday, December 30, 2013

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ


ሁኔ አቢሲኒያዊ
ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡A mass grave in Addis Ababa, Ethiopia
በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህን ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

Sunday, December 29, 2013

“ነፃ እስክትወጡ በደሌ አትጠጡ” ጃዋር መሀመድ


ሁኔ አቢሲኒያዊ
መቼስ ለአገር የሠራና የደከመ ቢያጠፋም እንኳን የቻለውን ያህል በመሞከሩ በክብር ማኖርና መንከባከብ የውዴታ ግዴታ ነው። የሚያሳዘነኝ ነገር ይሄ ሳይሆን እስካሁን እንዲህ ያለውን ነገር ሰምተንና አይተን ያለማወቃችን ነው ስንት የለፉላትን አገር በእነ መለስ እንዲህ መሆኗን ሳያዩ ማለፋቸው ሳይቀር ዛሬም ድረስ ቢያንስ ስራዎቻቸው በክብር እንደቅርስ አለመያዛቸው ሳያንስ በየጊዜው የሚነሱ የታሪክ ነቃፊዎች የትችታቸው ማሟሻ አድርገዋቸው ማየት ያስዝናል ለዚህም ይመስለኛል አገሪቷ የሠራላትን፣ የደከመላትንና የተቆረቆረላትን ማዋረድ እንጂ ማክበር እንደማታውቅ የሚለፈፈው። በዚያም ተዞረ በዚህ የውዷ ኢትዮጵያ ታሪክ ‘የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ’ በመሆኑ ምንም ማለት ልናዝን አይገባም።Ethiopian singer Teddy Afro, Bedele controversy
ከሰሞኑ ደግሞ እነ ጃዋር መሀመድ ተከታዩን ስብከት ነጻ ሊያወጡት ቃል ገብተውለት ለነበረው ኦሮሞ የኢትዮጵያ ልጆች መንፈሳዊውን ስብከታቸው ጀባ ብለዋል፡፡
የኦሮሞ ህዝብ ገንዘቡን እና ንብረቱን ለእነ ጃዋር መሐመድ ሰጥቶ ነፃ ያወጡናል ብሎ ሲጠብቅ ሰባኪ ወ ኮሜዲያኖቹ እነ ጃዋር እና የኦነግ አባላቶች በደሌ አትጠጡ የሚል ትዕዛዝ እያስተላለፉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ነጻ አውጪዎቹ ይህንን ያሉት ከአልኮል ነጻ የሆነ ትውልድ ለማየት ካላቸው የልብ ፍላጎት እና ሀሳብ ሲሆን በተጨማሪም ዘፈን ስንሰማም እየመረጥን መሆን እንዳለበት መክረዋል፡፡
በእነ ጃዋር ትእዛዝ መሰረት ከውጭ ማለትም ከኦሮሚያ ክልል ውጪ በተለይም በእነ ጃዋር እና መሰሎቹ ቅኝ ገዢ ተብለው ከተመደቡት ክልሎች በተገኙ አርቲስቶች የተዜሙ ዘፈኖችን መስማት የተቀደሱትን እና የተባረኩትን የእነ ጃዋር ስብከቶች የመስሚያ ጊዜ እንደሚሻማ የገለጹ ሲሆን ይህም የኦሮሚያ ህዝብ እርኩስ ሀጢያት እንደፈጸመ ተቆጥሮ በሜንጫ አንገቱን ሊባል እንደሚቻል አስጠንቅቀዋል፡፡
በዲያስፖራም ሆነ አሉ እጅግ የተባረኩ የአለም ቅዱስ ጃዋር መሀመድ በዲያስፖራም ሆነ ሀገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድብቅ አላማ በቅኝ ገዚዎች የተፈጠረች እና ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀውን ሀገር ከኢህአዴግ ነጻ ለማውጣት ስለሆነ ይህንን ድብቅ ኢትዮጵያን ነፃ የማውጣት አላማቸውን ተረድቶ በሜንጫ አንገታቸውን ሊላቸው ይገባል ካሉ በኋላ ኢትዮጵያ ነጻ ከምትወጣ ከእነ ጃዋር ጋር ተመሳሳይ አመለካከት እና አላማ ያለው ወያኔ ኢህአዴግ ከነሙሉ አላማው እና ክብሩ ለዘላለም ይንገስ ብለው ሲያበቁ ብዙዎች ታሪክን የኋሊት ብለው በሰየሙት የታሪክ ቡራኬያቸው ዳግማዊ ምንሊክ የተባሉ ከመቶ አመት በፊት የፈጠሯት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሜንጫውን ማንሳት እንዳለበት ሰብከዋል፡፡
ከጃዋር ስብከት እንውጣና ከስብከቱ መለስ ብሎ ከሰሞኑ በፌስ ቡክ ገጹ ለፈረንጁ ገና አክባሪዎች እንኳን አደረሳቹህ ሲል መልእክቱን አስተላልፏል ይህም ኢትዮጵያውያኑ ከሳውዲ ሲባረሩ የተባረሩት የኢትዮጵያ ልጆችን በመከፋፈል ሙስሊም የኦሮሞ ልጆችን ብቻ የሚመለከት ያደረገ ግለሰብ ለፈረነጆቹ ክርስቲያኖች መልካም ገና ብሎ መልካም ምኞት ማስተላለፍ ምን የሚሉት እብደት እንደሆነ ጃዋር እና መሰሎቹ ብቻ ነው የሚያውቁት እና ፍርዱን ለእነርሱ እንተወው፡፡
በመጨረሻም እነ ጃዋርን የመሳሰሉ ጃዋር ወ መለሶች የወያኔ ተምሳሌቶችን እየሰማን አለማውገዝ እንዲሁም እውነታውን አለማሰየት የታሪክ ተወቃሽ ከማድረጉም በላይ ዝምታችን ትክክል እንደሆኑ እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጃዋርን አላማ በመረዳት ድጋፍ ከመስጠት ሊቆጠብ ይገባል፡፡
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

Genocide or Terrorism? Transnational Advocacy and the Ogaden Conflict


by Terrence Lyons, Associate Professor of Conflict Resolution at George Mason University

Political processes and outcomes within particular nation-states today are significantly impacted by the migrant communities and diasporas of those polities. Understanding contemporary politics therefore requires a perspective that recognizes how political processes and actors increasingly operate both within and across specific territorially defined spaces. The polity often remains defined by a specific identity with attachments to a particular “homeland,” but these communities are now often transnational and characterized by patterns of ongoing migration and movement. 

Diverse political entrepreneurs — including, in some cases, the governments of migrant sending nations — increasingly see diaspora networks as effective instruments to mobilize resources and key constituencies in order to shape political outcomes on a particular issue in a specific state. (For more on transnational politics see the volume I edited with Peter Mandaville, Politics from Afar: Transnational Diasporas and Networks).

Abune Mathias arrested and released




Abune Mathias arrested and released
Ethiopian Review:-The TPLF-installed illegal patriarch in Ethiopia, Abune Mathias, has been temporarily placed under arrest and was released after being interrogated for 72 hours by Tsegaye Berhe, National Security Adviser to the Prime Minister, and other security officials, according to Ethiopian Review sources in Addis Ababa.Leaders of the TPLF junta are apparently upset with statements that have been uttered by Abune Mathias over the past 3 weeks that were critical of the tribal regime. In one particular meeting, Abune Mathias was heard saying that much of the problems facing the church are caused by the ruling party.The Ethiopian Orthodox Church’s
administration in Addis Ababa is currently paralyzed by a growing leadership crisis. Many church leaders are in open revolt and have refused to take orders from the Holy Synod.

Saturday, December 28, 2013

የኦሮሞ ሙስሊሞችን የበላይነትን በኦሮሞ ክርስቲያን ና ኦሮሞ ባልሆኑ ሙስሊሞች ላይ ለመጫን የታለመ ድብቅ አጀንዳ ይፋ ሆነ




aa
ጃዋር ማህመድ የተባለው ግለሰብ ባገኘው መድረክ ላይ ሁሉ በጣም የተሳሳቱ አዘናጊና አግላይ ንግግሮችን በማድረግ ይታወቃል :ባለፈው ወር በሙስሊም ኦሮሞች ስብሰባ ላይ በመገኘት የሰጠውም በጣም አደገኛ አስተያየት ብዙ ሰዎችን አስደንግጥዋል:: ጃዋር በንግግሩ ሙስሊሞች ያለኦሮሞ ነጻነት ሊሳካላቸው እንዳማይችልና የኦሮሞ ድል የ ሙስሊም ድል እንደሆነ ገልጽዋል::ክርስቲያን ኦሮሞዎችን እንዲሁም አማራና እንዲሁም ሌሎች ብሄሮችን ባገለለ መልኩ ጃዋር ጅቡቲ ና ሶማሊ ስላሉ ሙስሊሞች ሲናገር ተደምጥዋል:: የዘር ጉዳይና ሀይማኖት ሲደባለቁ ምን አይነት ችግር እንደሚፈጥሩ ያልተገነዘው ጃዋር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የተወሳሰብ የህዝብ ግንኙንት ባላገናዘብ መልኩ በየመድረኩ ላይ የሚሰጣቸው ይተጣመሙና በውሸት ላይ ይተመሰረቱ አስተያየቶች ብዙ ኢትዮጵያውያን እያስቆጣ ይገኛል::

‪ ጃዋር ሞሀመድ የፖለቲካ እብደት “እኔ ባለሁበት 99% ሙስሊም ነው ማንም ሰው ደፍሮ ቀና አይልም ‪#‎በሜንጫ‬ ነው አንገቱን የምንለው ” በአሜሪካ በተደረገ ስብሰባ ላይ ከተናገረው(ሜንጫ የማጭድ ቅርፅ ያለው ረዘም ያለ ባለስለት የቁጥቋጦ መቁረጫ መሳሪያ ነው)

ከሁሉ በባሰ ብዙ ኢትዮፕያውያንን ያስደነገጠው የሀጂ ነጅብ በጃዋር አስተያየት መስማማት ነው:: እንደ ሀጂ ነጅብ አስተያየት ከሆነ 50 ሚሊዮን ሙስሊም እንዳለና 80% ሚሊዮኑ ኦሮሞ እንደሆነ ተናግረዋል:: ይህም ማለት 40 ሚሊዮኑ ኦሮሞ ሙስሊም እንደሆነና ይህም ማለት መቶ በመቶ የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊም ነው ማለት ነው:: የኦሮሞ ህዝብ ብዛት 34.4 ሚሊዮን መሆኑ መዘንጋት የለበትም::
ሀጂ ነጅብ በማስከተልም ኦሮሞች ሙስሊሙን ነጻ ማውጣት እንዳለባቸው አስምረውበታል::ይህ በውነቱ በጣም አሳዛኝና ከሙስሊም ትግል ጀርባ ያለውን ኢትዮጵያን እስላማዊ ለማድረግ የታለመውን እቅድ ያሳያል::
የሙስሊምን እንቅስቃሴ በመደገፍ ክርስቲያኖች ያረጉት አስትዋጾኦ ቀላል አይደለም ከ ጳጳስት ጀመሮ የፖለቲካ መሪዎች አክቲቭኢስቶች ጭምር ይህንን ትግል በመደገፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል:: ይህንን ያረጉት በኢትዮጵያዊንት መንፈስ እንጂ መስሊም ወይም ኦሮሞ ስለሆኑ አይደለም ::አቶ ነጂብ እንደ ኢትዮጵያ ሙስሊም ተወካይነታቸው ሁሉንም ሙስሊም መወከል ሲኖርባቸው ወደ ዘር በተደራጀና ሀይልን መሰረት ባደረገው የጃዋርና የአክራሪዎች ስብሰባ ላይ ተገኝቶ እናንተ ናቹ ነጻ ምታወጡን ማለት በጣም ሚያሳዝን ነገር ነው::
ጃዋር መሀመድ ሌሎች የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ባገለለ መልኩና የራሱን ዘር ባስቀደመ መልኩ ባድረገው ንግግርን መደገፍ የሙስሊም እንቅስቃሴ ከጀርባው የያዘው ድብቅ አጀንዳ እንዳለ ሚያመላከት ነው::

ጃዋር መሀመድ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ድምጻችን ይሰማ ከሚባለው የሙስሊም የዲያስፖራ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ ሲያድረግ እንደነበር ይታወቃል:: የጃዋር አጀንዳ የሆነውን የኦሮሞ ሙስሊሞች ስልጣን መያዝ ከመድረክ ጅርባ ይነጋግሩበት እንደነበር ሀጂ ነጅብ አምነዋል:: ኢትዮፕያውንን አብሮ ሚያኖረው የህግ የበላይነት, ዲሞክራሲ, ፍትህና እኩልነት መሆኑ እየታወቀና ኢትዮጵያ የብዙ ሀይማኖቶች ብሄሮች አገር እንደሆነች እየታወቀ በየመድረኩ ላይ እንደዚህ አይነት ሀላፊነት የጎደለውና ዘረኛ አስተያየት መስጠትና ያንንም መደገፍ በጣም ሚያሳዝን ነው::
የነጃዋር አላማ ይፍትህ የበላይነትን በኢትዮጵያ ምድር ለማምጣት አይደለም::አላማቸው ግልጽና ግልጽ ነው:: የኦሮሞ ሙስሊሞችን የበላይነትን በክርስቲያን ና ኦሮሞ ባልሆኑ ሙስሊሞች ላይ ለመጫን ነው::ይህንን ደግሞ በፍጹም ምንቀበለው አይሆንም::ክርስቲያኑ አንድ ነን በሚል መማማል አንድ መሆን እንደማይቻል ሊገነዘበው ይገባል::

የጁነዲን ባለቤት በድርድር ተፈቱ !!/ከኢየሩሳሌም አርአያ/



የቀድሞ የኦህዴድ/ኢህአዴግ አመራር አባልና ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት በውስጥ በተደረገ ድርድር ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን የቅርብ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ። « ከሳኡዲ ኤንባሲ ገንዘብ ተቀብለው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል» በሚል በሽብርተኝነት ወንጀል እንዲከሰሱ የተደረጉትና ለአንድ አመት የታሰሩት የአቶ ጁነዲን ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሕወሐት መሪዎች በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ እንዲፈቱ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ይህ ሊሆን የቻለው በስደት ከሚገኙት አቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር በተደረገ ምስጢራዊ ድርድር ላይ “መንግስት ከዚህ ቀደም በወሰዳቸው እርምጃዎች፣ ፖለቲካዊ ምስጢራዊ ጉዳዮችና ገዢውን ፓርቲ የሚመለከቱ ማንኛውም ነገሮች በየትኛውም ቦታ ላለማጋለጥ፣ ላለመናገር፣..” ከጁነዲን ጋር ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ባለቤታቸው እንዲፈቱ መደረጉን አስታውቀዋል።

 በሙስና የተጨማለቁት አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ደ/ፂዮንና ፀጋዬ በርሄ ከጁነዲን ጋር እንደተደራደሩ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። መጀመሪያም ወ/ሮ ሃቢባ የሰሩት ወንጀል ኖሮ አይደለም የታሰሩት ያሉት ምንጮቹ አቶ ጁነዲን ከስልጣን ለማንሳት ሲባል ብቻ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል። ጁነዲን ባለቤታቸው ከታሰሩ በኋላ በስልጣን ላይ እያሉ እንዲያውም ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ሚሚ ስብሃቱ በምታዘጋጀው ራዲዮ ጣቢያ « ጁነዲን መታሰር አለባቸው፤ መንግስት እስከ አሁን እርምጃ የማይወስደው ለምንድነው?..ባለቤታቸው አሸባሪ ናት» በማለት የፍ/ቤትን ነፃነት ጭምር በሚጋፋ መልኩ ቅስቀሳ ይካሄድ እንደነበረ ምንጮቹ አስታውሰዋል። አቶ ጁነዲን ከአገር ከወጡ በኋላ እውነቱን እያወቁ መደራደራቸውና ባለቤታቸውን በማስፈታት ሌሎች ንጹሃን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ላይ በተዘዋዋሪ በመፍረድ የኢህአዴግና ካንጋሮው ፍ/ቤት ተባባሪ መሆናቸው አሳዛኝ ነው ብለዋል ምንጮቹ።

 አቶ ጁነዲን ምናልባትም « ባለቤቴ በፍ/ቤት ነፃ ተባለች» በሚል በኢትዮጲያ የፍትህና የፍ/ቤት ነፃነት እንዳለ አስመስለው ሊናገሩ እንደሚችሉ ማረጋገጫ የለም ያሉት ምንጮቹ አክለውም ጁነዲን ምንም አሉ ምን በስልጣን እያሉ ለፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው እንደማይቀር መታወቅ አለበት ብለዋል።

ከጅዳ የሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ የሚደርሰኝ ሮሮ !


"የሳውዲ መንግስት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ሳውዲን ለቀው አንዲዎጡ ያስተላለፈውን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስለወ መስሪያ ቤቶች ዜጎች ሀጉን አክብረው ወደ ሃገራቸው እንዲወጡ
ያስተላለፉትን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች በመረዳት ወደ ሃገር ለመግባት ወደ ሽሜሲ መጠለያ በመሄድ እጃችን የሰጠን ዜጎች እየተንገላታን ነው! " በማለት ሮሮና ቅሬታቸውን ያቀረቡ ወገኖች መጠለያ እንደገቡ በኢትዮጵያ መንግስት የመጓጓዣ ሰነድ የተሰጣቸው ቢሆንም የሳውዲ ፖስፖር ሃላፊዎች የቀረበላቸውን ሰነድ በማጣራት የመውጫ ሰነድ ለመስጠት አንግልት አያደረሱባቸው መሆኑን ገልጸውልኛል። ጉዳያቸውን ለማስፈጸም በአውቶቡስ ላይ እና በመጠለያው ግቢ ውስጥ ተበትነው በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ የገለጹልኝ እኒህ ወገኖች የአቅመ ደላማ ሴቶችና ህጻናትን እንግልት ከግምት ውስጥ በማስገባት የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ከሚመለከታቸው የሳውዲ መንግስት ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ትብብር ያደርጉላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

እኒሁ ሮሯችን ለሚመለከታቸው እንዳሰማ የተማጸኑኝ ወገኖች ወደ ጅዳ ቆንሰል ሃላፊዎች ስልክ ደውለው ስልክ ስለማያነሱ ወደ እኔ መደወላቸውን የገለጹልኝ ሲሆን ወደ ሃገር ግቡ ተብለን ወደ ሃገር እንግባ ባልን እንግልት ሊደርስብን አይገባም ሲሉ " አሁን በደል እያደረሰብን ያለው ሳውዲ ኢሚግሬሽን መፍትሄ እንዲሰጠን ዲፕሎማቶች የተቻላቸውን ያድርጉልን! " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። በሌላ በኩል ወደ መጠለያው ገብተው አስፈላጊውን ሰነድ ያሟሉ አንዳንድ ነዋሪዎች መካከል ሻንጣችን ጠፋብን የሚሉና ከአንድ ሻንጣ በላይ እንዳይዙ የተከለከሉ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ጉዳዪን ለማሳወቅና ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ወደ አቶ ዘነበ ከበደ እና ወደ ምክትላቸው አቶ ሸሪፍ ስልክ በመደወል ያደረግኩት ሙከራ ዛሬም አልተሳካም!

ካልተሳፈርኩ” ብሎ የታክሲ ሹፌሩን በሽጉጥ ገደለ




መገናኛ አካባቢ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መስመር፣ አንድ መንገደኛ ትናንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ካልተሳፈርኩ ብሎ ሾፌሩን ወንደሰን ደምሴን በሽጉጥ ገደለ፡፡ “ታክሲው ውስጥ ካልተሳፈርኩ፣ አትሳፈርም” በሚል በተነሳው ጭቅጭቅ፣ ሾፌሩን ገድሏል የተባለውን ደጀኔ ገመቹ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የገለፀው ፖሊስ፤ የአይን ምስክሮችን ቃል በመቀበል ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ ታክሲ እየጠበቁ የነበሩ የአይን ምስክሮች በወቅቱ አቶ ደጀኔ እጁን በማወዛወዝ ሚኒባስ ታክሲውን እንዳስቆመ ተናግረው፣ ከሾፌሩ ጋር ጭቅጭቅ እንደተፈጠረ ገልፀዋል፡፡ 

አቶ ደጀኔ በታክሲው ለመሳፈር ሲጠይቅ፣ ሾፌሩ “ቤተሰቤን ነው የጫንኩት፣ ሌላ ሰው አላስገባም” በማለት ምላሽ እንደሰጠው በአካባቢው የነበሩ መንገደኞች ተናግረዋል፡፡ ታክሲ የሚጠባበቁ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ስለነበሩ፣ ጭቅጭቁን ከመነሻው እስከ መጨረሻው የተመለከቱ እማኞች በርካታ ናቸው፡፡ የፖሊስ መረጃ እንደሚጠቁመው፤ የሾፌሩ አባት ታክሲው ውስጥ ነበሩ፡፡ “አትሳፈርም የምትለኝ ንቀት ነው” በሚል ክርክርና “የጫንኩት ቤተሰቦቼን ስለሆነ ሌላ ሰው አልጭንም” በሚል ምላሽ በተባባሰው ጭቅጭቅ፣ አቶ ደጀኔ ሽጉጥ እንዳወጣ እማኞች ተናግረዋል፡፡

 ሽጉጡን ሾፌሩ አንገት ስር በመደገን ነው የተኮሰው ብለዋል-ምስክሮች፡፡ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ዲቪዥን ክፍል ተወካይ፣ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

Thursday, December 26, 2013

ቴዲ አፍሮ እና ጥሬ ጨዋዎች

TeddyAfro_NYC-51

ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በብዙዎች ሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ስፍራየሚሰጠው ወጣት ከያኒ ነው፤ በሙዚቃዎቹ በሚያነሳው ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ታሪካዊና ወቅታዊ ጉዳዮች የተነሳ የብዙዎችን ቀልብ ለመግዛት የቻለ ይመስለኛል፡፡ የእርሱን ታላቅነት መግለፅ የዚህ ጹሑፍ ዓላማ፣ ጥያቄም፣ የማወቅም ፍላጎት አይደለም፡፡
ይልቁንም ለዚህ አጭር መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ ከሰሞኑ በአንዳንድ ጥቃቅን እና አነስተኛ ካድሬዎች እንዲሁም መንግስትን ለምን እንደሚቃወሙ እንኩአን በማያውቁት እንደ እነ ጃዋር መሀመድ የመሳሰሉ ሰሞንኛ ትችታቸውን በመሰንዘራቸውን ምክንያት እኔም የተሰማኝን ልጨምር በሚል ነው፡፡
እንደምናውቀው ቴዎድሮስ ካሣሁን በዚህች የሙዚቃ ህይወቱ ከዛቻ እስከመታሰር ድረስ የደረሰ መሆኑ እሙን ነው ይህም የደረሰበት የተለየ ሰው ስለሆነ ነው
ቴዲ ሺህ ዘመናት ስልጣኔያችንና ታሪካችን፣ ጥበባችን በፍቅር፣ ፍቅራችን በጥበብ የተገመደበት ውሉ ከየት ተጀምሮ የት እንደተቋረጠ ታሪክንእንጠይቅ ዘንድ እንዲህ ሲል በቅኔው ተመራምሮ ያመራምረናል፡-
ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ ባትሮኖሱ ላይ፣
የእነ ፋሲለደስ የእነ ተዋናይ፣
የት ጋር እንደሆነ ይታይ የእኛ ጥበብ መሰረቱ…፡፡
እናም እስቲ ታሪክ ይታይ፣ ይመርመር፣ ዘመናትን ያስረጁና የተሻገሩ ብራናዎቻችን ይውጡ፣የሺህ ዘመን የሃይማኖት፣ የጥበብ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔና የፍልስፍና ድርሳኖቻንን ይታዩይመርመሩ… በአክሱም ስልጣኔ፣ በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ትንግርት፣ በጎንደርበእነ ፋሲለደስ የስልጣኔ አየር ዝናዋ የናኘላት፣ እነዛ ፍቅርን በጥበብ አስውበው በቅኔያቸውናበማኅሌታቸው ሰማይ ሰማያትን ሰንጥቀው በመንፈሳቸው ጸባዖት የደረሱ፣ በፍቅር ጧፍ የነደዱበማሕሌታዩ ያሬድ መንፈስ የተነሱ እንደ ተዋናይ ያሉ የቅኔ የጥበብ ጉልላቶች እንደ አጥቢያኮከብ በደመቁባት ምድር ዛሬን ፍቅር የተራብን፣ ጥበብን የተራቆትን፣ ስለ ፍቅር የደከመንምንድነው ምክንያቱ የሚል ይመስለኛል ቴዲ…፡፡
ቴዲ በሙዚቃው ለታሪክ ያለውን ስሱነትና (sensitivity) እውቀትም (Indigenous Knowledge)አሳይቶናል፡፡ ተዋናይን ስንቶቻችን እናውቀዋለን ተብለን ብንጠየቅ የሚያስተዛዝበን ሳይሆንይቀራል፡፡ በተለይ ደግሞ ለዘመናችን ትውልድ ለአፉም ለልቡም ቅርቦቹ እነ አርሴናል፣ቼልሲ፣ ሜሲ፣ ሮናልዶ፣ እነ ፊፍቲ ሴንት እነ ቢዮንሴ፣ ወዘተ… የባሕር ማዶዎቹ ዝነኞች ናቸውእንጂ እነ ተዋናይን እነ ቅዱስ ያሬድን፣ እነ አጼ ፋሲልን ሊያስባቸው ወኔው ያለውአይመስልም፣ ኅሊናውንም ይደክመዋል እናስ እንዴት፣ ምን ሲደረግስ ሊያስባቸው ይችላል የኔትውልድ፡፡ በቅኔው የተራቀቀና በመንፈሳዊ እውቀቱ አንቱ ስለተባለው ስለ ተዋናይለመስማትም ሆነ ለማወቅ የታሪክ መዛግብትን ማገላበጥ ግድ ይላል፡፡ አሊያም ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች እግር ስር ቁጭ ማለት ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡
ቴዲ በየትኛው መንገድ የሀገሩንና የቤተ ክርስቲያኑን የጥበብ እና የሥልጣኔ ከዋክብቶችንሊያውቅ እንደቻለ ባይነገረንም የትናንትናዎቹን የሀገራችንን ባለውለታዎችና የዘመንፈርጦች ማንነት ለማወቅ እና እንዲሁም ታሪኩን ለመመርመር ግን የተጋና የሰላ አእምሮእንደተቸረው/እንዳለው የግጥሞቹ መልእክቶች ይነግሩናል፡፡ እናም ከታሪካችንናከስልጣኔያችን መሰረት ከአክሱም ተነስቶ በጊዜና በታሪክ ሃዲድ ላይ አሳፍሮን በትላንትታሪካችን ውስጥ ራሳችንን እንድንመረምር፤ ራሳችንን እንድናይ ይወተውተናል፡፡ ለዚህደግሞ ምክንያቱ ይለናል ቴዲ ስለ ፍቅር ዜማው ውብ የግጥሞቹ ስንኞች፡-
. . .የኋለው ከሌለ የለም የፊቱ፣
ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ፣
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ፡፡
በማለት ከታሪካችን ጋር እጅ ለእጅ በምናብ ሊያጨባብጠንና ሊያስተያየን ይፈልጋል፤ እናምያለ ትላንት ዛሬ የለም፣ ያለ ዛሬ ደግሞ ነገ አይታሰብም በሚል የመጣንበትና የተጓዝንበትንአኩሪና አሳፋሪ የታሪካችንን ምእራፍ ለማገላበጥ ለደከምን ለእራሱ እና ለእኛ ትልቅ ቁም ነገርያለው ምክር ያስተላልፋል፡፡ ይህ የከያኒው የግጥም ስንኝ የሮማውን ታላቅ የሕግ ሊቅ፣ፈላስፋና አስተማሪ የሆነውን የሲስሮን አባባል አስታወሰኝ፡- ‹‹ከመወለዳችን በፊት ያለውንታሪክ ካላወቅን ዕድሜ ልካችንን ሕጻን ሆነን እንቀራለን፡፡›› ታሪካችንን ለመመርመር እናከታሪካችን ለመማር የደከምን እኛ ዛሬም እንደ አዲስ ሰናፈርስ ስንጀምር ከመጀመር ሀ ሁሳንወጣ እንደ ህጻን ባለህበት እረገጥ የሆንበትና ታሪክን እንድንደግም የተፈረደብን ምስጢሩምን ይሆን በማለት ታሪክ ጠያቂ፣ የታሪክ ወዳጅ፣ ከታሪክ የምንማር እንድንሆን ያተጋናል፡፡
ከምንኮራበት ታሪካችንና ስልጣኔያችን ባልተናነሰ አንገት የሚያስደፋ ስማችንና ማንንታችንበዓለም ፊት በቀየረብን በበርካታ የራብ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና መበላላት ታሪክ ዘመናትንውስጥ አልፈናል፡፡ እናም የመጣንበት መንገዱ ረጅም ዘመናቶቻችንም መከራ ሰቆቃና ዋይታ የነገሰባቸው ናቸው ሲል የትናንቱን ታሪክ ለመድገም የተፈረደብን ይመስል ታሪክ ደጋሚዎች እንድንሆን የሆንበትን እውነታ መመርመርና ማየት እንችል ዘንድ ትልቅ ጥያቄያጭርብናል፡፡ ዛሬም እግራችን መሄድ ተስኖት ቆመናል
የእርሱ ደጋፊዎች እንዳሉ ሁሉ የእርሱ ተቃዋሚዎች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ነው ነገር ግን በአሉባልታ የቴዲን ስራዎች ጥላሸት ለመቀባት የሚደረግ ትግል ወይ ቅናት ነው አልያም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንደሚባለው ይሆናል፡፡
ለእምዬ ምንሊክ ያላቸው ጥላቻ ሰሞኑን ተቀስቅሶባቸው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ከርመዋል አስገራሚው ነገር ምንሊክን ለመሳደብ ቴዲን ሰበብ ማድረጋቸው ነው ሌላው ደግሞ መረጃውን እኔ ለቅቄዋለው ብሎ ማንም ኃለፊነቱን እሰከዚች ሰዐት ድረስ ሳይወስድ እነርሱ ቴዲን እና ምንሊክን መዝለፍ የየእለት ተግባራቸው አድርገውታል፡፡
ምንሊክን ህዝቡ እምዬ ብሎታል ቴዲን ደግሞ የዘመናችን የሙዚቃው ንጉስ ብሎ ሰይሞታል
ደበበ ሰይፉ ጥሬ ጨው በሚለው ግጥሙ እንዲህ ነበር ለነፈዞች የገጠመው
ጥሬ ጨው – ደበበ ሰይፉ
————
መስለውኝ ነበረ ፣
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፣
ለካ እነሱ ናቸው ፣
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፣
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፣
“እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው ።
ለማንኛውም እኔም እንደ ደበበ ሰይፉ ሰሞንኛ የቴዲ ተቺዎችን ጥሬ ጨው ብዬ ሰይሜያቸዋለው፡

Wednesday, December 25, 2013

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውና ያልተስማማችባቸው ነጥቦች ይፋ ተደረጉ


ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውና ያልተስማማችባቸው ነጥቦች ይፋ ተደረጉ

December 25/2013
ግብፅ የቅኝ ግዛት የውኃ ኮታዋ እንዲከበር አሁንም ጠይቃለች
•ለመስማማት የገባችውን ቃል አፍርሳለች
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በተመለከተ ከግብፅና ከሱዳን መንግሥታት ጋር እያደረገ የሚገኘውን ድርድር ውጤት አስታወቀ፡፡ የግብፅ መንግሥት ያቀረባቸው የግዴታ ሐሳቦች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አላገኙም፡፡ 
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከግብፅና ከሱዳን አቻ ሚኒስቴሮች ጋር በህዳሴው ግድብ ላይ እያደረጋቸው የሚገኙ ድርድሮችን ማክሰኞ ዕለት ለባለድርሻ አካላትና ለመገናኛ ብዙኃን ሲያሳውቅ፣ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የተስማማችባቸውንና ያልተስማማችባቸውን ነጥቦች ይፋ አድርጓል፡፡ 
በሚኒስቴሩ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ባቀረቡት ጽሑፍ፣ ሚኒስቴሩና ብሔራዊ የባለሙያዎች ቡድን ሥልታዊና የተጠና እንቅስቃሴ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጐን እንድትቆም ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ያቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ሪፖርትን ኢትዮጵያና ሱዳን መቀበላቸውን የገለጹት አቶ ፈቅ፣ ይህ ሪፖርት በግብፅ በኩል ተቀባይነትን ያላገኘ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ 
ነገር ግን የኢትዮጵያና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓመት መጨረሻ በአዲስ አበባ ተገናኝተው በተስማሙት መሠረት፣ የሦስቱ አገሮች የውኃ ሚኒስትሮች በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተግባራዊነት ላይ ውይይት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ 
በጥቅምት ወር መጨረሻ ሱዳን የተገናኙት የሦስቱ አገሮች ሚኒስትሮች በመፍትሔ ሐሳቡ ተግባራዊነት ላይ በመወያየት የሚያመቻችና የሚከታተል ኮሚቴ ለመመሥረት በሐሳብ ደረጃ መስማማታቸውን፣ ነገር ግን በኮሚቴው አባላት ስብጥር ላይ መግባባት ባለመቻላቸው ውይይቱ ተቋርጦ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን አስታውሰዋል፡፡ 
የኮሚቴው አባላት ሙሉ በሙሉ የሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች ብቻ መሆን አለባቸው በሚለው የኢትዮጵያ ፍላጎት መኖሩና በግብፅ በኩል የውጭ ባለሙያዎች እንዲካተቱ አቋም መያዙ፣ የልዩነቱ ምክንያቶች እንደነበሩ አቶ ፈቅ ገልጸዋል፡፡ 
ይህንን ልዩነት ለመፍታት ከተያዘው ቀጠሮ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ኮሚሽን ዓመታዊ ጉባዔን ምክንያት በማድረግ ወደ ሱዳን ማቅናቱንና በወቅቱም በሦስቱ አገሮች ድርድር ላይ የሱዳን መንግሥት የኢትዮጵያን አቋም እንዲረዳ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ 
የሱዳን የውኃና የኤሌክትሪሲቲ ሚኒስትር መንግሥታቸው የኢትዮጵያን አቋም ሙሉ በሙሉ ከመቀበል ባለፈ፣ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የማግባባት ሚና እንደሚኖራት በመተማመን ሁለተኛው የሦስቱ አገሮች ድርድር ከመጀመሩ ቀናት በፊት ወደ ግብፅ ማቅናታቸውን ገልጸዋል፡፡ 
የሱዳን ሚኒስትር በካይሮ ቆይታቸው ከግብፅ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት የኢትዮጵያን አቋም ማስረዳታቸውንና የግብፅ መንግሥት የኢትዮጵያን ሐሳብ እንደሚደግፍ ተገልጾላቸው መመለሳቸውን አስረድተዋል፡፡
‹‹ግብፅ የህዳሴው ግድብ ከፍታ ዝቅ ይበል የሚል ሐሳቧን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ የገንዘብ ብድር እንዳታገኝ የማደርገውን ሩጫ አቆማለሁ በማለት ለሱዳኑ ሚኒስትር ቃል ገብታ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሁለተኛው ዙር ድርድር እንዲቀጥል ተደርጓል፤›› ያሉት አቶ ፈቅ፣ በዚህ ድርድር ላይ ግብፅ ይዛ የቀረበችው ሰነድ ከገባችው ቃል የተለየ ነበር ብለዋል፡፡ 
በግብፅ በኩል ለሁለተኛው ዙር ድርድር የቀረበው ሰነድ በሦስቱ አገሮች የሚቋቋመው ኮሚቴ በኢትዮጵያ በኩል የሚገኙ አዳዲስ የጥናት ውጤቶችን እንዲዳስስና የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ኮሚቴው እንዲከታተል ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ማለትም የግብፅና የሱዳን የውኃ ደኅንነትና ፍላጐት ሙሉ በሙሉ መከበር አለበት የሚሉ ነጥቦችን በድጋሚ በሰነዱ አካታ ማቅረቧን ገልጸዋል፡፡ 
‹‹ይህንን በጭራሽ ኢትዮጵያ የምትቀበለው አይደለም፤›› ያሉት አቶ ፈቅ፣ በዚህና በሌሎች የመወያያ ነጥቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ውይይቱ እንዲቀጥል ለማድረግ እንደተሞከረ ገልጸዋል፡፡ 
በውይይቱ ላይ ግብፅ ከ20 በላይ ባለሙያዎችን እንዳሳተፈች በኢትዮጵያ በኩል ግን ስድስት ባለሙያዎች እንደተወከሉ የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፣ በግብፅ በኩል ሆን ተብሎ ውይይቶችን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በማጓተት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን የማዳከም ጥረታቸው ውጤት አልባ እንዲሆን በጥንካሬ መሠራቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ጥረት በሚመሠረተው ኮሚቴ አባላት ስብጥር ዙሪያ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሐሳብ ተቀባይነት ማግኘቱን አቶ ፈቅ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኮሚቴው በሚቋቋምበት ዓላማና በተወሰኑ የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነቶች ላይ ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው ሐሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸው ታውቋል፡፡
ኮሚቴው ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን የቀረበውን የመፍትሔ ሐሳብ ተግባራዊነት የመከታተል ዓላማ የሚኖረው በመሆኑ፣ እስካሁን በሦስቱ አገሮች ተቀባይነት ካገኙ የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረባቸው ሁለት የመፍትሔ ሐሳቦችን ማስጠናትና የጥናት ውጤቱን ማፀደቅ ይገኝበታል፡፡ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎቹ ቡድን ባቀረባቸው ሁለት ሐሳቦች በግድቡ ላይ ተጨማሪ የኃይድሮሎጂ፣ የአካባቢያዊና ማኅበራዊ ጥናቶች እንዲደረጉ ጠይቋል፡፡ 
በመሆኑም ኮሚቴው ለሁለቱ ጥናቶች አማካሪ ድርጅቶችን መቅጠርና ማስጠናት፣ የጥናቱን ሪፖርት መገምገም፣ ማስተካከልና ማቅረብ፣ በዚህ የጥናት ሪፖርት ላይ የኮሚቴው አባላት መግባባት ካልቻሉ ጉዳዩ ለሚኒስትሮች ቀርቦ እልባት እንዲያገኝ፣ በዚህ ካልተፈታ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ሙያዊ አስተያየት እንዲያቀርቡ የሚረዳ የቅጥርና የሥራ ዝርዝር ኮሚቴው እንዲያዘጋጅ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በቀሩ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትም ሦስቱ ሚኒስትሮች በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ በሱዳን ተገናኝተው ስምምነት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአማካሪ የሚጠኑት ሁለት ጥናቶች ሪፖርት ግምገማ ላይ የኮሚቴ አባላቱም ሆኑ ሚኒስትሮቹ መስማማት ካልቻሉ፣ ሙያዊ አስተያየት የሚሰጥ አማካሪ ለመቅጠር ስምምነት ተደርሷል፡፡ ነገር ግን ሙያዊ አስተያየት የሚሰጠው አማካሪ ቡድን ቅጥር የሚፈጸመው በሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች ስምምነት ነው የሚለው ላይ ከስምምነት አልተደረሰም፡፡ ሙያዊ አስተያየት እንዲሰጥ የሚቋቋመው ቡድን በጥናቶቹ የመጨረሻ ሪፖርት ላይ ብቻ አስተያየቱ ይወሰናል በሚለው የኢትዮጵያ አቋም ላይ ያለውን አለመግባባት መቅረፍ ሌላው የውይይቱ አካል ነው፡፡ 
እስካሁን የተደረጉ ድርድሮችን ውጤቶቹን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀው ውይይት ላይ የተገኙት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ላይ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ በእጅጉ አድንቀዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ በበኩላቸው፣ የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት የትኞቹንም የተፋሰስ አገሮች እንደማይጐዳ ለማሳወቅ ዩኒቨርሲቲው በአገር ውስጥ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በማስፋት ወደ ጐረቤት አገሮች እንደሚዘልቅ አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በመጪው መጋቢት ወር በሱዳን ሲምፖዚየም ለማዘጋጀት ከካርቱም ዩኒቨርሲቲ ጋር ስምምነት መፈረሙን ገልጸዋል፡፡ 

Monday, December 23, 2013

በደም የተገነባ ተቋም ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል::

    ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በሃዘን ሲመታ ፣ ደመናው ሲጠለሽ ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ ፤
የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው …….. የክፉው ቀን ጅማሮ ፣ የውርደት ሃሌታ ፣ የሃገር አልባነት ስሜትና የዜግነት
ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር ።
    ውርስ ከአባት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ካልቻለ ፤ አባት የጀመረውን ልጅ ካልቋጨው ፤ አዲስ መንግስት ሲቀየር
የድሮውን በጐ ነገር ሁሉ ብትንትኑን አውጥቶ ካጠፋ ፤ የትውልድ ቅብብሎሽ ገደል ገባ ማለት አይደል ? እናም
በአገሬ ምድር ላይ የእርግማን ዘመን ያኔ “ በ1991 “ “ ሀ “ ብሎ ጀመረ ።
     ሌባው ከሳሽ … ቀማኛው ፈራጅ የሆነበት ፤ አባት ተቀምጦ ልጅ የሁሉ ነገር አዛዥ ሲሆን ፤ አህያ ወደ ሊጥ …
ውሻም ወደ ግጦሽ ከተሰማራ …. እነሆ ዘመነ ብልሹ ላይ መድረሱን ያልተረዳ ካለ … እሱ ባይፈጠር …. እናቱ ሆድ
ውስጥ ውሃ ሆኖ ቢቀር ይሻለው ነበር ።
     ሲገነጠል ዝምታ ፤ ንብረት ከመሃል አገር ተግዞ ሲያልቅ ዝምታ ፤ ገዳማት ሲታረሱ ፣ ቤተ ክርስቲያናት
ሲዘረፉና ታቦታት በየገበያው ሲቸበቸቡ ዝምታ ፤ ደን ሆን ተብሎ በሰደድ እሳት እንዲወድም ሲደረግ ዝምታ ፤
ግዙፉ የአገር መከላከያ ኃይል እንደተረት አይናችን ስር ሲበተን ዝምታ …….. የምንወደው ዝነኛው የአየር
ኃይላችንም አብሮ ተደርምሶ እንዳልነበረ ሲሆን ዝምታ ነገሰ ። የሚቆጭ ፤ የሚመክር ፤ የሚቆጣና ሃይ የሚል
ወንድ ጠፋ ። የአድዋና የማይጨው አርበኞቻችን የክብር ሃውልቶች ሲፈርሱም ዝምታ ፣ የጦር ካምፖቻችንም
ታሪካዊ ስያሜ በማን አለብኝነት ለጐጠኞች ስያሜ ሲውልም ዝምታ ነገሰ ።
      ዛሬ ደግሞ ከአዲስ አበባ ዋሺንግተን በሚመላለሱና ከዘመነኞቹ ጊዚያዊ የይሁኝት ፈገግታ በተቸራቸው የኛና የኔ
ቢጤዎች አማካኝነት የቬተራን አሶሴሽን እናቋቁማለን ፤ የአየር ኃይሉንም ታሪክ እንፅፋለንና ለዕርዳታ እጃችሁን
ዘርጉ የምትል የኢሜል መልዕክት ደርሳን በትዝብት ተደምመናል ። እስኪ ከበጐ መንፈስ የመነጨ ነው ብለን
እንመን ። ግን ሥጋት አለን !
     የአየር ኃይላችንን ታሪክ ለትውልድ ዘግቦ ማስቀመጥ ምንኛ የተቀደሰ ዓላማ ነው ! የአቭዬሽን ቬተራን ማህበርን
ማቋቋምስ እንዴት ትልቅ ራዕይ አለው ? ነገር ግን የአንድ መንደር ልጆችን ዓላማ አድርጐ በጐጠኝነት ማማ ላይ
እየተንጠለጠለ እኛ እና እነሱ ፤ የቀድሞውና አዲሱ ፤ ዲሞክራቲኩና የአንድነት አርበኛ እያለ ሊለያየንና
ሊከፋፍለን ሌት ተቀን የሚተጋው ጐጠኛና ሽፍታ መንግስት የሚገነባውን ከእውነተኛው አየር ኃይል በቅጡ
መለያየት ያስፈልጋል ።
     ውሃና ዘይትን ለመቀላቀል በማምሺያ እድሜ መባጀት ጉልበት ማባከን እንዳይሆን ! የነፃነት አርበኛው ጀ/ል ተጫነ
መስፍንና የሽፍቶቹ ጀ/ል አበበ ተ/ሃይማኖት (ጆቤ) በምን ተዓምር ለአንድ ዓላማ ሊሰለፉ ይችላሉ ?
በምንስ ሂሳብ የህ.ው.ሃ.ቱ. አበበ ተ/ኃይማኖት (ጆቤ) የቬተራን አሶሴሽን መስራች ሆኖ በሸራተን አዲስ ይደግሳል ?
እነዚህ ሁለት ፍጥረታት ውሃና ዘይት ናቸው ። በዓላማም በራዕም አንድ አይደሉም ….. አሳዳጅና ተሳዳጅ !
ወንጀለኛና ወንጃይ … አርበኛና ባንዳ .. ውሃና ዘይት ናቸው ። ሊዋሃዱ አይችሉም ።
     የእኛው አየር ኃይል በጅምላ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ ተብሎ እንደ ጉም በተበተነበት ዘመን ላይ ተቆሞ ….. ለአገር
የደሙ ከያሉበት ታድነው በውርደት በየማጐሪያው ተወርውረው ልባቸው ተሰብሮና ጥሪት አልባ ሆነው በሰው
እጅ ላይ እንዲወድቁ በተበየነበት ዘመን ላይ ፤ ዛሬ ከሲሶው በላይ እውነተኛው አርበኛ አገር አልባ ሆኖና ተዋርዶ
አልጋ ላይ እየዋለ ያለ ደጋፊና አጋዥ ቀና ማለት ባቃተው ሰዓት ላይ የቬተራን አሶሴሽን እያቋቋምን ነው ሲሉንና
ግባታውን በገንዘብ እንድንደግፈው ስንጠየቅ እውን ለእውነተኛው የአየር አርበኛ አገልግሎት እንዲመስለን ይሆን ?
     በእርግጥ ጥቂቶች ደም የተገበረበትን አርበኝነታቸውን ሳይሆን የሽንፈት ታሪካቸውን አሜን ብለው በመቀበል
በውርደት በጅምላ የተለጠፈብንን የጨፍጫፊነት ማንነት ፤ በተጨማሪም ለአገር በመሞታችንና ደማቸንን
በማፍሰሳችን ምክንያት እንደ ተራ ነፍሰ ገዳይ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኞች መሆናችንንና/መሆናቸውን
ዘንግተው “ ማምሻም እድሜ ነው “ በሚል የመሰንበት ጉጉት በድለላ እያግባቡን ማየታችን ከላይ በበጐ መንፈስ
ተነሳስተው ነው የሚለውን አቋማችንን እየሸረሸረብን ተቸገርን ።
ለመሆኑ በማን አየር ኃይል ….. በነማንስ ደም ይቀለዳል ?
    የእነ ሚሽካ ባቢቼቭ አየር ኃይል …. የእነ ባህሩ ካባ አየር ኃይል …. የእነ ጀነራል አበራ ወ/ማሪያም …. የእነ ጀነራል
አሰፋ አየነ … የእነ ጀነራል አሰፋ ገ/እግዚ …. የነ ጀነራል ታዬ ጥላሁን ….. አየር ኃይል እንዴት ሆኖ ከዚህኛው ዘመን
ጋር ይዋሃዳል ?
      እነ ጀ/ል ለገሰ ተፈራ ፣ ኰ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ፣ ኰ/ል ታደለ አለሙ ፣ ኰ/ል ትርሲት ፣ ኰ/ል ወርቁ ፣ ሻ/ል
ጥላሁን በዛብህ ፣ መ/አ አባይነህ ኃይሉ ፣ መ/አ ደመላሽ መኰንን የመሳሰሉት በምርኰና በእስር መስዋዕትነት
የከፈሉበት ፤
    የነ መርዕድ ዳጨው ደም …. የነ አማኑኤል አምደ ሚካኤል …. የነ ጥላሁን ኃይሉ ፤ የነ ለዊ ደሬሳ …. የነ መንግስት
ዓለሙ … የእነ ሊ/ካዴት ይኩኖ ታደሰ ጨቅላና አድገው ያልጨረሱ ልጆች ደም ፤ የነ ተስፋዬ ብ/ሥላሴ …. የነ
ማ/ቴክ ደገፋ ሆራ …. የነ ኰ/ል ጥላሁን ቦጋለ ….. የነ ሰለሞን መክብብ …. የነ አብረሃም ስንቄ ደም ላይ እንዴት
ዳንኪራ ይጨፈራል ?
እነ ጀ/ል ፋንታ በላይ …. ጀ/ል አመሃ ደስታ …. ጀ/ል ሰለሞን በጋሻው …. ጀ/ል ተስፉ ደስታ … ጀ/ል ንጉሴ ዘርጋው
… ጀ/ል ገናናው መንግስቱ …… እንዲህ ደማቸው ደመ ከልብ ይሁን ? ለአፍታ ቀና ብለው ቢያዩስ ምንኛ
በባልንጀራቸው ያፍሩ ይሆን !
    ዘመናቸውን ሙሉ ለአገራቸው የአየር ክልል መከበር ጨርቄን ማቄን ሳይሉ …… ንብረት ማፍራት …. ሃብት ማካበት
…. ሚስት ማግባትና የአብራካቸውን ፍሬ ለማየት ሳይጓጉ እድሜያቸውን የጨረሱ የአየር ኃይሉ ጌጦችና የአገር
አለኝታዎች እንደ ወሮበላ ማጅራት መቺ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ በተሆነባት አገር ላይ እንዴት አይነቱ የአየር
ኃይል የአቪየሽን ቬተራን አሶሴሽን ይገነባል ?
       እነ ኰ/ል ታከለ አበበ ፣ ሻ/ቃ አለማየሁ እሳቱ ፣ ሻ/ቃ ከበደ ጫኬ ፣ በላይነህ ተገኝ ፤ ደበበ ሞላ …. ደሳለኝ
ስሜነህ … …. ወዘተ በጉልበት ከአገር ተሰደው በበረሃ ላይ ያለ አልቃሽና ቀባሪ ነፍሳቸውን እንዲሰጡ ላደረገ ሽፍታ
፤ እነ ሻ/ል ፍሰሃ መለስን በእስር ቤት ለገደለ ወንበዴ እንዴት ብለን ክብራችንን ዝቅ አናደርጋለን ?
እነ ኰ/ል ብርሃነ መስቀል ፤ ኰ/ል ሰለሞን ከበደ ፤ ኰ/ል ግርማ አስፋው ፤ ሻ/ል ክፍሌ ውቤ ከእድሜያቸው ከሩብ
በላይ በእስር የገበሩበት ምክንያት ምን ይሆን ? ዘንግተነውስ ይሆን ?
      እነ ማ/ቴክ ሽብሩን .. እነ ማ/ቴክ ፀጋዬ ሁሉቃን … እነ ማ/ቴክ ግርማ ሰቦቃንና የመሳሰሉትን በአጠቃላይ
አፕሬንቲሱን ፣ ኤርሜኑን ፣ ቴክኒሻኑን ፣ የአየር ፖሊሱን ፣ በራሪውን ፣ መኰንኑን ፣ ባሌ ላላ ማዕረግተኛውን
እንደ አሮጌ ቁና ሜዳ ላይ በትኖ በስተ እርጅና የሰው እጅ እንዲያዩ የተደረጉበትን እንደ ጨዋታ ቆጥረነው ይሆን ?
    እነ ኰ/ል ብርሃኑ ከበደን ፤ ኰ/ል ብርሃኑ ውብነህ ፤ ኰ/ል ጣሰው ወዳጄነህን ….. ኰ/ል ጌታቸው መንገሻን ….
ኰ/ል መንገሻ ሁንዴን …. ኰ/ል የሺጥላ መርሻን ….. ኰ/ል ይልቃልን … አለማየሁ አጐናፍርን …. አለማየሁ ኃይሌን
…. ስንታየሁ አሽኔን … መስፍን መንግስቴን ….. በኃይሌ ደግፌን … ጂልቻ ዱራን …. ኰ/ል ነብዩን …. አሰፋ ተገኝን ፤
አቦነህ ነጋሽን … ዳዊት ወንዲፍራውን ፤ መስፍን ግርማን ……. በአጠቃላይ ስማቸው ያልተዘረዘሩትን የተዋጊውን ፣
የትራንስፖርትና የሄሊኮፕተር ስኳሮኖች በራሪና የቴክኒክ ባለሙያ ሲቪል ሰራተኞችን ሁሉ አገር አልባ አድርጐ …
እንዴትስ አይነት የአቪዬሽ ቬተራን ማህበር ሊመሰረት ይችላል ?
      ጀነራል ተጫኔ መስፍን ደም ገብረው በአቀኑት አየር ኃይል ውስጥ አበበ ተ/ኃይማኖት አንዳችም የአየር ኃይል
ትምህርትና ዕውቀት ሳይኖረው የቬተራኖቹ አየር ኃይል አዛዥ ሆኖ በራሪ ተማሪዎችን ሲሸልም በአፍሪካ ውስጥ
በበረራ ሰዓታቸው ተወዳዳሪ የሌላቸው የተዋጊ አውሮፕላን በራሪና ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜ የተቃጣባትን ወረራና
ጥቃት በጀግንነት የመከቱ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጅ ጀነራል ተጫነ መስፍን በዚህ አይነት በአሳላፊነት
መታየታቸው ምን ያክል አገር አልባ እንደሆንን አያሳይ ይሆን ? እውን ታዲያ ይሄ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ነው ?
እንደዚህ አይነት አገር የማታከብረው ቬተራንስ የት አገር ነው ያለው ?
     ጀነራል ተጫኔም በዚህ አይነቱ ሁኔታ እራሳቸውን ለማሳነስ ባይፈቅዱ እንዴት ጥሩ ነበር ? እነ ጀነራል መስፍን …
ጀነራል ተሻለ … ኰ/ል ጥላሁን ነብሮን የመሳሰሉት ባለ ወርቅዬ ታሪክ ባለቤቶች እንደ አገር አልባና ሁለተኛ ዜጋ
ተገልለውና ተጥለው ያለ ፎቶ ግራፍ ይኖሩ የለ ?
በእርግጥ በዚህ ዘመን ጀ/ል ተጫነ ከአቻዎቻቸው በተለየ ሁኔታ ከነ ሙሉ ክብራቸውና ጥቅማቸው በአገራቸው
በቬተራን ማዕረግ እየኖሩ ያሉ ብቸኛ ሰው ናቸው ። ቀደም ሲልም እንደ ጀ/ል ተጫኔ ሁሉ ጀ/ል ሰለሞን በየነ
በዚሁ በተንቆጠቆጠው ማማ ላይ ተሰቅለው እንዳሉ እናውቃለን ፤ ይህ እንግዲህ የልደታ አየር ምድብ አዛዥ
ተደርጐ ተሹሞ የነበረውን ሻለቃ ተስፋዬ ተገኝን ሳንዘነጋ ፣ የሚሊታሪ አታቼውንና ጀ/ሉን ኃይለ ሥላሴ ገብሩንም
ማ/ቴክ ረዳዕይና ማ/ቴክ ክንድያን እንዲሁም ካላዩ አፅበሃንም በማሰብ ነው …….. ። በእርግጥ አድሎው አይን
ያወጣ ቢሆንም ከወደ ኰረም ፣ አዲግራትና አድዋ የመወለድ ጣጣ ነው እያልን ቆይተናእነሆ ምክር እንለግሳለን …….
የአየር ኃይላችንን ታሪክ መፃፉን እናበረታታለን ። ይሁን እንጂ …….
    ዛሬ የሚፃፍ ካለ … አየር ኃይሉ እንዴት እንደተመሰረተ ብቻ ሳይሆን እንዴትም እንደፈረሰ ፤ ለአገር የደሙና የሞቱ
እንዴት እንደወንጀለኛ በየማጐሪያው እንደተጋዙ … ህብረ ብሄሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እንዴት ወደ አንድ ዘር
የሽፍቶች ስብስብነት እንደተቀየረ የሚተርክ ካልሆነ …. ጀ/ል ተጫነ መስፍን ፣ ኰ/ል አስፋው አየልኝንና
የመሳሰሉትን የትውልድም የታሪክም ተወቃሽ ፤ የአገርም ክህደት እንዳይሆን ይታሰብበት ።
     የአቭዬሽን ቬተራን አሶሴሽንም ከመመስረቱ በፊት አርበኛውን ከጐጠኛው መለየት ፤ እውነተኞቹን የአየር
አርበኞችና ቬተራኖች ከብቀላ ፍርደኝነታቸው ነፃ ማድረግና ዝነኛውን አየር ኃይል በጅምላ ከተለጠፈበት
የጨፍጫፊነት ስያሜ እንድናላቅቅ የየበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል ።
ጨረስን ።
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ
Image

Sunday, December 22, 2013

ከ35 ሚ.ብር በላይ በሙስና አከማችቷል የተባለ የጉምሩክ ኃላፊ ተከሰሰ


የአዳማ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የህግ ማስከበር ሃላፊ የነበረው አቶ ተመስገን ጉላን በራሱና በወንድሙ ስም ከገቢው ጋር የማይመጣጠን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና ንብረት ይዞ በመገኘቱ ክስ የቀረበበት ሲሆን በፖሊስ ክትትል ስር የነበረው ወንድሙም ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት ቀርቦ ክሱ ተነቦለታል፡፡ ቀደም ሲል ተከሳሹ ሁለት ዶዘሮችን በ15ሚ.ብር መግዛቱን ደርሼበታለሁሲል አቃቤህግ መግለጫ መስጠቱ ይታወሣል፡፡ 
የ33 ዓመቱ የህግ ማስከበር ሃላፊ አቶ ተመስጌን ጉላን ዓለሙ፣ በሌላ ስሙ ተመስገን ስዩም አሰፋ፤ ሁለት ክሶች የቀረቡበት ሲሆን በግብረአበርነት በተያዙት የወልደሚካኤል ሃለፎም አጠቃላይ አስመጪና የፈሣሽ ትራንስፖርት ድርጅት ባለቤት አቶ ወ/ሚካአል ሃለፎም፣ የታደለ ብርሃኑ አስመጪና ላኪ ድርጅት ባለቤት አቶ ታደለ ብርሃኑ፣ ስራው ያልተገለፀውና እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ ሹመይ እንዲሁም የ24 አመቱ የ1ኛ ተከሣሽ ወንድም አቶ ካህሣይ ጉላን ዓለሙ ደግሞ በአንድ መዝገብ ተከሰዋል፡፡ 
በአቶ ተመስጌን ጉላን ላይ በተናጠል የቀረበው 1ኛው ክስ፤ ተከሣሹ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በተለያየ ሃላፊነት ላይ ተመድቦ ከ1999 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ለስድስት ዓመታት ሲሠራ፣ አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ሲያገኘው ከነበረው ህጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን፣ በወንድሙ በካህሣይ ጉላን ስም በዳሽን ባንክ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ፤ በራሱ ስም ደግሞ በወጋገን ባንክ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በማስቀመጥ እና በማንቀሳቀሱ በአጠቃላይ በራሱና በወንድሙ ስም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ አስቀምጦ በመገኘቱ ተከሷል፡፡ 
ተከሣሹ በጓደኛው ብርሃኑ ዝናቡ ስም ስድስት ቦቴ መኪናዎችን ከነተሳቢያቸው፣ በአቶ ወ/ሚካኤል እና ታደለ ብርሃኑ አማካኝነት ከባንክ 10.5 ሚሊዮን ብር በመበደር ከራሱ 10.5 ሚሊየን ብር በመጨመር በድምሩ በ21 ሚሊዮን ብር ከሰኢድ ያሲን ኃላ.የተ.የግል ማህበር ገዝቶ መኪኖቹን በ2005 ዓ.ም ለተለያዩ ግለሰቦች በመሸጥ፣ በወንድሙ ስም ከቢዩ ኃ/የተ/የግ/ማህ ሁለት ዶዘሮችን በብር 15 ማሊዮን ብር መግዛቱ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በወንድሙ ስም በቦሌ ክ/ከተማ 325 ሜ.ካ ቦታ ላይ የተሠራ መኖሪያ ቤት በማፍራቱ እና በ2.8 ሚሊየን ብር በመሸጡም ተከሷል፡፡ 
ቀሪዎቹ ተከሣሾች ደግሞ፣ አቶ ተመስገን ሙስና ፈፅሞ ያገኘው ገንዘብ እና ንብረት መሆኑን እያወቁ መኪኖቹ የሚገዙበትን ሁኔታ ሃሣብ በማፍለቅና በመርዳት፣ የባንክ ብድር እንዲገኝ በማመቻቸት እና በመበደር እንዲሁም በራሱ አስመጪና የትራንስፖርት ድርጅት ስር መኪኖቹ ተጠቃለው እንዲሠሩ በማድረግ አቶ ወ/ሚካኤል ሃለፎም ተጠያቂ ሲሆን አቶ ታደለ ደግሞ በሙስና ወንጀል የተገኘው ገንዘብና ንብረት እንዳይታወቅ ለማድረግ አቶ ብርሃኑ ዝናቡ እና ካህሣይ ጉባል የቀበሌ መታወቂያ እንዲያወጡ በማመቻቸት እና በቀበሌው መታወቂያ መነሻነት የተጠቀሡትን ወንጀሎች እንዲፈፅሙ በማድረጉ  በወንጀሉ በመሣተፉ መከሠሡ ተመልክቷል፡፡ በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ፤ መኪኖቹ በስሙ እንዲገዙ፣ የባንክ ብድርም በስሙ እንዲበደር በማድረጉ ክስ የቀረበበት ሲሆን ወጣት ካህሣይ ደግሞ ለወንድሙ ውክልና ሠጥቶ በስሙ ገንዘብ እንዲያስቀምጥና እንዲያንቀሣቅስ እንዲሁም መኖሪያ ቤት እንዲገዛ በማድረጉ ተከሷል፡፡ 
ቀደም ብሎ በነበሩት ሁለት ቀጠሮዎች አቶ ተመስገን፣ አቶ ወ/ሚካኤል እና አቶ ታደሰ፤ ክሡ ተነቦላቸው መቃወሚያቸውን አቅርበው፣ አቃቤ ህግም ለመቃወሚያው መልስ የሠጠ ሲሆን ካህሣይ ጉላል ለመጀመሪያ ጊዜ ከትናንት በስቲያ ቀርቦ ክሡ ከተነበበለት በኋላ፣ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ከሌሎች ተከሳሾች ጋር አብሮ እያየው ነው፡፡ 
አቃቤ ህግ በተከሣሾቹ ላይ 14 የሠውና 14 የሠነድ ማስረጃዎችን ከክሡ ጋር አያይዞ አቅርቧል፡፡ 
ከትናንት በስቲያ የዋለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛው ችሎት፤ በመዝገቡ ላይ የተለያዩ ትዕዛዞችን ያስተላለፈ ሲሆን በእለቱ የቀረበው 5ኛ ተከሣሽ፤ የዋስትና መብቱ ተከልክሎ በቀጣይ ቀጠሮ ከጠበቃ ጋር እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት፣ መዝገቡን ለጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡ -

የአቦይ ስብሀት ነገር!


ከአሁን በፊት በዚሁ ርዕስ ፅሁፍ እንደፃፍኩ አስታውሳለሁ። አጋጣሚ ሆኖ ዛሬም ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ በምነሳበት
ወቅት ከዚሁ ርዕስ ሌላ ሀሳቤን በአንድነት ጭምቅ አድርጎ ሊገልፅልኝ የሚችል ርዕስ ሊመጣልኝ ስላልቻለ እንደገና
በዚሁ ርዕስ መጠቀሙን ወደድኩ።
አባይ ስብሀት በልበወለድ ዓለም የተፈጠሩ ሰው ቢሆኑ ኖሮ እጅግ በጣም አጨቃቃጪ፣ አነጋጋሪና የተለየ ስብዕና
ያላቸው ገፀ ባህርይ ሆነው የተቀረፁ እጅግ በጣም የተዋጣለት ገፀ ባህርይ ይሆኑ ነበር። የሚገርመው ነገር በእውኑ
ዓለም ያሉ ሰው ሆኖው ሳለ እንዲህ ዐይነት አነጋጋረና ግራ አጋቢ የሆነ ገፀ ባህርይ ያላችው ሰው መሆናቸው ነው።
ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ብዙውን ጊዜ በሚናገሩት ነገር ሁሉ ትኩረት ሳቢ ሆነው የምናገኛቸው። ለዛሬ ባለፈው
በህዳር 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት ተጋብዘው
በተናገሩት ላይ ይሆናል ትኩረት የማደርግው። አቦይ ስብሀት በዩኒርሰቲው ተገኝተው ፖለቲካዊ ሀሳባቸውን ለተማሪዎች እንደሚያካፍሉ
ዜናውን እንደሰማሁ ደግሞ ምን ሊሉ ይሆን ብዬ ነበር ከተወሰኑ ጓደኞቼ ጋር በመሆን እዚያ የተገኘሁት። እኔም የዩኒቨርሲቲው ተማሪ
መሆኔ ጠቀመኝና የተማሪነት መታወቂያን አሳይቼ ወደ አዳራሹ ዘለኩ። አባይ ስብሀት ሙሉ ለሙሉ ጥቁር የሆነ ሱፍ ለብሰው፣ ከፊት ለፊት
በተደረደሩ መደዳ ወንበሮች ላይ ተሰይመዋል። ከዚያ ድፎ ዳቦ እንዲቆርሱ ተደረገና ወደ ዝግጅቱ፣ ዋናው ጉዳይ ተገባ። በአንድ
የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት ተማሪ ጥያቄ አቅራቢነት አቦይ ስብሀት ለጥያቄዎቹ ሰፋ ያለ መልስ መስጠት ጀመሩ። ለዛሬ
ትኩረቴን እጅግ ከሳቡኝና ግርምት ከፈጠሩብኝ የአቦይ ስብሀት ንግግሮች የተወሰኑትን እዚህ ላይ እያነሳሁ ሀሳብ እሰጥባቸዋለሁ።
1. ሀገር ማለት
አቦይ ስብሀት “ሀገር ማለት ህገ መንግስቱ ነው፤ ሌላ ነገር አይደለም።” የሚል ነገር ተናግሯል። ይሄ ለእኔ ምን ማለት እንደሆነ ግለፀው
ብባል፤ እንዲህ በሌላ ምሳሌ ላስቀምጠው እችላለሁ። ትዳር ምንድነው ለሚለው ጥያቄ “ትዳር ማለት የጋብቻ ሰርቴፍኬት ማለት ነው።”
ብሎ የመመለስ ያህል ነው። ይሄ አነጋገር ስሜት ሊሰጥ ይችላል?! ትዳርን ትዳር የሚያድርገው የጋብቻ ሰርቴፍኬት አይደለም፤ የጋብቻ
ሰርቴፍኬት ትዳሩን ህጋዊ ያደርገው እንደሆነ እንጂ ራሱ ትዳር ሊሆን የሚችል ነገር አይደለም። ሀገርም እንደዚያ ነው፤ ያለ ህገ መንግስት
ሀገር ሊኖር ይችላል፤ ሀገር ከሌለ ግን ህግ መንግስት የሚባል ነገር አይኖርም። ህገ መንግስት የተፈጠረው በጣም ትናንት በሚባል ጊዜ
ሲሆን፤ ሀገሮች የተፈረጡትና የኖሩት ግን ለብዙ ሺህ ዓመታት ነው። ለምሳሌ፤ የእኛ ሀገር ታሪክ ብንወስድ እንኳ የሀገሪቷ ታሪክ ከሶስት
ሺህ ዓመት በላይ ሲሆን በህገ መንግስት ስም መተዳዳር የጀመርንበት ጊዜ ሲታይ ደግሞ አንድ መቶ ዓመትም አልሞላንም። ለነገሩ
በሀገራችን በጠመንጃ ጉልበት እንጂ በአግባቡ በህገ መንግስት የሚያስተዳድረን መንግስት እስከዛሬ አላገኘንም ወይም አልፈጠርንም።
2. ስለኤርትራውያን
አቦይ ስብሀት ስለኤርትራውያን ሲናገሩ “ኤርትራውያን ከኢትዮጵያውያን በላይ ነው ኢትዮጵያዊነትን በጣም ይፈልጋሉ፤ በአንፃሩ
ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት የኤርትራ መሬት ነው ህዝቡ አይደለም። አሰብ ቀይ ምናምን ይላሉ።” ብለው እርፍ! ምንም እንኳ ንግግሩ
እጅግ በጣም የሚገርም ቢሆንም የአርትራውያንን ኢትዮጵያዊነት ከአቦይ ስብሀት መስማቴ ጥሩ ለውጥ ነው እላለሁ፤ ኤርትራውያን
ከእኛ በላይ፣ ከኢትዮጵያውያን በላይ ኢትዮጵያዊነትን ይሰማቸዋል የሚለውን ግን ቀልድ ነው ሊሆን የሚችለው። ሲጀመር እንዲህ
ብሎ ለመናገር በመጀመርያ ህዝቡ ስለዚህ ጉዳይ ያለው አቋም ተጠንቶ፤ በደንብ በተጠናቀረ መረጃ ተደግፎ ነው መቅረብ የነበረበት።
ከሁሉም በላይ እጅግ አድርጎ የሚያሳዝነው ደግሞ ኢትዮጵያውያን የኤርትራን መሬት እንጂ ህዝቡ አይፈልጉትም መባሉ ነው። እኔ
የማውቀው በተቃራኒው ነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለኤርትራውያን ጥልቅ የሆነ ፍቅር እንዳለው ነው፤ አሁን ይሄ ሁሉ ነገር ከተፈጠረ
በኋላ እንኳ እንደ ራሱ ህዝብ እንደወንድም ህዝብ እንጂ እንደ ጎሮቤት ህዝብ ወይም እንደባዕድ ህዝብ የሚያያቸው አይደለም።
አቦይ ስብሀት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ነገሮች እየሰከኑ ሲሄዱ ለምሳሌ በኤርትራ ያለውን ስርዓት
ሲቀየር በሆኑ ቅርፅ ተባብረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነታውን ማጠናከር የሚችሉበት እንድል እንዳለ፤ በፌዴሬሽንም
በኮንፌደረሽንም በሌላም መልኩ የነበራቸውን አንድነት መመለስ የሚችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩት በዚያን
ቀን ከተናገሯቸው አዎንታዊ ንግግሮች አንዱ ነበር። ስለ ኤርትራው ፕሬዚደንት ሲናገሩ ኢሳይያስ የሚፈልገው አጀብና እዩኝ እዩኝ
ማለት እንጂ ሌላ ነገር አይደለም ብሏል፤ እርሱ ገንዘብም አይፈልግም ብሏል። የምን ገንዘብ እንደሆነ ግልፅ ባያደርጉትም የእርዳታ
ገንዘብ ማለታቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት የሚቻል ነው። ሀበሻ አይደሉ፤ እኛ እና እርሱ ልዩነታን እዚህ ላይ ነው ማለታቸው
መሆን አለበት በቅኔ!
ይልቅ የሰሞኑ አንዱ ገጠመኝ ልንገራችሁ አንድ ኤርትራዊ ከሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተደባልቆ
እንደመጣ ሲነግሩኝ፤ እንዴት ነው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያውያንን የሚለዩበት ብልሀት አጥተው ነው ወይስ የኤርትራውያን
ኢትዮጵዊነት ተቀብለው ነው እንደዚህ ወጣት ያሉ ኤርትራውያን በነፃ ከእኛ ዜጎች ጋር ወደ ሀገራችን እያመጡ ያሉት ያስባል። ሻዕቢያ
ካልላካቸው ምንም ችግር የለውም፤ ኢትዮጵያም ሀገራቸው ነው። ድሮም ቢሆን በሻዕቢያ ፕሮፖጋንዳ ተታልለው ነው እንገንጠል
ብለው የሄዱት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ስለጠላቸው አልነበረም። አቦይ ስብሀት እንዳሉት እነዚህ ኤርትራውያን እየመጡ ያሉት
ትክክለኛ ኢትየጵያውያን እነርሱ ናቸው ተብሎ ከሆነ ግን በማን መንግስት እየተዳደርን እንደሆነ መጠየቃችን አይወሬ ይሆናል። “እናንተ
ከኤርትራውያን ያነሳችሁ ኢትዮጵያውያን ናችሁ” የሚለን መንግስት መቼውም ቢሆን ጤነኛ መንግስት ሊሆን አይችልም፤ የእኛ
መንግስትም የመሆን እድል የለውም።
3. የቀበጡ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች
በእስር ላይ ስለሚገኙ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ተጠይቀው ሲመልሱ “ይሄ ስርዓት በስንት መስዋዕትነት የመጣ ስርዓት ነው፤ በዚህ ላይ
ሁኔታ በመጣ ስርዓት ላይ ማንንም እንዲቀብጥ ሊፈቀድለት አይገባም። መለስ በፓርላማ ስላንዳንድ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች
አስመልክቶ ሲናገር ጉዳት እስካላደረሱ ድረስ ወንጀለኛ መሆናቸውን እያወቅንም እንታገሳቸዋለን ሲል ሰምታችሁት ይሆናል ተሳስቷል።
ማንም ሰው በህገ መንግስቱ ላይ በስርዓቱ ላይ የመቅበጥ ምልክት ሲያሳይ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም፤ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።
ስለዚህ ማንም ቀበጥ በስርዓቱ ላይ እንዲጫወትበት አንፈቅድም” ብሏል። እንግዲህ በእርሳcው አባባል ከሄድን እነ አንዷለም አራጌ፣ እነ
ርዕዮት ዓለሙ፤ እነ ውብሸት ታዬ፣ እነ እስክንድር ነጋ በቅብጠት ነው የታሰሩት ማለት ነው። በእስር ጉዳይ ላይ ቀብጠት አለ እንዴ!
ለዚያውም ብእኛ ሀገር! የኖርዌይ መንግስት እንደዚያ ቢል ብዙም ላይገርም ይችላል፤ ምክንያቱም የእስር ቤታቸው ሁኔታ እጅግ
የሚያማልል ነው። ከእኛ አንፃር ስታየው! በቃልቲ ለመታሰር እንዴት ነው ቅብጠት የሚሆነው። እነርሱ የታሰሩት የነፃነት የፍትህ ጥያቄ
እንስተው እንጂ ቀብጠው አይመስለኝም። እኔም ይሄን ጉዳይ አንስቼ ቅብጠት ሊሆን እኮ ነው በአቦይ ስብሀት አተያይ! ጠያቂው በመቀጠል “እነዚህ የታሰሩት ጋዜጦኞች በአንድ በእኩል ወንጀለኛ ተብለው ታስሯል በሌላ በእኩል የሀሳብን በነፃነት የመግለፅ
ታጋዮች ተብለው በዓለም አቀፍ እየተሸለሙ ነው ይሄ ሁለቱ ነገር አይጋጭም ወይ?” ብሎ ሲጠይቃቸው፣ ፈገግ ብለው ያሰራው አካል
እኮ አይደለም እየሸለማቸው ያለው! በማለት ተሳልቋል።
4. ስለሰማያዊ ፓርቲ
“ሰማያዊ ፓርቲ የምን ፓርቲ እንደሆነ ግራ የሚገባ ነው፤ የሃይማኖት ፓርቲ ይሁን የፖለቲካ ፓርቲ ይሁን አይታወቅም” አሉ።
በመቀጠል ደግሞ “ሰማያዊ ፓርቲ ሙስሊም ወንድሞቻችን ሲል ሰምታችሁ ይሆናል። እነርሱ ናቸው የሞስሊሞች ወንድም የሚሆኑት!
አቤት ሙስሊሞቹ ሲጠሏቸው ብታዩ! ወደ እኛ እየመጡ ለምን እንዚህን አታሳርፉልንም ነው እኮ የሚሉን።” በማለት ተናግሯል። እዚህ
ላይም መረጃ ሰብስበው ጥናት አድርገው አይደለም የተናገሩት። የተወሰኑ ሙስሊም ጓደኞቻቸው ጋር በጉዳዩ ላይ እውርተው ሊሆን
ይችላል፤ ነገር ግን በጣት የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ሀሳብ ማወቅና በብዙ ሚሊዮን የሚገመቱ ሙስሊሞች
ለሰማያዊ ያላቸውን አመለካከት ማወቅ የተለያየ ነገር ነው።
5. ስለሀብት ክፍፍል እና ስለኢህአዴግ ርዕዮተ ዓለም
ስለሀብት ክፍፍል ሲናገሩ ደግሞ “በአለም አንደኛ ፍትሀዊት ሀገር ዶብብ ኮርያ ስትሆን፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ሁለተኛ ናት፤ አሜሪካ ደግሞ
የመጨረሻዋ ነች አሉ። እንግዲህ አሜረካን በደንብ የምታውቁ መስክሩ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሁኔታ እንኳ በቅርብ እናውቀዋለን፤
ምስክር መጥራት የሚያስፈልገን ነገር አይደለም። አቦይ ስብሀት ስለኢህአዴግ ርዕዮተ ዓለም ሲናገሩ፤ “ኢህአዴግ ቀኝ ዘምም ግራ
ዘመምም አይደለም፤ ‘centrist’ ነው ‘pragmatic’ ነው” አሉ። አቶ ልደቱ አያሌው “ሶስተኛ አማራጭ” የሚሉትም ይሄ “centrist”
የሚባለውን በሌበራል ዴሞክራሲ ውስጥ የሚመደብ ርዕዮተ ዓለም ነው። ማንም ሰው ወይም ፓርቲ በቀኝ አክራሪነት ወይም በግራ
አክራነት ላለመመደብ በስም “centrist” መባለን ይፈልጋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በእኛ ሀገር በትክክል “centrist” ሊባሉ የሚችሉ
ፓርቲዎች ያሉ አይመስለኝም። በፓርቲው ውስጥ ወደ ቀኝ ጥግ የመሄድ ዝንባሌ እንዳለ ሆኖ በፕሮግራም ደረጃ ወደ “centrist”
የሚጠጋ አቋም ያለው አንድነት ፓርቲ ብቻ ይመስለኛል። ሌላው ሁሉ አንድም በቀኝ፣ አንድም በግራ የሚመደብ ነው። የኢህአዴግ
እንኳ ግራ ዘመምም ለመሆኑ ክርክር ውስጥም የሚገባ አይደለም።
አቦይ ስብሀት ወደ ጫካ ሲገቡ እድሜያቸው ሰላሳ ዘጠኝ እንደነበረ ራሳቸው በዚያው መድረክ ላይ የተናገሩ ሲሆን አስራ ሰባት ዓመት
በትግል 23 ዓመት ደግሞ በስልጣን የቆዩ ከመሆናቸው አንፃር አሁን የሰባ ዘጠኝ ዓመት አዛውንት ናቸው ማለት ነው። ነገር ግን አሁንም
ጠንካራ እንደሆኑ ታዝቤያለሁ፤ የዓይን መነፅር እንኳ ሳያድርጉ ነው ሲንቀሳቀሱ የነበረው። ነገር ግን አነጋገራቸው ሁሉም አይቶ
እንዳሳለፈ ሰው ሆኖ አላገኘሁትም፤ ይልቅ ገና የፖለቲካ ስሜቱ እንዳልነበረደለት ጎረምሳ ነው በትዕቢትና በማን አህሎኝነት ሲናገሩ
የነበሩት። በተለይ ስለተቃዋሚዎች ሲናገሩ ያላቸውን ጥላቻ በግልፅ ያስታውቅ ነበር። ጥላቻ በዚህ ዕድሜ በጣምም ጥሩ አይደለም።

Wednesday, December 18, 2013

“አና ጐሜዝ አሁንም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይቆረቆራሉ” – አቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)


ከአቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)
ከአና ጐሜዝ ጋር ከአንድ ሠዓት ተኩል ለማያንስ ጊዜ ነው የቆየነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ከእኛ ጋ የተገናኙት ገለፃ ለማድረግ አስበው ሣይሆን የእኛን አስተያየት ለመስማት ነበር፡፡ ውይይቱ፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነበር፡፡ በወቅቱ ከሞላ ጐደል ተደጋጋፊ እንጂ የሚቃረኑ ሀሣቦች አልተነሱም፡፡ በእኔ በኩል፣ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ ችግርና አደጋ ላይ እንደሚገኝ፣ ኢትዮጵያም መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሆነች፣ ከፊታችን አሳዛኝና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን አስመልክቶ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎች እያሣየ መሆኑን ገልጫለሁ፡፡

“ሰላማዊ ትግል” የሚለው “ሰላማዊ እንቅልፍ” የሚል ደረጃ ላይ ለመድረሱ ዋነኛ ምክንያቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትከሻቸውን ታስረው ለመንቀሣቀስ ያለመቻላቸው ነው፡፡ የህዝባዊ ስብሰባዎች እና የሰላማዊ ሰልፎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ መታገድ፣ የአዳራሽ መከልከል፣ ልሳናችንን እንዳናሳትም መታገድን ጨምሮ በርካታ ሕገ መንግስታዊ ጥሰቶች እየተፈጸሙብን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሕገ መንግስቱን እየጣሱ ነው እየገዙን ያሉት፡፡ ሕገ መንግስቱ እየተተገበረ ነው የሚያስብል ሁኔታ የለም፡፡ ከድጡ ወደ ማጡ እየገባ ነው ያለው፡፡ ነገሮች ተባብሰዋል፡፡
የስልጣን ኃይል ሚዛኑ በማን እጅ ላይ ይገኛል ብሎ መጠየቅ እስኪያስፈልግ ድረስ ሁሉም ነገር ተወሳስቧል፡፡ በሚኒስትር ደረጃ የተቀመጡት ሲቪሎቹ ናቸው ወይስ ከጀርባ የሚያስተዳድሩን አሉ? ሂደቱ ሀገሪቱን ወዳልተፈለገ ቀውስ ሊወስዳት የሚችል ትልቅ አደጋ ነው፡፡
ከአና ጎሜዝ ጋ በተተወያየንበት ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲ አንድ ተወካይ ብቻ በፓርላማ እንደሚገኝን ተናግሬያለሁ፡፡ አስቀድመውም ያውቁታል፡፡ በ1997 ዓ.ም. የተቀማውን ድምጽ ትተን 180 የሚሆኑ ተቃዋሚዎች በፓርላማው መቀመጫ ነበራቸው፡፡ አሁን ግን ወደ አንድ ወርዷል፡፡
ኤልሳቤት ሃይኒ የተባለች የቢቢሲ ጋዜጠኛ ያነሣችውን ጥናት ለአና ጎሜዝ አሳይቻቸው ነበር፡፡ አንድ ፓርቲ በምርጫ ከ51-59 ፐርሰንት አግኝቶ ካሸነፈ ታላቅ ድል ነው፡፡ ከ60-69 አምጥቶ ካሸነፈ “ዝረራ” የሚባል ውጤት ነው፡፡ ከ70-79 አምጥቶ ካሸነፈ ደግሞ የሕዝቡን ጥያቄዎች የመለሰ ፓርቲ ነው፡፡ ከ80-89 የሚያገኝ ፓርቲ ግን የሚፈራ፣ አምባገነን፣ ጉልበተኛ ፓርቲ ነው፡፡ ከ90-99 ፐርሰንት ከተገኘ ደግሞ ምርጫ አልተካሄደም ማለት ነው ይላል፡- ጥናቱ፡፡ በኛ ሀገር ይኸው “99” አልፎ ዜኀር ነጥብ ስድስት ሁሉ ተጨምሮበታል፡፡ ስለዚህ ይሄ በግልፅ የሚያሣየው ፍፁም የዴሞክራሲ ስርዓት መጣሱን ነው፡፡ ምህዳሩ ተዘግቷል ተደፍኗል፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲዎች በየጊዜው የምናቀርባቸው የውይይት እና የእንደራደር ጥያቄዎች ከስልጣን ጋር ግንኙነት የላቸውም፡፡ ሀገራዊ አጀንዳዎች ናቸው፡፡ ብሔራዊ ውይይት፣ ብሔራዊ ንግግር ይከፈት ብለን ደጋግመን ብንጠይቃቸው ባለሥልጣናቱ አሁንም ያሾፋሉ፡፡ “የምርጫ ስነምግባር ደንብ” ፈርሙ እንባላለን፡፡ እንኳን “የምርጫ ስነምግባር ደንብ” ይቅርና የማንወደውን፣ እየተጐዳንበት ያለውን “የፀረ ሽብር አዋጅ” ተቀብለን ነው የምንተዳደረው፡፡ ምክንያቱም በሕግ የተደነገገ ነው፡፡ እንዴት ተደርጐ ነው “የምርጫና ስነምግባር ህግ” በምክር ቤት ጸድቆ በነጋሪት ጋዜጣ በወጣ ህግ ለይ ዳግም ፈርሙ የምንባለው? የሚል ሀሳብም አንስቻለሁ፡፡
መንግስት “ፀረ ሽብር” አዋጁን የማጥቂያ መሣሪያ አድርጎታል፡፡ ሽብርተኝነት የአውሮፓም፣ የአሜሪካም ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ የፀረ ሽብር ህግ አውጥተዋል፡፡ ወደ እኛ ሃገር መለስ ስንል የፀረ ሽብር ሕጉ የወጣው ሽብርተኞችን ለመቅጣት ብቻ ሳይሆን፣ ሰላማዊና ሕጋዊ ፓርቲዎችን ጭምር ለማጥቃት ነው፡፡
ሽብርተኝነትን በማንኛውም መልኩ፣ በየትኛውም ገፅታው እንቃወመዋለን፡፡ ሽብርተኝነት ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በአፍጋኒስታን፣ በፓኪስታን፣ በኢራቅ፣ በናይጄሪያ /ቦኮ ሀራም/ እናውቀዋለን፡፡ እዚህም በሕዝብ፣ በህፃናት፣ በእርጉዝ ሴቶች፣ በሽማግሌዎች፣ በወጣቶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እናውቀዋለን፤ እንቃወማለንም፡፡ ኢትዮጵያውያን በባህላችን፣ በአስተዳደጋችን፣ በኃይማኖታችን፣ በእምነታችን… ለሽብርተኞች የተጋለጠ ስነ ልቦና የለንም፡፡ “ሽብርተኝነት” ይምጣብን የሚል ልመና ካልተያዘ በቀር ኢትዮጵያዊ ሽብርተኝነት የለብንም፡፡ የ“ጸረ ሽብር” አዋጁ በሽብርተኝነት ከፈረጃቸው ፓርቲዎች መካከል… ለአብነት ግንቦት 7፣ ዋና መቀመጫው በአሜሪካና አውሮፓ ከተማዎች ነው፡፡ ይሄ እንቆቅልሽ ይሆናል፡፡ አወሮፓውያን ከተማዎቻቸውን ለአሸባሪዎች ምሽግነት መርጠዋል ማለት ይሆን?
ሌላ እንቆቅልሽም አለ፡፡ ስርዓቱ “ሽብርተኛ” ብሎ ያሰራቸው ሰዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን እና ክብሮችን እያገኙ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ አንዱአለም አራጌ… ወዘተ በፀረ ሽብር አዋጁ ነው የታሰሩት፡፡ በ”ሽብርተኝነት” የተፈረጁት ግን በአሜሪካና፣ አውሮፓ ከተማዎች እንደፈለጋቸው እየተዘዋወሩ ነው፡፡ አውሮፓና አሜሪካ ሽብርተኞችን እየደገፉ ነው ማለት ነው?
የፖለቲካ ምህዳሩ ከድጡ ወደ ማጡ እየገባ ነው፡፡ የሕዝብን ችግር፣ እሮሮ በሳዑዲ አረቢያ በዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው እልቂት፣ የስራ አጥነት፣ በስታቲስቲክስ ማሣየት ይቻላል፡፡ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የኑሮ ውድነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የሙስና መንገስ፣ የስርዓቱ መገለጫ ሆኗል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች የአውሮፓ ህብረትን ትኩረትና ዕይታ ሊስቡ ይገባል፡፡ ይሄን የምንለው ግን ትግሉን ታገሉልን ለማለት አይደለም፡፡ ትግሉ የራሣችን ነው፡፡ ትግሉ የኢትዮጵያውያን ትግል ነው፡፡ ነገር ግን እናንተም ደግሞ ባላችሁ ደረጃ፣ ባላችሁ የግንኙነት መስመር፣ የሚደረገውን ነገር ለማድረግ ጥረታችሁን ቀጥሉ ብለናቸዋል፡፡ የተወሰነ ድጋፍ ካልተደረገ ወደፊት ሊመጣ የሚችለው ችግር ሁላችንንም ጉዳት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ጉዳቱ ስርዓቱን የሚመሩት ሰዎችንም ጭምር የሚምር አይደለም፡፡
አና ጐሜዝ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ያላቸው ግንዛቤና የመቆርቆር አቅም አሁንም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተረድቻለሁ፡፡ በውይይቱ ወቅት እንኳ ከሌላ የአውሮፓ ፓርላም አባል ጋር ያለመስማማት ሁኔታን አይቼባታለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብና፣ ኢትዮጵያ ልታከብራቸው ከሚገቡ በዓለም ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ስብዕና ካላቸው ሰዎች መካከል አንዷና ትልቋ አና ጐሜዝ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ጐሜዝ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ ይከታተላሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ያላቸው ተቆርቋሪነት ከ1997 ዓ.ም. ከነበረው የበለጠ ነው፡፡ የሰጧቸው ቃለ ምልልሶች ዛሬም ለኢትዮጵያ ሽንጣቸውን ገትረው እንደሚከታተሉ ያመላክታሉ፡፡
በውይይቱ ወቅት “እኔ እኮ ዛሬ ኢትዮጵያ ለመግባት የቻልኩት አቶ መለስ በሕይወት ባለመኖራቸው ነው፡፡ በሕይወት ቢኖሩ እዚህ ሀገር አልገባም” ነበር ያሉን፡፡ ከፍተኛ ጥንካሬና ተቆርቋሪነት ነው ያየሁባቸው፤ ውይይታችን የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞችን ጭምር የሚመለከት ነበር፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ ልዑካን ቡድን ኃላፊ በስብሰባው ላይ አልተገኘችም፡፡ እና ምክትሏ ሆና ነው ስብሰባውን የመራችው፡፡ “ኃላፊዋ በአሁኑ ሰዓት እዚህ ስብሰባ ላይ ያልተገኘችው ቃሊቲ እስረኞችን ለመጠየቅ ሄዳ ነው” ብላን ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ተወካዮች መጥተው፣ ጠ/ሚኒስትሩ ከፈቀዱ በኋላ “ቃሊቲ” ሄደው ተከልክለው ሣይገቡ ነው የተመለሱት፡፡ እርሷም በዛው እለት በዚህ ጉዳይ ተበሣጭታ ወደ ሃገሯ ተመልሣ ለምክትሏ ስለሁኔታው ገልጻላት ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የእስረኞቹን ጉዳይ በበቂ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያላቸው እውቀት አናሳ ነው፡፡ የሚያውቁት ጥቂቱን ነው፡፡ ግንዛቤ አላቸው ከተባለ ደግሞ ብዙ ትክክል ያልሆነ መረጃዎችን የያዘ ነው፡፡ ለምሣሌ ሀገሪቱ በልማት እየተራመደች መሆኗን፣ ኢትዮጵያ የአውሮፓ የፀረ ሽብር ከፍተኛ አጋር መሆኗን፣ የአፍሪካ መዲና መሆኗን… ይሄም የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ እንሚያሣይ የሚገልፁ አሉ፡፡ የአና ጐሜዝን ሩብ ያህሉን የማያውቁ አሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ከኛ ለመስማት ስለነበር ፍላጐታቸው የሚያውቁትን ለኛ ለመናገር አስፈላጊ አድርገው ላይመለከቱት ይችላሉ፡፡ በውይይቱ ወቅት ሁሉም ጊዜ ሰጥተው በጥሩ ሁኔታ ነው ያዳመጡን፡፡ በትኩረት ያነሱት ግን በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን መብዛት ነው፡

ኦባንግ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር ተነጋገሩ


“በራችሁን ዘግታችሁ እርቅ አውርዱ”
* “ባለውለታችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ አዝኖባችኋል፣ አርቃችሁ እዩ”
“በትግሉ ወቅት ለነጻነት ስትዋደቁ ኢትዮጵያ በጋምቤላ አኙዋክ ምድር ላይ ሙሉ ከለላና ዋስትና በመስጠት ያበረከተችው አስተዋጽኦ የሚረሳ ነው? ከነጻነት ታጋዮችችሁ ጎን በመሰለፍ ብረት ያነሱ የአኙዋክ ኢትዮጵያውያን ልጆች መስዋዕትነት ይዘነጋችኋል? አሁን ድረስ የትግሉ የመስዋዕትነት ቁስላቸው ያልዳነ የአኙዋክ ልጆች እንዳሉ ትዘነጋላችሁ?” በማለት የተናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ ናቸው።
በታላላቅ መድረኮችና በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተሰሚነታቸውና ስብዕናቸው እየጎላ የሄደው ጥቁሩ ሰው ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ከላይ የተገለጸውን ህሊና የሚፈታተን ጥያቄ ያቀረቡት ለደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን ነው። ለረዥም ሰዓት ጊዜ ወስደው ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ የጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ እንደዘገበው አቶ ኦባንግ ዶ/ር ባርናባን ያገኟቸው አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነበር።
በጁባ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ ይፋ ከተደረገበት አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ በተያዘ የውይይት መርሃ ግብር የተገናኙት ዶ/ር ባርናባና አቶ ኦባንግ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተው መነጋገራቸው ታውቋል። አቶ ኦባንግ የደቡብ ሱዳን የነጻነት ትግል ወቅት ኢትዮጵያ በመንግስት ደረጃ የሰጠችውን ሙሉ ድጋፍና፣ ድንበር ሳይከልላቸው በሁለቱም አገራት የሚገኙት የአኙዋክ ልጆች ትግሉን የነፍስ ዋጋ በመክፈል መደገፋቸውን በማስታወስ በውይይቱ ወቅት ያነሱት ያለ ምክንያት አልነበረም።
“በጆን ጋራንግ ይመራ የነበረው ትግል ፍሬ አፍርቶ ደቡብ ሱዳን ነጻ ስትወጣ የማይረሳ ውለታ ለሰራቸው ኢትዮጵያና የአኙዋክ ልጆች የተከፈላቸው ብድር አሳዛኝና የወደፊቱን ጊዜ ያላገናዘበ ነው” በማለት በውይይቱ ስለተነሱ ነጥቦች ማብራሪያ የሰጡት አቶ ኦባንግ፣ “ለህዝቦች ነጻነትና ለሰብአዊ መብት መከበር የታገለ ድርጅትና አመራሮች ለነጻነታቸው የተከፈለላቸውን የደም ዕዳ ያወራረዱትና እያወራረዱ ያሉት ከወያኔ መሪዎች ጋር በማበር ከለላ የጠየቁ ህጋዊ ስደተኞችን እያፈኑ ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት መሆኑ አሳዝኖኛል። ኢትዮጵያዊያን አዝነዋል” በማለት ነበር።
ህጋዊ ከለላ የጠየቁ ስደተኞች ቶርቸር እንዲደረጉ፣ እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና ኢሰብአዊ ግፍ እንዲፈጸምባቸው ለአምባገነኖች አሳልፎ መስጠት ዘግይቶም ቢሆን ዋጋ እንደሚያስከፍል አቶ ኦባንግ አስረግጠው ተናግረዋል። በ1993 የአኙዋክ ጄኖሳይድ /የጅምላ ጭፍጨፋ/ ሸሽተው በስደት ደቡብ ሱዳን የገቡ የአኙዋክ ልጆችን ለገዳዩ የወያኔ አንጋች ሃይል ማስረከብ መቆም እንዳለበት ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ይህንን ተግባር የፈጸሙትም ቢያንስ ዓለም አቀፋዊውን ህግ ተላልፈዋልና ሊጠየቁ ይገባል። እርስዎም ይህንኑ የማስፈጸም ሃላፊነት ይኖርብዎታል” በማለት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የአኙዋክና የበኩር ልጆችና የደቡብ ሱዳን ግንኙነት ከድንበር ያለፈ የደም ትስስርና ኢትዮጵያ የማይረሳ ውለታ በመክፈል ያከበረችው ውህደት በመሆኑ መንግስታቸው ቆም ብሎ ሊያስብ እንደሚገባው አቶ ኦባንግ ምክር አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ አስተማማኝ ከለላና ዋስትና በመስጠት የፈጸመችውን ሊዘነጋ የማይችል ተግባር አለማክበር ለወደፊቱ ወዳጅ የሚያሳጣ ብድር ለራስ የማስቀመጥ ያህል እንደሆነም በወጉ እንዲገነዘቡ ሚኒስትሩን ተማጽነዋል።
photoአምባገነኑና በህዝብ የሚጠላው የህወሃት አገዛዝ እድሜ አሁን ካለው ትውልድ እድሜ በላይ ዘሎ የሚሄድ ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ማቅረብ፣ መተዋወቅና መልካም ግንኙነት መመስረት ለወደፊቱ ጠቃሚ መሆኑንም አስረድተዋል። እርሳቸው በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄም /አኢጋን/ ከተመሰረተበት ዓላማ አንጻር የደቡብ ሱዳን መንግሥት ህወሃት/ኢህአዴግን ለማስደሰት ሲል ኢትዮጵያዊያን ላይ ፈጸመውና እየፈጸመ ባለው ተግባር ያዘኑ ወገኖች የቀድሞውን የፍቅር መንገድ እንዲከተሉ አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ሕዝብ ያልወደደው መንግስትና ህዝብ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት መጨረሻው ኪሳራ በመሆኑ የደቡብ ሱዳን መንግስት ሊጠነቀቅ እንደሚገባው አቶ ኦባንግ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል። ከደቡብ ሱዳን ተነስቶ በጋምቤላ አድርጎ ወደ ኬኒያና ጅቡቲ ይዘረጋል የተባለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ሕዝብን በመግፋትና በመበደል ከቶውንም ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ያለማቅማማት ጠቁመዋል።
ህዋሀት በጋምቤላ ንጹሃንን ከቀያቸው በጠመንጃ ሃይል በማባረር፣ መሬታቸውን በሳንቲም ቸብችቦ፣ የህይወታቸው ዋስትና የሆነውን ደናቸውን አስጨፍጭፎ፣ ለምን በማለት የጠየቁትን አስሮና ገድሎ ያቋቋመው ኢንቨስትመንት በዜሮ መጣፋቱን ለአብነት ጠቅሰው ማስረዳታቸው የጠቆሙት ጥቁሩ ሰው “ኢንቨስትመንት መልካም ነው። ህዝብ ካልተቀበለው ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ህዝብ ይሁንታ የማይሰጠው ኢንቨስትመንት ፍሬ አያፈራም። ከውስጥም ከውጪም ያላችሁን ግንኙነት መርምሩ። ያዘኑባችሁ ተበራክተዋል” ሲሉ መክረዋል።
በአዲስ የምትቋቋመው “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” ለደቡብ ሱዳን ወንድምና እህቶች ጭምር ቦታ በማዘጋጀት መሆኑንን አቶ ኦባንግ አረጋግጠው “በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ወቅት ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለዲሞክራሲ መከበርና ለነጻነት በተከፈለው መስዋዕት የተገኘውን ድል የደቡብ ሱዳን መንግስት በአግባቡ እየተጠቀመበት አለመሆኑን አቶ ኦባንግ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል። አዲሲቷ ደቡብ ሱዳን ከድል በኋላ የትግሉን መሐላ ሙሉ በሙሉ ረግጣለች በማለት መሪዎቹን ወቅሰዋል።
ከድል በኋላ በደቡብ ሱዳን በርካታ ችግሮች መከሰታቸውን በመዘርዘር የማስጠንቀቂያ ምክር መሰንዘራቸውን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሁን ባለው ሁኔታ በደቡብ ሱዳን ባሉ ሃያ አንድ ጎሳዎች መካከል ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም። ስለዚህ በራችሁን ዘግታችሁ እርቅ አውርዱ። በቀደሙት ሰማዐታቶች ደምና አጥንት ላይ ዴሞክራሲን መስርቱ። ይህንን ካላደረጋችሁና አሁን በያዛችሁት የአምባገነንነትና የአንድ ሰው ወይም ጎሣ የበላይነት መንገድ ከቀጠላችሁ ጣጣው ወደኛም ያመራል” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አስጠንቅቀዋቸዋል። አሁን ያለው የውስጥ ሽኩቻ መልኩን ሳይቀይር መፍጠን እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋቸዋል። (አቶ ኦባንግ ይህንን ለውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ የተናገሩት እሁድ መፈንቅለ መንግሥት ከመሞከሩና አሁን ደግሞ በዘር /ጎሣ/ መስመር ተከፋፍለው ደቡብ ሱዳናውያን መጫረስ ከመጀመራቸው አንድ ቀን በፊት ነበር)
ambassador 1
አቶ ኦባንግ በአሜሪካ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር
በደቡብ ሱዳን እውነተኛ እርቅ ለማውረድ የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት አንድ ግብረ ሃይል ወደ ጁባ እንደሚልክ መረጃ እንዳላቸው የጠቆሙት አቶ ኦባንግ በውይይቱ ወቅት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቀና ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል። በመጨረሻም አቶ ኦባንግ የሚመሩት ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ የእርቅ ደጆች የሚከፈቱበት አግባብ ላይ ከሚመለከታቸው ተጽዕኖ አድጊራዎችና አቅሙ ካላቸው አካላት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል። በማያያዝም “እኛ ሩቅ እያየን እየሰራን ነው። እኛ በስፋት እያሰብን በመራመድ ላይ ነን። በስፋት አስበን፣ ሩቅ እያየን ስንሰራ እናንተንም አንዘነጋም። በተቃራኒው እናንተ ለነጻነታችሁ የተዋደቁላችሁን የራሳችሁን ዜጎች እያነቃችሁ ለወያኔ አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ። ደም ያፈሰሱላችሁንና አጥንታቸውን የከሰከሱላችሁን ውድ ዜጎች ሳትታረቁ በምድራቸው ላይ ቱቦ ዘርግታችሁ ብር ልታመርቱ ታቅዳላችሁ። ይህ ከቶውንም ጤነኛ አካሄድ አይደለምና ህዝብን አስቀድሙ። አብረን እንስራ። ይህ መልካም ጅምር ነው” በማለት መሰናበታቸውን አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክትር አቶ ኦባንግ ሜቶ ከደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ጋር ለመወያየት የቻሉት ሚኒስትሩ አሜሪካ ከመምጣታቸው በፊት በኤምባሲያቸው አማካይነት አስቀድሞ በተያዘ መርሃ ግብር መሰረት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ ስለ ሰጡት አስተያየትና ምላሽ አቶ ኦባንግ በዝርዝር ለመናገር አልፈለጉም። አቶ ኦባንግ በትውልድ አኙዋክ ቢሆኑም እርሳቸው የሚመሩት ድርጅት /አኢጋን/ ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው ውጭ በስደት በሚሰቃዩበት ቦታ ዘር፣ ቀለም፣ ጎሣ፣ ቋንቋ፣ ወዘተ ሳይለይ ፈጥኖ በመድረስ እርዳታ በማድረግ እርሳቸውም በተመሳሳይ ተግባር ተጠምደው በቅንነት በማገልገል እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የእርቅ ደጆች እንዲከፈቱ አግባብ ካላቸውና አቅሙ ካላቸው ክፍሎች ጋር እየሰራን ነው በማለት አቶ ኦባንግ ለሚኒስትሩ የገለጹላቸውን ሃሳብ እንዲያብራሩ ከጎልጉል ተጠይቀው “ሁሌም የእርቅ ደጆች እንዲከፈቱ እንሰራለን። ይህ የጋራ ንቅናቄውና አርቀው የሚመለከቱ ዜጎች ሁሉ እምነት ነው። ብዙ ስራ እየሰራን ነው። ስንጨብጠውና ለህዝብ ሪፖርት የምናቀርብበት አሳማኝ ጊዜ ላይ ስንደርስ ብቻ ይፋ እናደርጋለን። ስራው በባህሪው ከንግግር በመቆጠብ ተግባር ላይ ማተኮርን ስለሚጠይቅ እኛም ባናወራው ጊዜው ሲደርስ ሁሉም በየፊናው የሚገልጸው ይሆናል። ስራው ሳይሰራ ፕሮፓጋንዳው ከቀደመ በሁሉም ወገን ተዓማኒነትን የማጣትና የመጣል አደጋ አለው። የኢትዮጵያ ህዝብ ተግባር የናፈቀው ይመስለኛል” የሚል ድፍን መልስ ሰጥተዋል።

ከወያኔ ክፋትና እብሪት እንጂ ፍትህ አይጠበቅም


ወያኔ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የአገራችንን የፍትህ ተቋሞች አንዴ አንደ ቂም መበቀያ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመባቸዉ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹንና ጥርስ የነከሰባቸዉን የህብረተሰብ አባላት እያሰረ፤ እያሳደደና እየገደለ ከርሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ ብዕርና ወረቀት ይዘዉ በሃሳብና በአመክኖ የታገሉትን ሰላማዊ ዜጎች “ሽብርተኞች”፤ ድምጻችን ይሰማ ብለዉ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበዉ በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ “አክራሪዎች” እያለ ፍርድ ቤት በማቅረብ በፍትህ ተቋሞች በኩል የፖለቲካ ዉሳኔ በማሳለፍ ሠላማዊ ዜጎችን ለረጂም ግዜ እስርና እንግልት ዳርጓል።
ወያኔ ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ ደንታ የሌለዉ እና ከስህተቱ የማይማር የግብዞችና የዘረኞች ስብስብ ስለሆነ አሁንም የአገሪቱን የፍትህ ተቋሞች እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ ሸብቦ እየገዛ ለመኖር የቆረጠ ይመስላል። ባለፈዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ የወያኔ አገዛዝ ከአንድ አመት ተኩል በላይ እስር ቤት ዉስጥ አጉሮ ያቆያቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ከፊሎቹን በነፃ ተለቅቀዋል የሚል ከፊሎቹን ደግሞ ተከላከሉ የሚል ትርጉም የለሽ ብይን ሰጥቷል። በህወሀት ታጋዮች የተሞላዉ ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት እንኳን ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ሽብር የመፈጸም ወንጀል ምንም አይነት ማስረጃ አልተገኘባቸዉም ሲል አገዛዙ ግን የፖለቲካ ክንዱን በመጠቀም ማስረጃ ያልተገኘባቸዉን ሠላማዊ ዜጎች የተከሰሱበትን መሰረተ ቢስ ክስ ተከላከሉ የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ ሰጥቷል።
የወያኔ አገዛዝ የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን መሪዎች ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ ለምዕራባዉያን ለጋሾቹና ለአለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ ያለ ለማስመሰል ነዉ እንጂ ወያኔ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የፈረደባቸዉ ያሰራቸዉ ቀን ነዉ። የወያኔ የፍትህ ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳየን ወያኔ ግለሰቦችን የሚያስረዉ ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ አግኝቶባቸዉ አይደለም፤ ይልቁንም ወያኔ ማስረጃዎችን እየፈበረከ ለፍረድ ቤቶች የሚያቀርበዉ ግለሰቦችን ካሰረና ሰብዓዊ መብታቸዉን ከገፈፈ በኋላ ነዉ። ለምሳሌ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን አስሮ ብዙም ሳይቆይ የእነዚህን ሰላማዊ ዜጎች ተክለ ሰዉነት ጥላሸት የቀባና ግለሰቦቹን ያለ ማስረጃ ወንጀለኛ አድርጎ የፈረጀዉን “ጂሐዳዊ ሀረካት” የሚል የፈጠራ ድራማ ሰርቶ ለህዝብ አቅርቧል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሽብር በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረዉ የቀረቡለትን ግለሰቦች በተከሰሱበት ወንጀል ማስረጃ አላገኘሁባቸዉም ካለ በኋላ ሁሉንም በነጻ አለማሰናበቱ የሚያሳየን የወያኔ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ አለመሆናቸዉን ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍርድ ቤቶች የገዢዉ ፓርቲ የማጥቂያ መሳሪያዎች መሆናቸዉን ጭምር ነዉ። የወያኔን አገዛዝ ከሌሎች አምባገነኖች ለይቶ አደገኛ የሚያደርገዉና በምዕራባዉያን መንግስታትና በቀላጤዎቻቸዉ እንዲወደስ ያደረገዉም ይሄዉ አገዛዙ የሚቃወሙትን ኃይሎች የሚያጠፋቸዉ እንደሌሎቹ አምባገነኖች በግልጽ ሳይሆን በህግ ሽፋን ዉስጥ በስዉር መሆኑ ነዉ።
የወያኔዉ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ወንጀል ተከስሰዉ የቀረቡለትን ነገር ግን ምንም መረጃ ያላገኘባቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ገሚሶቹን በነፃ ለቅቆ የተቀሩትን ጥፋተኛ አለመሆናችሁን አረጋግጡ ብሎ መወሰኑ የወያኔን ሁለት እኩይ አላማዎች ያሳየናል። የመጀመሪያዉ የወያኔ አላማ በአላማቸዉ ጸንተዉ የቆሙትን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች መከፋፈል ሲሆን፤ ሁለተኛ አላማዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸዉን የክስ መዝገቦች በሚገባ አጣርተዉ ዉሳኔ የሚሰጡ መሆናቸዉን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለማሳየት ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንደዚህ አይነቶቹን የወያኔ እኩይ ተግባሮች ካወቀ ዉሎ አድሯል፤ ስለሆነም ከወያኔ ፍትህ ጠብቆ አያዉቅም፤ ወያኔ የክፋትና የበቀል ምንጭ ነዉና ለደፊትም አይጠብቅም። የድምጻችን ይሰማ መሪዎችም ሆኑ ከእነሱ በፊት በግፍ ታስረዉ መከራቸዉን የሚያዩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበራት መሪዎች የታሰሩት ለቆሙለት የፍትህ፤ የነጻነትና የእኩልነት አላማ እንደ አለት ጸንተዉ በመቆማቸዉ ነዉ። እነዚህ ጀግኖች የታሰሩለት አላማ የሁላችንም አላማ ነዉና ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የጠማን ኢትዮጵያዉያን ክንዳችንን አስተባብረን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ በሆነዉ በወያኔ ስርዐት ላይ ክንዳችንን በጋራ እናንሳ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!