Friday, March 13, 2015

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ

OLYMPUS DIGITAL CAMERA

ቅዳሜ ጁለይ 12/2014 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን በሚል አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የደንነት ሀይሎች መታፈንና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ታላልፈው መሰጠታቸውን በተመለከተ ወደ ፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ በኖርዌ ኦስሎ ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል::
ሕዝባዊ ውይይቱ ከቀኑ 15: 00 ሰአት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያኖች የአቶ እንዳርጋቸው ምስል ያለበትና ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን የሚል ጹሁፍ የተጻፉበትን ቲሸርት በመልበስ ለስብሰባው ድምቀት የሰጡት ሲሆን ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውንም የትግል አጋርነት አስማስክራዋል እነዚህን ቲሸርቶች የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ በራሳቸው አነሳሽነት የሰሩ ሲሆን የድጋፍ ድርጅታችን ወጪውን በመሸፈን ለተሰብሳቢው በነጻ ኣድሏል።
ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አቢ አማራ በሃያ ሶስት አመታት በወያኔ ጨካኝ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉትና በግፍ ለሚሰቃይዩ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ አስጀምረውታል በመቀጠልም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር በስብሰባው ላይ የተገኛውን ሕዝብ እንኮን ደህና መጣችሁ በማለትና በማመስገን ፐሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ሲሆን አቶ ዮሀንስ በንግግራቸው የወያኔ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረሰው አፈና ግንቦት 7 የክተት አዋጅ ማስተላለፉን ጠቅሰው አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል እየታገሉ ባሉ ታጋዮች ላይ ሳይቀር እስር እያደረሰባቸው እንዳለ በማመልከት ሰሞንኑን እንኮን የሰመያዊ፣ የአንድነት፣ የአራና የፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ለስር ተዳርገዋል ብለዋል::
OLYMPUS DIGITAL CAMERAOLYMPUS DIGITAL CAMERA
ስለሆነም ህዝባችንን ለእስር እያደረገ ያለውን አገዛዝ ለመቃወም ሁሉም በአንድነት መሰባሰብ እንዳለበት አጠንክረው በመናገር በአሁን ሰአት የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታፈንና መታሰር መላውን ኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር እያንቀሳቀሰውና ሕዝቡም እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቅሰው በአሁን ሰአት ትግሉ የግንቦት 7 ብቻ አይደለም ይህን ትግል በዚሁ አንድ ሆነን መቀጠል እለብን ብለዋል::

የወደፊቱ፡ የዓለም ስጋትና የሀገራችን ሁኔታ፡(ማተቤ መለሰ ተሰማ)

Matebe Melese


የሰውን ልጅ ታሪክ ወደኋላ መለሥ ብለን ሥንመረምር፡ ከፍጡራን ሁሉ በተሻለ ሁኔታ ዓለምንና ተፈጥሮን አጣጥሞ በመግራት እየተጠቀመባት እንዳለ ለመረዳት አያዳግተንም፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ አንዱ ሌላውን የበታች አድርጎ ለመግዛትና ለመበዝበዝ ሌላው ላለ መገዛትና ላለመበዝበዝ በሚደረጉ ፍልሚያዎች መነሻ ነት ለጥፋትም እያዘጋጃት መሆኑን እናያለን፡፡ በእነዚህ ትንቅንቆች ሂደት መጠነ ሰፊ የህይወትና የንብረት ውድመቶች የደረሱና እየደረሱም ያሉ ወደፊትም በዳይና ተበዳይ በዝባዢና ተበዝባዥ በአንድ ቃል አምባ ገነኖች፡ ከምድራችን እስካለተወገዱ ደረስ እንደማያቆሙ የታወቀ ነው።
ለሰው ልጅ ደመኛ ጠላት የሆኑት አምባገነንነት፣ የግልጥቅም አሳደጅነት፣ ተስፋፊነት ወ.ዘ.ተ. ጨርሰው ተወግደው የሁሉም ሰባዊ ፍጡር ሰላም ዲሞክራሴና ነጻነት በውል እሰካልተከበሩ ድረስ የጥፋቱ መጠንና አይነት ይለያይ እንጅ ጦርነት የማይቆም ቀጣይ  ሂደት ነው የሚሆነው። ከዚህ አንጻር ፈጣሪያችን በስልጣኑ ካወረዳቸው ማታት ባሻገርየእውቀት አድማሳችን የፈቀደለንን ያህል ርቀን የዓለምን እውነታ በአይነሕሌናችን ብንዳስስ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ እንዳለው ጊዜ ሰብዓዊ ፍጡር ለጦርነት አደጋ የተጋለጠበት ወቅት ከዚያ በፊት የለም፡፡ ለተከሰተው ሁሉ ጥፋት ደግሞ መነሻዎቹም ሆነ መድረሻዎቹ እኛው እራሳችን ሰዎች ነን፡ ከፍጥረታት ሁሉ መጥፊያውን የሚሰራ ቢኖር ሰው ብቻ ነው ይባል የለ።
አዎ! እንደ ጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር፣ እንደ ኢጣሊያው ዶቸ ሞሶሌኒ፣ እንደ እስፔኑፍራንኮና፣ እንደ ፖርቱጋሉ ሳለዘር፣ እንደ ዩጋንዳው ኢዲያሚን ዳዳ፣ እንደ ማህከላዊ አፍሬካው ቦካሳ፣ እንደ ሰሜን ኮርያው ኪምኡል ሱንግ፣ እንደ ኢራቁ ሳዳም ኡሴን፣ እንደ ኮንጎው ሙቡቱ ሴሴሴኮ፣ እንደ ቻይናው ማኦ ሴቱንግ፣ እንደ ቱኒዚያው ዜን ቤናሊ፣ እንደ ግብጹ ሙባረክ፣ እንደ የመኑ አብደላ ሳላሀ፣ እንደ ሊቢያው ሙሀመድ ጋዳፊ፣ እንደ ኢራኑ ሙሀሙድ ነጃድ፣ እንደ ሶርያው አሳድ፣ እንደ ሱዳኑ አልበሽር፣ እንደ ዙባቤው ሙጋቤ፣ እንደ ኢትዮጵያው መለስ ዜናዊ ወ.ዘ.ተ. ባሉ አምባገነንና ሰግብግብ መሬዎች መነሻነት፣ አሁን ድረሥ በምድራችን ላይ በእኛ በሰዎች መካከል ከ14 ሺ ያላነሱ ጦርነቶች እንደተካሄዱ የታሪክ ምሁራን ይገምታሉ። ቀደም ያሉትን ትተን በቅርብ ታሪክ የመዘገባቸውን ጦርነቶች ብቻ ብናይ እንኳን የህይወትና የንብረት ጥፋት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱን እንረዳለን፡፡ ሻለቃ አባይነህ አበራ ካዝና በሚል እርዕስ አዘጋጅተው ለንባብ ባበቁት መጽሀፋቸው ያካተቱት ጥናታዌ  ዘገባ እንደሚያስረዳን፡
1ኛ/በ17ኛውክፍለዘመን በተካሄዱትጦርነቶች የ3ሚሊዮን ሕዝብ ህይወት ተቀስፏል።
2ኛ/ በ18ኛው ክፍለዘመን በተካሄዱት ጦርነቶች 5.5 ሚሊዮን ሰው አልቋል።
3ኛ/ በ19ኛው ክፍለዘመን፡ 16 ሚሊዮን ሕዝብ ህይወቱን አጥቷል።
4ኛ/ በ20ኛው ክፍለዘመን በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት 10 ሚሊዮን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት፡ ደግሞ 55 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል። ከላይ በተዘረዘሩት ጦርነቶች በድምሩ 89.5 ሚልዮን ህዝብ እንደቅጠል እረግፏል።
በሁለቱ የዓለማችን ታላላቅ ጦርነቶች ማለትም በ1ኛውና በ2ኛው የዓለም ጦርነቶች ከሞተው ሌላ 110 ሚሊዮን ሕዝብ አካለጎዶሎ ሆኗል። በገንዘብ በኩልም፡ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ያስከተለው ኪሣራ ከ260 እስከ 360 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርሥ ሲገመት።
በሁለተኛው ደግሞ ከሦስት እስከ አራት ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት ወድሟል። እልቂቱ በ20ኛው ክፍለዘመን ጦርነት ብቻ ያከተመ አይደለም። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በምንኖርባት ዓለም ውሥጥ 150 ያህል ጦርነቶች ተካሂደዋል፡ በእነዚህ ጦርነቶች ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አልቀዋል፡ በዚህ ስሌት የእኛዋ ሀገርም ከሱማሌ ወራሪ ከሻብያና ከወያኔ ጋር ባካሄደችው ጦርነት ያለቀውን ወገናችንን ታሳቢ ማድርግ እንችላለን። ለእነዚሁ ጦርነቶችና ለመሣሪያ እሽቅድምድም የሰው ልጅ 10 ትሪሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል። በጦርነት ሳቢያ ከሚደርሰው የሕይወት እልቂትና የንብረት ጥፋት ባሻገር በየጊዜው አይነቱና ጥራቱ እያደገ የሚሄደው የጦር መሣሪያ ጋጋታ ሌላው የወደፊቷ ዓለማችን አሣሣቢ ጉዳይ ነው።
የ17ኛው ክፍለዘመን ወደር የለሽ መሣሪያዎች ጠብመንጃና ሽጉጥ ነበሩ። በ18 እና 19ኛው ክፍለዘመን መድፍ በጦር ሜዳው አውድ የአንበሣ ድርሻውን ተረከበ። በ20ኛው ክፍለዘመን በተካሄዱት ሁለት የዓለም ጦርነትች ደግሞ ታንክና ጀት ተካፋይ ለመሆን በቁ። እንሆ! ዛሬ ደግሞ የኑክሌር መሣሪያዎች ጥፋት በዓለም ላይ ሲያንጃብብ ይታያል። ዛሬ በምድራችን ላይ ርሀብ እርዛት የተፈጥሮ አድጋ በሽታና ማይምነት አልተወገዱም። በልጽገዋል በሚባሉ ሀገሮችም ቢሆን የሰውልጅ በቴክኖሎጅ ድጋፍ ከተፈጥሮ ጋር የሚያደርገው ግብግብ ገና አላከተመም።

የ119ኛው የአድዋ ድል በዓል በኖርዌይ በርገን ከተማ ቅዳሜ መጋቢት 19.2007 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ለዲሞክራሲ ፣ ለፍትህ እና ለነጻነት ለሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው  የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርጫፍ ጽ/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት የ 119ኛው የአድዋ ድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከበረ ፡፡

norway-adwa-630x333
በዕለቱ የአድዋን በዓል ታሪካዊነት በዝርዝር የሚያስረዳ እና የአብዛኛውን ታዳሚ ቀልብ የሳበ ታሪካዊ ትንታኔ የቀረበ ሲሆን የአድዋን ድል የሚገልጹ ጽሑፎች ግጥም እና “የሚኒሊክ ወቀሳ” በሚል ርዕስ ድራማ ቀርቦ ታላቅ አድናቆትን አትርፏል፡ አሁን ሀገራችን ኢትዮጵያ ና ህዝቦቿ  ለ23 አመታት በወያኔ ስርአት እየደረሰባቸው የሚገኘውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣እስር ፣ ግድያና ዝርፊያ  የሚገልጽ በራሪ ወረቀት ለኖርዌጂያን ማህበረሰብ ታድሏል ፡
በመቀጠልም ከተጋባዥ እንግዶች ጋር በአድዋ ድል ዙሪያ ውይይት ተካሂዱዋል በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት ቀኝ ገዢው ጣሊያን ካደረሰብን በደል በላይ ባንዳው የወያኔ መንግስት እያደረሰብን የሚገኘው ውርደት ፣ ስደት፣ ሞትና  ስቃይ ምን መደረግ አለበት በሚል ሰፊ ውይይት ተካሂዶ አባቶቻችን ከዛሬ 119 አመት በፊት ያቀናጁንን ድል ዛሬም ታሪክ ሰሚና ተራኪ  ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪ ሆነን በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ ይህንን አስከፊ ስርዓት ለመቀየር  የሚታገሉ ሃይሎችን ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ጉልበት ያለው በጉልበቱ እውቀት ያለው በእውቀቱ በመደገፍ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔን ማስወገድ እንደሚገባ ፣ በታሪክ በስልጣኔ ለአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ክብሯ እንድትመለስ የዚህ ትውልድ አደራ መሆኑን ተገልጾ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆኗል ፡፡

Wednesday, March 11, 2015

ወያኔና ሽብርተኛነት !! [ መስፍን ወልደ ማርያም]

Prof. Mesfin

ወያኔነትና ሽብርተኛነት ትናንት ምን ዓይነት ግንኙነት ነበራቸው? ዛሬ ምን ዓይነት ግንኙነት አላቸው?
ወደዚያ ከመሄዳችን በፊት የአሸባሪነት የተግባር መገለጫው ምንድን ነው? ብለን እንጠይቅ፤ አሸባሪነት፡-
• ያለውን የሥልጣን ሥርዓት የማፍረስ ዓላማ ያለው ነው፤
• ዓላማውን ለማሳካት ጉልበቱን የሚያፈረጥመው ከሥርዓቱ ጠላቶች በሚያገኘው፡–
• የመሣሪያ እርዳታ፣
• የእውቀት ድጋፍና ገንዘብ
• ዓላማውን ለማሳካት
• ሰዎችን ገድላል
• ያስራል፤ ያሰቃያል
• ይዘርፋል፤ ይቀማል፤
• ዓላማውን ለማሳካት
o ሃይማኖቶችንና ባህልን ያዳክማል፤
o የጥንት ታሪክ ማስታወሳዎችንና የቆዩ መጻሕፍትን ያጠፋሉ፤
o የፖሊቲካ እምነትን ያግዳል፤
o የመሰብሰብ ነጻነትን ይከለክላል፤
o የመደራጀት ነጻነትን ይከለክላል፤
o ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ይከለክላል፤
o ጉልበትን ወደሥልጣን ይለውጣል፤
• አንድ ዓላማ፣ አንድ እምነት፣ አንድ ሀሳብ፣ አንድ ዘዴ. አንድ መንገድ በቀር ሌላው ሁሉ ይዘጋል፤ ይህንን ጥርነፋ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ ተብሎ ይታሰራል፤ የሲአይኤ ሰላይ ተብሎ ተሰቃይቶ ይሞታል፤
ከዚህ በላይ የተዘረዘረት በሙሉ የሽብርተኞች ወንጀሎች የሚባሉ ናቸው፤ እነዚህን እንደመመዘኛ አድርገን በአንድ በኩል ወያኔን፣ ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁን የሚያድርገውንና እያደረገ ያለውን በማስታወስ፣ በሌላ በኩል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትና በሽብርተኛነት ተከስሰው በእስር ቤት የሚገኙት ሰዎችን
• እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት ዓለሙ፣ ተመስገን ደሳለኝ
• የዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቁት ወጣቶች፣ (ማኅሌት ፋንታዬ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ኤዶም ካሣዬ፣ አቤል ዋበላ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ተስፋ ዓለም ወልደየስ፣ ዘለዓለም )
• አንዱዓለም አራጌ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ
• ሌሎች ከግንቦት ሰባት ጋር ንክኪ አላችሁ ተብለው የታሰሩት
ስናመዛዝን በሽብርተኛነት መመዘኛዎቹ ከብደው የሚታዩት የትኞቹ ናቸው? የአሸባሪነት የተግባር መግለጫ ተብለው በተዘረዘሩት ውስጥ ባሉት ዓላማዎችና መንገዶች የሚንቀሳቀሱት የትኞቹ ናቸው? ወያኔ ነው ወይስ የታሰሩት ሰዎች? ሽብርተኛ ተብለው ከታሰሩት ውስጥ ባንክ ሲዘርፍ የተያዘ አለ? እኔ አስከማውቀው የለም፤ ከወያኔ ውስጥስ ባንክ የዘረፈ አለ? ራሱ መለስ ዜናዊ በኩራት ነግሮናል! በሌሎች ወንጀሎችም ቢሆን ያው ነው፡፡
ተጨማሪ ማስረጃ የሚሆነው የዓለም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሁሉ በወያኔ በሽብርተኛነት የታሰሩት ሁሉ እንዲፈቱ እየወተወቱ በአንጻሩ የወያኔን የሰብአዊ መብቶችን መጣስ እያወገዙ ነው፤ ስለዚህ ጋዜጠኞችንና የፖሊቲካ ሰዎችን እየለቀሙ በሽብርተኛነት እየወነጀሉ በየእስር ቤቱ መወርወሩ አላዋጣም፤ አዝማሚያው እንደሚያሳየው የወያኔ ጸረ-ሽብርተኛ መምሰል ለሲአይኤም የሚሸጥ ሊሆን የሚችል አይመስልም፡፡
በዚያ ላይ ሽብርተኞች በኢራቅና በአፍጋኒስታን አድርገው የመን ገብተዋል፤ ከየመን ሶማልያ ቅርብ ነው፤ ኬንያን እየፈተሹት ነው፤ የሱዳን ትርምስ ሽብርተኞችን እንደሚጋብዝ ጥርጥር የለም፤ የናይጂርያው ወደሱዳን ሲጠጋ መፈናፈኛ ይጠፋል፤ በሽብርተኛነት የተከሰሰችው ኤርትራ ለመሸሸጊያ ትሆን ይሆን?
ጤናማ ሰው ሆኖ ሽብርተኛነትን የሚደግፍ ያለ አይመስለኝም፤ ዛሬ በኢራቅ የሚደረገውን በየቀኑ ስንመለከት ወደቤታችን አልተጠጋም ብለን ልንዝናና የምንችልበት ሁኔታ ላይ አይደለንም፤ በዋልድባና በበዙ ሌሎች ቦታዎች የኢትዮጵያ ቅርሶች አደጋ ላይ መሆናቸው ይሰማናል፤ ግን በአቅመ-ቢስነት በዝምታ እንመለከታለን፤ ይህንን የአዳፍኔ የፖሊቲካ አቅጣጫ ለመለወጥ የሀሰብ መለዋወጫ መድረክ የሚፈጥሩትን ወጣቶች ሁሉ በእስር ቤቶች እያጎሩ ነው፤ አዲስ የፖሊቲካ መድረክ እንፍጠር ብለው በሰላማዊ መንገድ የፖሊቲካ ትግል የጀመሩትን ሁሉ እያሰሩ ነው፤ በትግራይ ውስጥ አረና በትግራይ ያለውን የፖሊቲካ መሻገት ለማጥራት እንዳይሞክር እየተደረገ ነው፤ ከዚህ በፊት ገብሩ ዓሥራት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረትን በክፉ የጭካኔ ዘዴ እንዳዳከመ አሁንም አረናን ለማዳከም እየተሞከረ ነው፡፡
መቼ ነው ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው ነገን የማየት ዓይኖች የሚያበቅሉት?

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ከችሎት ውጭ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ ወሰኑ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት አቶ ገረመው ገ/ጻድቅ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ ከችሎት ውጭ በግላቸው መወሰናቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የምዕ/ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፀ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ መዋቅር ዕጩዎቻችን ያለ አግባብ ተሰርዘውብናል በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ የነበር ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ምድብ ችሎት የሰማያዊ ፓርቲ የዱር ቤቴ ዕጩዎች የተሰረዙት ያለ አግባብ በመሆኑ በዕጩነት እንዲቀርቡ ወስኗል፡፡
በተመሳሳይ የቀሪዎቹን ወረዳዎች ዕጩዎች ክርክርን ይዞ የነበረው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ምድብ ችሎት ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ጉዳዩን እኔ አየዋለሁ በማለት ጉዳዩን ከሁለተኛ ምድብ ችሎት ከወሰዱ በኋላ የሌሎቹ ወረዳዎች ዕጩዎች በዕጩነት እንዳይቀጥሉ በግላቸው መወሰናቸው ተገልጾአል፡፡
በአንድ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተያዘ ክርክር ተመሳሳይ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባ እንደነበር ግልጽ ነው ያለው አቶ አዲሱ ‹‹ፕሬዝደንቱ ዳኞቹ ለዕጩዎቹ እንደሚወስኑ ስላወቁ ጉዳዩን ከደኞቹ ቀምተው ወስደው በግላቸው ወስነዋል፡፡›› ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል፡፡
‹‹በአንድ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ውሳኔ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ሁለተኛ ጉዳዩን መጨረስ የነበረባቸው መጀመሪያም ጉዳዩን የያዙት ዳኞች ነበሩ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ም/ፕሬዝደንቱ ብቻቸውን ማየት አልነበረባቸውም፡፡ ጉዳዩን ችሎት ሳይሰየም በራሳቸው ስለወሰኑ የዳኞች ፊርማ የለበትም፡፡ ከምንም በላይ ግን ውሳኔው ትክክልና ግልጽም ባለመሆኑ የውሳኔ ግልባጭ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡›› ሲል ም/ፕሬዝደንቱ ከህግ ውጭ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ መወሰናቸውን ገልጾአል፡፡

Tuesday, March 10, 2015

ምርጫውን ለህዝባዊ እንቢተኛነት እንዴት?

ህዘባዊ እንቢታ ማለት ዜጎች የስርአት ለውጥን ሆነ መብታቸውን ለማስከበር በብዙ ቁጥር ሆነው በጋራ አንድን ነገር ማደረግ ወይ አለማድረግ ነው። አለቀ። ብብዙ ቁጥር ተቃውሞ አደባባይ መውጣት በጋራ ልናደርጋቸው ከምንችላቸው በትንሹ ከሺ ነገሮች ውስጥ አንዱ የህዝባዊ ተቃውሞ አካል ነው። ተቃውሟችንን ለመግለፅ በጋራ ልናደርጋቸው የሚቻሉን ነገሮች ሁሌ የግድ ከባድም አጋላጭም መሆንም የለባቸውም። በይበልጥም ስንጀምረው።

Statement from 9 Ethiopian coalition parties
ማወቅ ያለብን አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥር እስከነፃነቱ እንዲሆን አልሞ ነው። ሲፈጥረው ባስፈለገው ጊዜ አፈጣጠሩን በሙሉ ነፃነቱን ማስጠበቂያ አድርጎ እንዲጠቀምበት ነው። ሀሰት የሚል ካለ ይህንን አፈጣጠሩን ነፃነቱንና መብቱን ማስከበርያ አድርጎ ሊጠቀምበት አይችልም ይበል። እኛም ኢትዬጵያዊያን ሰዎች ነን። የሰው ልጅ እንደመሆናችን ስሜታችንን ፤ አካላዊ እንቅስቅሴያችንን፤ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ አካላችንን ፤ድርጊታችንን፤ አኗኗራችንን፤ የማሰብ ችሎታችንን፤ ፍላጎችንን፤ድምፃችንን ብቻ ሁለንተናዊ አፈጣጠራችንን መጠቀሙን እናውቅበታለን አናውቅበትም ነው እንጂ ጉልበታሞችን ልክ ማስገቢያ ካምላክ የተሰጠ ሀይላችን ነው።
ነፃነቱን ገፋፊው አንድ ግለሰብ ሲሆን ተገፋፊው ይሰራል ያለውን አፈጣጠሩን ተጠቅሞ በመዝጋትም ሆነ ልክልኩን በመንገር እንደሁኔታው አናቱን በድንጋይ በመበርቀስ ነፃነቱንና ክብሩን ማስመለስ ይችላል። ነፃነቱን የቀማው መንግስት ሲሆን ግን ብቻውን ሆኖ አደባባይ ላይ ወጥቶ በመጮህ ሆነ ተኩሶ እንዳሰበው ተፅኖ ፈጣሪና ውጤታማ ትግል ለማካሄድ ሁሌ የተሳካ ላይሆን ይችላል። በወረደ ምሳሌ፤- አንድ ሰው ብቻውን አገዛዝን ለመታገያና ተቃውሞውን ለመግለፅ አስቦ እደጅ ቢፀዳዳስ። ሲጀመር እስከጭራሹ ለምን እንዳደረገውም ላይታወቅ ሁሉ ይችላል። ነግር ግን ነፃነታቸውን የተነፈጉ በሙሉ አንድ ቀን ወስነው እጅ ለእጅ ተያይዘው እደጅ ቢፀዳዱስ። ይህ በቀጥታ ነቅንቅ የሆነ ተቃውሞ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ አይገባም። { አይዞን ምሳሌ ነው። ካስፈለገ ተባብሮ ማፅዳቱንም ቀጣይ የተቃውሞ አይነት ልናደርገውም እንችላለን }።

ገብሩ አስራት – ከህወሐት እስከ አረና

በቅርቡ “ሉአላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባወጡት መፅሐፍ የመጀመርያዎቹ አራት ምዕራፎች ላይ ራስዎንም ጭምር እየተቹ ፅፈዋል፡፡ የ1993 ክፍፍልና ከዚያ በኋላ ያለውን በሚተርከው ክፍል ላይ ግን ብዙ የተድበሰበሱ ጉዳዮች እንዳሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ….
እኔ ይሄን መጽሐፍ በሁለት አላማዎች ነው የፃፍኩት። አንዱ አላማ በኢትዮጵያ የሉአላዊነት ጉዳይ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ማስገንዘብ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሂደት በ40 አመት ውስጥ ከየት ወዴት እንደደረሰ ለማሳየት ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች ይሄን ግንዛቤ እንዲይዙ ከራሴ ልምድና ከነበርኩበት ድርጅት አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመነሳት የተቻለኝን ሁሉ አስቀምጫለሁ የሚል አስተያየት አለኝ፡፡
እኔ መጽሐፉ ከወጣ በኋላ ከደረሱኝ አስተያየቶች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ነገሮችን በግልጽ ማስቀመጤን የሚጠቁ ሲሆን እንዲያውም አንዳንዱ ከሚጠበቀው በላይም ተገልጿል የሚል ነው፡፡ በህወሐቶች ዘንድ ደግሞ አላስፈላጊ የሆኑ ሚስጥሮች አውጥቷል ተብሎ እንደሚታሰብ ተገንዝቤአለሁ፡፡ እኔ ግን ህሊናዬና አቅሜ በሚፈቅደው የተቻለኝን ያህል እውነታውን ገልጨዋለሁ፡
በግልፅ አልተብራራም ከተባሉት መካከል በ1993 ክፍፍል ወቅት እርስዎን ጨምሮ አቶ ስዬ፣ አለም ሠገድ፣ አባይ ፀሐዬ… በአቶ መለስ ቦናፓርቲዝም ዙሪያ ያቀረባችሁት ጽሑፍ በሚገባ አልተጠቀሰም የሚለው ይገኝበታል፡፡ ምን አይነት ጽሑፎች ነበሩ የቀረቡት?
በኔ በኩል ስለ መለስ ቦናፓርቲዝም በመጽሐፉ ውስጥ በዝርዝር አስቀምጫቸዋለሁ፡፡ የመለስ አቋም፤ በኢትዮጵያ አመራር ውስጥ ቦናፓርቲዝም በግልፅ ተከስቷል የሚል ነበር፡፡ የቦናፓርቲዝም ዋናው ጉዳይ ደግሞ ሙስናና ፀረ ዲሞክራሲያዊነት ነው ብሏል፡፡ የኛ ጽሑፎች ከዚህ የተለዩ ናቸው፡፡
የቦናፓርቲዝም ንድፈ ሃሳብ መለስ ከአስቀመጠው የተለየ ትርጉም ነው ያለው፡፡ የቦናፓርቲዝም ዋናው ቁምነገር ሁለት ሃይሎች/መደቦች ለመጠፋፋት ከጅለው፣ ይሄን መጠፋፋት አስታርቆ የሚመጣ መካከለኛ መንግስት ማለት ነው፡፡ በመለስ አገላለጽ ግን ቦናፓርቲዝም ሙስናና ፀረ ዲሞክራሲ ስርአትን ለማንገስ የመጣ ስርአት ነው፡፡ ከዚያ በላይ በእኛ ፅሁፎች በስፋት የተገለፀው መለስ በወቅቱ የነበረውን የኢትዮጵያን ችግር በስፋት አላቀረበም የሚል ሃሳብ ነው፡፡ በወቅቱ ከነበረው ትልቅ ችግር ለመሸሽ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው የሚል አቋም ነው የያዝነው፡፡ ምክንያቱም የወቅቱ ትልቁ የኢትዮጵያ ችግር የሉአላዊነት መደፈር ነው፡፡ በተለይ በኤርትራ መንግስት የተቃጣብን ወረራ በልማታችን ላይ ያስከተለውን ችግር ሣይናገር፣ ሌላ ጉዳይ አንስቶ ከዋናው አጀንዳ አፈግፍጓል ብለን ነው በጽሑፋችን ያስቀመጥነው፡፡ ሉአላዊነት ሲባል የድንበር ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ በሀገራችን፣ በህዝባችን፣ በመንግስታችን ላይ የተቃጣ መሆኑም ጭምር ነው። መለስና ጓደኞቹ ለውጭ ጫና ተንበርክከው፣ በወቅቱ ከእውነታው ሸሽተዋል የሚል ነው የጽሑፋችን ጭብጥ፡፡ እሱ ደግሞ ዋናው ጉዳይ የሙስናና የዲሞክራሲያዊነት ነው፤ የሉአላዊነት ጉዳይ ውጫዊ ጉዳይ ነው ብሎ ነው ያቀረበው፡፡ በአጠቃላይ አቶ መለስ ያቀረበው ጽሑፍ ከሉአላዊነት አጀንዳ የመሸሽ ነው፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ቅጣት ተላለፈባቸው

Habitamu

  • በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
  • ᎐ተጨማሪ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል
• ‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው›› አብርሃ ደስታ
• ‹‹ችሎቱ ላይ ያጨበጨብነው በማፌዝ ሳይሆን በምሬት ነው›› የሺዋስ አሰፋ
• ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፣ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› ዳንኤል ሺበሽ
በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እንዲሁም የዓረና ትግራይ ፓርቲዎች አመራሮች ‹ችሎት በመድፈር ወንጀል› ጥፋተኛ በመባላቸው ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በሦስቱ አመራሮች ላይ እያንዳንዳቸው በሰባት ወራት እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡
የካቲት 26/2007 ዓ.ም ተከሳሾች በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸውና ንብረትም እንደተወሰደባቸው በመግለጽ አቅርበውት ለነበረው አቤቱታ ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ሙሉ ለሙሉ በመቀበል አቤቱታቸውን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ 5ኛ ተከሳሽ አቶ የሺዋስ አሰፋ በማጨብጨቡና 3ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 4ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ሳይፈቀድላቸው ‹‹ጥሩ ፍርድ፣ ጥሩ ብይን›› በማለት አቶ የሺዋስን በመደገፍ ችሎት ደፍረዋል ተብለው ጥፋተኛ መሰኘታቸው ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ተሰይሞ በአብርሃ ደስታ፣ በየሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሺበሽ ላይ የሰባት ወራት እስራት በእያንዳንዳቸው ላይ ወስኗል፡፡ ሦስቱም ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ድጋሜ ችሎት ውስጥ አጨብጭበዋል፡፡ በዚህም ድጋሜ ጥፋተኛ ተብለዋል፤ ከሁለት ቀናት በኋላም የቅጣት ውሳኔ ይወሰንባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሦስቱ ተከሳሾች ‹‹እድል ስጡን እንናገር፣ አቤቱታም አለን ተቀበሉን›› ቢሉም ፍርድ ቤቱ ሊሰማቸው አልፈለገም፡፡ በተለይ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹ሌላ አቤቱታ አለኝ፣ ፍርድ ቤቱ ያዳምጠኝ›› ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ አሁንም ችሎቱ ላይ እያፌዛችሁ ነው በሚል ጥፋተኛ ሲላቸው ሦስቱም አመራሮች ፍርድ ቤቱን ማስፈቀድ ሳያስፈልጋቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
‹‹እኛ የደፈርነው ችሎት አሻንጉሊት ችሎት ነው፡፡ ‹Already› የተደፈረ ችሎት ነው›› ሲል አብርሃ ደስታ ተናግሯል፡፡ በዚህ ጊዜ ዳኞቹ ጣልቃ በመግባት፣ ‹‹የምትናገረው ነገር እንደገና ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚወስድህ ጉዳይ ነው፤ ምርመራ ይደረግበታል›› ሲሉ አብርሃ በበኩሉ ‹‹አሁንስ ቢሆን የምናገረውን ፖሊስ እየሰማ አይደለምን?›› ሲል መልሷል፡፡
አቶ የሺዋስ አሰፋ በበኩሉ ‹‹ከስምንት ወር በላይ ታፍነናል፡፡ በህግ አይደለም የተያዝነው፡፡ ደግሞ ማጨብጨባችን በችሎቱ ከማፌዝ ሳይሆን ከምሬት በመነጨ ነው፡፡ ህገ-መንግስታዊ መብታችን ተጥሷል፡፡ እኔ ለምሳሌ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆኔ ነው የታሰርኩት፡፡›› ብሏል፡፡
አቶ ዳንኤል ሺበሽ ድግሞ ‹‹አሁንም ችሎት ደፍራችኋል ካላችሁ ቅጣቱን ጨምሩብንና ሸኙን፡፡ በእርግጥ ዳኞች ላይ ያለውን ጫና እንረዳለን፡፡›› ሲል ችሎት ውስጥ ተናግሯል፡፡
በዚህ ሁኔታ በተከሳሾችና በችሎቱ መካከል ያለው አለመግባባት ሲጨምር ዳኞቹ መጋቢት 3/2007 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ የቅጣት ውሳኔ እንደሚሰጥ በመጥቀስ ሦስቱ ተከሳሾች ከችሎት በፖሊስ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ ከችሎት እየወጡ እያሉም አቶ ዳንኤል ሺበሽ ‹‹ፍትህ ተጠምተናል፤ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!›› እያለ ችሎቱን ለቅቆ ወጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ሦስቱ ተከሳሾች ከችሎት መውጣታቸውን ተከትሎ፣ ከዚህ ቀደም በማረሚያ ቤቱ ላይ በቀረበው አቤቱታ ዳኞች በሰጡት አስተያየት ላይ አቤቱታ አቅርቦ እንደነበር በማስታወስ አቤቱታው እንዲመዘገብለት የጠየቀው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ‹‹በበኩሌ ያሉኝን መረጃዎች እያቀረብኩ ስነ-ስርዓቱን አክብሬ ክርክሩን አቀጥላለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡

Tuesday, March 3, 2015

የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ከኃላፊነቱ አነሳ

Semayawi Party- Ethiopia's photo.

Semayawi Party- Ethiopia's photo.Semayawi Party- Ethiopia's photo.
‹‹ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው›› አቶ አዲሱ ጌታነህ
የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ተወካይ እንዲሁም የምዕራብ ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃምና አዊ ዞን የምርጫ ግብረ ኃይል አባል የሆነውን አቶ አዲሱ ጌታነህን ‹‹ማኔጅመንቱን ያውካል፣ የስራ ተነሳሽነት የለውም›› በሚል ከኃላፊነቱ ማንሳቱን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ይሁንና መስሪያ ቤት ጥቅምት 23/2007 ዓ.ም በብቃቱ መሰረት በኃላፊነት እንደመደበው በደብዳቤ የገለጸ ሲሆን አሁን የተወሰደው እርምጃ ከወቅቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ መሆኑን አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
‹‹ባህርዳር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ኃይል እየተፈጠረ ነው፡፡ በተለይ የአንድነት መዋቅር ሰማያዊን ከተቀላቀለ በኋላ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህንም ተከትሎ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ጋር ያደረግናቸው ውይይቶች ብአዴንን አስደንግጦታል›› ያለው አቶ አዲሱ መስሪያ ቤቱ የወሰደበት እርምጃ ፖለቲካዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል፣ እንዲሁም ምርጫ ቦርድ ከዕጩ ምዝገባ ጋር በተያያዘ የሚፈጥራቸውን ችግሮች ለሚዲያ በማጋለጥ ላይ መሆኑ ከኃላፊነት ለመነሳቴ አንድ ምክንያት ነው ሲል ገልጾአል፡፡
የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የቦርድ አባላት የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው፣ የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ኃላፊ አቶ አየነው ይገኙበታል፡፡

አየር ሐይልን ከድቶ በይፋ ግንቦት 7ን የተቀላቀለው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ታናሽ ወንድም ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ መሆኑ ታወቀ



“ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነዋል” በማለት የኢትዮጵያ አየር ሃይልን እና የገዢውን ፓርቲ አካሄድ በመቃወም ግንቦት 7ን መቀላቀላቸው የሚታወሠው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ቤተሠቦች አደጋ ላይ ይገኛሉ፡፡
ኮተቤ 02 አካባቢ በተለምዶ ቆርቆሮ ሠፈር እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የሚኖሩት የሻለቃ አክሊሉ ቤተሠቦች ሻለቃ አክሊሉ በተለያዩ ምክንያቶች ግንቦት 7ን መቀላቀላቸውን ተከትሎ በቤተሠቡ ላይ የሚካሄደው ምርመራ እና ክትትል በገዢው ፓርቲ የደህንነት ሀይሎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በተለይም በታናሽ ወንድሙ ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡
ይህንን ዜና በኢሜይል የላከልኝ ወጣት እንደገለፀው ከሆነ ወጣት ሠይፈ መዘነ ማዕከላዊ እንደሚገኝ ያወቁት ቤተሠቦቹ ወደስፍራው በማቅናት ለመጠየቅ ቢሞክሩም በፖሊሶች መከልከላቸውንና ቤተሠቦቹም እስረኛን መጠየቅ መብታቸው መሆኑን ሲገልፁ ፖሊሶች ሠይፈ አዘነ እስረኛ ሣይሆን አሸባሪ ነው በማለት መልሠዋቸዋል፡፡
ሻለቃ አክሊሉ አዘነ ሴፕቴምበር 2013 ኢሳት ላይ ቀርቦ አየር ሐይል እንደገና ካልተዋቀረ አገርን መከላከል የሚችልበት ደረጃ እንደማይገኝ የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነው እንደሚአገለግሉ፣ አብራሪ የሚባሉት በሚሊሻ ደረጃ መገኘታቸው፣ የዘር መድልዎ እንደሚደረግ፣ የህወሃት ድጋፍ ያላቸው ብቻ የሚስተናገዱበት መሆኑ፣ ከችግሮቹ በግንባር የሚገለጹ ናቸው ሲሉ መግለፃቸው ይታወሳል።
ሻለቃ አክሊሉ ላለፉት 15 ዓመታት ያህል በታማኝነት የኢትዮጵያ ህዝብን ያገለገሉ ሲሆን በአየር ሃይል ውስጥ የሚሰራው የቡድን፣ የዘርና አጠቃላኢ አለው አሰራር ብልሹነት አሳሳቢ በመሆኑ አገር ጥለው በመውጣት ከሶስት ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ግንቦት7 ንቅናቄን መቀላቀላቸውን በወቅቱ ገልፀው ነበር።

Monday, March 2, 2015

Ethiopia government intensified its crackdown on dissent ahead of the May 2015 elections – HRW


Hopes that Ethiopia’s government would ease its crackdown on dissent ahead of the May 2015 elections were dashed in 2014.
Instead the government continued to use arbitrary arrests and prosecutions to silence journalists, bloggers, protesters, and supporters of opposition political parties; police responded to peaceful protests with excessive force; and there was no indication of any government willingness to amend repressive legislation that was increasingly condemned for violating international standards, including at Ethiopia’s Universal Periodic Review at the United Nations Human Rights Council.
Freedom of Peaceful Assembly
Security forces have harassed and detained leaders and supporters of Ethiopian opposition parties. In July, leaders of the Semawayi (“Blue”) Party, the Unity for Democracy and Justice (UDJ), and the Arena Tigray Party were arrested. At time of writing, they had not been charged but remained in detention.
The Semawayi Party’s attempts to hold protests were regularly blocked in 2014. Its applications to hold demonstrations were denied at least three times and organizers were arrested. Over the course of the year, authorities repeatedly harassed, threatened, and detained party leaders.

Sunday, March 1, 2015

British support for Ethiopia scheme withdrawn amid abuse allegations

The Guardian

Department for International Development will no longer back $4.9bn project that critics claim has funded a brutal resettlement programme.
The UK has ended its financial support for a controversial development project alleged to have helped the Ethiopian government fund a brutal resettlement programme. Hundreds of people have been forced from their land as a result of the scheme, while there have also been reports of torture, rape and beatings.
Until last month, Britain’s Department for International Development (DfID) was the primary funder of the promotion of basic services (PBS) programme, a $4.9bn (£3.2bn) project run by the World Bank and designed to boost education, health and water services in Ethiopia.
On Thursday, DfID said it had ended its PBS contributions because of Ethiopia’s “growing success”, adding that financial decisions of this nature were routinely made after considering a recipient country’s “commitment to partnership principles”.
It has been alleged that programme funds have been used to bankroll the Ethiopian government’s push to move 1.5 million rural families from their land to new “model” villages across the country.
Opponents of the commune development programme (CDP) say it has been characterised by violence. One Ethiopian farmer is taking legal action against the British government, claiming UK money has funded abuses against Anuak peoplein the Gambella region. The man, an Anuak known as Mr O, says he was beaten and witnessed rapes and assaults as government soldiers cleared people off their land. DfID has always insisted it does not fund Ethiopia’s commune development programme.
scathing draft report from the World Bank’s internal watchdog recently concluded that inadequate oversight, bad audit practices, and a failure to follow the bank’s own rules had allowed operational links to form between the PBS programme and the Ethiopian government’s resettlement scheme.
Although the bank’s inspection panel found that funds could have been diverted to implement villagisation, it did not look into whether the resettlement programme had involved human rights abuses, claiming such questions were outside its remit.
DfID, which has contributed nearly £745m of UK taxpayer money to the PBS programme, said the decision to withdraw financial support was prompted in part by Ethiopia’s “impressive progress” towards the millennium development goals.
“The UK will now evolve its approach by transitioning support towards economic development to help generate jobs, income and growth that will enable self-sufficiency and ultimately end poverty,” it said.
“This will go alongside additional funding for specific health, education and water programmes – where impressive results are already being delivered – resourced by ending support for the promotion of basic Services programme.”
A DfID spokesman said the move had nothing to do with Mr O’s ongoing legal action or the World Bank’s internal report, but added: “Changes to programmes are based on a number of factors including, but not limited to, country context, progress to date and commitment to partnership principles.”
The department said its overall financial commitment to Ethiopia, one of the largest recipients of UK aid, would remain unchanged, with almost £256m due to be spent between 2015 and 2016.
The Ethiopian government said DfID’s decision was not a matter of concern.
“They have been discussing it with pertinent government bodies,” said the communications minister, Redwan Hussien.
“What they said is that the aid that they’re giving will not be refused or stopped, it will be reorganised.”
The World Bank’s executive board met on Thursday to discuss the internal report on the PBS programme and the management response.
In a statement released on Friday, the bank said that although its inspection panel had concluded that the seizing of land and use of violence and intimidation were not consequences of PBS, it had determined that the programme “did not fully assess and mitigate the risks arising from the government’s implementation of CDP, particularly in the delivery of agricultural services to the Anuaks”.
The World Bank Group president, Jim Yong Kim, said that one of the institution’s core principles was to do no harm to the poor, adding: “In this case, while the inspection panel found no violations, it did point out areas where we could have done more to help the Anuak people. We draw important lessons from this case to better anticipate ways to protect the poor and be more effective in fighting poverty.”
Opponents of the villagisation process have been vocal in their criticisms of the bank’s role. Jessica Evans, senior international financial institutions researcher atHuman Rights Watch, said the inspection panel’s report showed the bank had “largely ignored human rights risks evident in its projects in Ethiopia” and highlighted “the perils of unaccountable budget support” in the country.

ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።


የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ ወታደር ጋር በመሆን የሰላም ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት መልካምነት ሲሰብኩ ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።
አለማየሁ እና ኢዛና ለወያኔ በሰሩት ውለታ ሆላንድ ገብተው እንዲቀሩ ተደረገ። ይህም የተደረገበት ምክንያት በአውሮፓ የሚኖሩ ኢዮጵያውያንን ተቃዋሚ በመምሰልና በረቀቀ መንገድ እንዲያበጣብጡና እንዲሰልሉ ነው።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።
አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ መሆኑን መናገር ጀምሯል። ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል።