Saturday, April 6, 2013

የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚደርስባቸውን ግፍና በደል ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ (IOM)አስታወቀ:


  • ከኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ ወገኖቻችን ለኤደን ባሕር አሳ አዞ ገብረው ቀይ ባህርን የተሻገሩ ኢትዮጵያውያን ስቃይ ሰቆቃ እንስማ ::
የመን ከነዓን ጩኧቱ ይቀጥላል::የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚደርስባቸውን ግፍና በደል ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ዓላም አቀፉ ድርጅት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (IOM)አስታወቀ:: ዓለም ድርጅቱ እንደሚለው በተለይ የመንን የሳውዲ አረቢያ ጋር በሚያዋስነው አካባቢ የሰፈሩ ስረተኞች ከምግብና ከመጠለያ ባለፈ ችግር በወረበሎች እየታገቱ የሚደርስባቸው ግፍ ከሚነገረው በላይ ነው::በኢትዮጵያ IOM የመገናኛ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ደምሰው ብዙወርቅ እንደሚሉት መውሪያ ቤታቸው ስደተኞችን ለመርዳት ቢሞከርም በገንዘብ እጥረትና በስደተኞች ቁጥር መብዛት ምክንያት ተፈላጊውን ርዳታ መስጠት አልተቻለም::
ወደ ሰሜን አፍሪካ እስከ ሊቢያ ፥ ሽቅብ እስከ ሜድትራኒያን ማዶ እስከ ሞልታ ወይም ኢጣሊያ ደግሞ በተቃራኒው ቁልቁል ወደ ደቡብ አፍሪቃ እስከ ታንዛኒያ ፥ ማላዊ ፥ ሞዛምቢክ ወይም ደቡብ አፍሪቃ ጥግ እስ_ ቢሉ የኢትዮጵያውያን ፥ የኤርትራና የሱማሌ ስደተኞች ስቃይ ሰቆቃ እስኪያንገቸሸግሽ ይሰማሉ::

ጩኧት ይቀጥላል::ከኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ ወገኖቻቸውን ለኤደን ባህር አዞ ገብረው ቀይ ባህርን የተሻገሩ ኢትዮጵያውያን ስቃይና ሰቆቃውን አልፈው ወደ ከነዓን የገቡ ብዙ ግዜ እንደሚገለጸው የመኖሪያ ፍቃድ አያገኙም ::ስራ የላቸውም ስራ ቢያገኙ እንኳን አንዳንድ አሰሪዎች ይደበድቧቸዋል ፥ ክፉዎች ይደፍሯቸዋል ፥ ደሞዝ ሳይሰጡ የሚያባርሩም ብዙ ናቸው ::ሳውዲ አረቢያ ጥቅሐራጥ በምትባል ከተማ ካሉት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የሰነዓዎቹ ችግርና ግፍ ልክ የለውም :: ስደተኞች እንደሚሉት የመን መቆየት የመደብደቢያ ፥ የመቆረጫ ፥ የመደፈሪያን ቀን መጠበቅ ነው::
ወደ አገር የሚመልሳቸው የለም::የኢትዮጵያ መንግስት ኤምባሲማ “አሳፋሪ” መሆኑ የታወቀ ነው::በኢትዮጵያ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የIOM የመገናኛ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ደምሰው ብዙወርቅ እንደሚሉት የስደተኞችን ስቃይ መከራ መስሪያ ቤታቸው ያውቀዋል::ለመርዳት የፈልጋል ፥ ይሞክራል ::ሁሉንም ችግር ለመርዳት ግን ገንዘብ የለም::
ስቃይ ሰቆቃው ቀጥሏል መፍትኤው ላሁኑ አይታወቅም ::
የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጩኧት አላበቃም::

No comments:

Post a Comment