እንደ ቀልድ ‹‹በሽብርተኝነት ተጠርጥረው›› እየተባለ ወደ እስር ቤት የሚወረወሩት በርካታ ናቸው፡፡***ልንታደጋቸው ግድ ይላል!!!
በአደባባይ መግደልና በሚስጥር መግደል ሁለቱም የወንጀል ልዩነት የላቸውም፡፡ የዜጎችን ነፃነት ቀምቶ፣ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዳይገልፁ እያሸማቀቁ ፤ ተቃዋሚዎችንም የተለያየ ስም እየለጠፉ ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከት ህውሃት/ወያኔ ሰውን እያሰሩ መኖር ጊዜውን ጠብቆ በወንጀለኝነት እንደሚያስጠይቅ ካለፉት ታሪኮቻችን አልተማረም ፡፡ ኢህአዴግ ካለፉት የታሪክ ኪሳራዎች በመማር ታጋይን በማሰር ትግሉን ማቆም እንደማይቻል ተገንዝቦ የፖለቲካ እስረኞችን በአስቸኳይ በመፍታት አለበት፡፡
ኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት ህግ ለውጪው ዜጋ እንደሚስፈልጋት እሙን ነው ለኢትዮጵያ ህዝብ ግን አያስፈልገው ህዝቡ በባህልም በአይማኖትም የታነፀ ነውና ፡፡ሽብርተኝነት ህግ ከአገለገለም የአገሪቱን ሉአላዊነት የሚዳፈሩና ህዝቦቿን ለአደጋ የሚያጋልጡ የውጭ ጠላቶችን ለመከላከልና ለመቅጣት ያገለግላል፡፡ በሃገራችን እየሆነ ያለው ግን ሌላ ገፅታ ያለው ነው ፡፡ የፀረ- ሽብር ህጉና የደህንነት መስሪያ ቤቱ በመተባበር በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን ያጠቁበታል ፡፡ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን ጥቅም ይነካሉ ተብለው የሚታሰቡ ኢትዮጵያውያን ገለል እንዲሉ ይደረግበታል፡፡ በሃገራችን ይሄው ህግ እየተጠቀሰባቸው እንደ ቀልድ ‹‹በሽብርተኝነት ተጠርጥረው›› እየተባለ ወደ እስር ቤት የሚወረወሩት በርካታ ናቸው፡፡ ስለዚህ መንግስት ህጉን ለተቀናቀኞቹ እንደ ማጥቂያ መሳርያ እየተጠቀመበት ነው ብዬ አምናለው ፡፡ ዓርብ ሐምሌ 6 ቀን 2004ዓ.ም በወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱዓለምአራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ስም የተከሰሱ ኢትዮጵያውያንና በታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተበየነው ከስምንትዓመት እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ፅኑ እስራት የሚያመላክተን ገዥው ፓርቲ እየተከተለው ያለው አቅጣጫ አደገኛና ሃገሪቱን ወደ መጥፎ ሁኔታ የሚከት ተግባር እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ‹‹የፀረ-ሽብር ህጉ›› እና ‹‹ሽብርተኛ›› የሚለውን ጨዋታ በማቆም እንዲሁም ከተቃዋሚዎች ጋር በመወያየት አፋጣኝ እርምጃዎች መውሰድ ይገባዋል፡፡ በተጨማሪም ገዥዎች ህግ ጠቅሰው ሲፈርዱ ህዝቡ ምን እንደሚላቸው ጆሮ ሰጥተው በመስማት እውነቱን ለማየት መሞከር ይጠበቅባቸዋል፡፡ መንግስት ህዝብን ማዳመጥ ውዴታው ሳይሆን ግዴታው ነው ፡፡ እንደ እኔ እምነት ታጋይን በማሰር ትግሉን ማቆም ፈፅሞ አይቻልም፡፡ ትውልድ እስከቀጠለ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል፡፡ብዙ ሺ አንዷለዓሞች ብዙ ሺ እስክንድሮችም ይፈጠራሉ፡፡ ለዚህነው ማሰርና ማሳደድ ፈፅሞ መፍትሄ አይደለም የምለው፡፡ሞት ለአባገነን ድል ለሰፊው ህዝብ!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

No comments:
Post a Comment