Tuesday, June 25, 2013

የሰንደቅ አላማ ክብር እና የብሔራዊ መዝሙራችን ጉዳይ

አንዲት ሀገር አንድነቷን፣ሉዓላዊነቷን እና የወደፊት ተስፋዋ ከሚግለፅበት መንገድ አንዱ ብሔራዊ
መዝሙሯ ነው። የብሔራዊ መዝሙርመከበር፣መወደድ እና ዋጋ መሰጠት ከሚገለፅባቸው መንገዶች
አንዱ ደግሞ ትምህርትቤቶች ናቸው። ከትምህርት መጀመር በፊት ተሰልፈውየሚያደርጉት
የ ሰንደቅ አላማ ማውጣት እና ማውረድ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።
የነገ ተረካቢ ልጆች የብሔራዊ መዝሙርን እንዲዘምሩ ብቻ ሳይሆን ከሁለንተናቸው ጋር ተዋህዶ
ነገ ለሀገራቸው ፍቅር ያላቸው ዜጎች እንዲሆኑ የማድረጉ ፋይዳ ትልቅ ነው።
 አለመታደል ሆኖ ግማሽ ምዕተ አመት ባልሞላ ጊዜ ብቻ ሁለት ጊዜ የብሔራዊ መዝሙር መቀያየር
ከ መንጋሥታት መቀየር ጋርገጥሞናል።ይህም ሁል ጊዜ ከ ዜሮ የመጀመር አባዜ አዲስ መጤውን
ባለዙፋን የመጠናወቱ ውጤት መሆኑ ነው።
የቀደሙት ሁለትመንግሥታት የ ንጉሱም ሆነ የደርግ ስርዓታት የብሔራዊ መዝሙር በየዘመናቸው
ለነበሩት ትውልዶች ውስጥ የማስረፁ ሥራእንደተሳካላቸው በየዘመኑ የነበሩት ትውልዶች እስካሁ ድረስ ከህሊናቸው ያለመጥፋቱ ጉዳይ ምስክር ነው።
የንጉሱን ዘመን ባላስታውስምበደርግ ዘመን ግንትምህርትቤቶች ዝናብ ሆነ ፀሐይ ሳንል በክብር ሰንደቅ
አላማ የመስቀል ስነስርዓት ይከናወን እንደነበረ እናበ ትምህርትሚኒስቴርም ቁጥጥር የሚደረግበ ጉዳይ ነበር።የመስርያቤት ሰንደቅ አላማዎችም በጥበቃ አባላት ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ
ተሰቅሎከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ በክብር ወርዶ ይቀመጥ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።
ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ያክል የብዙ አመትየመንግስትነት ታሪክ ያላት ቀርቶ በቅርቡ የመንግስትነት
ቅርፅ የያዙ መንግሥታትም ትኩረት የሚሰጡት ትልቅ አብይ ክንውን ነው።
ኢህአዲግ ወደስልጣን ከመጣ ጀምሮ ”የሰንደቅ አላማ ቀለም  ይቀየር ወይንም በነበረበት ይቆይ?” በሚል በምክርቤቱ ውስጥ  የመነጋገርያአጀንዳነት ድምፅ
ማሰጠቱም በላይ የብሔራዊ መዝሙሩም እንዲቀየር ሆኗል።ባንዲራ (ሰንደቅ አላማ) የመቀየር ጉዳይ
 በውይይት የሚነሳውምሆነ ለ አንጀንዳነት የበቃበት ጊዜ በዓለም ታሪክ ላይ እንደምንረዳው ሀገሮች
 ከቅኝ ግዛት ሲላቀቁ  ብቻ ነው።
በኢትዮጵያ ግንለውይይት ቀርቦ በመጨረሻ የህዝቡ ስሜት ከፍተኛ መሆኑ ስለታወቀ
በሰንደቅ አላማው መሃል ላይ የኮኮብ ምልክት ብቻእንዲደረግ አስመወሰነ።
 የዛሬው ጥያቄዬ ግን ይህ ብቻ አይደለም። የአሁኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር በ ኢትዮጵያ
ትምህርት ቤቶች ከገጠር እስከ ከተማይዘመራል ወይ? ትምህርት ሚኒስቴር ምን ያህል በምን
አይነት ደረጃ ይቆጣጠራል? ሰንደቅ አላማውስ የክልሉን ነው እንዲያከብርየሚደረገው ወይስ ብሄራዊውን?
አሁን ያለው ትውልድ ነገ ኢትዮጵያን እንዴት እንዲገልፃት እየተደረገ ነው? የኢትዮጵያ ባለስልጣናትበተለይ
የ ሰራዊቱ መኮንኖች ብሔራዊ መዝሙርን ከቀድሞ ታጋይ ዘፋኞች ዘፈኖች በላይ በምን ያህል ክብር
እና ዋጋ ይወዱታል? ሕብረተሰብአመለካከቱ በአንድቀን አይቀየረም የዘመናት ስራዎች ውጤት ነው
 ሀገር ወዳድም ሆነ የሀገር ጠላት የሆነ ትውልድ የሚፈራው በየዕለቱ በሚሰሩ ስራዎች ጥርቅም ነው።
ብሔራዊ መዝሙር መዘመር እና ሰንደቅ አላማ በክብር መስቀል ደግሞ ሀገር ገንቢ ትውልድ የመፍጠር አካል ነው።
 ተቃዋሚ ፓርቲዎች (በተለይ በሀገር ቤት ያሉት) ሊያነሱዋቸው እና የህብረተሰቡን አትኩሮት የሚስቡ
ብቻ ሳይሆኑ ለውጥ ማምጣትየሚገባቸው እንደ ብሔራዊ መዝሙር የመሰሉ  የሀገር አንድነት እና የተከታታይ ትውልድ የማፍራት ስራዎችን ልብ ሊሉ ይገባል። ስልታዊየአንድነት የመናድ ስራዎች እንደ ብሔራዊ መዝሙር ባሉት ጉዳዮችን 
ችላ በማለት ይገለጣሉ። ትምህርት ሚኒስቴር ምን እየሰራነው? ምን አይነት ትውልድ ለኢትዮጵያ
እየተደገሰላት ነው? ኢህአዲግም በፓርላማ መክፈቻ መርሃግብር ላይ
 (መስከረም ወር ላይበሚደረገው ስነ-ስርአት) ከአስር በላይ የሆኑ የባንዲራ ጨርቆች ሕፃናትን
አስይዞ በመዘመር
መከፋፈሉን እያረዳን ነው።ፓርላማ ያሰባሰበጉዳይ ኢትዮጵያ በሚል ስም እስከ ሆነ ድረስ አስር
አይነት ጨርቅ ማሳየት እና በፓርላማው መድረክ ላይ ማዘመር ለምን አስፈለገ? ለእዚህም ለምን ሕፃናት ተመረጡ? ትምህርትቤቶች በተለይ በክልል ደረጃ ባሉ ትምህርትቤቶች የክልሉ ባንዲራ ከኢትዮጵያ ባንዲራ የበለጠ ዋጋ ሲሰጣቸው አንዳንዱ ጋር እንዲያውም የክልል መዝሙሮች እንዲዘመሩ ሲደረጉ ምን ያህል የተለያየ ትውልድ ለመፍጠር ተተተግቶ እየተሰራ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው።

No comments:

Post a Comment