አሸባሪነት እና አተረጓጎሙ !!!!!

ወያኔ ለእኛ የሾማቸዉ እራሳቸዉን በእኛ ላይ የሾሙ ካድሬዎች የቅጂ መብትን ከመጣሳቸዉ ያፈፃፀም ስህተታቸዉ
የስህተትን ድንበር እየተሻገረ ስለሆነ በህግ ልንላቸዉ ይገባል ያለመከሰስ መድታቸዉን ከካድሬዎቹ ላይ
ያንሳልንና፤(ልብ ልንለዉ የሚገባዉ ያለመከሰስ መብት በህግ የተሰጣቸዉ ህዝብን ወክለዉ ፓርላማ የገቡ ብቻ ናቸዉ)
የዛሬዎቹ ግን ያለመከሰስ መብታቸዉ ለገዢ ከወገኑ እስከ ቀበሌ የወረደ ይመስላል፡፡
ወደ ዋና ጉዳዬ ስመለስ ሰሞኑን በሰዉ በሰዉ የማዉቃቸዉ የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸዉ ቤቱን ተረክበዉ የመጨረሻ
የማጠናቀቂያ ስራ እየሰሩ ሳለ አንዱን ሲያጠናቅቁ ወደ ሌላዉ ሲገቡ በስሜት እየሆኑ የጋራ መኖሪያዉን ህግ እየዘነጉ
ዉበትን እያሰቡ ግንባታዉን ያጣጡፉት ቀጠሉ(ባለቤቶቹ የህንፃ ግንባታ ባለሙያ ናቸዉ) ስራዉን የሚሰሩት አንድም
ዉበትን አንድም በህንፃዉ ላይ የነርሱ ቤት ያለዉን ክብደት ለመቀነስ አብዛኛዉን በመስታወት የመጠቀም ስራ ነበር
የሰሩት ስራዉም ተጠናቋል፤ … … የሰፈር ደንብ አስከባሪ 10 እና 20 ብር ሲቀበል ፣ ሲያሰራ ከርሞ መጨረሻ ላይ
ወይ የተቀበለዉ አላረካዉ ወይ በቅናት ወይ ለህግ ተገዢነቱ ትዉስ ብሎበት በአስቸዃይ አፍርሱት ይላቸዋል፡፡ ይኸ
ነገር ከመኖሪያ ሰፈሩ ተነስቶ ቀበሌ፣ ከቀበሌ እንደገና ይነሳና ቤቶች ልማት፣ ክፍለከተማ … እያለ ይቀጥላል፤….
…. የቤት ባለቤቶቹ (ተከሳሾች) እሺ አጥፍተናል! እኛ ስንጀምረዉ ብዙዎቹ የሚመለከታቸዉ ሰወች አይተዉታል አሁን
አፍርሱ ብለዉ የሚማገቱን በስፍራዉ ነበሩ የምንሰራዉ ስህተት መስሎ ስላልታየን ግንባታዉን ከምናፈርስ መቀጣት
ያለብንን እንቀጣና ቤቱ ባለበት እንቀጥል ብለዉ ሃሳባቸዉን ቢገልጡላቸዉ ሊሰሙአቸዉ አልቻሉም እንዲያዉም እስጣገባ
ዉስጥ ገብተዉ ነገሩ ተጠምዞ የፈረደባቸዉ ባለራዕዩ ጠቅላይ ሚኒስተር በማያገባቸዉ ገብተዉ እሳቸዉ የመረጡትን ፕላን
እናንተ ማን ስለሆናችሁ ትቀይሩታላችሁ? እንደያዉም አሸባሪዎች ናችሁ እንዲህ አይነት ስራ ከአሸባሪነት ተለይቶ
አይታይም ተብለዉ በትርጉም አልባ ቃላታቸዉ ሰዉን መፈረጅ ሲፈልጉ በቃላት በሚዋጉት ካድሬዎች አሸባሪ ተብለዉ
ተፈርጀዉ ግንባታዉን እንዲያፈርሱ ታዘዉ ተመለሱ፡፡ እስኪ ነገሮችን በቅንነት እናስበዉ፣ እንከባበር አንድ ሰዉ መሪ
ስለሆነ ሁሉን አዋቂ ነዉ ብለንም አንመን ምናልባት የፖለቲካዉ መሃንዲስ እንደሆነ እንጂ በፍፁም የህንፃ መሃንዲስ
ይሆናል ማለት ዘበት ነዉ፣ መጥቀስም አስፈላጊ ከሆነ የሞተ ሰዉ ለቀቅ አርገን በነዋሪዎች እንማል ራዕያችንም
ግባችንም እስከመቼ ነዉ ሙት የሚሆነዉ? እናንተ ማን ናችሁ ላሉት መሃንዲሶች መሆናቸዉን ዘንግተዉት አይመስለኝም ክፉ
መንፈስ ተፀናዉቶአቸዉ ካልሆነ በቀር እንዃን ከጠያቂዎቹ ከተባለዉም ሰዉ በሙያቸዉ ይሻላሉ ብዬ አምናለሁ፡፡
እስኪ በዚህ አገር ህግ ሲወጣ ህዝብ ማዕከል ያደረገ የሚሆነዉ መች ነዉ? ህዝቡስ ይህ ጉዳይህ ስለሆነ እንመካከር
የሚባለዉስ? ህዝቡ ይዞት የመጣዉ መቼ ነዉ ተቀባይነት የሚያገኘዉ? መቼ ነዉስ ከመፈረጅ የሚድነዉ?(አሸባሪ፣
ነፍጠኛ፣ አደገኛ ቦዘኔ፣ሙሰኛ፣…) ህጋችንስ ባህላችንን አገናዝቦ ህዝቡን ግምት ዉስጥ ከቶ ካለዉ ነባራዊ ጉዳይ
አንፃር ጋር ተዛምዶ በእናዉ ሰዉ ለእናዉ የሚወጣዉ መቼ ነዉ? ከቀጪነቱ(ከተበቃይነቱ) ባለፈ አስተማሪ(አንዱ ካንዱ
ሳይጣረዝ) የሚሆነዉ መቼ ነዉ?በጋራ ጉዳያችን በጋራ የምንወስነዉ መቼ ነዉ?ሁሌ መቼ ነዉ እኛ ለአገር የማናስብ፣
አጥፊ፣ አሸባሪ፣ ሌባ ፣ ወንበዴ፣… የሚለዉ አስተሳአብና ትርጓሜ የሚነሳልን?
የሆነዉ ሆነ ግን እስኪ እያንዳንዱን ትርጓሜ እናጢነዉ (ኪራይ ሰብሳቢና ጉቦ እስኪ ምን ያገናኛቸዉ ነበር?) ልብ
አርጉ የቀጣዩ ትዉልድ ዕጣ ፈንታ በእጃችን ነዉ፤ ቀጣይ ትዉልድ የምናፈራ እንጂ የምናጠፋ አንሁን!
No comments:
Post a Comment