ለሁለት ኣመት ከኣራት ወር /48 ወራት/ በከሳሽ የመንግስት ኣቃቢ ህግና በተከሳሽ ኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኣል ክስ በ13/3/2006 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰኣት በመቀሌ ሰሜን ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ተፈረደ፡፡
ኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ የህወሓት የ17 ኣመት የትግል ጉዞ ጠንካራና ደካማ ጎኑ በግልፅ በመፃፍ ኣምስት መፅሃፍቶች ለንባብ ኣብቅታል። ኣቶ ኣስገደ የፃፉት መፅሃፍ ታሪክ ስለሆነ ታሪክ ሲፃፍ ደግሞ በታሪኩ መሰረት ከነባሩ ግለሰዎችና ብዱኖች ሊያያዝ ግድ ይላል። በመሆኑም የኣቶ ኣስገደ መፅሃፍቶችም በውስጣቸው ብዙ ታሪኮች ኣጣቅሰዋል፡፡
እነዛ የተፃፉ መፅሃፍቶች ግን ለህወሓት መሪዎችና የነሱ ቅርብ ተላላኪዎች ብዙም የሚያስደስቱ ኣይደሉም፡፡ በመፅሃፉ የተጠቀሱ ሰዎች እንደ ኣቶ ብስራት ኣማረ ዜግነቱ ኣሜሪካዊ ትውልድ ኢትዮፕያዊ የሚኖርበት ኣገር በኣሜሪካ በኣሆዩ ኮሎምፐስ ክ/ሃገር ነው ፡፡ ኣቶ ብስራት ኣማረ በ 1986ዓ.ም ምክንያቱ ባልታወቀ ወደ ኣሜሪካ ኣገር ሄደው ለህወሓት መሪዎች በተለይ ደግሞ ለ ጠ/ሚንስትር መለስ እንደጠላት በማሰለፍ ብዙ ተናግረዋል፤ ፅፈዋል፤ ከህውሓት ተቃውሞ ጎራ ተሰልፈውም ጠንካራ ተቃዋሚ ሆነው ተንቀሳቅሳል፡፡
ኣቶ ብስራት በ1997ዓ.ም የህወሓት ኢህአደግ በተቃዋሚ ሃይሎች ተሸንፎ የህወሓት ኢህኣደግ ምርጫው ሲያፍነው ኣቶ ብስራት ኣማረም እኔ ከዛሬ ጀምሮ ከምጠላው ከህውሓት ጎን እሰለፋለው ብለው በሚድያ በመናገር ድንገት ከህወሓት መሪዎች ታረቁ። ኣቶ ብስራት ጠንካራ ተቃዋሚ የሚመስሉ የነበሩ ድንገት ተቀይረው እኔ ህውሓት ነኝ ሲሉ ለብዙ ኢትዮዽያዊያን ኣግራሞት ፈጥሮባቸዋል። ኣቶ ብስራት የህወሓት ኢህኣደግ ጠላት ሆነው በኣሜሪካ የሚታወቁ የነበሩ ብስራት ኣማረ በ1997ዓ.ም ያለ ኣንዳች ችግር ኣዲስ ኣበባ ገብተው እስከ ትግራይ በመምጣት ልዩ ኩብራ መኪና ተሰጡታቸው ይንሸራሸሩ ነበሩ፡፡
ቆየት ብለውም በኢንቨስትመንት ተሰማሩ። ኣቶ ኣስገደ ጋህዲ 1፤2፤3 ፅፈው ለንባብ ከበቁ በኃላ መፅሃፍች ለህወሓት መሪዎች ስላላስደሰቱ በግልፅ የማይነገርለት ቁጣን ፈጠሩ፡፡ ግን ደግሞ መፅሃፍቶቹ በተነበቡበት ቁጥር በህዝብ ላይ ደስታን በመሪዎችም ጥላቻ መፍጠር ጀመሩ። ከሁለት ኣመት በኃላ ኣቶ ኣስገደ ለመክሰስ ተፈለገ ።ግን ደግሞ ባገር ውስጥ ካሉ ሰዎች እንዳይከሰሱ የይርጋ ጊዜ ኣልፋል ኣልተቻለም፡፡
እንደ ኣጋጣሚ ግን ብስራት ኣማረ ተገኘ። በወቅቱ ገብቶ ስለነበር መፅሃፉ ስማቸው ተጠቅሶ ስላለ በውጪ ስለነበር የተፃፈው ስለሚያውቅ ክሱ በብስራት ኣማረ ይመስረት፤ ኣስገደ በሆነ መንገድ መታሰር ኣለበት ብለው ወሰኑ። ዋና ተከሳሽ መፅሃፉ ጋህዲ 3 ነው ከታተመ ሁለት ኣመት ከሶስት ወር በኋላ በብስራት ኣማረ ስም ክስ ተመስርቶ ክርክሩ በመንግስት ኣቃቢ ህግ እንዲመሰረት ተደረገ ። ኣቶ ብስራትም ታማኝነታቸው ለማረጋገጥ ክሱን መስርተው ኣሜሪካ ገቡ፡፡ ኣቶ ኣስገደ በቀደማይ ወያኔ ወረዳ ፖሊስ ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዳኛ ሙኡዝ ፍሱሕ ስልጣኔ ኣይደለም ብለው ኣሰናበቱዋቸው። ለ2ኛ ጊዜ በሰሜን ወረዳ ምድብ ችሎት በፖሊስ ተይዘው ቀረቡ ዳኛ ወ/ሮ ኪዳን ኣብርሃ በይርጋ ጊዜ ዘጉት። ኣቃቢ ሕግ ወደ መቀሌ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ኣለ። የመቀሌ ፍርድ ቤት ዳኛ ሃይለ ገ/ስላሴም በይርጋ ሊዘጋ ኣይቻልም ብሎ በወረዳ ተመልሶ ባላየው ዳኛ ትእዘዛዝ ሰጠ። እንደገና የሰሜን ወረዳ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ወ/ሮ መብርሂት ሃዱሽ በኣቶ ኣስገደ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጡ። ኣቶ ኣስገደም ጥፋተኛ ኣይደለሁም የፃፍኩት መፅሃፍ ሃቀኛ ታሪክ ነው። በመሆኑ ደግሞ ጠ/ሚንስተር መለስ ዜናዊ ያሉበት 18 የህወሓት ማ/ኮሚቴ ያሉበት መከላክያ ምስክሮች ኣቀረቡ። ዳኛ መብርሂት ሓዱሽ መጀመርያ ለመከላክያ ምስክሮች ለማቅረብ ወስነው ማቅረብያ ደብዳቤ ከፃፉ በኃላ በማን ተፅእኖ እንደደረሰገቸው ኣይታወቅም ውሳኒያቸው በመሻር ያለ መከላከያ ምስክር ፈረዱት፡፡
ኣቶ ኣስገደ በ6ወር እስራትነና 1000 ብር ተወሰነበባቸው ።ነገር ግን ኣቶ ኣስገደ መጥፎ ሪከርድ ስለሌላቸው በኣንድ ሺ ብርና ሁለት ኣመት ገደብ ተፈረደባቸው፡፡
ኣቶ ኣስገደ እንደገና ወደ መቀሌ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው የመከላክያ ምስክርነት የማቅረብ መብት ይጠበቅልኝ ኣሉ፡፡የመቀሌ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ስብሀትም<< ወደ ወረዳ ፍርድ ቤት ወርደው ያስመስክሩ >>ብሎ የፍርድ ትእዛዝ ሰጠ። ኣቶ ኣስገደ እንደገና በመቀሌ ሰሜን ወረዳ ፍርድቤት ምድብ ችሎት 10ወር ከተከራከሩ በኃላ በ13/03/2006ዓ.ም 10 ሰኣት በዳኛ ክብርኣብ ብርሃነ ጭራሹን መዝገቡ ዘጋው፡፡መቋጫ አገኘ።
የኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ መከሰስ በመቀሌ ህዝብ ትእዝብትም የኣቶ ብስራት ኣማረ የህውሓት መሪዎች መሳርያ ሆነው ለኣቶ ኣስገደ በማንገላታት ሰውን መጉዳት እንጀራን ማብሰል ብለው ትልቅ ትችት እየተሰጡባቸው ነው፡፡
ከጎመራው
ከመቀሌ
ከመቀሌ
No comments:
Post a Comment