Saturday, November 30, 2013

የ132 መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን ማህተም እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችን እና የተለያዩ ግለሠቦችን ማህተም በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረው ተከሰሰ

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና የኢ/ር ሃይሉ ሻውል ቲተርና የፓርቲያቸው ማህተም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ማህተም
የኦነግና የኢሜሬት ኢምባሲ ማህተሞች ተገኝተዋል
የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የ132 መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን ማህተም እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችን
እና  የተለያዩ ግለሠቦችን ቲተር በህገወጥ መንገድ በመያዝ ለግለሠቦች ሃሠተኛ ማስረጃዎችን ሲሠራ ነበር የተባለው
ተጠርጣሪ ላይ በፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ የቀረበው ክስ እንዲሻሻል ፍ/ቤት ብይን ሰጠ፡፡
አቃቤ ህግ በተጠርጣሪው አቶ ኮከብ ጥላሁን አማረ ላይ ሁለት ክሶችን ያቀረበ ሲሆን በመጀመሪያው ክስ ላይ የውጭ
ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የኤምባሲዎች፣ የግልና የመንግስት
ዩኒቨርስቲዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የሃገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የአስተዳደሩን
የተለያዩ ቢሮዎች የክልል መንግስታት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ
ኮሚሽን  የቦሌ ኢምግሬሽን የኢትዮ ቴሌኮም እና የንግድ ሚኒስቴር የተለያዩ ቢሮዎችና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ማህተም
እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችና ኢንስፔክተሮችን ጨምሮ የተለያዩ ግለሠቦችን ቲተር በተጨማሪም የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ
ጋዜጠኞች ማህበርንና የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ማህተምና የሊቀመንበሮቻቸውን ቲተር ይዞ መገኘቱን
አመልክቷል፡፡
ተከሳሹ ከመንግስት ሚኒስቴር መስርያ ቤቶችና ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ባሻገር እንዲሁም አሜሪካ እና የግብፅ
ኤምባሲዎችን ማህተም፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ደግሞ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)፣ የአንድነት
ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ማህተሞች እና የሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ
ድርጅቶች ማህተም ይዞ መገኘቱ ተገልጿል፡፡ የኢ/ር ኃይሉ ሻውል እና የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ቲተሮችም ይዞ ተገኝቷል
ይላል የክስ ዝርዝሩ፡፡
ከግል ተቋማት መካከልም የእንይ ሪል ስቴት ማህተም፣ ብዛት ያላቸው የግል ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማህተም፣
የተለያዩ ባንኮችን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማህተም እንዲሁም መንግስት ወደ ግል ይዞታነት እንዲዞር በማሠብ ተደጋጋሚ
ጨረታ የሚያወጣበት የግዮን ሆቴሎች ድርጅት ማህተም ይገኙበታል፡፡
በአቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ላይ ተከሣሹ በድምሩ 132 ከሆኑት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ማህተምና ቲተር እንዲሁም ህጋዊ
ሠነዶች በተጨማሪም ኮምፒውተሮች፣ ስካነር፣ ልዩ ልዩ የሃሠት ሠነዶች ተዘጋጅተው የሚገኙባቸው ሲዲዎችን ይዞ
በመገኘቱ፣ በፈፀመው የመንግስትን ወይም የመንግስት ባለስልጣናት ማህተሞችንና የህዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ነገሮችን
ሃሠተኛ አድርጐ ወይም አስመስሎ ለመስራት የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል፡፡
በኮሚሽኑ አቃቤ ህግ በሁለተኛ ክስነት የቀረበውም ግለሠቡ እነዚህን ማህተሞች፣ ቲተሮችና ሠነዶች በመጠቀም ለተለያዩ
ግለሠቦች ህገ ወጥ የትምህርት ማስረጃ፣ የልደት ሠርተፊኬት፣ የተለያዩ ድጋፍ ሠጪ ደብዳቤዎች፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የስራ
ልምድ፣ የንግድ ፈቃድ፣ የመኪና ሊብሬ፣ የኤምባሲ ደብዳቤዎች እንዲሁም ፓስፖርቶች እና ሌሎች ብዛት ያላቸውን
ህገወጥ ሠነዶች እጁ እስከተያዘበት ሐምሌ 2005 ዓ.ም ድረስ አስመስሎ በማዘጋጀት፣ ተከሣሹ በፈፀመው መንግስታዊ
እና የህዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ሠነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ተከሷል ይላል፡፡
የመንግስት እና የግል ተቋማት ሠነዶች መስለው በተከሣሹ የተዘጋጁ ሃሠተኛ ሠነዶች በተከሣሹ መኖሪያ ቤት በተደረገው
ብርበራ መገኘታቸውም በክሱ ተመልክቷል፡፡
ከትናንት በስቲያ ሃሙስ እለት የዋለውና የሙስና ጉዳዮችን የሚመለከተው የከፍተኛው ፍ/ቤት  1ኛ ወንጀል ችሎትም
ቀደም ባለው ቀጠሮ ከተከሣሽ የቀረበውን የክስ መቃወሚያ እና ከአቃቤ ህግ የተሠጠውን የመቃወሚያ መልስ ከመረመረ
በኋላ በሠጠው ብይን፤ ተከሣሹ ኮሚሽኑ ክሡን የማቅረብ ስልጣን የለውም በማለት ያቀረበውን ተቃውሞ
እንዳልተቀበለው አስታውቆ፤ ከሣሽም ሊያሻሽላቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ብርበራ
የተካሄደበትን ቤት አድራሻ በተመለከተ አቃቤ ህግ በተገቢው መንገድ አሟልቶ እንዲያቀርብ፣ “ሌሎች በርካታ ሃሠተኛ
ሠነዶች” ተብለው የተመለከቱ በዝርዝርና በቁጥር እንዲጠቀሱ እንዲሁም የመንግስት እና የግል ሠነዶች ተለይተው
እንዲቀርቡ ሲል ፍ/ቤቱ ብይን የሠጠ ሲሆን በአጠቃላይ አቃቤ ህግም ክሡን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ብሏል፡፡
ቀጣዩን ሂደት ለመመልከትም መዝገቡን ለታህሣስ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ

Europa

በአወዛጋቢው የ1997 ዓ.ም ምርጫ የታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት አና ጐሜዝን ጨምሮ “ለአፍሪካ ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክና
የአውሮፓ ህብረት” የጋራ ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ሰሞኑን ከተቃዋሚ ፓርቲ
መሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡
ፓርቲያቸውን ወክለው በውይይቱ እንደተካፈሉ የተናገሩት የኢዴፓ ማዕከላሚ ኮሚቴ አባል አቶ ልደቱ አያሌው፤
የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት የኢትዮጵያ የዲሞክራሲና የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ምን አዲስ ነገር አለ? የወደፊቱ
አቅጣጫ ምን ይሆናል? በማለት ጥያቄ እንደሰነዘሩ ገልፀዋል፡፡ የፓለቲካ ምህዳሩ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊጠናከሩ
የሚችሉበት እድል ከጊዜ ወደ ጊዜ መጥበቡን ተናግሬያለሁ የሚሉት አቶ ልደቱ፣ የሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሂደት
እንደሚያሳስበንና የአውሮፓ ህብረት እርዳታ የፓለቲካ መጠቀሚያ እንዳይሆን ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለባቸው
አስረድቻለሁ ብለዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ለአገራችን እርዳታ መስጠቱን እንደማንቃወም፣ የእኛን ችግር እነሱ እንዲፈቱ
እንደማንጠብቅ ገልፀንላቸዋል ያሉት አቶ ልደቱ፤ ከዲሞክራሲያዊና ከሰብዓዊ መብት አያያዝ አኳያ ማድረግ
የሚገባችሁን ወደኋላ ትታችኋል፤ እርዳታ ሰጪ እንደመሆናችሁ ማድረግ ያለባችሁን ነገር ዘንግታችኋል የሚል አስተያየት
ሰጥቻለሁ ብለዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አስራት ጣሴ በበኩላቸው፣ የፓለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን፣ የሠላማዊ ትግል ተስፋ
መዳፈኑንና ህገ መንግስቱ እየተከበረ አለመሆኑን እንዳስረዱ ጠቅሰው፤ በነፃው ፕሬስ ህግ፣ ተሻሽሎ በወጣው የፓርቲ
ህግ፣ በፀረ ሽብርተኛ አዋጁ ዙሪያ እንደተወያዩበት ተናግረዋል። በ2002 ዓ.ም. ምርጫ በዝርፊያና በንጥቂያ ኢህአዴግ
99.6 በመቶ ድምፅ አግኝቶ ማለፉን በመጥቀስ፤ 2007ዓ.ም. የሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ አጣብቂኝ እንደሆነብን
ለአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት አስረድቻለሁ ብለዋል – አቶ አስራት፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህዝቡን ሰብስበን ማነጋገር፣ ሠላማዊ ሰልፍ ማድርግ እንዳልቻልንም፣ የመንግስትን ጫና በማሳየት
ገለፃ አድርጌያለሁ በማለት አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት አባላት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም
ጋር ቀደም ብለው ውይይት ማድረጋቸውን የተናገሩት አና ጎሜዝ፣ አገሪቱ በኢኮኖሚ ማደጓለ እንደሚገልፅና ልማቱ ግን
ህዝቡን ከድህነት ያላወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በ2007 ዓ.ም. ለሚደረገው አገራዊ ምርጫም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አና ጐሜዝ ገልፀው፤ ታዛቢዎችን ከመላክ
በተጨማሪ በየሁኔታው እና በየወቅቱ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡
መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በውይይቱ ላይ ተካፋይ እንደነበሩ ታውቋል፡፡

Friday, November 29, 2013

ተገን ጠያቂዎቹ ክስ መሠረቱ

ባህር ዉስጥ ከመስጠም የተረፉ ሶስት ኢትዮጵያዉን ተገን ጠያቂዎች ከትናንት በስተያ የቤልጂየም ጦር ሠራዊት ላይ ክስ መሠረቱ። ከሁለት ዓመታት በፊት በጀልባ የተጫኑ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ወደጣሊያን ሲጓዙ ለአደጋ መጋለጣቸዉን ከተመለከቱ በአካባቢዉ ከነበሩ ኃይሎች ርዳታ ባለማግኘታቸዉ 63ቱ ህይወታቸዉ አልፏል።

6tyrpp
በጎርጎሪዮሳዊዉ 2011 መጋቢት ወር ላይ ነዉ 72 ስደተኞች ከሊቢያ ወደጣሊያን ለመጓዝ ሜዲትራኒያን ባሕር መሀል ሲደርሱ የጫነቻቸዉ የፕላስቲክ ጀልባ ድንገት ተሰናከለች። እናም ያለምንም ርዳታ፤ ምግብ እና ዉሃ ለ15 ቀናት ባህር መሃል ሊንሳፈፉ ግድ ሆነ። በወቅቱ ሊቢያ ዉስጥ በነበረዉ ሕዝባዊ አመፅ ሰበብ በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ባህሩ ላይ የተለያዩ ሃገራት የባህር ኃይሎች ተሰማርተዋል፤ አንዳቸዉም ግን ስደተኞችን ሊያድኗቸዉ አልፈለጉም። ከአደጋዉ ከተረፉት አንዱ እንደገለጸዉ፤ አንዲት ሄሊኮፕተር አራትና አምስት ጊዜ አንዣበበችባቸዉ፤ እንደዉም ባልተለመደ ሁኔታ ዝቅ ብላ ስለነበር አብራሪዉን ሁሉ ተመልክተዋል፤ እናም ሊታደጉን ነዉ የሚል ተስፋ አደረባቸዉ። ግን ማንም ብቅ አላለም። የተጨነቁት ስደተኞች በወቅቱ ስልክ እንደደወሉላቸዉ የሚናገሩት ለስደተኞች የሚሟገተዉ አዠንሲያ ሃበሻ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አባ ሙሴ ዘርዓይ ሁኔታዉን እንዲህ ይገልጻሉ።
አባ ሙሴ እንደሚሉት በተባሉት 15 ቀናት የተለያዩ ሃገራት መርከቦች ስደተኞቹ ያሉበትን አደገኛ ሁኔታ አይተዋል። ግን ሊረዷቸዉ አልሞከሩም። በአጋጣሚዉም ከመካከላቸዉ 63ቱ ስደተኞችም በርሃብና ጥማት ለሞት ተዳረጉ። በሂደቱም ዓለም ዓቀፍ የባህር ሕግ በመጣሱ በሕግ ሊጠየቁ የሚገባቸዉ አሉ።
የስደተኞቹ የድረሱልን ጥሪ ለጣሊያን የባህር ድንበር ጠባቂዎች ሲተላለፍ፤ እነሱንም ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን የትብብር ማዕከል እንዲሁም በስፍራዉ ለነበሩ የጦር መርከቦች ማስተላለፋቸዉ ነዉ የተነገረዉ። ይህ ጥሪም ለተከታታይ 10 ቀናት በየአራት ሰዓት ልዩነት መደጋገሙም እንዲሁ። ሊረዳቸዉ የመጣ አካል ግን አልነበረም። አዉሮፕላን፤ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር፤ የአሳ ማስገሪያ ጀልባዎች እንዱሁም ትልቅ ወታደራዊ መርከብ ሁሉ እያዩዋቸዉ እንደዋዛ አልፈዋል። ከሞት ጋ ተፋጠዉ 15 ቀናትን ከገፉት መካከል በህይወት የተረፉት 11 ናቸዉ። 63ቱ 20 ሴቶችና 3 ህጻናትን ጨምሮ ሞቱ።
ጉዳዩን የመረመረዉ የአዉሮጳ ምክር ቤት የፓርላማ ኮሚቴ በወቅቱ የስደተኞቹን ህይወት ማትረፍ የሚያስችሉ አጋጣሚዎች መታለፋቸዉን፤ የሀገራቸዉን ሰንደቅ ዓላማ እያዉለበለቡ ሳይረዷቸዉ በአካባቢዉ ያለፉ መርከቦችም የባሕር ሕግ መጣሳቸዉን አረጋግጧል።
እንደእሳቸዉ እምነትም ለዚህ የሚገኘዉ ምላሽ በቅርቡ ላምፔዱዛ ደሴት ተቃርበዉ ሳለ የሚረዳቸዉ አጥተዉ ሰጥመዉ ካለቁ ወገኖች ጋ አብረዉ የነበሩና ተገደዉ ወደሊቢያ እንዲመለሱ የተደረጉትንም ጉዳይ ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ መንገድ ይከፍታል።

በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አጠገብ የተገኘው ጥቅል ቦምብ መሆኑ ተረጋገጠ


በሩሲያ ሞስኮ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ በፖሊስና አነፍናፊ ውሻ አማካይነት የተገኘው ጥቅል፣ ቤት ሠራሽ ቦምብ መሆኑን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎት ማረጋገጡን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡
ዘ ቮይስ ኦፍ ራሺያ (የሩሲያ ድምፅ) የተሰኘው የአገሪቱ ሬዲዮ በድረ ገጹ እንዳለው፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ በፖሊስና በአጋዥ አነፍናፊ ውሻ አማካይነት በኢትዮጵያ ኤምባሲ አቅራቢያ ተቀምጦ የተገኘው ጥቅል ዕቃ ወደ ላብራቶሪ ተወስዷል፡፡
በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አካባቢ ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ አቅራቢያ ወድቆ ከተገኘውና በኋላም በቤት ውስጥ እንደተሠራ ከተረጋገጠው ቦምብ ጋር አብሮ የሞባይል ስልክ ተያይዞ መገኘቱን የአገሪቱ የደኅንነት አገልግሎትን የጠቀሰው ዘገባ ያመለክታል፡፡
በሩሲያ የአገር ውስጥ ደኅንነት አገልግሎት ላብራቶሪ የተመረመረው ጥቅል ዕቃ፣ በሦስት የፕላስቲክ ብልቃጦች ውስጥ በግምት 400 ግራም የሚሆን ፓይሮ ፓውደርና ሮው ቦልትስ የተሰኘ ተቀጣጣይና የፈንጂ ዱቄት ተሞልቶ ታሽጐ ነበር፡፡ የታመቀ ተቀጣጣይ ዱቄት ከተሞሉ ብልቃጦች ጋር ተያይዞ የተቀመጠው የሞባይል ስልክም ከርቀት ፍንዳታውን ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን ምርመራው አረጋግጧል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማግኘት ያረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

Thursday, November 28, 2013

ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢያጥቡት የማይጠራ ወያኔ ነው


የኢትዮጵያ ህዝብና እናስተዳድረዋለን የሚሉት አምባገነን ገዢዎቹ ተስማምተውና አንዱ ሌላውን አክብሮ የኖረበት አንድም የታሪክ አጋጣሚ የለም። የእስከዛሬው ታሪካችን ምዕራፍ በጥቅሉ ሲታይ ታሪካችን የሚቋጨው ህዝብ ተረገጠ፤ ተጋዘ፤ ገዢዎች ደግሞ ረገጡ፤ ገዙ፤ አሰሩ፤ አጋዙ እየተባለ ነው።
ቴዎድሮስ አድሃኖም Tewodros Adhanom
አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ባለው ታሪኩ ተግዟል፤ ተረግጧል፤ ተንቋል፤ ተንቋሿል። የዘንድሮው በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት እየደረሰብን ያለው ብሄራዊ ውርደትና ንቀት ግን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ልዩ ከልዩም ልዩ ነው። በቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደዛሬው ሰብዓዊ መብቱ ተረግጧል፤ ፍትህ ተነፍጓል፤ ነጻነቱን ተገፍፏል፤ ሆኖም አገር ውስጥም ከአገር ውጭም ፈላጊና ባለቤት አንደሌለው የቤት ውስጥ እንስሳ የወገንም የባዳም እጅ አልተረባረበበትም። አንገፍግፎን አንፈልግም በቃ ብለን ያስወገድነው የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ስርዐት በስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ “ኢትዮጵያ” የሚለው ስምና “ኢትዮጵያዊነት” አገር ውስጥም ሆነ አውሮፓ፤ አሜሪካና አፍሪካ ውስጥ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ ስም ነበር።
ዛሬ ወያኔ ነጻ አወጣኋችሁ፤ እኩልነት አመጣሁላችሁ እያለ በሚሰብክበት ዘመን ግን የኢትዮጵያ ሀዝብ አገር ውስጥም በውጭ አገሮችም ባለቤት አንደሌለው ፈረስ ማንም የሚጋልብበት ፈላጊ እንደሌለው ዕቃ ያገኘ ሁሉ እንዳሰኘው እጁን የሚያሳርፍበት የተናቀ ሀዝብ ሆኗል። ለመሆኑ ለምንድነው ኢትዮጵያዊነት እንደዚህ እንደ ተራ ዕቃ የቀለለው? ኢትዮጵያውያንስ ለምንድነው በየሄዱበት እንዲህ አይነት ውርደትና ስቃይ የሚደርስባቸው? መልሱ ቀላል ነው። “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” ወይም “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም” ነው።
የወያኔ አገዛዝ እኛ ኢትዮጵያውያን “ኢትዮጵያዊነት” እያልን ስለምንሳሳለትና ስለምንከባከብለት ትልቅና ክቡር ሀሳብ በፍጹም ግድ የለውም። እንዲያውም ወያኔ ሽንጡን ገትሮ ከሚታገላቸው ዋና ዋና ብሄራዊ እሴቶቻችን ውስጥ “ኢትዮጵያዊነት” የመጀመሪያው ነው። ስለዚህም ነው ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት በግልጽ እንደተመለከትነው “ኢትዮጵያዊነት” ብለው የተጣሩ፤ የጮሁ፤ ህዝብን ያስተማሩና የታገሉ ግለሰቦች በወያኔ እየተለቀሙ የታሰሩትና የተገደሉት። ከአገር ውጭም ቢሆን በየውጭ አገሩ የሚገኙት የወያኔ ኤምባሲዎች ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው ውጭ ማግኘት የሚገባቸውን የዜግነት አገልግሎት የሚሰጡት ዜግነታቸውን እያዩ ሳይሆን ቦንድ የገዛ ያልገዛ፤ “ልማታዊውን መንግስት” የደገፈ ያልደገፈ እያሉ ወይም “የወርቃማው ዘር” አባልነቱን እያጣሩ ነው።
እነዚህንና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ሰንካላ የወያኔ መስፈርቶች ያላሟሉ ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥም ከአገር ውጭም ወያኔ በዜግነት ሳይሆነ በጠላትነት የሚመለከታቸው ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ዜጎች ናቸው። ዛሬ ከአፍሪካ፤ ከኢሲያና ከላቲን አሜሪካ አገሮች ስራ ፍለጋ ሳዑዲ አረቢያ ከሄዱ ዜጎች ውስጥ እንደ ኢትዮጵውያን እጁንና እግሩን ታስሮ የተገረፈ፤ እንደሴቶቻችን በሳዑዲ ጎረምሶች የተደፈረና እንደ ኢትዮጵውያን በየአደባባዩ የተገደለ የሌላ አገር ዜጋ የለም። ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኙ የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች የዜጎቻቸው መብት በሳዑዲ መንግስትና ህዝብ ሲደፈር ለምን ብለው ይጠይቃሉ ወይም ለዜጎቻቸው ግዜያዊ መጠለያ፤ የህክምና እርዳታና የህግ ሽፋን ይሰጣሉ እንጂ ኤምባሲያቸው በራፍ ላይ “ዝግ ነው” የሚል ጽሁፍ አይለጥፉም።
የወያኔ ኤምባሲ ግን ከስረ መሠረቱ የተቋቋመው የወያኔን የራሱን እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ስላልሆነ ይህንን የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች ለዜጎቻቸው የሚያደርጉትን ጥበቃና እንክብካቤ ለወገኖቹ ለማድረግ አልታደለም፤ ፍላጎቱም የለውም። ይህንን ቅሌትና ውርደት ደግሞ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በግልጽ ተመልክተናል። ጂዳና ሪያድ ውስጥ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን መከራና በደል ተቃውመው ሠልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ፖሊሶች ታድነው እንደታሰሩ ሁሉ አዲስ አበባ ውስጥም በወንድሞቻችንና እህቶቻች ላይ እንዴት እንዲህ አይነት በደል ይፈፀማል ብለው ሳዑዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን በአረመኔዎቹ የወያኔ ፖሊሶች ታድነው ታስረዋል፤ተደብድበዋል። አዎ! ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ ውስጥም ኢትዮጵያ ውስጥም ለምን የሳዑዲን መንግስት ተቃወማችሁ ተብለው በሁለቱም አገር ፖሊሶች እየታደኑ ታስረዋል ተደብድበዋል።
ከወያኔና ከጥቂት ሆድ አምላኪ ደጋፊዎቹ ውጭ በአገር ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአንድ አላማ ዙሪያ የተሰባሰበበትና አንድ ሳምንት ሙሉ አንድ ቃል በአንድ ትንፋሽ የተነፈሰበት ግዜ ቢኖር ወርሃ ህዳር 2006 የመጀመረያው ነው ማለት ይቻላል። የአንድ አገር ህዝብ በአንድ አላማ ስር ሲሰባሰብና በአንድነት ሲቆም ከማንም ከምንም በላይ በዚህ አንድነት መጠቀምም መደሰትም ያለበት መንግስት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የወያኔ አገዛዝ ግን ዕቅዱና ስራው ሁሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ማስጨነቅና ማበሳጨት ነው እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚሰራው ስራ ተደስቶ አያውቅም፤ ለወደፊትም የሚደሰት አይመስልም። ከሰሞኑ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ልክ የሌለው ስቃይና መከራ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀፎው እንደተነካ ንብ ከዳር ዳር ሲያስቆጣ ወያኔና ሞራለ ብልሹ ሹማምንቶቹ ግን ከዚህ ወገኖቻችንን በባዕድ አገር ለከፍተኛ ጥቃት ካጋለጠና ብሄራዊ ውርደት ካከናነበን ክስተት ትርፍ ለማግኘት የፖለቲካ ቁማር እየተጫወቱ ነው።
ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ ውስጥ በአሰሪዎቻቸው፤ በመንደር ውስጥ ጎረምሶችና በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ፤ እንግልትና ውርደት ሲደርስባቸው ኤምባሲው በራፍ ላይ “ኤምባሲው ዝግ ነው” የሚል ጽሁፍ በመለጠፍ ይበላችሁ እያለ አፉን ዘግቶ የተመለከተው የወያኔ አገዛዝ ዛሬ የወገን አሳቢና ተቆርቋሪ ለመመሰል የጭቃ ውስጥ እሾኩን ቴዎድሮስ አድሀኖምንና የአገዛዙን የውሸትና የቅጥፈት ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲን በግምባር ቀደምትነት በማሰለፍ የፖለቲካውን ገደል ቁልቁል ተያይዞታል።
ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢከፋም ቢለማም የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነው፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የስራ ሀላፊነት ደግሞ አገሪቱንና ዜጎቿን ከውጭ አገሮች ጋር በሚያገኛኙ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ነው እንጂ በአገር ውስጥ የሚሰራው ይህ ነው ተብሎ የሚነገር ስራም ሀላፊነትም የለውም። አንዴ ወዳጅ አንዴ ጠላት እየመሰለ እንደ እስስት መልኩን የሚቀያይረው ቴዎድሮስ አድሀኖም ግን ሳዑዲ ውስጥ ድረስልን ብለው ሲጣሩት ፊቱን ያዞረባቸው ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ ሲመለሱ ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ሲሞክር ይታያል። ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ቅርቅር አድርጎ ዘግቶ የወገን ያለህ ብለው የመጡትን ኢትዮጵያውያን እንጃላችሁ ብሎ ፊቱን ያዞረባቸው የአዛኝ ቅቤ አንጓቹ ቴዎድሮስ አድሃኖም እነዚሁኑ እንደ ባዳ ፊቱን ያዞረባቸውን ኢትዮጵያውያን አገር ቤት ሲመጡ “እንኳን ደህና መጣችሁ” ማለቱ የገደለውን ወታደር ለማከም ከሞከረው የናዚ ጀርመን ወታደር ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ቴዎድሮስ አድሀኖም እንደ ፈረስ ገርተው ለዚህ ባደረሱት በነመለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ ጭቅላት ሳይሆን በራሱ ጭንቅላት የሚያስብ ሰው ቢሆን ኖሮ የሱ የስራ ድርሻና ሀላፊነት ዜጎቻችን አገር ቤት ከገቡ በኋላ ሳይሆን ሳዑዲ ውስጥ እያሉ ነበር።
ዛሬ ቴዎድሮስ አድሃኖምም ሆነ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከሳዑዲ በሚመለሱት ወገኖቻችን ዙሪያ የሚያደርጉት ልታይ ልታይ የፎቶ እሽቅድምድም ወገኖቻችንን ለመርዳት ሳይሆን ዘረኛ መሪያቸው መለስ ዜናዊ ሲሞት ሳያስቡት በድንገት ከእጃቸው የወጣውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ መልሰው እጃቸው ለማስገባት ወይም በሚቀጥለው አመት በሚደረገውና ወያኔ ከወያኔ ጋር በሚወዳደርበት ትርጉም የለሽ ምርጫ የፈረደበት ኃ/ማሪያም ደሳለኝን በቴዎድሮስ አድሃኖም ለመተካት ነው። አዎ! ለመተካት … ለመተካካት። ወያኔ መተካካት እያለ አንዱን ጌኛ በሌላ ጌኛ በልቶ የጠገበውን አህያ በተራበ አህያ መተካት ከጀመረ ውሎ አድሯል። የአሁኑም ሩጫቸው ቢጭኑት አልሸከም ቢቀመጡበት አልመች ያላቸውን ኃ/ማረሪያም ደሳለኝን የራሳችን ሰው ብለው በሚጠሩት በቴዎድሮስ አድሃኖም ለመተካት ነው (ኃይለማሪያምማ አሁንስ ቢሆን በቁሙ አልተተካም ብላችሁ ነው … ድፍን አበሻ ውጭ አገርም አገር ውስጥም ሲተራመስ ኃ/ማሪያም አንዲት ቃል አልተነፈሰምኮ)
ሳዑዲ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ፓስፖርታቸውን ሲቀሙ፤ ሲደበደቡ፤ሲታሰሩና ሲገደሉ ቴዎድሮስ አድሀኖም የሰጠው ምላሽ ቢኖር የኤምባሲውንና የቆንስላ ጽ/ቤቶችን በር መዝጋት ነበር። አዎ መዝጋት። ልክ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ከመለስ ዜናዊና ከአግዓዚ ነብሰ ገዳዮች የጥይት እሩምታ ለማምለጥ ወደ ቤተክህነት ጽ/ቤት ግቢ ሸሽተው ለመግባት በሞከሩ ወጣቶችና ህፃናት ላይ አባ ጳውሎስ በሩን እንደዘጉባቸው ዛሬም የአባ ጳውሎስ ታናሽ ወንድም የሆነው ቴዎድሮስ አድሃኖም በባዕድ አገር ውስጥ አድነን ብለው በተጠጉት ወገኖቻችን ላይ የኤምባሲን በር ቀርቅሮባቸዋል።
ለመሆኑ ቴዎድሮስ አድሃኖም በየአመቱ ከ40ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በለጋ ዕድሜያቸው ከወላጆቻቸው ተለይተውና ትምህርታቸውን ትተው ስራ ፍለጋ ወደ አረቡ አለም የሚጎርፉት እሱ ሊነግረን እንደሚፈልገው በአትራፊ ደላላዎች ተታልለው ወይም የአረብ አገር ኑሮ ጥሟቸው ሳይሆን ወያኔ በሚከተለው የዘረኝነት ፖሊሲና የተበላሸ የኤኮኖሚ ስርዐት የተነሳ መሆኑን ያውቅ ይሆን? በተለይ ወጣት ሴቶቻችን በአረቡ አለም የሚደርስባቸውን ውርደትና መከራ እያወቁ በነጋ በጠባ አረብ አገር የሚሄዱት አገራቸው ውስጥ ሰርተው መኖር ስላልቻሉ ከወያኔ ጋር ከመኖር አረብ አገር ሄዶ መሰንበት ይሻላል ብለው ነው አይናቸው እያየ የሞት ወጥመድ ውስጥ የሚገቡት።
ወያኔ በእጥፍ ድርብ አሳደግኩት የሚለው የአለማችን ፈጣኑ ታዳጊ ኤኮኖሚ ለእነዚህ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሮ ቢሆንና ዜጎች ስራ የሚያገኙት ችሎታቸው ብቻ እየታየ ቢሆን ኖሮ ይህ ዛሬ የምናየው ብሄራዊ ችግርና ውርደት አይኖርም ነበር። ይሉኝታና እፍረት የሚባል ነገር አብሮት ያልተፈጠረው ቴዎድሮስ አድሃኖም የዜጎቻችንን ወደ አረብ አገር መጉረፍ በደላሎችም ሊያሳብብ ሞክሯል። አሱ ለሚከስሳቸው ደላሎች የስራና የንግድ ፈቃድ ሰጥቶ በዜጎች ንግድ እንዲከብሩ መንገዱን ያመቻቸውና የከፈተው የራሱ የቴዎድሮስ ፓርቲ ነው፤ ብዙዎቹ አትራፊ ደላላዎችም የራሱ የቴዎድሮስ ጓደኞች ናቸው። የቴዎድሮስ አድሃኖም ጉድ ብዙ ነው፤ ተዘርዝሮ አያልቅም።
ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሳዑዲ ውስጥ ሲጋዙና ሲገደሉ ቁጥሩ ተገኗል እያለ በወገኖቻችን ላይ ያፌዝ የነበረው ቴዎድሮስ አድሃኖም ነበር፤ ኢትዮጵያውያን ወገንና ረዳት አለን ብለው ወደ ኤምባሲው በብዛት ሲመጡ ኤምባሲውና ቆስንላ ጽ/ቤቶች በራፍ ላይ “ዝግ ነው” የሚል ጽሁፍ ለጥፎ ወገኖቻችንን ለባዕዳን ጥቃት አሳልፎ የሰጠው ቴዎድሮስ አድሀኖም ነው፤የሳዑዲ መንግስት በአገሩ ውስጥ ወንጀል ሲፈጸም ህጋዊ እርምጃ መውስድ መብቱ ነው ብሎ የወገኖቻችንን መገደልና የሴቶች እህቶቻችንን መደፈር ህጋዊ ለማድረግ የሞከረውም ቴዎድሮስ አድሃኖም ነው። የሚገርመው ይህ ወገኖቻችንን በባዕድ አገር “አይናችሁን ለአፈር” ብሎ በሩን የዘገባቸው ከሃዲ ሰው ነው ዛሬ የወገን አሳቢና ደራሽ መስሎ ቀልዱ እንዳማረለት የመድረክ ላይ ኮሜዲያን እዚህም እዚያም ሽርጉድ የሚለው። ሳዑዲ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ይህ ነው የማይባል ትልቅ በደልና ጥፋት የኢትዮጵያ ህዝብ በዋናነት ተጠያቂ ከሚያደርጋቸው የወያኔ ባለስልጣኖች ውስጥ ቴዎድሮስ አድሃኖምና ተላላኪው ዲና ሙፍቲ የመጀመሪያዎቹ ናቸው።
ከሰሞኑ ፊቱን እያሳመረ በየደቂቃው ኢቲቪ ላይ መቅረብ የጀመረው ቴዎድሮስ አድሃኖም “ሳዑዲ ውስጥ ለደረሰው ጥፋት መንግስት ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል” እያለ ሲዘለብድ ተሰምቷል፤ የሱ ተላላኪ የሆነው ዲና ሙፍቲ ደግሞ “በዜጎች ላይ ምን ግዜም ድርድር የለም” ብሎ ሲናገር ተደምጧል። ይህንን በሁለት ባዶዎች የተነገረ ባዶ ንግግር ያዳመጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን “ጽድቁ ቀርቶበኝ በወጉ በኮነንከኝ” እያለ የቴዎድሮስንና የዲና ሙፍቲን “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” ንግግር ሰምቶ እንዳልሰማ አልፎታል። የሚገርመው ይህ ወገኖቻችንን በክፉ ቀን ወግዱ ብሎ ፊቱን ያዞረባቸው ቴዎድሮስ አድሀኖም ነው ዛሬ የሳዑዲ መንግስት በራሱ ወጪ አዲስ አበባ የሚልካቸውን ዜጎች ዘመድ መስሎ ለመጠየቅ የሚሄደው። ደግሞኮ እስከዛሬ ድረስ አዲሰ አበባ ገብተዋል የሚባሉት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችም ቢሆኑ በተለመደው የወያኔ የዘመድ አሰራር እየተመረጡ የመጡ እንጂ ዜግነታቸው፤ ዕድሜያቸውና የጤንነት ሁኔታቸው እየታየ የተመረጡ ሰዎች አይደሉም።
በአጠቃላይ የተጣለበትን አገራዊ አደራና የተሰጠውን ህዝባዊ ሀላፊነት መወጣት የተሳነውን ቴዎድሮስ አድሀኖምን በየሜድያውና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እያሽሞነሞኑ ለማቅረብ የሚደረገው ጥረት እንደ ህፃን ልጅ ሽንት መቀበያ የቆሸሸውን የወያኔ ፊት በቆሻሻ ውኃ ከማጠብ ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ወያኔ ከአሳማ አሳማ እየመረጠ ለማሳመርና ለማሽቀርቀር የሚያደርገው ጥረት አሳማውን ወደ ለመደው ወደ ጭቃው ውስጥ ይበልጥ ይስበዋል እንጂ በፍጹም አያሳምረውም፤ ምክንያቱም አሳማ አጌጥነው አላጌጥነው ምን ግዜም አሳማ ነው። የቴዎድሮስ አድሃኖም ነገርም እንደዚሁ ነው ፤ ወያኔ ያሻውን ያክል ቢቀባውና ቢያሳምረው ቴዎድሮስ አድሃኖም ወያኔነቱን አይለቅም! ወያኔ ደግሞ በልቶ የማይጠግብ ታጥቦ የማይነጻ አሳማ ነው።

ዶክተር ሀይሉ የተቃዋሚዎችን ድክመት በድፍረት ተናገሩ


የዛሬዋ ኢትዮ ምህዳር ስለ ተቃዋሚዎች ውህደትና ህብረት ሰፊ ሀተታ ይዛ ወጥታለች፡፡ በተለይ ዶክተር ሀይሉ አዕያ ስለ ተቃዋሚዎች ውህደት ያነሱት ሀሳብ ወቅታዊና አንገብጋቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
ዶክተር ሀይሉ የተቃዋሚዎችን ድክመት በድፍረት ጽፈዋል፡፡ ዶክተሩ ተቃዋሚዎች ካልተዋሃዱ፣ ካልተባበሩ በስተቀር ምርጫ ሊያሸንፉና ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ አስረግጠው ነግረዋቸዋል፡፡ ዶክተሩ የሚሉት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ተዋሃዱ፣ ካለፈው ስህተት፣ ከሌሎች አገራትም ተማሩ፣ ህዝብን አታስገዙ፣ ጥቂት ተስፋ ሰጥታችው ዋናውን ተስፋውን አትንጠቁ ነው፡፡
እንደ እሳቸው አባባል ግን የተቃዋሚው ጎራ ለመዋሃድ የሚያስችል አላማም ሆነ ወኔ አይታይበትም፡፡ እስካሁን ያዳከመውና፣ ህዝብን ተስፋ ያስቆረጠውም ይህ አመሉ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ያሉትን ሁሉ በሰፊው ተንትነዋል፡፡ እንደ እኔ ዶክተሩ ያነሱት እጅግ ወቅታዊ ጥያቄ ነው፡፡ አጀንዳውን ያነሱትም በገለልተኝነት መሆኑን ከጽሁፋቸው መረዳት ይቻላል፡፡ ውጥንቅጡ ለወጣው የተቃዋሚው ጎራም ከዚህ ውጭ መፍትሄ ያለው አይመስለኝም፡፡ ዶክተሩ ጉዳዩን በሚዲያ ብቻ ሳይሆን ለተቃዋሚዎች እንዲወያዩበትም መድረክ አዘጋጅተው አቅርበውታል፡፡
የዶክተሩን ጩኸት የሚሰማቸው ከተገኘ በተቃዋሚው ጎራ መልካም ነገር እንደሚኖር የሚጠበቅ ነው፡፡ ግን ይች በተናጠል ሰላማዊ ሰፍል ከመጥራት፣ አዳራሽ ውስጥ በጥቂት ሰዎች ስብሰባ ከማድረግ፣ መግለጫ ከማውጣት፣ በዓመት አንድ ቀን በኢቲቪ ከመከራከር ውጭ ግብ የሌላቸው በርካታ ፓርቲዎች በተሰበሰቡበት ማን ይሰማቸው ይሆን? እጅ መጠቋቆሙን፣ መጠላለፉን፣ ግለሰብ ማግነኑን እንደ ትልቅ ስኬት የሚያዩት፤ ከህዝብ ስልጣን ይልቅ ‹‹ፓርላማ›› ለመግባት የሚቋምጡት ‹‹ፖለቲከኞች›› ያዳምጧቸው ይሆን? ምሁራን ምን ያህል ይደግፏቸዋል?
የጥናቱን ሶፍት ኮፒ ያገኛችሁ ኢትዮ ምህዳርን ለማያገኙ ኢትዮጵያውያን ፌስ ቡክ ላይ ብትለጥፉላቸው መልካም ነው፡፡

‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡

ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን  ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር  በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል፡፡
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ድራማው የመንግሰትን ስራ እያንቋሸሸ ፤ ከመንግስት ፍላጎት ውጭ እየሄደ በመሆኑ እንዲቀየር የኢቲቪን አስተዳዳሪዎች ማዘዛቸውን የወስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
ውስጥ አዋቂዎች ድራማው የወ/ሮ አዜብ መስፍንን ታሪክ የተከተለ እና አብዛኛውን የመንግስት ባለስልጣናት የመክበሪያ ዘዴ የጠቆመ በመሆኑ መንግሰት እንደ ነገሪ ሰሪ ተመልከቶታል ብለዋል፡፡
ጉዳዩ ዙሪያ የኢቲቪን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Monday, November 25, 2013

“አንድ ጊዜ ሆድ ብሶኝ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬ ነበር” – ከሳዑዲ ተመላሿ ሃያት አህመድ (ቃለምልልስ)

ከዚህ በፊት ባቀረብናቸው ሁለት ዜናዎች ከሳዑዲ አረቢያ ስቃይ ተርፈው ለሃገራቸው መሬት ከበቁት ኢትዮጵያውያን መካከል የሁለቱን ከአዲስ አድማስ ጋዜጠና አበባየሁ ገበየሁ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል። አሁንም የምናቀርብላችሁ ሓያት አህመድ የተባለችውን ከሰሞኑ ለሃገሯ ምድር የበቃችውን እህታችንን ቃለምልልስ ይሆናል – እንደወረደ ይኸው፦
ስምሽን ንገሪኝ..?
ሀያት አህመድ
እስቲ አካሄድሽን ንገሪኝ …
ከደሴ ነው በኤጀንሲ የሄድኩት፡፡ የምሰራው በጠለብ/በህጋዊ መንገድ ነበር፡፡ ሰዎቹ ሳይመቹኝ ሲቀሩ..ብዙ ጓደኞቻችን ችግር ሲደርስባቸው ሳይ፣ ስልካችንን ቀምተው ቤተሰቦቻችን በሃሳብ ሲያልቁ፣ እኔም ነገሩ ስላልተመቸኝ ጥዬ ጠፋሁ፡፡ ከዛም በሃጂና ኡምራ የሄድኩ አስመስዬ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ፡፡
በጠለብ ስንት ጊዜ ሰራሽ?
ሶስት ወር ነው የሰራሁት፡፡
አሰሪዎችስ ቤት የሚደርስብሽ ችግር ምን ነበር?
በቤት ውስጥ ያሉ ወንዶች ያስቸግሩኝ ነበር፤ አስገድዶ ለመድፈር ይተናነቁኛል፡፡ አሰሪዬ በስራዬ አትደሰትም፣ ያጠብኩትን ነገር እንደገና እጠቢ ትለኛለች፡፡
“የኢትዮጵያ ሰራተኞች ሞያ የላቸውም፣ “ሞዴስ እንኳን በአግባቡ መጠቀም አይችሉም፣ በዚያ ላይ ወንዶቻችንን ያባልጋሉ” የሚል ክስ ከሳኡዲ ሴቶች ይሰማል፡፡ አንቺ ምን ትያለሽ?
በጭራሽ! እኛ ደልቶን ይሄን ልናስብ? አንገታችንን ቀና አድርገን እንኳን ለመሄድ እንቸገራለን እኮ፡፡ እዛ ቦታ ላይ እኛን ብታይ ኢትዮጵያዊነት ያስጠላሻል፡፡ አለባበሳችን ምንድን ነው፣ ሁኔታችንስ፣ ኑሮዋችንስ..እኛ የእነሱን ባል የምናባልግ ምን አምሮብን፣ እንዴት ሆነን ነው? እኛን እኮ ይጠየፉናል፡፡ በምን አንገታችን ቀና ብለን ነው የእነሱን ወንዶች የምናባልገው? እኛ እኮ ለህይወታችን እየሰጋን ነው… እያንዳንዷን ቀን የምናሳልፈው፡፡ በርግጥ የገጠር ልጆችም ይሄዳሉ። እንግዲህ በንፅህና የሚታሙት እነሱ ናቸው፡፡ ግን ስንቱን አእምሮውን አሳጡት…. ወይኔ!!..አሁን ስንመጣ እንኳን ጅዳ ኤርፖርት ውስጥ ሰባት ያበዱ ልጆችን አይቻለሁ፡፡ ‹‹ይዛችኋቸው ሂዱ›› ሲሉን ነበር፤ እንዴት አድርገን እንይዛቸዋለን? ጥለናቸው ነው የመጣን፡፡ አይ ዜጎቻችን! እየቀወሱ፣ እየተደፈሩ፣ እየተደበደቡ፣ እየተጣሉ ነው ሜዳ ላይ ….ተመልካች አጥተው፡፡
ጣትሽ ላይ የጋብቻ ቀለበት አያለሁ … ባለትዳር ነሽ?
ፈትቻለሁ፡፡ የአስር ዓመትና የስምንት ዓመት ልጆች አሉኝ፡፡ እነሱን ላሳድግ ብዬ ነው በሰው አገር የተንገላታሁት፡፡ ገንዘብ እልክ ነበር፡፡ ሆኖም እኔም አልተለወጥኩም፤ ለልጆቼም አልሞላልኝም፡፡ አንድ ጊዜ ሆድ ብሶኝ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬ ነበር፡፡ ታውቂያለሽ… ልጆቼ በዓይን በዓይኔ መጡብኝና … ከድርጊቴ ታቀብኩ፡፡
አይኔ እንቅልፍ ካጣ ስንት ጊዜው ሆነ መሰለሽ… አይኔ ስር ጥቁር ብሎ የምታይው፣ የበለዘ የሚመስለው እኮ በእንቅልፍ እጦት የተፈጠረብኝ ነው፡፡ ጀርባዬን ያመኛል፡፡ ብዙ ሰዓት የምቆምበት እግሬንም እጅግ ታምሚያለሁ፡፡ አሁን ለትንሽ ጊዜ ማገገም አለብኝ፡፡
ጂዳ ኤርፖርት ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የሚጠባበቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አሉ ይባላል…?
በጣም ብዙ እንጂ! ‘ኢትዮጵያዊ ሁሉ አገር ነቅሎ ነው እንዴ የወጣው ብዬ ተደንቄያለሁ፡፡ በጣም ያዘንኩት ግን ወደዚህ ስመጣ ኤርፖርት ሰባት ያበዱ ልጆች ስመለከት ነው፡፡
እዛ ያለው ኤምባሲያችን እንዴት ወደ አገራቸው አይመልሳቸውም?
‹‹እህ›› ብሎ ችግራቸውን የሚያደምጣቸው ይፈልጋሉ፡፡ እስቲ አስቢው…ሰባት ሴቶች አብደው አይቻለሁ፤ በአይኔ በብረቱ፡፡ አንዷ ልጅዋ ሞታባት (በረሃብ ነው) የቀወሰችው፡፡ ስድስቱ ደግሞ በስራ ቦታቸው ቀውሰው፣ አሰሪዎቻቸው ናቸው አምጥተው የጣልዋቸው፡፡ የምናየው ነገር ሁሉ ለዓይን ይዘገንናል፡፡
ከዕረፍት በኋላ ምን ልትሰሪ አቀድሽ…?
አሁን ጤንነት አይሰማኝም፤ ካገገምኩ በኋላ እንግዲህ … እንጃ ምን እንደምሰራ፡፡ አንድ ዓመት ከሶስት ወር ተቀምጬ ነው የመጣሁት፡፡ ከአስርና አስራ አምስት ዓመት በላይ የኖሩትም ‹‹ምንድነው የምንሰራው..›› የሚል ነው ጥያቄያቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ኖረው ቢመጡም ምንም የያዙት ነገር የላቸውም፡፡ በጣም ያሳሰበኝ እሱ ነው፡፡
ከአሁን በኋላ ወደ ሳኡዲ የመመለስ ሃሳብ አለሽ?
አላህ ያውቃል፡፡

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ 4 በ 2 አሸነፉ ከመቀሌ

ለሁለት ኣመት ከኣራት ወር /48 ወራት/ በከሳሽ የመንግስት ኣቃቢ ህግና በተከሳሽ ኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኣል ክስ በ13/3/2006 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰኣት በመቀሌ ሰሜን ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ተፈረደ፡፡
ኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ የህወሓት የ17 ኣመት የትግል ጉዞ ጠንካራና ደካማ ጎኑ በግልፅ በመፃፍ ኣምስት መፅሃፍቶች ለንባብ ኣብቅታል። ኣቶ ኣስገደ የፃፉት መፅሃፍ ታሪክ ስለሆነ ታሪክ ሲፃፍ ደግሞ በታሪኩ መሰረት ከነባሩ ግለሰዎችና ብዱኖች ሊያያዝ ግድ ይላል። በመሆኑም የኣቶ ኣስገደ መፅሃፍቶችም በውስጣቸው ብዙ ታሪኮች ኣጣቅሰዋል፡፡
እነዛ የተፃፉ መፅሃፍቶች ግን ለህወሓት መሪዎችና የነሱ ቅርብ ተላላኪዎች ብዙም የሚያስደስቱ ኣይደሉም፡፡ በመፅሃፉ የተጠቀሱ ሰዎች እንደ ኣቶ ብስራት ኣማረ ዜግነቱ ኣሜሪካዊ ትውልድ ኢትዮፕያዊ የሚኖርበት ኣገር በኣሜሪካ በኣሆዩ ኮሎምፐስ ክ/ሃገር ነው ፡፡ ኣቶ ብስራት ኣማረ በ 1986ዓ.ም ምክንያቱ ባልታወቀ ወደ ኣሜሪካ ኣገር ሄደው ለህወሓት መሪዎች በተለይ ደግሞ ለ ጠ/ሚንስትር መለስ እንደጠላት በማሰለፍ ብዙ ተናግረዋል፤ ፅፈዋል፤ ከህውሓት ተቃውሞ ጎራ ተሰልፈውም ጠንካራ ተቃዋሚ ሆነው ተንቀሳቅሳል፡፡
ኣቶ ብስራት በ1997ዓ.ም የህወሓት ኢህአደግ በተቃዋሚ ሃይሎች ተሸንፎ የህወሓት ኢህኣደግ ምርጫው ሲያፍነው ኣቶ ብስራት ኣማረም እኔ ከዛሬ ጀምሮ ከምጠላው ከህውሓት ጎን እሰለፋለው ብለው በሚድያ በመናገር ድንገት ከህወሓት መሪዎች ታረቁ። ኣቶ ብስራት ጠንካራ ተቃዋሚ የሚመስሉ የነበሩ ድንገት ተቀይረው እኔ ህውሓት ነኝ ሲሉ ለብዙ ኢትዮዽያዊያን ኣግራሞት ፈጥሮባቸዋል። ኣቶ ብስራት የህወሓት ኢህኣደግ ጠላት ሆነው በኣሜሪካ የሚታወቁ የነበሩ ብስራት ኣማረ በ1997ዓ.ም ያለ ኣንዳች ችግር ኣዲስ ኣበባ ገብተው እስከ ትግራይ በመምጣት ልዩ ኩብራ መኪና ተሰጡታቸው ይንሸራሸሩ ነበሩ፡፡
ቆየት ብለውም በኢንቨስትመንት ተሰማሩ። ኣቶ ኣስገደ ጋህዲ 1፤2፤3 ፅፈው ለንባብ ከበቁ በኃላ መፅሃፍች ለህወሓት መሪዎች ስላላስደሰቱ በግልፅ የማይነገርለት ቁጣን ፈጠሩ፡፡ ግን ደግሞ መፅሃፍቶቹ በተነበቡበት ቁጥር በህዝብ ላይ ደስታን በመሪዎችም ጥላቻ መፍጠር ጀመሩ። ከሁለት ኣመት በኃላ ኣቶ ኣስገደ ለመክሰስ ተፈለገ ።ግን ደግሞ ባገር ውስጥ ካሉ ሰዎች እንዳይከሰሱ የይርጋ ጊዜ ኣልፋል ኣልተቻለም፡፡
እንደ ኣጋጣሚ ግን ብስራት ኣማረ ተገኘ። በወቅቱ ገብቶ ስለነበር መፅሃፉ ስማቸው ተጠቅሶ ስላለ በውጪ ስለነበር የተፃፈው ስለሚያውቅ ክሱ በብስራት ኣማረ ይመስረት፤ ኣስገደ በሆነ መንገድ መታሰር ኣለበት ብለው ወሰኑ። ዋና ተከሳሽ መፅሃፉ ጋህዲ 3 ነው ከታተመ ሁለት ኣመት ከሶስት ወር በኋላ በብስራት ኣማረ ስም ክስ ተመስርቶ ክርክሩ በመንግስት ኣቃቢ ህግ እንዲመሰረት ተደረገ ። ኣቶ ብስራትም ታማኝነታቸው ለማረጋገጥ ክሱን መስርተው ኣሜሪካ ገቡ፡፡ ኣቶ ኣስገደ በቀደማይ ወያኔ ወረዳ ፖሊስ ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዳኛ ሙኡዝ ፍሱሕ ስልጣኔ ኣይደለም ብለው ኣሰናበቱዋቸው። ለ2ኛ ጊዜ በሰሜን ወረዳ ምድብ ችሎት በፖሊስ ተይዘው ቀረቡ ዳኛ ወ/ሮ ኪዳን ኣብርሃ በይርጋ ጊዜ ዘጉት። ኣቃቢ ሕግ ወደ መቀሌ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ኣለ። የመቀሌ ፍርድ ቤት ዳኛ ሃይለ ገ/ስላሴም በይርጋ ሊዘጋ ኣይቻልም ብሎ በወረዳ ተመልሶ ባላየው ዳኛ ትእዘዛዝ ሰጠ። እንደገና የሰሜን ወረዳ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ወ/ሮ መብርሂት ሃዱሽ በኣቶ ኣስገደ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጡ። ኣቶ ኣስገደም ጥፋተኛ ኣይደለሁም የፃፍኩት መፅሃፍ ሃቀኛ ታሪክ ነው። በመሆኑ ደግሞ ጠ/ሚንስተር መለስ ዜናዊ ያሉበት 18 የህወሓት ማ/ኮሚቴ ያሉበት መከላክያ ምስክሮች ኣቀረቡ። ዳኛ መብርሂት ሓዱሽ መጀመርያ ለመከላክያ ምስክሮች ለማቅረብ ወስነው ማቅረብያ ደብዳቤ ከፃፉ በኃላ በማን ተፅእኖ እንደደረሰገቸው ኣይታወቅም ውሳኒያቸው በመሻር ያለ መከላከያ ምስክር ፈረዱት፡፡
ኣቶ ኣስገደ በ6ወር እስራትነና 1000 ብር ተወሰነበባቸው ።ነገር ግን ኣቶ ኣስገደ መጥፎ ሪከርድ ስለሌላቸው በኣንድ ሺ ብርና ሁለት ኣመት ገደብ ተፈረደባቸው፡፡
ኣቶ ኣስገደ እንደገና ወደ መቀሌ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው የመከላክያ ምስክርነት የማቅረብ መብት ይጠበቅልኝ ኣሉ፡፡የመቀሌ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ስብሀትም<< ወደ ወረዳ ፍርድ ቤት ወርደው ያስመስክሩ >>ብሎ የፍርድ ትእዛዝ ሰጠ። ኣቶ ኣስገደ እንደገና በመቀሌ ሰሜን ወረዳ ፍርድቤት ምድብ ችሎት 10ወር ከተከራከሩ በኃላ በ13/03/2006ዓ.ም 10 ሰኣት በዳኛ ክብርኣብ ብርሃነ ጭራሹን መዝገቡ ዘጋው፡፡መቋጫ አገኘ።
የኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ መከሰስ በመቀሌ ህዝብ ትእዝብትም የኣቶ ብስራት ኣማረ የህውሓት መሪዎች መሳርያ ሆነው ለኣቶ ኣስገደ በማንገላታት ሰውን መጉዳት እንጀራን ማብሰል ብለው ትልቅ ትችት እየተሰጡባቸው ነው፡፡
ከጎመራው
ከመቀሌ

Monday, November 11, 2013

ዜግነት ዋጋ ሲያጣ

ዜጋህ እንደ ወንጀለኛ በየመንገዱ እየታፈሰ ሲታሰር፣ ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ደግሞ አንዱ የአገርህ ልጅ በአረብ ፖሊስ ጥይት ተመትቶ ዋዕዩ በሚነድደው አስፓልት ላይ ደሙ ረግቶ ስትመለከት ምን ይሰማኻል? ይህ ሁሉ በሳዑዲ ምድር ላይ በየቀኑ እተፈጸመ መሆኑን ስትረዳ ውስጥህ ምን ይልኻል? ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሌላ ዜግነት በቅጡ አንሶ ይሆን?
ትናንት ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችባቸው 5 ዓመታት ብዙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን አድርሳለች። ከነዚህ መካከል  በግራዚያኒ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የደረሰው የየካቲት 12 ጭፍጨፋ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ በግፍ የተጨፈጨፉት የየካቲት 12 ሰማዕታት በሚዘከሩባቸው ቀናት አንድም ፈረንጅ በአዲስ አበባ መንገድ ዝር አይልም ነበር አሉ። ኢትዮጵያውያን በቁጭት ስለሚወጡ። እንኳን ጣሊያን እና የጣሊያን ዝርያ ያለው ቀርቶ ሌላ ፈረንጅም ቢሆን ይፈራ ነበር። ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ጥቃት ይኼን ያህል ቁጭት ነበራቸው።
ዛሬ ኢትዮጵያን ወገኖቻችን በአረቦች እንደ ውሻ በየመንገዱ የሚደበድቧቸው በዚያን ዘመን ቢሆን ኖሮ አንድም አረብ በአዲስ አበባ ጎዳና በሰላም ይኼድ ነበር? ኢትዮጵያዊነት እንዲህ የረከሰውና የተዋረደው ድሆች ስለሆንን ብቻ ነው? ስንት ድሃ አገር ሞልቶ የለምን? ምነው እንደዚህ አልተንቋሸሹ?
ኢትዮጵያዊውን “አለኹልህ” የሚለው ማነው? ውስጤ ሐዘን ሳይሆን ንዴት፣ ቁጭት፣ እልህ ነው ያለው።  ካልተንገበገብን ታዲያ ምን ዋጋ አለን?
አንድ ታሪክ የመጽሐፍ ቅዱስ አስታወሰኝ። ታሪኩ የብርሃነ ዓለም የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ ነው። ይህ በእግዚአብሔር ተዓምር፣ በመባርቀት የተጠራ ሐዋርያ ታሪክ ነው። ቅ/ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በሚያስተምርበት ጊዜ ትምህርቱን የተቃወሙ አይሁድ በብርቱ፡ያስቸግሩት ነበር። ከማስቸገርም አልፈው ሊያስሩትና ለገ ዎቻቸው አሳልፈው ሊሰጡት ይፈልጉ ነበር። ይህንንም ራሱ ቅ/ጳውሎስ ቀድሞ ተረድቶ ነበር። በዘመኑ የነበረ አጋቦስ የተባለ ነቢይ ተንብዮ ነበር። ይህንን ያወቁ ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ቢለምኑትም በጀ አላላቸውም። ለምን “ልቤን እንዲህ አድርጋችሁ ትሰብሩታላችሁ? እኔ እኮ ተስፋ የማደርገው እግር ብረትና ሰንሰለትን ብቻ አይደለም። … በኢየሩሳሌም ለመሞት ደግሞ ቆረትኩ ነኝ” በማለቱ ልመናቸውን ተዉ። (የሐዋ. 20፡24)
ወደ ኢየሩሳሌምም ሄዶ ማስተማሩን ቀጠለ። እስያ በነበረበት ወቅት ስብከቱን የሰሙ አይሁድ ባዩት ጊዜ በጣሙን ተናደዱ። ሰዎችን አስተባብረው አስያዙት። “ሊደግሉት ሽተው ብዙ ደበደቡት” (የሐዋ. 21፡31። የሮማ ወታደሮች ባይደርሱ ኖሮ ይደግሉት ነበር። በወታደሮች ከተያዘ በኋላም ቢሆን የተያዘበት ምክንያቱና አይሁድ ለምን እንደጠሉት ያልተረዳው ሻለቃው ለወታደሮቹ ትዕዛዝ ሰጠ፦ ጳውሎስን “ወደ ቅጣት መቀበያው ቦታ እንዲያገቡትና እየገረፉ የሠራውን እንዲመረምሩት አዘዘ።”
ይህንን የተረዳው ቅ/ጳውሎስም ትውልዱ አይሁዳዊ ቢሆንም በዜግነቱ ሮማዊ መሆኑን ተናገረ። ሊገርፉት የተዘጋጁት ወታደሮች ደነገጡ። “የመቶ አለቃውም በሰማ ጊዜ ወደ ሻለቃው ቀርቦ። ይህ ሰው ሮማዊ ነውና ታደርገው ዘንድ ካለህ ተጠበቅ ብሎ ነገረው። የሻለቃውም ቀርቦ። አንተ ሮማዊ ነህን? ንገረኝ አለው፤ እርሱም፦ አዎን አለ። ስለዚህም ሊመረምሩት ያሰቡት ከእርሱ ወዲያው ተለዩ፤ የሻለቃውም ደግሞ ሮማዊ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ፈራ፥ አሳስሮት ነበርና።” ይለናል ታሪኩ (የሐዋርያት ሥራ 22፥26 -29/23፥27)። ከዚያም ፈትቶታል።
በዚያን ዘመን ሮማዊ መሆን ወይም ሮማዊ ዜግነት ከመገረፍ ያተርፍ ኖሯል። ሮማዊ ዜጋ የትም ይኑር የት ስለ ሮማነቱ ብቻ ይከበር ነበር። በዚህ ሮማዊ ዜግነት ባለው ሰው ላይ አንድ ዓይነት አደጋ ማድረስ ብዙ መዘዝ እንዳለው ይታወቃል።
በዘመናችንም ብዙ ታላላቅ አገሮች ዜጎቻቸው በየትም ይኑሩ በየት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ። ከሰሞኑ ለዕይታ የበቃ አንድ አዲስ ፊልም (“Captain Phillips”) የመመልከት ዕድል ገጥሞኝ ነበር። ታሪኩ በሶማሌ የባሕር ላይ ዘራፊዎች መርከቡ ስለተጠለፈችና እርሱም በጠላፊዎቹ ስለተያዘ አንድ አሜሪካዊ ካፒቴን እውነተኛ ታሪክ የሚያትት ነው። ታሪኩ በ2009 የተከሰተ ሲሆን የአሜሪካ ወታደሮች ካፒቴኑን ያስጣሉበትን የአጋች-ታጋች ታሪክ የሚያስረዳ ነው። ጭብጡ፦ ዜጋህን እንዴት ትታደገዋለህ ነው።
ንጉሰ ነገሥት አጼ ካሌብ የመን እና ዐረቢያ ድረስ ዘልቅ የወረሩትና ሹሞቻቸውን ሰይመው የተመለሱበትን የታሪክ ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለን እንመልከት። ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች ተደርገው የሚቆጠሩባቸውና የሚንገላቱባቸው የዐረብ አገሮች የአጼ ካሌብ ፈረሶች የሮጡባቸው፤ እንደ ገል ቀጥቅጠው እንደ ሰም አቅልጠው የገዙባቸው አገሮች ናቸው።
ልቤ በታሪክ መዘውር ወደ ኋላ የሚወረወረውን ያህል ወደ ዘመናችንም ተመልሶ ከክብር ዙፋን የወደቅንበትን እና በአረቦች ጫማ ሥር የተደፋንበትን የውርደት ምክንያት ሊመረምር ይፈልጋል? ከሌላው አገር ሁሉ ተርታ ተለይተን ወደ ኋላ መቅረታችን ብቻ ሳይሆን እጅግ አምርረው በሚጠሉን በአረቦች ጓዳ ባርነት የገባንበትን ምክንያት ለማወቅ ኅሊናዬ ይጨነቃል።
እጅግ የማከብራቸው ፕ/ር መስፍን እንዲህ አሉ፦ “በሀገረ-መንግስትነት (state) ኢትዮጵያ ብዙዎቹን የአውሮፓ አገሮች ትቀድማቸዋለች። ታላቋ ብሪታንያ ሀገር የተባለችው በ1707 አካባቢ ነው። ጀርመን ከ1815 እስከ 94 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ሀገር የተባለችው። ኢጣሊያ በ1870 አካባቢ ነው ሀገረ-መንግስት የሆነችው። ፈረንሳይም በ18 መቶ ግድም ነው፤ ኢትዮጵያ በ525 ዓ.ም ሀገረ-መንግስት ከመሆን አልፋ ንጉስ ካሌብ የመንን የወረረበት ዘመን ነበር። እና ኢትዮጵያ ገና እንግሊዞች ሀገረ-መንግስት ለመሆን በሚፍጨረጨሩበት ጊዜ እኛ ግን ሀገረ-መንግስት ነበርን። እነሱ ‘‘ማግና ካርታ’’ የሚሉት በምዕራባውያን ለመጀመሪያው ጊዜ የመብት ጥያቄ ያነሱት እ.ኤ.አ በ1215 ዓ.ም ነበር። … 1215 ዓ.ም የዛጉዌ ስርወ መንግስት ወደ ሰሎሞን ስርወ-መንግስት የተለወጠበት ጊዜ ነበር። እኛ በዚያን ጊዜ የተደራጀን ሀገረ-መንግስት (state) ነበርን።” (‘‘የኢትዮጵያ ወጣትና የወደፊት ኃላፊነት’’ ከሚለው ንግግር የተወሰደ)
ዛሬ ግን ይህንን ሁሉ ጸጋ አጥተናል። በየአረብ አገሩ ያሉ ኤምባሲዎቻችን እንኳን መጠጊያ አልሆኑንም። ለኢትዮጵያዊው አለኹልህ የሚለው የለውም። ከአርባ ዓመት በፊት በአረብ መንገዶች ላይ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ እና በአሜሪካ ጎዳናዎች በኩራት ይራመድ የነበረ ዘረ-ኢትዮጵያ አሁን ግን በሱዳንና በግብጽ በረሃዎች፣ በሜዴትራኒያን ባህር፣ በሞዛምቢክና በዚምባቡዌ እስር ቤቶች ይሰቃያል። በየመን የስደተኛ ካምፖች ይገረፋል። በሳዑዲ አረቢያ መንገዶች ይደበደባል። ኢትዮጵያዊ ክብር ወዴት ወደቀች? ከአጼ ካሌብ እስከ ኮሎኔል አብዲሳ አጋ በባዕድ አገሮች ለማንነታቸው ክብር የቆሙ ኢትዮጵያውያን ልጆች አልነበርንም?
ኢትዮጵያዊነት ንጹህ ዕንቁ በቆሻሻ ተበላሽታለች። ለሚያዩዋት በሙሉ ዕንቁነቷ ሳይሆን ቆሻሻነቷ ብቻ ይታያል። የተደፋባት ጉድፍ የምታበራ ዕንቁ መሆኗን ሸፍኖታል። ኢትዮጵያ ዕንቁዬ፤ አብሪ!!! በድህነትና በስደት፣ በእስርና በአምባገነንት ከተቀበርሽበት ጉድጓድ ውጪ። አብሪ!!! ከሰሜን ተራሮች እስከ ደንከል ዋዕዮች፣ ከቀይ ባህር ውኃዎች እስከ ጋንቤላ ደኖች ደወልሽን አሰሚ። በዓለም የተበተነውን ልጅሽን አይዞህ በዪ!! ኢትዮጵያ አብሪ!!!

Sunday, November 10, 2013

ሚስት እህቶቻችን አይደፈሩ ነው

የማለዳ ወግ …ከጎደፈው ስም ላይ ሌላ ጉድፍ ! – ነቢዩ ሲራክ
በሪያድ መንፉሃ በተከሰተው ሁከት ግራም ነፈሰ ቀኝ ተጎጅዎች እኛ ነን ! እንኳንስ ሰው ተደብድቦ ፣ ሞቶባቸው ፣ እንኳንስ መኪና ተሰብሮባቸው እንዲያውም እንዲው ናቸው ።
ከማለዳ እስከ ሌሊት የዘለቀውን ሁከት መቆጣጠር ይቻል ዘንድ ገና ሲጀመር አቅጣጫውን አይተው የመንግስት ተወካዮችን የመከሩ በርካታ ነበሩ። የሰማ አካል ግን የለም !
ስልክ ተደውሎ የማይነሳበት ፣ አልፎ አልፎ መስመሩ ሲነሳ ሃላፊዎችን ማግኘት በማይቻልበት ዲፕሎማቲክ መስሪያ ቤት ድክመት ገና ከጅምሩ መላ ሊገኝበት የሚችለው ጉዳይ ወዳልተፈለገ
አቅጣጫ አምርቶ ለዚህ አሳፋሪ አሳዛኝ ቀን በቅተናል …
የቀኑን ሁከት ተከትሎ ትናንት ሌሊት በጸጥታ ሃይሎችና ” ሸባብ ” ተብሎ በሚጠሩት የአረቦች ወጣቶች ኢትዮጵያውያንን በማያዳግም እና ሊሰሙት ሊያዩት በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ንብረታቸውን
ዘርፈው ፣ ሴቶች ደፍረው፣ ደብድበው ከመቁሰልና እስከ ሞት ያደረሰ ግፍ ፈጽመውባቸዋል። ሳውዲዎችም ቢሆን በገዛ ሃገራቸው ተንቀው ንብረታቸው ወድሟል ፣ ተደብድበዋል ተገድለዋል ። ( አንድ መሞቱን ሰምቻለሁ) በሁሉም ወገን ትልቅ ጥፋት ተሰርቶ እዚህ ላይ ደርሰናል! በሁሉም ወገን ችግሩን ለመፍታት የተኬደው መንገድ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ያላስገባ ነበረና ጭፍኑ አካሔድ ለዚህ አስከፊ ቀን አድርሶናል! ያም ሆነ ይህ ጥፋቱ እና ጉዳቱ ለእኛ ይከብዳል! ድሮም ከማያምረው ከጎደፈው ስማችን ላይ ሌላ ጉድፍ ጨምረንበት ለዚህ በቅተናል !
የትናንቱ ምሽት ለእኔ ፍጹም አስቀያሚ ነበር ፣ ኢትዮጵያውያን የመንፉሃ ህገ ወጥ ነዋሪዎች ግፍና ዱላው በዝቶባቸው ትናንት ማለዳ ሳውዲ ይሰራልነተብሎ የማይገመር ስራ ሰሩ! ለአመጽ ሻንጣና ቤተሰብ ይዘው በመውጣት “ወደ ሃገራችን በሰላም ስደዱን ፣ አትዝረፉን ሴቶቻችን አትለያዩብን ፣ አትድፈሩብን! ” ብለው አደባባዩን በዋይታ አቀለጡት! እንኳንስ የውጭ ዜጋ ሳውዲው በአመጽ አደባባይ መውጣት በማይታሰብበት ሃገር የኢትዮጵያውያኑ እርምጃ ቢያስገርምና ቢያስደነግጥም ” በሌሊት ቤት እየተሰበረ ከምንዋረድ የመጣው ይምጣ!” በሚል ስሜት ለአመጹ መነሳሳታቸው እውነት ነው ።
የመንፉሃው የትናንት ማለዳው አመጽ በአብዛኛው ብሶትን በመግለጽና ውሰዱን በማለት ያተኮረ ሲሆን የአካባቢው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ከመግታት አልፎ ወደ መኪና ማውደም እንቅስቃሴ ያመራ አልነበርም። ከቀትር በኋላ ግን ከሶስት በላይ የፖሊስ መኪና ላይ በድንጋይ ጥቃት ተፈጸመ። ብዙ ሳይቆይ አካባቢው በልዩ ሃይል ተከበበ። መንገድ ዳር የነበረው ሰው ተበተነ ። እንዲህ ሆኖ ቢያልፍ መልካም ነበር። አልሆነም! በፖሊስና በጸጥታ ሃይሎች ከበባ ቀጣይ እርምጃ ፍርሃት በነዋሪው መካከል ስጋትን ጫረ ! ኢትዮጵያውያኑ ወጣቱቶች ተመልሰው በመንፉሃ አውራ መንገድ አደባባዮች ላይ ወጡ… ሁኔታው እየከረረ ሲሄድ የሳውዲ እና የኢትዮጵያ መንግስት ሃላፊዎች ቀደም ባሉ ቀናት መስራት በነበረባቸው ዜጎችን በሰላም የመሸኘት ድርድር ላይ ተቀመጡ … ከፍተኛ የጸጥታ ሃላፊዎችን ጋር ውይይቱ በቀጠለበት ምሽት ግን መንፉሃ በከፋ ቀውስ ውስጥ ወድቃለች ! ሌላ ሁከት … ሌላ አደጋ … ሌላ አደጋ …ሌላ መከራ ተከተለ !
ምሽት ላይ የምህረት አዋጁን ተከትሎ ትምህርት ቤታቸው የተዘጋባቸውን ልጆቸን ለማናፈስ ጭምር ከቤት ስወጣ ከሰአታት በፊት በትምህርት ቤቱ ጉዳይ ካንድ ብርቱ ወዳጀ ጋር ለመመካከር ጭምር ነበር ። በሪያድ የመንፉሃ ሁከት ሲያውክን በጅዳ የኮሚኒቲ የተበለሻሸ አሰራርና በቆንስል ሃላፊዎች ክትትል ጉድለት 3000 ሶስት ሽህ ታዳጊ ትምህርት ለጊዜውም ቢሆን ተሰናክሏል። ወደ 70 ሰባ የሚጠጉ መምህራንና ሰራተኞች ስራቸውን አቁመዋል። እንደ ወላጅ በቻ ሳይሆን እንደ ዜጋ መምከር ግድ ነበርና ተገናኘን… ከወዳጀ ጋር በአንድ ሻሂ ቤት ተቀምጠን ስናወራ በርከት ያሉ ባልንጀሮቻችን ከዚህም ከዚያ መጥተው ክብ ሰርተን ተቀምጠን መጨዋዎት ጀመርን ። በትምህርት ቤቱ ዙሪያ አውርተን መፍትሄው ያው ተጎልቶ ትምህርት ቤቱ እስኪዘጋ የጠበቀው ቆንስል መስሪያ ቤቱን ሃላፊዎች ድክመት ከየአቅጣጫው እያነሳን ቦጫጨቅናቸው።
ወሬው ደርቶ እየተቀባበልን ስንከካው ስልኬ ደጋግሞ ይጮሃል፣ እኔም ደጋግሜ ተነስቸ በመውጣት አውርቸ ስመጣና ከፊስ ቡክ ወዳጆቸ ጋር በወሬው መካከል መልዕክት ስለዋወጥ የተመለከተኝ አንዱ ጠርጣራ ወዳጀ “ለመሆኑ ስለ ሪያድ ባህር ሃይሎች ምን አዲስ ነገር አለ እባክህ? ” በሚለው ጥያቄ ወደ ሪያድ የመንፉሃ ጉዳይ ይዞን ሄደ ። ጨዋታው መድራት ያዘ ከመንፉሃ “ባህር ሃይሎች” እስከ ለፍቶ ግሮ አዳሪው ሰላማዊና ህጋዊ ነዋሪ ሁሉንም እያነሳን ማውራት መወያየት ጀመርን። በየመን ባህር በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ሪያድ ደርሰው በህንጻ ግንባታ የተሰማሩት “ባህር ሃይል ” በሚል ቅጽል ስም ይታወቃሉ ። “ባህር ኋይሎች” በመንፉሃ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ በተለይም ጩቤ ይዘው እርስ በርሳቸው ሳይቀር ሲጋደሉ መክረማቸው አንስተን ተወያየን። በመጨረሻም “የሳውዲ መንግስት የምህረት አዋጁ እንዳለቀ በመንፉሃ የወሰደው ከባህር ሃይሎችን የማስወገዱ ዘመቻ ትክክል ነው !” በሚለው ሁላችን ተስማማን ፣ በመካከል ላይ ከአንድ አሜሪካን ሃገር ካለ ወዳጀ ጋር በሳውዲ ጉዳይ ለመነጋገር ቀጠሮ ነበረንና ስለኬ ተንጫረረች … ስልኬን አንስቸ ውይይቱን አደርጌ ስመለስ ከሻሂ ቤቱ መግቢያ የጠበቀኝ ወዳጀ ከመንፉሃ የመጣ ሰው ላገናኝህ ብሎ አንድ ልጅ እግር ወንድም አገናኘኝ። ለ15 ደቂቃ ያህል የሆነውን እና በአይኑ ያየውን ሁሉ አጫወተኝ ። የቤት ሰበራውን ድብደባ፣ ዘረፋውን እና ግድያውን ጨምሮ ሴት እህቶች መደፈራቸውን አጥብቄ ጠየቅኩት ሞተ ላለው ሃገር ቤተሰቦችን ጠቅሶ ፣ ተደፈረች ላለት ቤተሰቦቿን ላገናኝህ ብሎ አስረግጦ ነገረኝ እና ስልኩን ተቀብየው ተለያየን ..
ተመልሸ ክቧን ጠረጴዛ ስቀላቀል ከሪያድ የመጣው እማኙን የሰጠኝን ቃል በአጭሩ አስረድቻች ውይይታችን ቀጠልን ። …የሳውዲ መንግስት የምህረት አዋጁ ሲያልቅ ያወጣው “ቤት ለቤት ፍተሻ አይደረግም! ” የሚለው መመሪያ ተጥሶ የኢትዮጵያውያን ቤት ብቻ እየተሰበረ ንብረት መዘረፉና በዋናነት ሴት እህቶች የመደፈራቸው ጉዳይ በዚህችው ጠረጴዛም ተነሳ … በዚያ የተስማማነው በዚህ ግን በሃሳብ ተለያየን ፣ የትናንቱ የመንፉሃ አመጽ በሳውዲ ለሚንገኝ ነዋሪዎች ትልቅ ጠንቅ እንደሚፈጥር ግን ሁላችንም በአንድ ድምጽ ተስማማን ! “ቀይ መኪና ሰው ገጨ” ከተባለ ቀይ መኪናን ሁሉ የሚያሳድዱት ሳውዲዎች “ሃበሻ አጠፋ ” ተብሎ ሲነገራቸው በገዛ ምድራችን አመጹብን ብለው በቀጣይ ቀናት የሚሆነውን አስቡት … ይህንና ያንን ስጋት ተነጋግረን ተለያየን!
ውጭ በቆየሁበት የሶስት ሰአት ልዩነት ሰላማዊዋ የአለም ቁንጮ ነዳጅ አምራች ሃገር ዋና ከተማ በአንድ የከተማዋ አካል ታይቶ የማይታወቅ መልኩ ተቀውጣለች … በእኛና በእነሱ በተፈጠረ ሸምጋይ የጠፋለት ሁከት መንፉሃ ጸጥ ረጭ ብላ ሰማዩ መከራ አዝሎ ፣ ሃገሬውና ኢትዮጵያዊው ተፈራርቶ ማምሸቱን ወዳጆች በተከታታይ ካደረሱኝ መረጃዎች ተረዳሁ! ሁከቱ ከማለዳ እስከ ምሽት ደምቆ ታይቷልና የነዋሪውን ትኩረት በአያሌው ስቦ መስተዋሉንም ሳውዲ ባልንጀሮቸ “ምን አደረግናችሁ! ” በሚል ቀልድ በጀመሩት ጭውውት የሁኔታውን አሳሳቢነት ገለጹልኝ … እንዲያ እያለ ምሽቱ ምሽት ተብሎ እያመመኝ ተገፋ !
እኩለ ሌሊት ላይ ደግሞ አሳዛኝና አስገራሚውን ትዕይንት ደም እያፋሰሰ ሲቀጥል ሰማሁ ፣ ተጨባጭ መረጃዎችም ደረሱኝ ። አሁንም ገልጋይ ሸምጋይ አልነበረም… በሳውዲ እምብት በሪያድ መንፉሃ ድሮ በህገ ወጥ ስራ እንጠራ ነበር ። ያ ጋብ ሲል ያለ ህጋዊ የሃገራት ሰምምነት እድሜያቸውን እየቆለሉ ወደ ሳውዲ የሚላኩ ታዳጊ እህቶች ተበድለው እያለ በዳይ እየተባሉ የጥቂቶች እርምጃ ብዙሃኑን በከለው ። “እዕምሮ ህሙማን ኢትዮጵያውያን የኮንትራት የቤት ሰራተኞች የአሰሪዎቻቸውን ህጻናት እስከ መግደል ደረሱ! ” በሚል የከፋው ስማችን ዳግም ከፍቶ እንገለል ዘንድ መንፉሃ ላይ ሌላ ጥቁር ታሪክ አስመዘገብን ! ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ዙሪያ ገቡ በተኩስ ፣ በሰው ጩኽት ፣ በፖሊስ እና የአንቡላንስ መኪናዎች ኡኡታ ሲናጥ በአካባቢው የኢትዮጵያዊ የተባለ ተፈልጎ እየታደነ ነበር …ውክበት ፣ ድብደባ እና ግድያው ጨለማውን ሽፋን ያደረገ ስለነበር ትናነት ሌሊት የሆነውን በትክክል መናገር የሚችል ከቶ ያለ አይመስለኝም !
ከእኩለ ሌሊት በኋላ ሁከቱ ባልበረደበት ሁኔታ የመሳሪያ ጩኸት በሚስተጋጋባት በሪያድ በመንፉሃ ነገሮች በፍጥነት ይቀያየሩ ይዘዋል! በደረሱኝ እና በሚለቀቁ ተንቀሳቃጨሽ ምስሎች ዋይታ ገኖ ይሰማል! ተከበው የሚገኙ ህጋዊ መኖሪያ የሌላቸውን እና ህጋዊ መኖሪያ ያላቸውን ነዋሪዎች አነጋገርኩ ! አንዱ ወዳጀ አረብ መስጊድ ደርሶ ሲመለስ አንድ ሃበሻ በነጭ ለባሽ ተተኩሶ ከተመታ በኋላ በፍጥነት መነሳቱን የአይን ምስክር እንዳረጋገጠለት አጫወተኝ። ሌላው ወዳጀ ከሁለት በላይ መገደላቸውን መስማቱን እና በአይኑ ያየውን በጋዜጣ የተሸፈነ የወገን ሬሳ ምስል ላከልኝ!
በማከታተል የነዋሪውን አስተያየት ማነፍነፍ ያዝኩ ! ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር የተፋጠጡትን በስልክ አግኝች ለምን የምህረት አዋጁ ሳያልቅ እንዳልወጡ እና የአሁኑ አመጽ ምክንያት ምን የሚል ነው በሚል ጠየቅኩ ” ሳውዲዎች ሁሌ ህግ ያወጣሉ፣ ግን አይፈጽሙትም ። ይህ አዘናግቶኛል! ምንም አይፈጠሩም እርምጃ አይወስዱም ብለን እንጅ ከዚህ መከራስ መውጣት ይሻለን ነበር! ሃገራችን አንሂድ አላልንም ፣ ቤት እየሰበሩ ወንዶችን ይወስዳሉ። የእኛን መያዝ የተመለከቱ የሳውዲ ወጣቶች (ሸባቦች) ሚስት እህቶቻችን ይደፍራሉ ፣ ንብረታችን ይዘርፋሉ! ይህ ለሶስት ቀናት ሲቀጥል የደረሰልን የለም ! ኢንባሲ ደወልን ምንም ማድረግ አንችልም ይሉናል ፣ አንተም ድንጻችን ታሰማናለህ ብለን ብንደውልልህ ፈራህ መሰል አታነሳልንም! የት እንድረስ ? ምን እናድርግ? ንብረታችን እየተዘረፍን ሴቶቻችን እየተደፈሩ ዝም ብለን ማየት ነበረብን? ይህን በመቃወም ሻንጣና ቤተሰቦቻቸር ይዘን ወደ ሃገራችን ስደዱን ነው ያልናቸው ” የሚል እየተቆጣና ድምጹን ከፍ እያደረገ መልስ የሰጠኝን አንድ ወንድም መጨረሻችሁ ምን ሊሆን ይችላል ? አልኩት “… ወደ ሃገራችን ከነሚስት እህቶቻችን ይውሰዱን ነው የምንለው! ያለበለዚያ መንፉሃን እና ሚስት እህቶቻችን አንለቅም! ገድለው ያስለቅቁን ” ሲል ክችም ያለ መልሱን ሰጥቶ ስልኩን ጀሮየ ላይ ዘጋው…
“ከኑ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ፣ አብረህ ተወቀጥ !” እንዲሉ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንም የሁከቱ ቀዳሚ ተጠቂዎች ሆነዋል ። አንዳንዶችን አነጋግሬ ነበር ። ነገሩ እየከረረ ሌላ ጦስ እንዳያመጣ ስጋታቸውን በመግለጽ በጭንቀት እያለቀሱ ያሉበትን የከፋ ሁኔታ ገልጸውልኛል። ስለ ችግሩ አነሳስ፣ሴቶች ይደፈራሉ ስለሚባለው እና ስለ መፍትሔው ጠይቄያቸው የመለሱልኝ እህት ” የእኛ ወጣቶች በጩቤ ይዋጋሉ በሚልና በህገ ወጥነት ስለሚታወቁ ስማቸው ከፍቶ እንጅ አሁን የተሰራው ስራ ትክክል አይደለም ። ቤት እየተሰበረ ዝርፊያ አለ ። ሴት ትደፈራለች ። እነሱ እውንት አላቸው ! ሚስት እህቶቻችን አይደፈሩ ነው ። አላህ ምስክሬ ነው ።እኔ ሁለት የተደፈሩ እህቶች አውቃለሁ። ኢትዮጵያ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ልዩ ልዑካንን በአስቸኳይ በመላክ መፍትሔ ካልተገኘ እዚህ ያሉት የኢንባሲ ሰወችን ተዋቸው! የሚያሳስበኝ የእንግዲሁ ኑሯችን ኑሮ ነው ! አንድ ነገር ካልተደረገ ኑሮው ኑሮ አይባልም”ብለውኛል።
የፊስ ቡክ ወዳጆቸም ጠንክረው መረጃውን ያዥጎደጉዱት ይዘዋል ። አንዳቸውንም ለጥፊ በጭንቀት ያለውን ላስበርገግ አልፈለግኩምና መረጃውን ብቻ በስሱ በጽሁፍ መልክ ማስተላለፉን መረጥኩ … አንድ የፊስ ቡክ ወዳጀ የኢትዮጵያዊ ደም የረከሰበትን ጉድ አየሁ ብለው በላኩልኝ መልዕክት ” ሰላም አመሸህ ነብዪ? የሚፈሰውን ደም እያየህ ነው?ኧረ ምንድ ነው መጨረሻችን ?” ሲሉ አጠይቀዋል ! ጥያቄው እኔ መመለስ የማልችለው ግን የብዙሃኑን የሳውዲ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ነዋሪ ነው … የተፈራው ደረሰ …እኔም መጨረሻው አልገባኝምና መጨረሻችን በማጠየቅ የማለዳ ወግ እያልኩ መብተክተኬን እዚህ ላይ ቆም አደረግኩት …

Friday, November 8, 2013

የኢትዮጵያዉያን ስቃይና መከራ በሳዉዲ አረቢያ

የመጣኸዉ ባዶህን ነው! ባዶ ሆነህም ትመለሳለህ!…ኢንተ-ጃኢ-ፋዲ ወተርጃእ-ፋዲ…የሳዉዲዎች አመለካከት!
የፈለጋቹበት ዉሰዱን ግን አትደብድቡን…ይላል ኢትዮጵያዊዉ…ለካስ አትደብድቡን ማለቱ የሚያስደበድብ ነበር…
አይደለም የሰዉ ልጅ እንስሳ እንኳ እንደዚህ አይደረግም። የምታዩአቸዉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በሳዉዲ ዜጎች ተይዘዉ ወደ ጀዋዛት (የስደተኛ መምሪያ) ሲወሰዱ ነዉ። እነዚህን ደሃና ከርታታ ኢትዮጵያዉያን በቁጥጥር ስር ያዋለዉ ያገሪቱ ፖሊስ ሳይሆን ያገሪቱ ዜጎች ናቸዉ።”እክስር የዱ!…እጁን ስበረዉ!…” ይላል አንዱ። ከታች ሆኖ የጣር ድምጽን የሚያሰማዉ ኢትዮጵያዊ “ሐላሊ…ሐላሊ… ላቤን ያፈሰስኩበት የልፋቴ ዋጋስ? በማለት ሲጠይቅ ዱላዉ ይጠነክርበታል።
ሰዉ የመሆን ማእረግን የተነፈገዉ ሌላኛዉ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ዱላዉን እርግጫዉን እየዋጠ ስቃዩን ለመቀነስ “ኻላስ-አነ-ገልጣን…በቃ! በቃ! እኔ-ነኝ-ጥፋተኛ” ይላል። ከሳዉዲ ዜጎች አንደኛዉ ኢትዮጵያዉያኑ በመያዛቸዉ ባይከፋም ዱላዉን እንዲህ እያለ ይቃወማል “ተራ ኤይብ-መጅሙዓ-ተድርቡነ?… ይህ ነዉር ነዉ በህብረት ትደባደባላችሁ?” ግን ማን ሊሰማዉ። የኢትዮጵያዉያኑን የሰራ-አካል ማሰቃየት ብቻ ሳይሆን የሚያራግፉባቸዉም የቃላት ናዳ ስነልቦናን ይሰብራል።The Misery of Ethiopians in Saudi Arabia
አገር ዉስጥ ካለዉ ስቃይ ለመዳንና የተሻለን ህይወት ለራስም ለቤተስብም ለማምጣት የሚሰደዱት ኢትዮጵያዉን የሚደርስባችዉ መከራና እንግልት ተቆጥሮ አያበቃም። የሳዉዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) የሌላቸዉ ወይም ከአሰሪያችዉ ጋር የማይሰሩ (ከፊል) በመጡበት የስራ ዓይነት (ሚህና) የማይሰሩት ከአገር እንዲወጡ ወይም የመኖሪያ ፈቃዳቸዉን እንዲያስተካክሉ የሰጠዉ ግዜ ስላበቃ ሰዎችን በዜግነት በሐማኖት ሳይለዩ ማፈሱን ተያዘዉታል። ባንጻሩ እነዚህ ሰደተኞችን ወደ ሳዉዲ በማስገባት ህገወጥ ተግባር የሚፈጽሙን የሳዉዲ ዜጎች መንግስቱ ወጥ የሆነ እርምጃ ሲወስድባቸዉ አይስተዋልም። ስለዚህ የሳዉዲ ዜጎችም ይሁኑ መንግስቱ ተጠያቂ ከመሆን አይድኑም።
ሰዎች ወደ ሳዉዲ እንዴት ይገባሉ የሚለዉን ስንቃኝ…
1) በሐሃጅና በኡምራ(ጸሎት)
ሰዎች ከተለያዩ አገራት ጸሎት እናደርጋለን በማለት ወደ ሳዉዲ ከደረሱ በሗላ እዚያዉ ይቀራሉ። እነዚህን ሰዎች ቀጥሮ በማሰራትም ይሁን ከቦታ ቦታ በድብቅ በማመላለስ ህገወጥ ተግባር ላይ የሚሰማሩት የሳዉዲ ዜጎች ናቸዉ። በነዚህ የሳዉዲ ዜጎች ላይ መንግስቱ በቂ የሆነ እርምጃ አይወስድም፤ የርምጃዉ ሰለባ የሚሆኑት ስደተኞቹ ብቻ በመሆናቸዉ መንግስቱ ተጠያቂ ነዉ።
2) የኮንትራት ስራ (ጠለብ)
በኮንትራት የሚመጡት ሰራተኞች ከዘመናዊ ባርነት ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸዋል። ረጅም ሰዓታትን መስራት ብቻ  ሳይሆን ከኮንትራቱ ዉል ዉጪ ለዘመድና ለጎረቤት በተጨማሪ እንዲሰሩ የሚገደዱ አሉ። የጠለብ (የኮንትራት) ሰራተኞች ድብደባ፣ግርፋት፣አስገድዶ መድፈር (rape)ወዘተ ይደርስባቸዋል፤ በዚህም ሳቢያ ከአሰሪያቸዉ በመጥፋት በግል ተቀጥረዉ መስራት ይጀምራሉ።የሳዉዲ መንግስት ዜጎቹ የሰራተኛን መብት እንዲያከብሩ በቂ ግንዛቤን ባለመፍጠሩና  ይሕንን መስል ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፍጽሙትን ዜጎች ሕግ ፊት በተገቢዉ መልኩ ባለማቅረቡ ተባባሪ ያስመስለዋልና ተጠያቂ ነዉ።
2) በባህርና ድንበር አቋርጦ መግባት
የሳዉዲ ጎረቤት ከሆነችዉ የመን በኩል ብዙ ስደተኞች ወደ ሳዉዲ ይገባሉ። በተለይም ጀዛን የሚባለዉ የሳውዲ ግዛት ቀድም ሲል የየመን የነበረ ሲሆን ድንበሩን አንድ አይነት ጎሳዎች ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦችም ይጋሩታል፤ በሁለቱም አገራት ያሉ የህግ አስከባሪ አካለት የሚዛመዱበት አጋጣሚ ብዙ ነዉ። በተቀነባበረ የኮንትሮባንድ ስራ ፖሊሶችና ድንበር ጠባቂ ሐይላት ሰዎችን በህገወጥ መንገድ በማስገባት ይተባበራሉ። የሳዉዲ መንግስት በድንበሩ ላይ ባሉ የህግ አስከባሪ ሐይላት ላይ በቂ ቁጥጥር ባለማድረጉ ተጠያቂ ነዉ።
ስደተኞች ወደ ሳዉዲ ሲገቡ የአገሪቱን ግዛቶች አቋርጠዉ ከቦታ ቦታ እንዲዘዋወሩ የኮንትሮባንድን ስራ የሚሰሩት የሳዉዲ ዜጎች ናቸዉ። ለምሳሌ አንድ ስደተኛ ከየመን ድንበር-ጀዛን ወደ ሪያድ ወይም ወደ ጂዳ መግባት ቢፈልግ በጭነት መኪና ከእቃ ጋር ተደብቆ እንዲገባ ይደረጋል፤ካልያም ወንዱ እንደሴት ቀሚስ-ሻሽ-የፊት መሸፈኛ እንዲለብስ ይደረግና የሳዉዲ ዜጎች እንደ ሚስት ወይም ልጆች ጭኖ በኮንትሮባንድ ሰዎችን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። በዚህ የኮንትሮባንድ ተግባር ፖሊስ (ሹርጣ) ተባባሪ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነዉ። ለዚህ ህገ ወጥ ተግባር ከሳዉዲ መንግስት ሌላ ማንም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።
ወደ ሳዉዲ ለምግባት ኢቃማ (የመኖሪያ ፈቃድ) በዉድ ገዝተዉ የሚገቡ ስደተኞች አንዳንዴ የውሸት አሰሪያቸዉ (ከፊል) ጠፍቶባቸዉ የመኖሪያ ፍቃድ ለማዉጣት የሚቸገሩበት አጋጣሚ አለ። አንዳንዴም የመኖሪያ ፍቃዱን ቢያገኙም ፈቃዳቸዉ ሲቃጠል ለማደስ (ተጅዲድ) አሰሪያቸዉ ጠፍቶ ወይም ፍቃደኛ ሳይሆን ይቀርና ሳይወዱ በግድ ህገወጥ ይሆናሉ። ለዚህ ህገወጥና የተዝረከረከ አሰራር ከሳዉዲ መንግስት ሌላ ማን ተጠያቂ ሊሆን ይችላል?
በሳዉዲ ከተሞች ዉስጥ በስፋት ያሉት ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮዎች (መክተበል ሙአቂብ) የመኖሪያ ፍቃድን በተመለከተ የተለያዩ የማጭበርበር ስራዎች (ተዝዊር) በመስራት ይታወቃሉ። እነዚህን ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ ከፍቶ ለመስራት የሳዉዲ ዜጋ መሆኑ ግዴታ ነዉ። በነዚህ ቢሮዎች የዉሸት የመኖሪያ ፍቃድን ከማዘጋጀት ጀምሮ፤ስደተኞች ያለ አሰሪያቸዉ (የዉሸት አሰሪም ቢሆን) ፍቃድ ከአገር ወጥተዉ እንዲመለሱ (ኹርጀል አዉዳ) እስክማድረግ ይሰራል። በነዚህ ቢሮዎች ዉስጥ ሌላዉ ቀርቶ ከስራ ሰዓት ዉጪ ከኢምግሬሽን (ጀዋዛት) በመመላለስ ባዶ ኢቃማ የመኖሪያ ፈቃድ በማምጣት የዉሸት የምኖሪያ ፍቃድ የሚሰጡ የመንግስት ሰራተኞች በርካታ (ነበሩ)ናቸዉ። በዉሸት ከአንድ አሰሪ ወደ ሌላ አሰሪ (ተናዙል-ነቅለል-ከፋላ) በማድረግም የሳዉዲ ህግ አስከባሪ አካላት በመተባበር ህገወጥነትን ያስፋፋሉ። ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠያቂዉ ዛሬ በየመንገዱ እንደ እንስሳ እየታደኑ ኢሰብዓዊ ተግባር የሚፈጽምባቸዉ ስደተኞች ሳይሆኑ የሳዉዲ መንግስት ነዉ። ከሳዉዲ መንግስትም ባሻገር አገሪቷን የተቆጣጠሩት የንጉስ አብድልአዚዝ ቤተሰቦች ያንበሳዉን ደርሻ ይይዛሉ።
በሳዉዲ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆኑ በትክክለኛዉ መንገድ ሰርትዉ የከበሩ፤ላገር፣ለቤተሰብ፣ለወገን የተረፉ በርካታ ናቸዉ። ባንጻሩም እንደ ወጡ የቀሩ፤ ጤነኛ ሆነዉ ታመዉ የተመለሱም ይኖራሉ። በህገወጥ መንገድ አረቄና አስካሪ መጠጥን በመጥመቅ ብሎም በዝሙት የሚተዳደሩም ይኖራሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ እዚያዉ-ሳዉዲ የተወለዱ ኢትዮጵያዉያን ህጻናት ሲኖሩ በአገሪቱ ደንብ መሰረት ሁለተኛ ደረጃን ከጨረሱ በሗላ የኮሌጅ ትምርት የማግኘት እድላቸዉ የመነመነ ነዉ (አይቻልም ማለት ይቻላል)። አቅም ያለዉ ልጆቹን ወደ አዉሮፓ እና አሜሪካ ለከፍተኛ ትምርት ሲልክ ዉስን አቅም ያለዉ ልጆቹን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ በተለያዩ ኮሌጆች ያስተምራል። ሁለቱንም ማረግ ያልችለ ልጆቹ ያለትምርት የሚባክኑበት አጋጣሚ ሰፊ ነዉ።የባህረ ሰላጤዉን ስደት አስመልክቶ ብዙ ግዜ የሚነገረዉ ለአቅመ አዳምና ሔዋን ለደረሱት ኢትዮጵያዉያን ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የወደፊት እጣ ፈንታቸዉን የማያዉቁ ሕጻናት ስለተዘነጉ ለነርሱም ማሰቡ ታላቅ ሰብዓዊ ግዴታ ነዉ።
በዚህ መከራና ስቃያ ዉስጥ ላሉ ኢትዮጵያዉን ለመታደግ ለዜጎቹ የሚቆረቆር ሁነኛ መንግስት ቢያሻም ሪያድ ያለዉ የሳዉዲ ኤምባሲና ጅዳ ያለዉ የቆንስላ ጽ/ቤት በመጣመር ዜጎችን የሚበድሉ ቢሆኑ እንጂ ለዜጎች ደራሽ ሲሆኑ አይታይም። ከተወሳሰበዉ የሳዉዲ ህግ ለመዳንና የመኖሪያ ፍቃድን ለማደስ ለፓስፖርት እድሳት ኤምባሲ የሚሔዱ ኢትዮጵያዉን ከፍላጎታቸዉ ዉጪ ለአባይ ቦንድ ግዙ ተብለዉ እንደሚቸገሩ ቀደም ሲል የተዘገበ እዉነታ ነዉ።ኤምባሲዉ ኢትዮጵያዉያንን በዘር በብሔር እየመተረ በልማት ስም አፍን ብልጓም ሲዘጋ ኢትዮጵያዉያን በየመንገዱ ላይ ከእንስሳ ባነሰ መልኩ እየተደበደቡ እየተገረፉ ክብራቸዉ ተገፎ ወደ ማጎሪያ ቤት (ተርኺል) እየተወረወሩ ነዉ።
ይህ ኢሰብዓዊ ተግባር አለም አቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝ ለተለያዩ የስብዓዊ መብት ድርጅቶች ማሳወቁ ተገቢ ሲሆን ጉዳዩ ከፍትኛ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ኢትዮጵያዉያን በያሉበት መንቀሳቀስ አለባቸዉ።የፖለቲካ ድርጅቶችም ኢትዮጵያዉያኑ የሚደርስባቸዉን በደል በማዉገዝ ለጉዳዩ ልዩ አትኩሮትን በመቸር አቅማቸዉ በቻለዉ መጠን ሊንቀሳቀሱ ይገባል። የተለያዩ የሐይማኖትና የሲቪክ ማህበራትም ይሁኑ አክቲቪስቶች በመጣመር የሳዉዲ ኤምባሲዎች በሚገኙበት አገራት ሰላማዊ ሰልፍን ቢያረጉ መግለጫዎችን ቢያወጡ የወገኖቻንን ስቃይና መከራን ማስቆም ባይችሉ እንኳ ሊቀንሱት ይችላሉና-ወገን ለወገን መድረሱ ግድ ይላል።
የመጣኸዉ ባዶህን ነው… ባዶ ሆነህም ትመለሳለህ…(ኢንተ፡ጃኢ፡ፋዲ ወተርጃእ፡ፋዲ) ለሚባሉት ኢትዮጵያዉይን ከኛ  ሌላ ደራሽ የላቸዉምንና እንድረስላቸዉ። ልብ ያለዉ ልብ ይበል!

የሚዲያ ነፃነት ይረጋገጥ፤ የታሰሩ ጋዜጠኞችም በአስቸኳይ ይፈቱ!!! – ከአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
ከጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ትቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስድስተኛው የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡ ፓርቲያችንም ይህንን ጉባዔ በአንክሮ እየተከታተለው ሲሆን በርካታ የአፍሪካ ሚዲያ ባለሙያዎች የፕሬስ ነፃነት ባልተረጋገጠበት፣ የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች ተልካሻ ሰበብ እየተፈለገ በሚዘጉበት፣ ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው እንዲሰዱ በሚደረግበት፣ በሀገር ውስጥ አንድም የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ባልተቋቋመበት፣ ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች ወደ እስር የሚወረወሩበትና የሚታሰሩበት ገዥ ስርዓት ወዳላት ሀገራችን መጥተዋልና አቋማችንን ማሳወቅ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ጉባኤው በሀገራችን መካሄዱ ላይ ምንም ተቃውሞ ባይኖረንም በገዥዎች የሚጨቆነው የአፍሪካ ሚዲያ ላይ ለውጥ ያመጣል የሚል ተስፋ ግን የለንም፡፡ ምክንያቱም ለሚዲያዎች ነፃና ገለልተኛ አለመሆን አምባገነን ገዥዎችና ስርዓታቸው ቀን ከሌሊት ነፃ ሚዲያና ነፃ አስተሳሰብ እንዳይኖር ስለሚሰሩ ነው፡፡ ስለዚህ ሚዲያውን የሚጨቁኑትና የሀሳብ ልዕልና እንዳይኖረው የሚያደርጉት ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት አምባገነን መሪዎች መሆናቸውን በስብሰባው ላይ የታደሙ የአፍሪካ መሪዎች ልብ እንዲሉ እንፈልጋለን፡፡

Breaking news የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ

በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ።
ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ የደህንነት ሀላፊዎች ጋር በስልክ ሲያደርግ የነበረው የስልክ ለውውጥ በህዝባዊ ሀይሉ የመረጃ ክፍል ሲቀዳ ቆይቷል።
ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም በሚል የተመራው የግድያ ዘመቻ -በነገው እለት ጥቅምት 30/2006 ዓም ሊካሄድ ታቅዶ እንደነበር የድምጽ መረጃው ያመለክታል። ( )
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል ሰራዊት የምረቃ በአል በነገው እለት የሚካሄድ መሆኑን መነሻ በማድረግ በእለቱ በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎችንና የኤርትራ ባለስልጣናትን ለመግደል የታቀደው ዘመቻ ከመነሻው ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ፣ በፍጻሜው ዋዜማ ላይ ሲድርስ ሙሉቀን መስፍን የተባለውን ለግድያ የተላከውን ግለሰብ ህዝባዊ ሀይሉ በቁጥጥር ስር በማድረግ ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም የተባለው ኦፕሬሽን ከሽፏል።
የድምጽ መረጃውን ኢሳት ዌብሳይት ላይ ተከታተሉ
xx

Thursday, November 7, 2013

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ!!!



የወያኔ ገዢ ጉጅሌ በባህርዩ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አጋጥሟት የማያውቅ ፍጹም ኢሰብዓዊና ነውረኛ ስብስብ እንደሆነ ለመረዳት ኢትዮጵያዊያንን ለማዋረድ የሚጠቀሟቸውን ተግባራትና ቃላትን ማጤን ይበቃል።
በሶማሌ ክልል የኦብነግን ታጣቂዎች ቅስም ለመስበር ልጃገረዶችንና እናቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም ጭምር በቤተሰብ ፊት በደቦ የሚደፍሩ፤ ለዚህ ተግባር የሠለጠኑ የልዩ ጦር አባላት መኖራቸው በስፋት የሚታወቅና በተደጋጋሚም የተዘገበ ጉዳይ ነው። ወያኔ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን በዚህ ጥቃት ተሸማቀው ያነገቡትን መሣሪያ ጥለው ፀጥ-ለጥ ብለው ይገዛሉ ብሎ ተስፋ ያደረገ ቢሆንም እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ዛሬ የሶማሌ ክልል ወንዱም ሴቱም፤ ወጣቱም አዛውንቱም በፀረ-ወያኔ አቋም የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል። በኦጋዴን የወያኔ አስነዋሪ ጥቃት የፈጠረው ምሬት በውጭ አገራትም በሚደረጉ የፀረ ወያኔ ትግሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ተሳትፎ እንዲጎለብት አድርጎታል። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
በአፋር ክልልም ተመሳሳይ ጥቃት የዘወትር ትዕይንት እየሆነ መጥቷል። የአፋር የወል የግጦሽ መሬቶች ለሸኮራ አገዳ ልማት በሚል ሰበብ ሲነጠቁ የተቃወሙ የአገር ሽማግሌዎች ተደብድበዋል፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ተደፍረዋል። በአፋርም ውስጥ ለጾታዊ ጥቃት የሰለጠነ የወያኔ ልዩ ጦር ተሰማርቶ በሴቶች ብቻ ሳይሆን በወንዶችም ላይ አስነዋሪ ጥቃት አድርሷል። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
በጋምቤላ ውስጥ ወያኔ ወገኖቻችን ከፈጀ በኋላ በሕይወት የተረፉትም ቅስማቸውን ለመስበር ጾታዊ ጥቃት በመሣሪያነት ተጠቅሟል፤ አሁንም እየተጠቀመ ነው። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።
የወያኔ ዝቅጠት ዘግናኝ ነው። ወያኔ ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ጾታዊ ጥቃት ያላደረሰበት የአገራችን ክፍል የለም። ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ቤንሻንጉል … በሁሉም ቦታዎች ያልተነገሩ ጥቃቶች በዜጎታችን ላይ ደርሷል፤ እየደረሰም ነው።
በአንድ ወቅት በመሀል አገር፤ በሰሜን ሸዋ አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት በእብሪተኛ ወያኔ የተገደለውን ባለቤትዋን ብልት ይዛ አስክሬኑን እንድትጎትት መደረጉን ከዓይን እማኞች አንደበት ሰምተናል። በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሰበብ መስዋዕትነት እየተቀበሉ ያሉ ወገኖቻችን “ሽንታም አማራ” እየተባሉ ብልቶቻቸው ይቀጠቀጥ እንደነበር የሰማነው እና የምናውቀው ጉዳይ ነው። በወያኔ መዳፍ ውስጥ ውስጥ ገብተው በእስር ቤቶች በሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ ዘግናኝ ተግባራት እንደሚፈፀሙ መረጃዎች አሉ። በአዲስ አበባ በየቦታው ባሉት ስውር የማሰቃያ ቤቶችም ተመሳሳይ ተግባራት ዘወትር እንደሚፈፀሙ ይታወቃል።
ወያኔ ለጾታዊ ጥቃት ያሰለጠናቸው ሰዎችን በከተሞችም ውስጥ አሰማርቷል። በእነዚህ ጥቃቶች ግለሰቦች ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ቢሆንም የተደፈርነው፣ የተዋረድነው ሁላችንም መሆናችን አጽንዖት ሊሰጠው ይገባል። የተደፈርነው እኛ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነን። የተዋረደችው የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያ ነች።
ኢትዮጵያ አገራችን እፍረት ባልፈጠረባቸው ነውረኛ የወያኔ ዋልጌዎች እንድትገዛ እንድትረገጥ በመፍቀዳችን ጥፋቱ የኛም ጭምር ነው። ይህን ነውረኛ ቡድን በሥልጣን ላይ እንዲቆይ በፈቀድንለት መጠን በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያችን ላይ የሚደርሰው በደል እየባሰ እንደሚመጣ በዓይኖቻችን እያየን በጆሮዎቻችን እየሰማን ነው።
ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባል ላይ የደረሰው ጥቃት የዚሁ አካል ነው። እኚህ ወገናችን የደረሰባቸውን ዘርዝሮ ለመናገር የሚከብድ መሆኑ ገልፀዋል። ማፈር የነበረባቸው ጥቃት አድራሾቹ መሆን ይገባቸው ነበር፤ ሆኖም ግን ይሉኝታ አልፈጠረባቸው። ምንም ይሁን ምን በወገናችን ላይ የደረሰው ጥቃት በእሳቸው ላይ ብቻ የደረሰ ሳይሆን በሁላችንም ላይ የደረሰ መስሎ የሚሰማን መሆኑን ልንነግራቸው እንወዳለን። የተዋረደችው ኢትዮጵያ አገራችን ነች።
ይህ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔ ከሥልጣን መወገድ ይኖርበታል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ” ቀዳሚ ሥራችን ነው የሚለው ኢትዮጵያን ለማዳን ከዚህ የሚበልጥ አንገብጋቢና አጣዳፊ ሥራ ስለሌለ ነው። ወያኔን ለማስወገድ እንተባበር።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

Woyane restarted the taxi bombing game

Woyane restarted the taxi bombing game
Ethiopia’s ruling junta again killed innocent civilians by planting a bomb in a minibus. Many people have been warning the possibility of such an attack coming from the terrorist organization which is leading Ethiopia now. It has been a known fact that the ruling party in Ethiopia conducts such criminal acts in order to keep the assistance it gets from the so called ‘allies’ in the name of antiterrorism operations. According to wikileaks documents, even the US is well aware of such criminal acts of the ethnic minority junta in power in Ethiopia, but is still keeping its assistance without any restriction
Source:Reuters
Four people were killed when a bomb blast tore through a minibus in western Ethiopia late on Tuesday, at about the same time that the government warned of imminent attacks by militants, an official said.
The official, speaking to Reuters on Wednesday, said nobody had claimed responsibility for the blast.
Addis Ababa put its security forces on heightened alert on Tuesday night after receiving strong evidence that Somalia’s Islamist al Shabaab group was plotting assaults.
It was not clear whether the blast occurred before or after that warning.
“The bomb exploded on Tuesday inside a minibus travelling in Segno Gebeya,” government spokesman Shimeles Kemal said, referring to a region bordering Sudan.
“No one has claimed responsibility yet. The case is under investigation.”
The warning came three weeks after officials said two Somali suicide bombers accidentally blew themselves up while preparing for an attack on football fans during Ethiopia’s World Cup qualifying match against Nigeria.
Al Shabaab has warned Ethiopia of revenge attacks for deploying troops inside Somalia to fight the al Qaeda-linked militants, alongside African Union forces from Uganda, Burundi and Kenya.
The National Intelligence and Security Service also urged the public on Tuesday to inform police if they encountered “suspicious” activity, and urged hotel staff and private landlords to verify the identity of visitors.
Al Shabaab gunmen killed at least 67 people in September when they raided a mall in the neighboring Kenyan capital of Nairobi.
Addis Ababa says it has foiled several attacks in the past few years planned by domestic rebel groups and Somali insurgents.
There have also been sporadic explosions in recent years. Thirteen people were wounded when an explosive device ripped through a bus in the north in 2010, while a bomb explosion near a court in the capital injured two in 2011.