ወደፊት የሚወጣውን አዋጅ የጣሱ ሴቶች ታሰሩ፤
ለአለም አቀፉ የሴቶች ቀን ክብረ በአል በተዘጋጀ የሩጫ ዝግጅት፤ በሀገራችን ሰላም አጣን ሲሉ ሃሳባቸውን የገለጹ ሴቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፤
ከስፍራው የደረሰን ዜና እንደሚያስረዳው ሴቶቹ እንደተለመደው ባሎቻቸውን እየኮነኑ መንግስትን ማሞካሽት ሲገባቸው እነርሱ ግን መንግስትን በመኮንን በሀገራችን ሰላም አጣን በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ከዛም አልፈው ተርፈው ቀኑ ደረስ ቀኑ ደረሰ… እያሉ የምርጫ ቀን መቃረቡን በመጠቆም ኢሀአዴግ ላይ ፍርሃት ለቀውባታል።
ሴት እህቶቻችንን ሃሳባቸውን ከመግለጽ ወጪ የሰሩት ጥፋት ምን ሆኖ ነው የታሰሩት ብለን ያልጠይቅናቸው የመንግስት ተበካይ፤ ሃሳብን በአደባባይ መግለጽ ምንም እንኳ ለጊዜው በሽብርተኝነት አዋጁ ላይ ባይጠቀስም በመንግስታችን እና በድርጅታችን ላይ ታላቅ ሽብር እየፈጠረ በመሆኑ ወደፊት እናካትተዋለን የሚለውን ታሳቢ በማድረግ ሴቶቹ ወደፊት የሚወጣውን አዋጅ በመጣሳቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ ግራ አጋብተውናል።
የሴቶቻችንን ድምጽ ከሰማያዊ ፓርቲ ፌስ ቡክ ላይ አገኝተን ድረ ገጻችን ላይ አድርገነዋል፤
No comments:
Post a Comment