Saturday, February 1, 2014

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ከሃገር ፈረጠጡ

omot obang

(ዘ-ሐበሻ) ራሳቸው በጠሩት ግምገማ፣ ራሳቸውን አስገምግመው ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸው የንጽህናቸው ውጤት መሆኑን ሲናገሩ እንደነበረ የሚነገርላቸውና በአንድ ወቅት በጋምቤላ ስለነበረው ጭፍጨፋ ተጠያቂ ነህ ሲባሉ “መሳሪያውን ያቀበለው መለስ ዜናዊም መጠየቅ አለበት” ብለዋል የተባሉት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የፌዴል ጉዳዮች ሚ/ር ደኤታ አቶ ኦሞት ኦባንግ ከሃገር መፈርጠጣቸው ተሰማ።

በስልጣን ዘመናቸው ፕሬዚዳንቱ የክልሉን ደን እያስጨፈጨፈና ህዝቡን እያፈናቀለ ስላለው የመሬት ሽያጭና ነጠቃ የክልሉ እጅ የለበትም በሚል የተናገሩት ኦሞት ሂይውማን ራይትስ ዎች ባወጣው ሪፖርት ላይ በክልሉ ስለሚካሄደው የመሬት ነጠቃ አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው ምላሽ ሲሰጡ በክልሉ ከሶስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ ባለቤት የሌለው መሬት መኖሩን መናገራቸው አይዘነጋም።
ኦሞት ኦባንግ ከሃገር እንዳይወጡ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ ሲደረግባቸው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በተለይም በጋምቤላ ክልል ስለተፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋዎች በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ምስክር ይሆናሉ በሚል ፍራቻ በሕወሓት/ኢሕአዴጎች ከሃገር እንዳይወጡ ይፈራ እንደነበርና የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር ደኤታ የተደረጉትም “ጠላትህን አታርቀው፤ አቅርበውና እንስቅቃሴውን ተከታተለው” በሚለው የፖለቲካ አካሄድ እንደነበር የውስጥ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ይህን በማስመልከትም አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለጋራ ንቅናቄ በአንድ ወቅት ባወጣው መረጃ “አቶ ኦሞት ካገር ከወጡ አቶ መለስና መንግስታቸው ላይ ምስክር ይሆናሉ። አቶ ኦሞት ከተሰደዱ በአካል ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምስክርነታቸውን መስጠት ግዳጃቸው በመሆኑ የህወሃት ሰዎች ስጋት አለባቸው። ስለዚህ አቶ ኦሞት በተቀመጠላቸው የስድስት ወር የሃላፊነት ዘመናቸው አድርጉ የተባሉትን እየፈጸሙ ይኖራሉ። የህወሃት ሂሳብ ይህ ቢሆንም በመጨረሻ ያልታሰበ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል እገምታለሁ። ምክንያቱም ነገሮች ተነካክተዋል” የሚል አስተያየት አስነብቦ እንደነበር ይታወሳል።
የሚኒስትር ዲኤታውን ኩብለላ በተመለከተ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተጠየቁት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም አቶ ኡመt በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ማረጋገጣቸውን ገልጸው መስሪያ ቤታቸው ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝ ሲናገሩ አቶ ኡመትም ወደ ሃገራቸው መመለስ እንደማይፈልጉ መናገራቸውን ጨምሮ የመጣው መረጃ ሲጠቁም፤ አሁን ግን የት ሃገር እንዳሉ ለጊዜው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ተጠቁሟል።
በጋምቤላ በተፈፀመው ጭፍጨፋ የሚከተሉት ሰዎች በዋነኝነት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።
1. አባይ ፀሀዬ (በጊዜው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበረ)
2. ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ (በጊዜው ሚኒስትር ደኤታ የነበረና በቦታው በመገኘት ጭፍጨፋውን ያስተባብር የነበረ)
3. ኮለኔል ፀጋዬ (በጊዜው በቦታው የነበረው ወታደራዊ ሀይል አዛዥ)
4. ኡመት ኦባንግ (አሁን ከሃገር የፈረጠጡት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል አስተዳዳሪ)።

ትራፊክ ጥሶ ለመሄድ በሞከረ ሚኒባስ ላይ በተተኮሱ ጥይቶች ሦስት ሰዎች ተጎዱ

ባለፈው ሐሙስ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ በተሳፋሪዎች ተሞልቶ ደሴ ሊጓዝ ነበር የተባለ አንድ ሚኒባስ፣ ለትራፊክ ዝግ የሆነ መንገድ ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር በፀጥታ አስከባሪዎች በተተኮሱ ጥይቶች ሦስት ሰዎች መጎዳታቻውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ጥር 22 ቀን 2006 ዓ.ም. የተጀመረውን የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ምክንያት በማድረግ፣ በተለያዩ ሰዓታት መሪዎቹ የሚተላለፉባቸው መንገዶች ለተወሰነ ጊዜ ለትራፊክ ዝግ የሚደረጉ መሆኑ ቢታወቅም፣ ከምሽቱ አራት ሰዓት ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ሊወጣ እንደነበር የተገለጸው ኮድ 3 የሆነና ለከተማ ትራንስፖርት ድጋፍ ከሚሰጡ ሚኒባሶች አንዱ የሆነው ተሽከርካሪ ሾፌር፣ ለምን ትራፊክ ጥሶ ለማለፍ እንደፈለገ በቁጥጥር ሥር ውሎ በምርመራ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሚኒባሱ ከካዛንቺስ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከፊት በር ሁለት መቶ ሜትር በላይ አለፍ ብሎ ከፓርላማ መቶ ሜትር ያህል ዝቅ ብሎ በሚገኘው የታላቁ ቤተ መንግሥት መግቢያ በር አካባቢ በፀጥታ አስከባሪዎች ተኩስ ሊቆም ቢችልም፣ ከተሳፋሪዎቹ መካከል ባልና ሚስትን ጨምሮ ሌላ አንድ ግለሰብ በመቁሰላቸው፣ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ባጋጠመው ድንገተኛ ሁኔታ የሞቱም ሆነ በከባድ ሁኔታ የተጎዱ ተሳፋሪዎች ባይኖሩም፣ በወቅቱ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች በድንጋጤ ራሳቸውን ስተው እንደነበሩ በሥፍራው የተገኙ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
የሚኒባሱ አሽከርካሪ መንገዱ ለትራፊክ ዝግ መሆኑን እያወቀ ጥሶ ለማለፍ የፈለገበትን ምክንያትና በምርምራ ወቅት የተገኘ ሌላ ምክንያት ካለ፣ እንዲሁም ጉዳት ደርሶባቸዋል ስለተባሉት ሦስት ግለሰቦች ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና የፌደራል ፖሊስን ለማነጋገር የተደረገው ጥረት፣ ‹‹ጉዳዩ በምርመራ ላይ ስለሆነ ምንም ማለት አንችልም›› በሚል ምላሽ ሊሳካ አልቻለም፡፡
ከወራት በፊት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚደረጉ የሕዝብ ትራንስፖርት ጉዞዎች መታገዳቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ ቁጥጥሩ በመላላቱ ምክንያት ጉዞዎች እንዳልተገቱ እየተነገረ ነው፡፡

Friday, January 31, 2014

ይድረስ ለዶክተር ታደሰ ብሩ – ባሉበት! | Zehabesha Amharic

Thursday, January 30, 2014

በጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድን አባላት በፖሊስ ታሰሩ


ጥር 22/2006 (BlueParty Ethiopia)
እስካሁን 14 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በጎንደር የታሰሩ ሲሆን ከታሰሩት ውስጥ አራት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ይገኙበታል፣
1. ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ)
2. ብርሃኑ ተ/ያሬድ (የሀዝብ ግንኙነት)
3. ዮናታል ተስፋዬ (የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
4. ይድነቃቸው ከበደ (የህግ አማካሪ)

ሁለት ሹፌሮች እና አንድ ፊልም አንሺም (Cameraman) ከታሳሪዎቹ ውስጥ ናቸው፣ በአሁኑ ስዓት ታሳሪዎቹ በወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣብያ ሲገኙ ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ) እና አግባው ሰጠኝ ወደ ጎንደር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተወስደዋል።
ጥር 25 2006 ዓ.ም. የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለልን ህገወጥነት በተመለከተ በጎንደር መስቀል አደባባይ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ሉኡካን ቡድን በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ሲሆን ጎንደር የገባው ቡድን በጠቅላላ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ የቅስቀሳው አባላት በጎንደር ከተማ እና በተለያዩ ቦታዎች ቅስቀሳውን እንደጀመሩ የፓሊስ አባላት ፈቃድ ስለሌላችሁ መቀስቀስ አትችሉም ያሏቸው ሲሆን አባላቱም በህጉ መሰረት ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ የሚጠበቅብን ስላልሆነ ለሚመለከተው አካል ያሳወቅን በመሆናችን ህጋዊዎች ነን በማለታቸው ፓሊስ በማዋከብና በመደብደብ ጎንደር ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ መጉላላትና እንግልት እያደረሱባቸው ይገኛል፡፡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችም ፖሊሶቹን ምን አደረጓችሁ በማለት እና ይህ ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው በማለት አባላቱን ከፖሊስ ለማስለቀቅ የተቻላቸውን ያደረጉ ሲሆን ፖሊስም ሐይል በመጨመር ህዝቡን በዱላ በማባረር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድኑን እንዲሁም የጎንደር የፓርቲው መዋቅር አባላትን ጨምሮ አስረዋቸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎንደር ነዋሪ ህዝብ የፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ የታሰሩት እንዲፈቱ እየጠየቀ ሲሆን ሰልፉ በተያዘለት ቀን እንዲደረግ ለማድረግ ሌላኛው የሉኡካን ቡድን ከአዲስ አበባ በዛሬው እለት መንቀሳቀሱ ታውቆአል፡፡
A protest call in Gonder, Ethiopia

ህወሓት የፈሪዎችና የጨካኞች ስብሰብ መሆኑ አውቅ ነበረ::(አብርሃ ደስታ )


በሌሎች ላይ የምትፈፅሙት ተግባር ሁሉ በራሳቹ ላይ እንደምትፈፅሙ (እንደሚፈፀም) አስቡ። በስልጣን ላይ ያለ ሁሉ በስልጣን አይኖርም። የስልጣን ዕድምያቹ በጣም አጪር መሆኑ እናንተም ታውቁታላቹ። በሰዎች ላይ ግፍ ስትፈፅሙ ሰዎች ይጠሏችኋል። በሰዎች ስትጠሉ የስልጣን ዕድምያቹ ያጥራል። እናንተ ያላቹ የህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠመንጃ ነው። ጠመንጃ ስልጣን ለመያዝ ይረዳ እንደሆነ እንጂ በስልጣን ለመቆየት አያስችልም። ስለዚህ በጠመንጃ አፈሙዝ የስልጣን ዕድምያቹ ለማራዘም የምታደርጉት ጥረት ከንቱ ልፋት ነው። እናንተ ከስልጣን ወርዳቹ ስልጣን የህዝብ ሲሆን፣ ፍትሕ ሲነግስ፣ እኩልነት ሲሰፍን ለፈፀማችሁት ወንጀልና ላደረሳችሁት በደል በሕግ እንደምትጠየቁ አያጠራጥርም። በስልጣን የኖረ የለም። እንኳን አምባገነኖች ዴሞክራሲያዊ ስርዓቶችም በስልጣን ኮረቻ ተቀምጠው ለዘላለም አይኖሩም።
ምናልባት እናንተ ምግባራችሁ አውቃቹ በህዝብ ስትተፉ ሀገር ለቃችሁ በመውጣት ለማምለጥ ትሞክሩ ይሆናል። ገንዘቡም አላቹ። ሁሉም ካድሬዎች (በሰዎች ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ እየታዘዙ ያሉ የህወሓት አባላት) ግን እንደናንተ (እንደ ህወሓት መሪዎች) ከሀገር ወጥተው ለማምለጥ ዓቅሙ የላቸውም። ደግሞ ዓቅሙ ቢኖራቸውስ ለምን በሰሩት ጥፋት ከሀገራቸው ለመሰደድ ይወሰንባቸባል? የህወሓት ባለስልጣንናት ከስልጣን ወርደው በሀገራቸው በሰላም የሚኖሩበት ሁኔታ ለምን አያመቻቹም? ለምን መርሃቸውን ከ «ስልጣን ወይ ሞት» ወደ «ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ በሀገር በሰላም መኖር» አይቀይሩም? ለካድሬዎቹስ አያስቡም እንዴ? የህወሓት ዕድሜኮ ትንሽ ነው። ህወሓት ሲሞት የህወሓት አባላትም ከህወሓት ድርጅት ጋር አብረው መሞት የለባቸውም። ህወሓትም ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ ተቃዋሚ ፓርቲ ሁኖ መቀጠል ይችል የለ?! ዕድምያችሁ ከህወሓት ድርጅት ዕድሜ በላይ እንዲሆን አድርጉ።
እኛ ሰለማዊ ታጋዮች ነን። ያላቹ ሃብትና ጠመንጃ በመጠቀም እኛን መደብደብ፣ ማሳሰር፣ ማሰቃየት፣ መግደል ትችላላቹ። አምባገነን ስርዓት የሚችለው ነገር ቢኖር ሰው ማሳሰርና መግደል ነው። የዓላም አምባገነን መሪዎች በማሳሰርና በመግደል የስልጣን ዕድምያቸው ዘለአለማዊ ማድረግ ከቶ አይቻላቸውም። ዛሬ እኛን ብትደበድቡና ብትገድሉ ዕድምያቹ እያሳጠራቹ እንጂ እያሸነፋቹ አይደላችሁም። እኛ ብንገደል ሌላ ሰው አለ። ሁሉም ሰው መግደል አይቻልም። ምክንያቱም ሁሉም ሰው ከተገደለ ማንን ትጨቁናላቹ? የሚጨቆን ሰው ያስፈልጋችኋል። ሰው ጭቆና ሲበዛት በመሪዎቹ ላይ ያምፃል። እናም ትሸነፋላቹ። አምባገነን ተሸናፊ ነው። የማይሸነፍ ህዝብ ብቻ ነው። ምክንያቱም ህዝብ ለጭቆና አይነሳም። እኛን በማሰቃየት ሰለማዊ ትግሉ መግደል አይቻልም። ሰለማዊ ትግሉ በመግደል የሰዎች የነፃነት ጥያቄ መግደል አይቻልም። የሰዎች የነፃነት ጥያቄ በመግደል ሰዎችን ለዘላለም መጨቆን አይቻልም። ስለዚህ መሸነፋቹ አይቀርም።

Wednesday, January 29, 2014

የኢትዮጵያ መንግስት የግንቦት7 መሪዎችን ኮምፒዩተሮች በዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች ሲሰልል እንደተደረሰበት አንድ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ

-የህዝቦችን ደህንነት ከመንግስታት ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው  ተቋም ለእንግሊዝ መንግስት የገቢዎቸና ጉምሩክ መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ “ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአለም ላይ የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ለሚታወቁ አገሮች ኮምፒይተሮችን፣ የሞባይልና የስካይፕ የስልክ ግንኙነቶችን እንዲሁም የኢሜል ልውውጦችን በርቀት ሆኖ ለመከታተል የሚያስችለውን ፊን ፊሸር ወይም ፊን ስፓይ በሚል ስም የሚጠራውን የመሰለያ መሳሪያ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ላሉ አገሮች በመሸጥ ዜጎች እንዲሰለሉና ደህንነታቸው አደጋ ላይ እንዲወድቅ በማድረጉ  ምርመራ እንዲጀመር” ሲል ጠይቋል።

የግንቦት7 ከፍተኛ አመራር በሆኑት በ ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግል ኮምፒዩተር ላይ የመሰለያ ቫይረሱ መገኘቱን በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የሙንክ ስኩል ግሎባል አፌርስ የምርምር ተቋም የሆነው ሲትዝን ላብ ማረጋገጡን ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል በደብዳቤው ገልጿል።
የመሰለያ መሳሪያው የሰብአዊ መብቶችን በሚጥሱ 36 አገራት ላይ መሸጡን የገለጸው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል፣ በተለይም በቬትናም፣ ማሌዚያና ኢትዮጵያ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ለመሰለያነት እየዋለ ነው ብሎአል።
በኢትዮጵያ የግንቦት7 ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኮምፒተራቸው ሲሰለል መቆየቱን የገለጸው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል፣ በአንድ የብሃሬን የሰብአዊ መብት ተማጓች ኮምፒዩተር ላይም ተመሳሳይ የስለላ ሶፍት ዌር መገኘቱን ገልጿል።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለፕራይቪሴ ኢንተርናሽናል ጠበቃ የምስክርነት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። ፕራይቪሲ ኢንተርናሽናል የስለላ ቫይረሱን የሸጠውን ጋማ ኢንተርናሽናልን የተባለውን ድርጅት ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ማቀዱን ዶ/ር ታደሰ ገልጸዋል፡ ኢሳት ዜና

በ6 የሱዳን ወጣቶች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት በእስር ላይ እንደምትገኝ ታወቀ


ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሪያ እንድሪስ የተባለች ኢትዮጵያዊት ወጣት በ6 የሱዳን ወጣቶች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስትደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ ኢሳት የደረሰው ሲሆን ፣ ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አረጋ ልጂቷ መደፈሩዋን አምነው ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ግን ከፍተኛ ባለስልጣኖች መፍቀድ አለባቸው በሚል ዝርዝር ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ጥቅምት ወር አካባቢ ቤት ለመከራየት በአካባቢው የነበሩትን ወጣቶች የጠየቀችው ኢትዮጵያዊት፣ ወጣቶችም ” እኛ የሚከራይ ቤት እናሳይሻለን” ብለው በመውሰድ በአሰቃቂ ሁኔታ እየደፈሩ በእርቃኑ ላይ የተለያዩ አስጸያፊ ስራዎችን እየሰሩ በቪዲዮ እየቀረጹ ተጫውተውባታል።
ለራሱ ምስል የተጠነቀቀው የሱዳን መንግስት ቀድሪያንና ሞርጋን ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ አስሮአት እንደሚገኝ ኢሳት ከኢምባሲው የውስጥ ምንጮች መረጃ የደረሰው ሲሆን፣ የኢምባሲው የዲያስፖራ ሃላፊ ግን ልጅቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ብሎአል። የሱዳን ፍርድ ቤት ድርጊቱ ሲፈጸም በወቅቱ ለምን ሪፖርት አላደረግሽም በሚል ወጣቷንም ተጠያቂ ለማድረግና የአገሪቱን መንግስት ከተጠያቂነት ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩን የውስጥ ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ወጣቷ በበኩሏ ” መረጃውን የምታወጪው ከሆነ እንገድልሻለን ስለተባለች በፍርሃት በወቅቱ ሪፖርት ለማድረግ እንዳልቻለች ገልጻለች።” በአሁኑ ጊዜ ወጣቷ ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳትገናኝ በመደረጓ ኢሳት ለማነጋገር ሳይችል ቀርቷል። ወጣቷን በእስር ቤት ለማነጋገር የሚፈልጉ ሰዎች ልዩ ወረቀት ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ማምጣት የሚኖርባቸው ሲሆን፣ አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ወጣቷን ለመጠየቅ ፈልጎ በወረቀት ክልከላ ምክንያት ሳይችል ቀርቷል።
በወንጀል ከሚፈለጉት ወረበሎች መካከል የተወሰኑት የታሰሩ ቢሆንም ሌሎች ደፋሪዎች ግን እስካሁን አለመታሰራቸው ታውቋል። በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን እየተከታተልኩት ነው ቢልም እስካሁን በእስር ላይ የምትገኘዋን ወጣት ለማስፈታት አልቻለም።

ወጣቷ በአሁኑ ጊዜ ነፍሰጡር ስትሆን፣ የእርግዝናዋ ምክንያት ከመደፈሩዋ ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም

Tuesday, January 28, 2014

ሂውማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ይበልጥ ጠቧል አለ



መንግስት፤ ተቋሙ የተቃዋሚዎች የፕሮፖጋንዳ ማስፈፀሚያ ነው
“በኢትዮጵያ የነፃ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ ነው”
“በኤርትራ የመብት ጥያቄ ማንሳት ነውር ሆኗል” ብሏል

የኢትዮጵያ መንግስት የዜጐችን  ሰብአዊ መብት በስፋት ይጥሳል በማለት ተደጋጋሚ ወቀሳና ስሞታ የሚያቀርበው ሂውማን ራይትስ ዎች የተሰኘው አለማቀፍ የመብት ተቋም፤  ሰሞኑን ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነፃነት ይበልጥ መጥበቡንና የነጻ ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ የተቋሙን ሪፖርት ያጣጥላል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ነፃነትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማካሄድ እድል (የፖለቲካ ምህዳር) እየጠበበ የመጣው ከምርጫ 97 በኋላ መሆኑን የገለፀው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ከዚያ ወዲህ በመንግስት የፀደቁትን የፀረ - ሽብር እና የበጐ አድራጐት ማህበራት አዋጆችን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ በፀረ - ሽብር አዋጁ መነሻነት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ሽብርተኛ ተብለው እንደታሠሩና እንደተፈረደባቸው የተቋሙ ሪፖርት ጠቅሶ፣ በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፍርሃት እንዲሸበቡ ተደርገዋል ብሏል፡፡
ጋዜጠኞች የፀረ-ሽብር አዋጁን በመፍራት የሙያ ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ መታፈናቸውን ሲገልጽም፤ የአዋጁ አንቀፅ እየተጠቀሰ እሥራት የተፈረደባቸው ጋዜጠኞች መኖራቸውንም አውስቷል፡፡

በኢትዮጵያ ጐልተው የሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የፖለቲካ ምህዳር መጥበብና የኘሬሶች አፈና ቢሆኑም፤ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም መሻሻል አላሣዩም ብሏል ሪፖርቱ፡፡

Saturday, January 25, 2014

የትግሬ እና የኦሮሞ ልሂቃን፣ ዐማራን በጅምላ ለመፍጀት የቀየሱት የተጠቂነት ፖለቲካ ሥልት


ለመሆኑ የተጠቂነት ፖለቲካ ሥልት ምን ማለት ነው? የተጠቂነት ፖለቲካ ሥልት፣ የአንድ ማኅበረሰብ ልሂቃን፣ ባልነበሩበት እና ባልኖሩበት የታሪክ ዘመን፣ በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ጉዳዮች አስገዳጅነት የተፈጠሩ ግጭቶችን እና የተከሰቱ ክስተቶችን ለማብራራት የተጣመመ ትንታኔ በማቅረብ፣ ለራሣቸው የፖለቲካ ዓላማ ማሣኪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። እኒህ ልሂቃን በግጭቶቹ ወቅት ራሱም ጉዳት ደርሶበት፣ ነገር ግን የድል ባለቤት የሆነው አካል የወሰዳቸውን ዕርምጃዎች፣ ትክክለኞቹን ከሐሰት ፈጠራዎች ሣይለዩ፣ እንዲያውም ልብ ወለድ ድርሣኖችን በመጨማመር፣ «ይህ ተፈጸመብን፣ እንዲህ ተደረግን፣ ይህን ተቀማን፣ ይህ በደል ደረሰብን፣ እንዲህ ይሉናል፣ ወዘተርፈ» እያሉ ያልተባሉትን እንደተባለ በማራገብ፣ ያልተደረገውን እንደተደረገ በማቅረብ፣ «ተምኔታዊ ተጠቂነትን» እንደ ኃይል ማሰባሰቢያ ሥልት ይጠቀሙበታል። ይህ ዓይነቱ ዘዴ ለነገዳቸው አባሎች የሥነልቦና የበታችነትን፣ ተዋራጅነትን እና ተሸናፊነትን የሚያሸጋግር ከመሆኑም በላይ፣ ትውልዱ ትናንትን እንጂ ነገን እንዳያይ በመሸበብ፣ ለ«ተበደልኩ» ባዩም ሆነ «በዳይ» ለተባለው ወገን የወል መጠፋፊያ የሚሆን የበቀል ጎዳናን ይጠርጋል።
የዐማራው ነገድ በየዘመኑ በተለያዩ የውጪም ሆነ የአገር ውስጥ ኃይሎች ከፍተኛ የሆነ ግፍ እና በደል የተፈጸመበት መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። የዐማራው አባቶች ግን ምንጊዜም ቢሆን ለልጆቻቸው «የእነ እገሌ ነገድ/ጎሣ እንዲህ አደረጉን»፣ ወይም «እንዲህ ይሉናል» የሚል የሥነልቦና እና የሥነምግባር ስብራትን የሚፈጥሩ ትውፊቶችን ለልጆቻቸው አያስተላልፉም። በመሆኑም በተጠቃም ጊዜ ቢሆን ዐማራው በሥነልቦና እና ሥነምግባር ደረጃ በአጥቂዎቹ ላይ የበላይነቱን እንደያዘ እንዲቀጥል አድርጎታል። በዚህም የተነሣ በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ውስጥ በተከሰቱ «የተገዛ አልገዝም፣ የገብር አልገብርም» ጦርነነቶች፣ ዐማራው በተለያዩ ነገዶች እና ጎሣዎች አያሌ ጥቃቶች እና በደሎች እንደደረሱበት ቢታወቅም፣ አንድም ጊዜ የተጠቂነት ፖለቲካን አራምዶ አያውቅም። የዐማራው ነገድ ታላቅነት የሚመነጨውም በአርቆ ተመልካቸነቱ ከዚህ «የተጠቂነት ፖለቲካ» ራሱን ያራቀ በመሆኑ ነው። በቆየው ትውፊት እንደሚነገረው፦ «ዐማራና ሠንበሌጥ አንድ ናቸው» ይባላል። ምክንያቱም ሠንበሌጥ ኃይለኛ ወዠቦ ዝናም ሲመጣ ለጥ ብሎ እንደሚያሳልፈው ሁሉ፣ ዐማራም ከዐቅሙ በላይ የሆነ ነገር ሲገጥመው አንገቱን ደፍቶ ያሣልፋል። እንዲሁም «የበቆሎ ሠብል እና ዐማራ መከራን ይቋቋማሉ። የበቆሎ ሠብል በቡቃያነቱ የሚያዝያን እና የግንቦትን ፀሐይ ጠውልጎ አሣልፎ፣ በክረምት ዝናም ለምልሞ፣ በጥቢ ወራት በመስከረም እና በጥቅምት እሸቱ እንደሚደርስ ሁሉ፣ ዐማራም የሚደርስበትን ማናቸውንም መከራ እና ስቃይ ተቋቁሞ በመጨረሻ የድል ባለቤት ይሆናል።» የሚሉት አባባሎች ዐማራ የዚህ የተጠቂነት ፖለቲካ ሰለባ አለመሆኑ ጉልህ ማሣያዎች ናቸው።
ዐማራው ለተጠቂነት ሥነልቦና ሰለባ ያልሆነባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ። ከባህላዊ ትውፊት እና ታሪካዊ መረጃዎች መገንዘብ እንደሚቻለው፣ ዐማራው ማግኘት እና ማጣትን፣ ማሸነፍ እና መሸነፍን፣ መግዛት እና መገዛትን ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህም የረዳው በዚች ዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ነገሮች አላፊዎች እንደሆኑ፤ ቋሚዎቹ እና ፈራጆቹ ግን ታሪክ እና ሕዝብ ብቻ መሆናቸውን በኃይማኖታዊ ሥርዓቱ በሚገባ በመማሩ እንደሆነ ይታመናል። በመሆኑም «ዐማራ ገዛባቸው» በተባሉት ዘመናት እንኳን ልክ የዛሬው የትግሬ-ወያኔ ቡድን እንደሚያደርገው፣ በነገድ ፖለቲካ ላይ የተመሠረተ የኃብት ዘረፋ እና የሥልጣን ቅርምት አድርጎ አያውቅም። ዐማራው እንደ ትግሬ ልሂቃን የንብነት፣ እንዲሁም እንደ ኦሮሞ ልሂቃን የባሕር-ዛፍነት ባሕሪ የሌለው ስለሆነ፣ «ለብቻየ ልብላ እና ልጠቀም» ያለበት ወቅት የለም።
ንብ እና የትግሬ-ወያኔ አንድ ናቸው። ንብ ሩቅ አገር ተጉዛ፣ አበባ ቀስማ፣ ወደ ቀፎዋ ተመልሣ፣ ማር ትሠራለች። ሰው ንብ የሠራችውን ማር ለመቁረጥ ሲሞክር ተናድፋ ታባርረዋለች። የትግሬ-ወያኔም የኢትዮጵያውያንን ኃብት በሙሉ ከአገሪቱ አራቱ ማዕዘናት በመዝረፍ ወደ ትግራይ ያጓጉዛል። ትግራይ የገባ ንብረት ደግሞ የትግሬ ብቻ አንጡራ ኃብት ነው።
ዐማራው እንደ ኦነግ እና ኦሕዴድ የባሕርዛፍነት ጠባይ የለውም። በምድራችን ካሉት ራስ-ወዳድ ዕፅዋት መካከል ባሕርዛፍ አንዱ ነው። ባሕርዛፍ ከሥሩ እንኳን ሌላ ተክል፣ የራሱም ዘር ትንሽ ከዕድገቱ ጎተት ካለ አያሳድገውም፤ አቀጭጮ ያጠፋዋል እንጂ። ምንም እንኳን ኦነጎች የሻቢያ፣ ኦሕዴዶች ደግሞ የወያኔዎቹ ተላላኪዎች እና ትዕእዝ አስፈጻሚ ቢሆኑም፣ እንደ ባሕርዛፍ ከዘራቸው ውጪ ሌሎች ኢትዮጵያውያን በክልላቸው እንዲኖሩ አልፈቀዱም። «ኦሮሞያ ለኦሮሞዎች» በሚል የጭፍን ዘረኞች መፈክር በመመራት፣ ሌሎችን ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም ዐማሮችን በጅምላ ጨፍጭፈዋል፣ አባርረዋል አሁንም ከዚህ ድርጊታቸው አልታቀቡም። ሆኖም እነርሱ «ኦሮሚያ» ብለው የሚጠሩት ግዛት፣ ከ፲፮ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን አጋማሽ ጀምሮ በወረራ የያዙት መሬት ሲሆን፣ ጥንተ ሥረ-መሠረቱ ግን የዐማራው፣ የሐዲያው፣ የከንባታው፣ የዛዩ፣ የጠምባሮው፣ የአላባው፣ የሲዳማው፣ የጉራጌው፣ የአርጎባው፣ የሺናሻው፣ የጋሞው፣ የዳውሮው፣ የአንፊሎው፣ የየሙ፣ ወዘተረፈ ርስት የነበረ መሆኑ ይታወቃል። አልፎ ተርፎም እንደ ጋፋት፣ እናርያ፣ ዳሞት፣ ገንዝ፣ ወጅ፣ ቢዛሞ፣ አንጎት፣ ቤተ-ዐማራ እና የመሣሠሉትን ነገዶችን እና ታላላቅ የግዛት ስሞችን የኦሮሞ ወራሪዎች ሙሉ በሙሉ እንዳጠፏቸው ታሪካዊ ሃቅ ነው።
ዐማራው በማኅበራዊ ግንኙነቱም ሆነ በፖለቲካ አቋሙ እንደ ዋርካ፣ ዝግባ፣ ሾላ ዛፎች ነው። እኒህ ዛፎች በሥራቸው በርካታ የቁጥቋጦ እና ዕፅዋት ዘሮች እንዲበቅሉ፣ እንዲያድጉ እና እንዲራቡ ያደርጋሉ። ለምሣሌም ያህል ለአገራችን ለኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ የሆነው «አረንጓዴው ወርቅ» በመባል የሚታወቀው ቡና አድጎ፣ ለፍሬ የሚበቃው፣ በነዚህ ዛፎች ጥላ ሥር ነው።
ከዚህም በተጨማሪ አጋሙ፣ ቀጋው፣ እንኮዩ፣ ጠንበለሉ፣ ኮሽሙ፣ ሐረጉ ወዘተርፈ በእነዚህ ዛፎች መከታነት እና ጥላነት ሥር
ተንሠራፍተው ይራባሉ።
በአገራችን ታሪክ ዐማራው በዐማራነቱ ኢትዮጵያን ለብቻው ጠቅልሎ የገዛበት ወቅት ባይኖርም፣ በዐማራው ስም ኢትዮጵያ
ተገዛች በተባሉባቸው ዘመናት እንኳን፣ አንዳች ኃብትም ሆነ ንብረት ተዘርፎ አሁን ወያኔ «የዐማራው ክልል» ብሎ ወደከለለው አካባቢ
አልተጓጓዘም። የሌሎች ነገዶች እና ጎሣዎች አባሎችም «አገራችሁ አይደለምና ውጡ» የተባሉበት አጋጣሚ የለም። እንዲውም
በተቃራኒው ከታሪክ የምንገነዘበው፣ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፦ እንደ ንጉሥ አባ-ጅፋር አባ-ጎሞል፣ ራስ ጎበና ዳጨ፣ ፊታውራሪ
ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ፣ ደጃዝማች ባልቻ ሣፎ፣ ደጃዝማች ገብረእግዚአብሔር (ኩምሣ) ሞረዳ፣ ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ፣ ወዘተርፈ
የመሰሉት ስመጥር የኦሮሞ የጦር መሪዎችን ወደ ከፍተኛው የሥልጣን ማማ ያወጡ መሆናቸውን ነው። ይህ ሁሉ የዐማራው ሥነልቦና
የበላይነት ያለው እና የተጠቂነት ፖለቲካ ሰለባ ያለመሆኑ ውጤት ነው።
የተጠቂነት ስሜት የበታችነት ስሜት የሚወልደው አደገኛ እና ተወራራሽ የሥነልቡና በሽታ ነው። በዚህ ደዌ የተለከፉ
ልሂቃን፣ ለነገዳቸው አባሎች በዓለም ላይ ያለው መልካም ነገር ሁሉ ቢደረግላቸው እንኳን፣ ዘወትር ከማማረር እና ከማሤር
አይቆጠቡም። የበታችነት ስሜቱ ተላላፊ በሽታ የሚሆነውም፣ የነገዱ ልሂቃን የሆኑት የተጠቂነት ፖለቲካ አራማጆች፣ ነጋ ጠባ «እንዲህ
ሆንን፣ እንዲህ ተባልን፣ እንዲህ ተደረግን» በማለት ተከታዩ ትውልዱ ወደፊት ሣይሆን ወደኋሊት እንዲያይ በማድረግ፣ ለበቀል
እንዲነሣሣ ስለሚያደርጉት ነው። በዚህም ሁኔታ ተከታታይ ትውልዶች የበታችነት ስሜትን እንዲቀበሉ በመሣሪያነት በመጠቀም፣
የተጠቂነት ፖለቲካን ተሸካሚ የሆነ ማኅብረሰብን በመፍጠር፣ የዚያ ነገድ አባሎች ከዚህ ደዌ እንዳይፈወሱ ያደርጋሉ። ስለሆነም
የተጠቂነት ፖለቲካ ማራመድ፣ ቂም እና ጥላቻን አርግዞ በቀልን የሚወልድ የአመለካከት ስብራት ነው። ይህ ደዌ ደግሞ በቀላሉ
በሕክምና ሊፈወስ የማይችል ታላቅ ተላላፊ በሽታ በመሆኑ፣ አገራችን ኢትዮጵያ በዚህ ዓይነቱ የፖለቲካ አመለካከት አራማጆች
ስትታመስ ትኖራለች።
የተጠቂነት ፖለቲካ የሚያራምዱ ሰዎች ትናንትን እንጂ፣ ነገን አሻግረው ማዬት የሚችሉ አይደሉም። ወደ ኋላ እንጂ፤ ወደ
ፊት መመልከት የማይሹ ናቸው። በመሆኑም የእንቅስቃሴአቸው ዜማ በቀል ነው። በቀል ደግሞ ጥፋት ነው። ያለፈውን፣ እነርሱ በደል
ነው ያሉትን፣ በሌሎች ላይ ለመፈጸም መዘጋጀት ነው። ያውም ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት በሌላቸው ሰዎች ላይ! በደል በደልን
እንደሚወልድ ካለመገንዘባቸውም ሌላ፣በዳያችን ነው ያሉት አካል መልሶ ያኑ በደል ሊፈጽም የማይችልበት ምንም ዓይነት ማረጋገጫ
ሳይኖራቸውና ያ ዓይነት ጥቃት ተመልሶ በእነርሱ ላይ ሊፈጸም እንደማይችል የሚተማመኑበት ዘዴ ሳይኖራቸው፣ ለበቀል ከበሮ
ይመታሉ። በዚያም ቤት እሳት እንዳለ ይዘነጋሉ። የተጠቂነት ፖለቲካ ሰለባ መሆን በለቅሶ፣ በዋይታና ሰዎች በፈጠሩት የፈጠራ ድርሰት
ማመንን የግድ ስለሚል፣ባለቀሱና እንዲሆኖ ፤እንዲህ ተደርጎ ያላቸውን ሁሉ ዕውነት አድርገው በመቀበል ተከታይ ትውልዳቸው ያኑ
የተጠቂነት ፖለቲካን እንዲያራምድ ዉሸትንና ልብ ወለድ ድርሳኖችን በገፍ ያቀርባሉ። ይህም ትውልዱ መቻቻልን እና አብሮነትን
እንዲጠላ እንዲሁም መነጠልን ብቸኛ መንገድ አድርጎ እንዲነጉድ በማድረግ ከማኅበረሰብ ዕደገት ተፃራሪ በሆነ አቅጣጫ እንዲጓዝ
ያደርጉታል። ትርፉም ጥፋት፣ አመድ እና ፀፀት ይሆናል። ከኤርትራ መገንጠል የምንማረው ይህን ነው።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አያሌ የተጠቂነት ፖለቲካ አራማጅ የሆኑ ልሂቃን ነበሩ፣ አሉም። በእኒህ ልሂቃን ግፊት
የተነሣ የነገዳቸውን መጠሪያ ስም እስከማስቀየር መድረሳቸውን ስናስተውል፣ አሁንም ለትውልዳቸው በማስተላለፍ ላይ ያሉት
ትምህርት በተጠቂነት ፖለቲካ የተቃኘ መሆኑን አለመገንዘባቸውን ያመለክታል። ሆኖም ለሌላው ወገን እነርሱ በነባሩ ስማቸው ተጠሩ
ወይም «በዚህ ስም ጥሩን» ባሉት ተጠሩ፣ ነገሩ አቅማዳ ቀልቀሎ-ቀልቀሎ አቅማዳ ከመሆን ያለፈ ትርጉም አይኖረውም። የስም ለውጡ
ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት «በዚያ ስም እንዲህ ተብለናል» ከሚለው ለመሸሽ በመሆኑ፣ ሽሽቱ የበለጠ ጥያቄን በማስነሣት፣ የጥንቱን
ማንነት በምርምር የበለጠ እንዲታወቅ ከማድረግ የዘለለ ጥቅም ያመጣል አይባልም። በመሆኑም የነገድ መጠሪያ ስም መቀየሩ
የበታችነት ስሜት መኖሩን ያረጋግጣል እንጂ፣ የበላይነትን ስሜት ያጎንጽፋል ተብሎ አይጠበቅም። በአጠቃላይ አነጋገር፣ የስም መጠሪያ
ለውጡ የማንንት ቀውስ የፈጠረው የተጠቂነት ፖለቲካ ውጤት ከመሆን አያልፍም።
ባለፈው ዓመት በ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ማገባደጃ፣ አርሲ ውስጥ የኦሮሚያ ባህል ማዕከል ተብሎ በተገነባ ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ «አኖሌ
ሠማዕታት» የተሰኘ ሐውልት ቆሟል። ሐውልቱን ያስገነባው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ነው። ሐውልቱ ወደላይ በተዘረጋ የቀኝ እጅ መዳፍ
መሐል የተቆረጠ ጡት ጉች ያለበት ነው። ይህም ሐውልት እንዲወክል የተፈለገው፣ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአገር ግንባታ ወቅት
በ«ገብር፥ አልገብርም» ሽኩቻ ምክንያት በተካሄደው ጦርነት፣ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሠራዊት «በአርሲ ኦሮሞ ሴቶች ላይ አደረሰ»
የሚሉትን ጉዳት ለመዘከር እንደሆነ የሐውልቱ ባለቤቶች ገልጸዋል። አኖሌ፣ ተስፋዬ ገብረአብ «የቡርቃ ዝምታ» በሚል ርዕስ
ባሳተመው ልብወለድ መጽሐፍ ውስ ዋና ገጸ-ባሕርይ ነው። መጽሐፉን ያነበቡ ሰዎች፣ በዕውኑ ዓለም «ይህ ሰው ሌንጮ ለታ» ነው
የሚሉ አሉ። እርግጠኛው የአኖሌ ገጸ-ባሕርይ ማንን እንደሚወክል የሚያውቁት የልብወለድ ታሪኩ ጠንሣሾች የሆኑት የወያኔ እና
የሻዕቢያ ሰዎች ብቻ ናቸው። ይህ ልብወለድ መጽሐፍ ዐማራን እና ኦሮሞን እስከ ወዲያኛው እንዳይገኛኑ በማድረግ፣ ኢትዮጵያን እና
ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ታጥቀው በተነሱት በሻዕቢያ እና በወያኔ የተቀነባበረ እንደሆነ ያነበቡት ሁሉ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው።
ነገሩ ያልገባቸው እና የተጠቂነት ፖለቲካ አራማጅ የሆኑት የኦነግ እና የኦሕዴድ ጀሌዎችም «ለካ ይኸን ያህል ተበድለን ኖሯል» በሚል
ስሜት፣ ልብወለዱን ገሃድ፣ ውሸቱን ዕውነት በማድረግ፣ የተሸናፊነት እና የተጠቂነትን ሥነልቦና በአሁኑ የኦሮሞ ትውልድ ላይ ለመጫን
ቋሚ የመልዕክት ማስተላለፊያ ሐውልት ሠርተው ስናይ፣ የዘመናችን የኦሮሞ ልሂቃንን የቱን ያህል ለተጠቂነትና ለተሸናፊነት ሥነልቦና
እንደተጋለጡ እናያለን።
በትክክለኛው አቅጣጫ ከታዬ፦ በሐውልቱ ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት የሚወክለው የዐማራውን የጦርነት ባህል
ሣይሆን የኦሮሞ ወራሪዎችን ታሪካዊ ድርጊቶች ነው። ዛሬ ሳይቀር ብልት መስለብና ጡት መቁረጥ ተዘውትሮ የሚታየው በኦሮሞው
ማኅበረሰብ እንጂ፣ በየዐማራው አለመሆኑን ትውልዱ በየዕለቱ የኑሮ ገጠመኙ የሚያየው ስለሆነ፣ ማንም ቢሆን እንዲህ ያላው ሥራ
የራሱ የኦሮሞ እንጂ፣ የዐማራው ነው ብሎ ይቀበለዋል ለማለት አይቻልም። ጡት የመቁረጥ እና ብልት የመስለብ የወራሪነት ባህል፣
በዐማራው የታሪክ እና የባህል ትውፊት መኖራቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ሊያቀርብ የሚችል ሰው ፈጽሞ የለም። ትናንት «ጋላ» ይባል የነበረው፣ ዛሬ ኦሮሞ በመባሉ ብቻ «የዚህ ባህል ባለቤት አይደለም» ካልተባለ በስተቀር፣ ሰለባ እና ጡት መቁረጥ ያለአንዳች ጥርጥር የኦሮሞ ባህል ነው። አንድ የኦሮሞ ወጣት የወደዳትን ሴት ለማግባት፣ ሰለባ መጣል ግዴታው እንደነበር ይታወቃል። ዛሬም ድረስ ይህ ድርጊት በኦሮሞ ማኅበረሰብ ተወላጆች አማካይነት ከእነርሱ ነገድ ወጪ በሆኑ ወንዶች ላይ ይፈጸማል። ይህን የሚያውቁ፣ በተግባርም ያከናውኑ የኦሮሞ ሰዎች ባሉበት እና ሰለባ ከኦሮሞ ባህል ውስጥ ዓይነተኛው መሆኑ በግልጽ በሚታወቅበት ሁኔታ፣ « የእምዬን እከክ በአብዬ ልክክ» እንዲሉ፣ ሰለባን እና ጡት ቆረጣን ወደ ዐማራ ማዞር፣ ራስን ካለማወቅና ራስን ሆኖ ካለመገኘት ሌላ የትውልዱን የማመዛዘን ችሎታ ዝቅ አድርጎ መመልከት ከመሆን ውጭ ሌላ ትርፍ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም። ትርፍ ያመጣል ከተባለም ትውልዱን ለበቀል ማነሳሳት እና የመጠፋፋትን ከበሮ መደለቅ ይሆናል። ይህ ደግሞ ለወንጃዮቹም ለኦሮሞ ልሂቃን አይበጃቸውም። ለሁሉም የሚበጀው፣ ወደኋላ ማየትን ትቶ ወደፊት በመመልከት፣ የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን እንዴት እንገንባ? በኢትዮጵያውያን መካከል መቻቻልን እና በሰላማዊ ሁኔታ አብሮ መኖርን እንዴት እናስፍን? በሚሉት ዙሪያ መመካከሩ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ዐማራውም የሚያነሣቸው እጅግ መሠረታዊ ጉዳዮች ይኖሩታል።
በነባራዊ ዓለም የሌለ እና ያልነበረ፣ የተስፋዬ ገብረአብ የልብወለድ ድርሰት ውጤት የሆነው የአኖሌ ሐውልት የቆመበት ቦታ እኮ፣ እስከ ፲፮ኛው መቶ ክፍለዘመን አጋማሽ ድረስ የሐዲያዎች እና የከንባታዎች መኖሪያ የነበረ ነው። ዛሬ ኦሮሞው ከደቡብ እስከ ሰሜን፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ተንሰራፍቶ የሚገኝበትን ቦታ የያዘው በወረራ ነው። ኦሮሞው ሲወርር ደግሞ የወረረውን ሕዝብ በጅምላ እየገደለ፣ የማረካቸውን ወንዶች ብልት እየሰለበ የሴቶችን ጡት እየቆረጠ እንደሆነ በታሪክ የተረጋገጠ ሃቅ ነው። ዛሬ የኦሮሞው ቁጥር ከሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች በአንፃራዊ ሁኔታ በልጦ የመገኘቱ ሚስጢርም ሌላ ምንም ሳይሆን፣ ከ፲፮ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ባደረጉት የመስፋፋት ወረራ ወቅት፣ ከግራኝ አህመድ ጭፍጨፋ የተረፈውን ኢትዮጵያዊ እነርሱም በተራቸው በጅምላ በመፍጀታቸው እና በመስለባቸው የተነሣ ነው። ይህ ታሪካዊ ሃቅ ነው። ሆኖም ነገሩ «ብጥለው ገለበጠኝ» ነውና፣ በኦሮሞው ወረራ የተጎዳው ሌላው ኢትዮጵያዊ ሆኖ ሳለ፣ የተጠቂነት ሥነልቦና ስለሌለው ብቻ «ይህ ግፍ በኦሮሞዎች ተፈጸመብን» ባለማለቱ፣ ጉዳት አድራጊዎቹ ኦሮሞዎች እንደ ተበዳይ ሐውልት መሥራታቸው እጅግ የሚያስገርም ነው።
መቼም የአኖሌን መታሠቢያ ሐውልት በማቆም የኦሮሞ ሕዝብ የሚጠቀመው አንዳችም ቁሣዊ ጥቅም አለ አይባልም። ስለሆነም በዚህ የልብወለድ የፈጠራ ሥራ ተመርኩዞ በቆመው ሐውልት የሚጠቀሙት የኢትዮጵያ ጠላቶች ብቻ ናቸው። ምክንያቱም የኢትዮጵያውያንን አንድነት ንደውበታል። በድርጊታቸውም ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላቸውን የዐማራን እና የኦሮሞን ነገዶች እንዳይገናኙ የሚያደርግ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረዋል። ሁለቱንም ለዝንተ-ዓለም በአጥፊና በጠፊነት እንዲቆሙ አድርገዋል። እንዲህ ያለው የዐማራ-ኦሮሞ መናቆር፣ ከአናሣው የትግሬ ነገድ የበቀሉት የትግሬ-ወያኔዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ላለፉት ፳፫ ዓመታት ቀጥቅጠው እንዲገዙ የተመቻቸ ዕድል እንደሰጣቸው ሁሉ፣ ለወደፊትም ላልተወሰኑ ዓመታት አገዛዙ እንዲቀጥል በሩን ወለል አድርጎ ይከፍትላቸዋል። ሆኖም ሠሞኑን በተለያዩ የሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች እንደተገለፀው፣ በአሶሳ፣ በበደኖ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በወተር፣ በአርባጉጉ እና በሌሎችም ሥፍራዎች ይኖሩ በነበሩ የዐማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ዋና አስፈፃሚ የነበረው ሌንጮ ለታ እና ጓደኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ (የገቡ) መሆኑ ይሠማል። ሌንጮ ለታ እና ሌሎችም የኦነግ አመራር ጓደኞቹ፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ የሻቢያ እና የወያኔ ዓላማ አስፈፃሚዎች መሆናቸውን አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ስለዚህ የእነ ሌንጮ ዳግም ወደ ወያኔ መጠጋት ተልዕኮ ሌላ ሣይሆን ቀደም ብለው የጀመሩትን አስፀያፊ የዐማራ የጅምላ ጭፍጨፋቸውን ለመቀጠል እንደሆነ ማንም ኅሊና ያለው ሰው ይገነዘበዋል። እኒህ ሁሉ ድርጊቶች የሚከናወኑት፣ የዐማራውን ነገድ ሆን ብሎ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት ስለሆነ ዐማራው ከያዘው የቀን ሠመመን ሊነቃ ይገባል። ዐማራው የሥነልቦና የበላይነቱን ጠብቆ፣ እንደትግሬ እና ኦሮሞ ልሂቃን «የተጠቃን» ሥነልቦና ሰለባ ሣይሆን፣ ሊያጠፉት የተሰለፉትን «አውቀንባችኋል» ማለት እንዲችል የአኖሌ ሐውልት ጥሪ እያቀረበለት መሆኑን አስተውሎ፣ ከወዲሁ ሁለንተናዊ ዝግጅት ሊያደርግ ይገባዋል። በዚህ ረገድ የዐማራው ምሁራን ፊታውራሪዎች ሆነው፣ የአሁኑን እና ተከታዩን የዐማራ ትውልድ ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግ ግዴታ አለባቸው። ምንጊዜም ቢሆን የአኖሌ ሐውልት የተገነባው ዐማራውን ለማጥፋት ለተጀመረው አዲስ ዙር የጅምላ ጭፍጨፋ ዘመቻ የጥሪ ደወል መሆኑን ዐማራው ሊጠራጠር አይገባም።

አብረሃ ደስታ በአዲግራት ድብደባ ተፈጸመበት






Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele
አብረሃ ደስታ
(ECADF) አብረሃ ደስታ ፌስቡክን በመጠቀም ከመቀሌ (ትግራይ) በሚያሰራጫቸው ወቅታዊ መረጃዎች፣ የፖለቲካ ትንታኔዎች እና ዜናዎች በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ አብዝቶ ይታወቃል። የአረና-ትግራይ ፖለቲካ ፓርቲ አባል እንደመሆኑ ደግሞ የፓርቲውን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ይዘግባል።
ሰሞኑን እንደተለመደው ዓረና እና መድረክ በዓጋመ (አዲግራት) ጥር 18 ስለሚያካሂዱት ህዝባዊ ስብሰባ እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር፣
ዓረና መድረክ ከዓጋመ (ዓዲግራት) ህዝብ ጋር በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለመወያየት ለእሁድ ጥር 18, 2006 ዓም በዓዲግራት ህዝባዊ አዳራሽ (ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ) ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል…
የአብረሃ ቀጣይ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ በተቃዋሚዎች ህዝባዊ ስብሰባ መጥራት የተሸበሩት ህወሀቶች የስብሰባው ቀን ከመድረሱ በፊት እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ነበር፣
ዓረና ፓርቲ በዓዲግራት ከተማ ለእሁድ ከጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ጋር በተያያዘ ዛሬ ዓርብ ሁለት የዓረና አመራር አባላት (አቶ ዓምዶምና መምህር ገብረጨርቆስ) በዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ፖሊስ ታስረዋል። የታሰሩበት ምክንያት ህዝብ በስብሰባ እንዲሳተፍ ቀስቅሳችኋል የሚል ነው። ህወሓቶች በተምቤን የፈሩትን ያህል በዓጋመ ፈርተዋል። በተምቤን ተመሳሳይ የእስር ሁኔታ አጋጥሞናል። ስብሰባ ፈቅደው ስለ ስብሰባው ህዝብ እንዳይሰማ ግን ከለከሉ። ይገርማል።
በማግስቱ አብረሃ ደስታ እና ታጋይ ጓደኞቹ በህወሀት ቅጥረኛ ወንጀለኞች፣ በፖሊሶች እና በከተማው አስተዳዳሪዎች ፊት ከፍተኛ ድብደባ ተካሄደባቸው። ሁኔታውን አብረሃ እንዲህ በማለት ገልጾታል፣

We are attacked by TPLF mercenary gangsters in front of administrators and police officers in Adigrat.
ሌሎች መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ አብረሃ ደስታን ጨምሮ አቶ አሰግድ ገብረስላሴ እና አቶ አምዶም ገብረስላሴም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፣ ከድብደባው በኋላ ሁሉም ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስደው ምርመራ የተደረገባቸው ሲሆን አቶ አሰግድ እና አቶ አምዶም ህክምና ለማግኘት ወደ ሆስፒታል መሄዳቸው ታውቋል።

Wednesday, January 15, 2014

ይህን አንብባችሁ ዝም አትበሉ ይህን መልዕክት ለሌላው በማስተላለፍ ተባበሩ:: !

3ኛ ወንጀል ችሎት በእኔ ላይ ፍርድ ሲሰጥ የተሰማኝን ሃዘንና ባዶነት የትኛውም ኢትዮጵያዊ ድጋሚ እንዲሰማው አልሻም ::በፈጣሪ እርዳታ ከእድሜም ልክ በላይ ምት ቢፈርዱብኝም ለምቀበል ተዘጋጅቼ ነበር :: ይሁንና ይኼን ያህል የሚያስፈርድ ወንጅል ቀርቶ አንድ ምሽት ወህኒ የሚያሳድር ወንጀል ባለመስራቴ ህሊናዬ ፍፁም እረፍት ይስማዋል ::እንዲህ አይነት ” የፍትህ ስርዓት ” ያለባት ሃገር ልጅ መሆኔ ግን የሃፍረት ማቅ አከናንቦኛል:: ዳኞቹ አሳዘኑኝም ፤ አሳፈርኝም::

ያም ሆነ ይህ እኔና እኔን መሰል ስዎች ያልሆነውን ሆናችሁ ተብለን የምንገፍው የመከራ ህይወት በኢትዮጵያችን የነፃነት ቀን እንዲጠባ የሚረዳ ክሆነ ፤ የሚከፈለው መስዋዕትነት ቢያንስ እንጂ ፈጽሞ አይበዛም:: በትውልድና በታሪክ ፊት ለከበረ ነፃነት ሲባል ዋጋ መክፈል ተመርቆ መፈጠር እንጂ ከቶም አለመታደል አይሆንም:: የልጆቻችንና የሚስቶቻችንም ስብራት ሁላችንም የምንኮራባት ሀገር ስትኖረን ያን ግዜ ይጠግን ይሆናል ::
ዛሬ ግን በዚች ሀገር የፍትህ ስርዓት አለን ብለን መናገር ፈጽሞ የማንችልበት ደረጃ ላይ እንገኛለን :: እንደዚህ ዘመን ፍትህ መሬት ላይ ተጥሎ የተዘበተበት ዘመን ይኖር ይሆን ? ፍርድ ቤቶቻችን የፍትህ መባ የሚፈታባቸው ምኩራቦች እስኪሆኑ ድረስ አበክረን ልንታገል ይገባል:: ይኽንን የነፃነት ብርሃን የሚናፍቅ ህዝብ በልበ ሙሉነትም የሚታገል ትውልድ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል:: ለመታግል ገዠዎችን መፍራት አያስፈልግም:: በተላይ ወጣቱ ለነገዋ ሀገሩ ዛሬ በእውነትና በልበ ሙሉነት ይቁምላት :: የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ከልብ የማይሰራ የኢህአዴግ አመራር ከፕለቲካ ሜዳው በአስቸኳይ ሊወጣ ይገባዋል፤ በተቃዋሚ ጎራውም ይኽን መሰል አስተሳሰብ ያለው ወገን ካለ መንገዱን ይልቀቅ:: ከዚህ በላይ ኢ-ፍትሐዊነትንና ኢ-ሰብአዊነትን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያሰፈኑ ሊቀጥሉ አይችሉም፤ ለፍትህ ለወንድማማችነትና ለነፃነት መንገዱን መልቀቅ አለባቸው:: በእኔ እይታ ሁሉንም የድርድር በሮች ዘግቶ የምላችሁን ብቻ ተቀበሉ ለሚል ጠቅላይ አገዛዝ መታዘዝ በሽታው እንዲብስበት ማድረግ ብቻ ነው :: ዘላቂ መፍትሄው ደግሞ በየግዜው የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈሉ ከእውነትና ነፃነት ጋር መቆም ብቻ ነው::
በቃልቲ እስር ቤት የሚገኘው አቶ አንዱዓለም አራጌ ዋለ ” ያልተሄደበት መንገድ ” መጽሐፍ የተወሰደ
Image

የአፍሪካው ልዑል የተሰኘውን መጽኃፍ በሬዲዩ ፋና መተረኩ ተቃውሞ ገጠመው

ኢሳት ዜና :- በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በመተረክ ላይ ባለው በታጋይ መዝሙር ፈንቴ ተርጓሚኒት  በአቶ ዳንኤል ግዛው ጸኃፊነት የቀረበው መጽሀፍ  በአማራ ህዝብ  ላይ  ጥላቻ እንዲፈጠር እያደረገ ነው በማለት የብአዴን አባላት ተቃውመውታል።

አባላቱ በብር ሸለቆ በመካሄድ ላይ ባለው ስልጠና ላይ  እንደተናገሩት ሬዲዩ ፋና ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ነው ፡፡ “የህውሃት ድብቅ አላማ እውን እየሆነ ነው” ያሉት ፤ መካከለኛ እና ታዳጊ የብአዴን አመራሮች ፤ ከደቡብ ወንድሞቻችን ጋር ታሪክን በማሳሳት እና በማጥላላት የትውልድ ጠላትነትን አስፍቶ አሁንም የህውሃት የበላይነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው በማለት በጽኑ ተቃውመውታል።
ጥያቄው የቀረበላቸው  የኢህአዴግ የስልጠና ዋና ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ “መፅሃፉ እየተተረከ መሆኑን በፍጽም አላውቅም” ያሉ ሲሆን ፣ ምላሹን አጣርተው እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡ የመጽሃፉ ትረካ ባሰቸኳይ እንዲቆም የጠየቁት አመራሮች ፣ ፋና ራዲዮን መስማት ማቆማቸውንም ለአቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡ የመለያየት ፖለቲካው  መርዛማነት እያሰቃየን ነው ሲሉም አባላቱ አክለዋል፡፡
ከቀናት በሁዋላ ወደ ተለያዩ አካላት  በመደወል መረጃ ያሰባሰቡት አቶ አዲሱ ለገሰ፣ ” ሃይለማርያም እንደፈረመበት እና  ፍቅር እስከ መቃብር ሲል እንዳወደሰው”  በማሾፍ መልክ መናገራቸውንና  ከፋና ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረው ” የመጽሃፉ ትረካ ቢቋረጥ በሬዲዩ ጣቢያው ላይ የሚፈጥረው ችግር ታይቶ ቢያንስ ቢያንስ የአድማጭ አስተያየት ባለመቀበል ልናጠፋው እንሞክራለን” ሲሉ መልስ እንደሰጡዋቸውና ሰልጣኞችን ለማረጋገት እንደሞከሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ “መጽኃፉን አንብቤ እከታተለዋለሁ” ያሉት አቶ አዲሱ፣ ስህተቱ መፈፀም የለበትም ሲሉ አክለዋል፡
“ስህተቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሁቱና ቱትሲ አይነት ግጭት የሚፈጥር ነው” ያሉት አባላቱ፣ ከደቡብ ወንድሞቻችን ጋር የሚፈፀም ቅራኔን አንፈልገውም” ሲሉ ለአቶ አዲሱ ገልጸውላቸዋል።
ሟቹ ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊና አቶ በረከት ስምኦን መጽሀፉ እንዲታተም ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ነበር ያሉት ምንጮች፣ ሬዲዮ ፋናም የሩዋንዳውን የራዲዮ ሚሊኮልን ስራ እየሰራ ነው ሲሉ” ተቃውመውታል።

“የህዝባዊ አንድነትና ኃይል የወያኔ ሕወሐት ማጥፊያ መድሃኒት”

ከሮባ ጳዉሎስ


ካለመታደል ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።


በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።

ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።

Monday, January 13, 2014

የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ግልፅ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል

 



Ethiopia map


በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከተካተቱት ንዑስ አርዕስቶች ውስጥ -
  • የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀጣይ እርምጃ ምን መምሰል ይገባዋል?
  • የኢትዮጵያ የቅርብ ወቅታዊ ተግዳሮት ምንድን ነው?
  • የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ህዝብን የሚንጥ እና ሚልዮኖችን ከጎናቸው የሚያሰልፍ የፖለቲካ ራዕይ ለሕዝቡ ማሳየት ለምን አልቻሉም?
እና ሌሎችም…
መግቢያ 
ኢትዮጵያን ውክፕድያ በድህረ ገፁ ላይ እንዲህ ይገልፃታል:-
”ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ርዕሰ ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ ዓመት የሚያንስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ ነገሥታት እና ንግሥተ ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።” ይላል
ወግ አጥባቂ የአረብ መንግሥታት እና ፍላጎታቸው
የዛሬ ሰላሳ ሰባት አመት በምዕራቡ አለም የተከፈተው የቀዝቃዛው ጦርነት እጅግ በተፋፋመበት፣ የኢትዮጵያ አብዮት ተጠምዞም ይሁን በጥቂት የወቅቱ ‘ልሂቃን’ ለደርግ በቀረበ ሃሳብ ወደ ሶሻሊዝም ስርዓት ሀገሪቱን ለማስገባት በሚውተረተርበት፣በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን ክፍል በወቅቱ ከሶቭየት ህብረት ባገኘው የመሳርያ ድጋፍ የተመካው የሱማልያ-ዚያድባሬ መንግስት የኢትዮጵያን መሬት በኃይል የወረረበት ወቅት ነበር። በእዚህ ጊዜ ነበር የ’ፋይናንሻል ታይምስ’ ጋዜጣ የአፍሪካ ቀንድን ፖለቲካ ከቀዝቃዛው ጦርነት በዘለለ እይታ የሚያመላክት አንድ ፅሁፍ ይዞ የወጣው። ፅሁፉ እንዲህ የሚል ነበር:-
“በወግ አጥባቂ የአረብ መንግሥታት በሳውድ አረብያ ቀንደኛነት በግብፅ፣ ሱዳን እና ሶርያን ጨምሮ በቀይባሕር እና በአካባቢው ሃገራት የአረብ ወይንም የእስልምና መንግሥታት እንዲመሰርቱ የሚደረጉ ጥረቶች አሉ።’’
“the conservative Arab states, marshalled by Saudi Arabia and including Egypt, Sudan and Syria, want to create a band of Arab or Muslim states along the shores of the Red Sea and its approaches.” (Financial Times May 2, 1977)
የ ሶስት ሚልዮን ሕዝብ አናሳነት  በፖለቲካ ስሌት አንፃር 
ከሱማልያ ጎን ቆማ የቀዝቃዛውን ጦርነት ትዋጋ የነበረችው ሶቭየት ህብረት (የዛሬዋ ሩስያ) ከቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ መውረድ በኃላ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ለማዞር አፍታም አልቆየችም። ለእዚህ ውሳኔ ካበቃት ጉዳይ አንዱ የኢትዮጵያ ስልታዊ ጠቀሜታ ዘለቄታዊ ጥቅሟን የሚያረጋግጥባቸውን ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነበር።እነኚህም ኢትዮጵያ በአካባቢው ያላት በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ መካከል እንደ ድልድይ የምትጠቅም ብቸኛ መሬት መሆኗ እና በሕዝብ ብዛትም ሆነ በተፈጥሮ ሃብቷ ከአካባቢው ሃገራት የምታማልል መሆኗ ነበር። በሕዝብ ብዛት አንፃር ካላት ጠቀሜታ አንፃር ሶቭየት ህብረት ኢትዮጵያን እንደምትመርጥ የገለፀችበትን ሰነድ የሚያመላክተው አሁንም ከዛሬ ሰላሳ ሰባት አመት በፊት እ ኤ አቆጣጠር ግንቦት 14/1977 ዓም በሱማልያ የሶቭየት ህብረት አምባሳደር የተናገሩትን  ’ዘ ኢኮኖሚስት’ መፅሄት እንዲህ ፅፎት ነበር:-

አጼ ምኒልክ መልካም መሪ አልነበሩም የሚሉ ካሉ መብታቸው ነው” – ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት

“አጼ ምኒልክ መልካም መሪ አልነበሩም የሚሉ ካሉ መብታቸው ነው” – ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ከሕብር ራድዮ ጋር ቃል የተመላለሱት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ‘አጼ ምኒልክ መልካም መሪ አልነበሩም የሚሉ ካሉ መብታቸው ነው፤ እኛ አጼ ምኒልክን እየዘከርን ያለነው በሃገር ግምባታ ላይ ባደረጉት መልካም ነገር ነው” አሉ። ኢንጂነሩ “አጼ ምኒልክን መልአክ ናቸው ብለን ታቦት ባናስቀርጽም ለአፍሪካ ሕዝብ ነፃነት ....

የኢትዮጵያና የግብፅ ድርድር - ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ



የኢትዮጵያና የግብፅ ድርድር - ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ






















በአሁኑ ወቅት 30 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀውና በሦስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ፣ ‹‹ቴክኒካዊ›› በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ድርድሮች እየተደረጉ ነው፡፡

በእያንዳንዱ ድርድር ከሚስተዋሉ አቋሞች ግን ለዘመናት የቆዩ ሴራዎች መልካቸውን ቀይረው እየመጡ ይመስላል፡፡

በታላቁ የዓባይ ግድብ ላይ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ጥናት ውጤት የያዘው ሪፖርት አሁን እየተደረጉ ላሉት ድርድሮች መሠረት የሚጥል ነው፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው፣ የግድቡ ግንባታ እንዲቋረጥ ምንም መሠረታዊ ምክንያት ባለመኖሩ፣ በተቻለ መጠን በታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ላይ ሊያስከትለው የሚችለው የውኃ ፍሰት መጠን መቀነስና ቴክኒካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሦስቱም አገሮች ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በጋራ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው ነው፡፡ በተረፈ የግድቡ ግንባታ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ሪፖርቱ አጽንኦት ይሰጣል፡፡

የግብፅ ዥንጉርጉር አቋሞች

ኢትዮጵያና ሱዳን ሪፖርቱን በፀጋ የተቀበሉት በመሆናቸው ሚስጥርነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይም የሚቻላቸውን ጥረት አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ግብፅ በሪፖርቱ ላይ የተዘበራረቀ አቋም እያንፀባረቀች በመሆንዋ ሪፖርቱ ይፋ በሆነበት ወቅት በተጠራው ብሔራዊ ምክክር፣ በተለይ የግብፅ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ ጦር ኃይሉ እንዲዘምት ድምፃቸው ተሰምቷል፡፡ ግብፅ ባጋጠማት ቀውስ ምክንያት እየተደረጉ ያሉት የባለሥልጣናት መቀያየር የግብፅ መንግሥት አቋም ለትንተና የማይመች ቢሆንም፣ አንዱ የሌላውን ስህተት እየደገመ ይመስላል፡፡ አንዱ ከሌላው ስህተት እየተማረ አይመስልም፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የሽግግር መንግሥት ከአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታ ጊዜ በኋላ የተባረረውን የፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ መንግሥት በኢትዮጵያና በዓባይ ግድብ ላይ የተለሳለሰ አቋም መያዙ ለውድቀቱ ምክንያት መሆኑን እየተናገረ ነው፡፡

Sunday, January 12, 2014

የባለሥልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አያልቅም እንዴ?


የሃብታቸው መጠን ይፋ የሚደረገው ከስልጣን ሲወርዱ ይሆን? (ያመለጡን አሉ!)
በሃብት ምዝገባው ላይ የትዳር አጋርም ሊካተት ይገባል (መነጣጠቅ ተጀምሯላ!)
“Grand corruption” አለ የሚባለው ገንዘብ ሚኒስቴር ሲዘረፍ ነው እንዴ?
የእነቴሌ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት “ፅድቁ ቀርቶብኝ–” ያሰኛል!
ኢትዮ- ቴሌኮም በየበዓሉ የሚልከው የ “እንኳን አደረሳችሁ” መልካም ምኞት አሁን አሁን “ሙስና” እየመሰለኝ መጥቷል፡፡(ግራንድ ኮራፕሽን ሳይሆን ሚጢጢዬ ሙስና!) ለነገሩ ቢመስለኝም እኮ አይፈረድብኝም፡፡ ለምን መሰላችሁ? ዓመቱን ሙሉ በብዙ የአገልግሎት አሰጣጦች ችግር ሲያማርረን ከርሞ — በዓል ሲደርስ እንደ ደህና አገልጋይ “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን ሊደልለን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? (“ደለለኝ — ደለለኝ” ነው ያለችው ድምፃዊቷ) ነፍሷን ይማረውና! እውነቴን እኮ ነው… ኔትዎርክ ሳይኖር፣ ኢንተርኔት ተቋርጦ፣ የቢሮና የቤት ስልክ ጠፍቶ… እንዴት ነው “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን? (ያውም ለእኛ አሻፈረኝ በሚለን ኔትዎርክ!) እኔ የምለው —- እኛና ቴሌ የምንተዋወቀው በስልክ አገልግሎት አይደለም እንዴ? (ከዚያ ውጭ የት ስንተዋወቅ ነው!) ከሁሉም የሚገርመኝ ደሞ ”ከመጪው ዘመን ጋር አገናኛችኋለሁ” የሚለው ፉከራው ነው፡፡ (“ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” አሉ!) እንኳንስ ከመጪው ዘመን… ከዛሬ ጋር እንኳን መች ተገናኘን! (ማን ነበር “አቅምን አውቆ ማደር ጥሩ ነው ታላቅ ችሎታ ነው” ያለው?!) አሁንማ ከምንፈልገው ሰው ጋር መገናኘት አይደለም— ሂሳብ ለመሙላትም ኔትዎርክ ማግኘት መከራ ሆኗል (ቴሌኮም በነፃም እንኳን ገንዘብ አልቀበልም እያለን እኮ ነው!) እስካሁን የውሃና የመብራት መ/ቤቶች ለገና በዓል “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት አለማለታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምናልባት ሳልሰማቸው ብለውን ከሆነ ግን የእነሱንም ከ“ሙስና” ለይቼ አላየውም፡፡ ለምን ብትሉ… ገንዘብ የምንከፍልበትን ዋናውን አገልግሎት በቅጡ ሳናገኝ በየበዓሉ “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት ለእኔ ተራ መደለያ ነው፡፡
(የመረረው ደንበኛ አታውቁም!?) ለነገሩ እዚህ አገር እኮ ቀድመው የሚናደዱት አገልግሎት ሰጪዎቹ እንጂ ደንበኞች አይደሉም፡፡ እኛ ደህና አገልግሎት የሚሰጠን አጣን ብለን ከመናደዳችን በፊት እነሱ ቀድመውን ይናደዱብናል (“ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ” አለች አስቱ!) እናላችሁ—የበዓላት ጊዜው ድለላ ቀርቶብን አንዴም ክፍያው ተቋርጦ የማያውቀውን የውሃና የመብራት አገልግሎት ሳይቆራረጥ፤ሳይጠፋ እናገኝ ዘንድ ለብዙ መቶኛ ጊዜ እንማጠናለን፡፡ (“Where is my beef?” አለ ፈረንጅ!) ምን እንደሚገርመኝ ታውቃላችሁ? ሦስቱም የመንግስት ተቋማት ለአገልግሎታቸው መቋረጥ የሚሰጡት ሰበብ ሁሌም ተመሳሳይ ነው – እንደሰነፍ ተማሪ እየተኮራረጁ፡፡ (አዲስ ሰበብ መፍጠር ሮኬት ሳይንስ ሆነ እንዴ?) እናላችሁ —- ውሃም መብራትም ኔትዎርክም የሚጠፉትና የሚቆራረጡት በ“ልማቱ” የተነሳ ነው፡፡ መብራት ለምን ይቋረጣል? ግድቦች እየተሰሩ ስለሆነ! ኔትዎርክ ለምን ይጠፋል? ኔትዎርክ እየተስፋፋ በመሆኑ! ውሃ ለምን ትጠፋለች? አዲስ የውሃ መስመር እየተዘረጋ ነዋ! ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ታገደ? ልማቱን ለማፋጠን! እኔ የምለው ግን —- ነባሩ አገልግሎት ሳይቋረጥ፣ እኛም ሳንማረር — ልማቱን ማስፋፋት እንዴት አቀበት ይሆንብናል? ሳስበው ግን አቀበት ሆኖብን አይመስለኝም፡፡ በልማት ሰበብ የስንፍናን ካባ ደርበን ለሽ ስላልን ነው፡፡

Saturday, January 11, 2014

ኢሕኣዴግ ከግንቦት ሰባት ጋር ተቆራኝተዋል ያላቸውን አባሎቹን ሊያባርር ነው:: ‪ ጦር ሰራዊቱ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ሊያደርግ ነው:

‪‬

ሕወሓት መራሹ ገዢ መደብ ኢሕኣዴግ በድርጅቱ ውስጥ ባደረገው ውስጣዊ ጥናት እና ግምገማ መሰረት ከተቃዋሚው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ቁርኝት አላቸው ግንኙነት ፈጥረዋል ለዲሞክራሲያዊ ስርኣቱ እንቅፋት ሆነዋል የድርጅቱን መረጃ አቀብለዋል ያላቸውን አባሎቹን ሊያባርር መሆኑን ከአዲስ አበባ የኢሕኣዴግ ጽ/ቤት የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል::
በዚሁም መሰረት የተደረገው ውስጣዊ ጥናት እና ግምገማ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ የተገኘ ማስረጃን መሰረት በማድረግ የሚባረሩትን አባላት እና ከተባረሩ በኋላ ሊወሰድባቸው የሚገባ እርምጃ እየተጠና መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጦር ሰራዊቱ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል::ከሻለቃ ማእረግ ጀምሮ ወደላይ እስከ ጄኔራሎች ድረስ የሚደረገው ግምገማ አጀንዳው ሙስናን ያጠቃል/አያጠቃል ባይታወቅም በዚህ ሰሞን በሕወሓቱ ጄኔራል ሳሞራ ቢሮ የተሰበሰቡት ጄኔራሎች በከፍተኛ መኮንኖች ላይ ግምገማ እንዲደረግ መወሰናቸው ሲታወቅ በግምገማው ላይ የሚገመገሙ መኮንኖች ስም ዝርዝር እንዲዘጋጅ ለወታደራዊ ደህንነት ክፍል ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ስም ዝርዝራቸው ያልተጠቀሱ መኮንኖች እንደማይገመገሙ ሆኖም እንደሚገመግሙ ታውቋል::ምኒልክ ሳልሳዊ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ እና የኢትዮጵያ ምህዳር ጋዜጣ አዘጋጆች ለውሣኔ ተቀጠሩ


በህገመንግስቱ ላይ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት፣ የህዝብን ሃሳብ በማናወጥ እና “ጨፍጫፊ” በማለት የመንግስትን መልካም ስሙን በማጥፋት የተከሰሰው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ በመከላከያ ማስረጃነት ያቀረበው የቢቢሲ ዶክመንተሪ ፊልም፣ የቢቢሲ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ሲል ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለውሣኔ ቀጥሯል፡፡

ተከሳሹ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ቢቢሲ ያዘጋጀው ነው በሚል በመከላከያ ማስረጃነት የቀረበው የድምጽ ምስል ዶክመንተሪ ፊልም በእርግጥም የቢቢሲ ስለመሆኑ ጥያቄ በማስነሳቱ ከጣቢያው ሃላፊዎች ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ቀደም ባለው ቀጠሮ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠው፡፡ ከትናንት በስቲያ በዋለው ችሎት የተከሳሽ ጠበቃ ለፍ/ቤት እንዳስረዱት፤ ማረጋገጫውን ለማግኘት ከቢቢሲ ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ጠቁመው ለዚህኛው ቀጠሮ ሊደርስላቸው ባለመቻሉ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሠጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ቀደም ሲል በአቃቤ ህግ የቀረበበትን ማስረጃ ይከላከሉልኛል ያላቸውን የሰው ምስክሮች ለፍ/ቤቱ ከማሰማቱም በተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ መከራከሩ ይታወሳል፡፡

Friday, January 10, 2014

የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም!


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የብሔራዊ ደህንነት መረጃ እና የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል የጋራ ኃይል አድርጎ ራሱን የሚጠራ አካል የዜጎችንና የተቋማትን ሕገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ መብት በመጣስ ጥፋተኝነታቸው በፍርድ ቤት ሳይወሰን ወንጀለኛ ሲያደርጋቸውና ስማቸውን ሲያጎድፍ ማየት እየተለመደ የመጣ ተደጋጋሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ተቋማት ተውጣጥቶም ይሁን ተቀናጅቶ የሚሰራ አካል በተደጋጋሚ ጊዜ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በመክሰስ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ እያደረገ ጉዳያቸው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ እንደፈለገ በሚቆጣጠረው ወይም በሚያዘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አማካኝነት የፈለገውን ዓይነት ፍረጃና ሥም ማጥፋት ሲያካሒድባቸው ቆይቷል፡፡
ይህ ራሱን ከሕግ በላይ የሰቀለ አካል ያለምንም ገደብ ከሚሰራቸው ተግባራት እንዲታቀብ በሕግ የሚያስቆመው በመጥፋቱ እስካሁን የፈፀማቸውን የማንአለብኝነት ተግባራት እንደጥፋት ሳይሆን እንደ መልካም ሥራ ቆጥሯቸው በተመሳሳይ የሥም ማጥፋትና የፍረጃ ተግባሩ እንዲገፋበት አድርጎታል፡፡ በዚሁም መሰረት ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባስተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ፕሮፓጋንዳ አሸባሪ ያላቸውን ድርጅቶችና ግለሰቦች አድርሰውታል ያለውን ጥፋት በዝርዝር አቅርቧል፡፡ ፓርቲያችንን በዚሁ ዘገባ ከተጠቀሱት “አሸባሪ” ድርጅቶች ጋር በማገናኘት ስም ለማጉደፍና ለማስፈራራት የተደረገውን መፍጨርጨር አይተናል፣ ሰምተናል፣ ተገርመናል በመጨረሻም አዝነናል፡፡
በዘጋቢ ፊልሙ የቀረቡ ፓርቲያችንን የማይመለከቱ ጉዳዮችን ትተን ከፓርቲያችን ጋር በማገናኘት የተጠቀሰው “ኢሳት” የተባለ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለትና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ የመገናኛ ብዙሃን እንዳንጠቀም የማስጠንቀቂያ ዛቻ ተላልፎልናል፡፡ ይህ አስፈራሪ አካል ራሱን ሕግ አውጭና ሕግ ተርጓሚ በማድረግ የፈለገውን አካል ለመፈረጅ፣ ለመክሰስና ለመፍረድ ሥልጣኑን ከየት እንዳገኘ የማይታወቅ ሲሆን የዚህች ሐገር ዜጎችም ሃሳባችንን የምንገልፅበትንና የማንገልፅበትን የመገናኛ ብዙሃን እየመረጠልንና እየወሰነልን ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲህ ዓይነቱን የእብሪት መልዕክት ከተራ ርካሽ ፕሮፓጋንዳነት የማያልፍ የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ገደብን ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ነው ብሎ ያምናል፡፡
የገዥው ቡድን ሰዎች ሀሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እንደማይችሉ ስለሚያውቁት የቀራቸው አማራጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሃሳባቸውን የሚያሰራጩባቸውን መንገዶች መዝጋት ብቻ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ ነገር ግን ማንም አካል በሕግም ሆነ በሞራል ተጠያቂ የሚሆነው የሚያስተላልፈው መልዕክት ይዘት የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ መሆን አለመሆኑ እንጂ ገዥው ቡድን በጠላው ወይም በወደደው የመገናኛ ብዙሃን መልዕክቱን ማስተላለፍ አይደለም፡፡ መልዕክትን የገዥው ቡድን ሰዎች በጠሉት የመገናኛ ብዙሃን ማስተላለፍ በራሱ ወንጀለኛ ወይም ሽብርተኛ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም ዓይነት የሕግ መሰረት የለም፡፡ ማንም መልዕክት የሚያስተላልፍ አካል የሚያሰራጨው ሃሳብ የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ ከሆነ መልዕክቱ የተላለፈበት መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ይሁን ሌላ ህጋዊ የተባለ የመገናኛ ብዙሃን መሆኑ ብቻ መልዕክት አስተላላፊውን አካል ከተጠያቂነት ሊያድን እንደማይችልም ለማንም የተሰወረ ይሆናል የሚል እምነት የለንም፡፡
በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም እንዲወስንለት የማይፈልግ መሆኑን ግልፅ እያደረገ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ማንም ሰው በመረጠው መንገድ ሃሳቡን የማስተላለፍ መብቱን በመጠቀም በኢሳትም ሆነ እድሉን ካገኘ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቋሙንና እምነቱን ማስተላለፍ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይወዳል፡፡ በዚሁ አጋጣሚም የፓርቲያችንን መልካም ስም በሃሰት ለማጉደፍ የተሰነዘሩ ቃላትን በቀላሉ የማንመለከታቸው መሆኑን ሕግ ባለበት ሐገር ራስን ከሕግ በላይ በማስቀመጥ ማንንም አካል መፈረጅና ስም ማጉደፍ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የዘጋቢ ፊልሙ ባለቤቶች እንዲያውቁትና ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡