Thursday, March 6, 2014

በመንግስት ታጣቂው በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ባልና ሚስት ፎቶ ተገኘ




እብሪተኛ የመንግስት ታጣቂዎች ለሚቀጥፉት የሰው ህይወት መንግስት ተጠያቂ የሚሆነው መቼ ነው?ከዳዊት ሰለሞን
የመንግስት ታጣቂዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ደማቸው በትንሽ በትልቁ እየፈላ ሲቪል ዜጎችን የሚጨርሱበት አጋጣሚ ከቀን ቀን እየጨመረ ነው፡፡
የባህር ዳሩን ዘግናኝ እልቂት ለጥቆ ቂርቆስ ቤ/ክ አካባቢ ሁለት ሰዎችን በጥይት በመምታት የወሲብ ደምበኛው እንደነበረች የተነገረላትን ሴት ሲገድል አብሯት የነበረውን ማቁሰሉ አይዘነጋም፡፡የታክሲ ሹፌሩ አልጭንህም ስላለው የታጠቀውን ሽጉጥ በመምዘዝ ለፍቶ አዳሪውን በአጭር አስቀርቶታል፣አራት ኪሎ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በሚሄድ መኪና የተርከፈከፈ ጥይት ስንቱን እንዳስቀረ እግዜር ይወቀው ፡፡በየአካባቢው እንዲህ አይነት ዘግናኝ ዜናዎችን መስማት አዲስ አይደለም፡፡
ከትናንት በስቲያ በላፍቶ ክፍለ ከተማ አቦ ማዞሪያ አካባቢ በምስሉ የምትመለከቷቸውን የሶስት ልጆች ወላጆች እብሪተኛው ታጣቂ በጥይት በመደብደብ ገድሏቸዋል፡፡ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡እሰየው ነው ፡፡ግን በቃ?እነዚያን ሶስት ህጻናት ማን ነው የሚያሳድጋቸው?ግለሰቡን አምኖ ክላሽ ያስታጠቀው አካል የማይጠየቀውስ እስከመቼ ነው?
መንግስት የመኪና አሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ እንዲገቡ እያስገደደ መሆኑ በመኪኖቹ አደጋ ለሚደርስበት ሰው አንዳች ነገር ነውና ይበረታታል፡፡መንግስት በነካ እጁ የሚያስታጥቃቸው ሰዎች ለሚያደርሱት የመብት ጥሰት ኢንሹራንስ ይግባ!!!በእኔ እምነት ስለ ተገደሉት ወላጆችና ወላጅ አልባ ስለሆኑት ልጆች መጮህ የሁላችንም ግዴታ ነው።

Tuesday, March 4, 2014

ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ


ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮች በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮችን በመሰብሰብ “አንድነት ፓርቲ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀታችን ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች በጊዜ በግምገማ ካልተራገፉ ቀጣዩ ምርጫ ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡” ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ምንጮቹ ጨምረው እንደተናገሩት ኢህአዴግ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀቱን የሚያስተባብሩ ከፍተኛ ካድሬዎችን አንድ-ለ-ሰላሳ ማደራጀት መጀመሩን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች አሉ በመባሉ ካድሬዎች እርስ በእርስ መሰላለል እና አለመተማመን ጀምረዋል፡፡ ይህ በካድሬዎቻቸው መካከል የተጠፈጠረው ትርምስ ያሰጋቸው የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት አመራሮች ለክፍለ ከተማ አመራሮቻቸው አንድነት ሊይዝብን የሚችለው 30 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ነው የተቀረውን በኮንዶሚኒየም ፣ በአነስተኛ ጥቃቅንና በየአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀት ይዘነዋል ብለዋቸዋል፡፡
ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መረጃ የሰጡት የስብሰባው ተሳታፊዎች «750ሺ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ፣ 30ሺ የኮንዶሚኒየም እጣ ተጠባባቂዎች ኢህአዴግን ነው የሚመርጡት» በሚል ከመድረክ የቀረበው መደምደሚያ እንዳላሳመናቸውም ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን በሚመለከት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የደረሰው ዶክሜንት እንደሚያስረዳው ፓርቲው የአዲስ አበባ አደረጃጀቱን ኢህአዴግ በዘረጋው ልክ 138 ያደረሰ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም የወረዳ ደረጃና የሴል አደረጃጀቶቹን በኢህአዴግ የአደረጃጀት ቁጥር ልክ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያመለክታል፡፡

እስክንደር የጻፈው ለነጻነት ነው፤ የሞራል ድፍረት ያለው ነው – ጆን ኬሪ


ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ሽብርተኛ ነህ በሚል መስረት የሌለዉ ክስ ተከሶ የ18 አመት እስራት ፣ በፖለቲካ ዉሳኔ እንደተፈረደበት ይታወቃል። የአሜሪካው የዊጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሄን ይቃወማሉ። ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን፣ ለነጻነቱ የጻፈ ሲሉ፣ ከሌሎች አንጋፋ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እኩል አስቀምጠዉታል።
1394241_527514827333456_269824761_n
የጆን ኬሪ ይፋዊ ዘለፋ፣ የጋዜጠኛ እስክንደር ሆነ የሌሎች በርካታ ጋዜጠኞችና የሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መታሰር፣ ኢሕአዴግ በአገሩ ካሉ ዜጎቹ ጋር ብቻ ሳይሆን ከበርካታ የአለም አቀፍ ማህበረሰብና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር እንዲጋጭ እያደረገዉ እንዳለ የሚያመላክት ነው።
አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት ዋና ደጋፊ እንደሆነች ይታወቃል። በርካታ የአገዛዙ ቱባ ቱባ ባለስልጣናር በአሜሪካ ቤት ያላቸው፣ በአሜሪካ ባንኮች ገንዘብ የሚያሰቀምጡ እንደሆነ ይነገራል። በአመት ከ370 ሚሊዮን ዶር እርዳታም አሜሪካ ለኢትዮጵያ እንደምትሰጥ ይታወቃል።
በአምባሳደሯ ወይም በስቴት ዲፓርትመንት በአፍሪካ ጉዳይ ሃላፊ ደረጃ ሳይሆን፣ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደረጃ የነ እስክንደር ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት፣ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ጆን ኬሪ፣ በአደባባይ እስክንደርን መጥቀሳቸው፣ ምን ያህል በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ከላይ ያሉ የአሜሪካ ባለስልጣናት እያሳሰበ እንዳለ የሚያሳይ ነው።
ጆን ኬሪ የሚከተለውን ነበር ያሉት፡
“The truth is that some of the greatest accomplishments in expanding the cause of human rights have come not because of legislative decree or judicial fiat, but they came through the awesomely courageous acts of individuals, whether it is Xu Zhiyong fighting the government transparency that he desires to see in China, or Ales Byalyatski, who is demanding justice and transparency and accountability in Belarus, whether it is Angel Yunier Remon Arzuaga, who is rapping for greater political freedom in Cuba, or Eskinder Nega, who is writing for freedom of expression in Ethiopia, every single one of these people are demonstrating a brand of moral courage that we need now more than ever.”

Monday, March 3, 2014

የታመቀው ሮሮ ፈንድቶ ዛሬ በሽሚሲ ሁከት ነግሷል ! (ከነብዩ ሲራክ)


* የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለወገኖቻችሁ ድረሱላቸው!
* ተጸወእኖ ፈጣሪዎችም እታድክሙን ፣ ሂዱና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ!
ሰሞኑን ከጅዳው የሽሜሲ ጊዜያዊ የእስር ማቆያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለወራት በእስር ተንገላታን ሲሉ የመረረ ሮሯቸውን ገለጹልኝ ። ሮሯቸወ ሰሚ ማጣቱን አምርረው የገለጹልኝ ወገኖች ከእኔ አልፎ ተርፎ ለጀርመን ራዲዮ የዝግጅት ክፍል ሳይቀር ምሬት ሮሯቸውን ማስተላለፋቸውን ገልጸውልኛል።Nebiyu Sirak
ዛሬ ረፋድ ላይም በተንቀሳቃሽ ስልኬ ደውለው እጃችሁን ስጡ ተብለው በሰጡ እየደረሰባቸው ያለው መጉላላት በመክበዱ ወደ የሞት ሽረት አድርገው ቁርጡን ለማወቅ እንደሚገደዱና ይህንንም ” ለጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና ለአለም ድምጻችን አሰማልን !” ሲሉ እያለቀሱ ሃሳባቸውን ሲያስረዱኝ መጭውን ለመገመት አዳጋች አልነበረም!
የግፉአኑ የአደራ ቃል አለብኝና ስልኬን እንደዘጋሁ ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ወደ ተጠባባቂው ቆንስል ጀኔራል ሸሪፍ ከይሩ ደወልኩ ። ስልካቸው ይጠራል ግን አያነሱትም! ደጋግሜ ደወልኩ መልስ የለም … ተስፋ ሰንቄ ወደ ሌላኛዋ የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሃላፊ ወደ ቆንስል ሙንትሃ ደወልኩበ። እርሳቸውም አያነሱም! ደጋገምኩት ፣ መልስ ግን የለም ! የሚያዝ የሚጨበጥ ማጣት እንዴት ያማል?
ከሰአታት በኋላ እኩለ ቀን ከዚያው ከሽሜሲ ተደውሎለወኝ ስልኩን ሳነሳው የሰው ጫጫታ ፣ እሪታ ፣ አኡኡታና የጥይት ድምጽ ሰማሁ … ደዋዩን ወንድም ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ? አልኩት “መረረን ፣ ድረሱልን አልን ፣ የሚሰማን አጣን ፣ እስር ቤቱን ሰብረን ወጣን !” አለኝ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ መለሰልኝ … ከዚያን ሰአት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ከሽሜሲ የሚደርሰኝ መረጃ ደስ አይልም ! የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በአካባቢው የተገኙ ቢሆንም መፍትሄ ማምጣት ግን የቻሉ አይመስልም !

የደሴ ሕዝብ በኢሕኣዴግ የግዳጅ መዋጮ ተማሯል::በደሴ ወንጀል በመበርከቱ የሰአት እላፊ ገደብ ተጥሏል:: በከተማዋ ፌዴራል ፖሊሶች በምሽት ወታደራዊ ልምምድ ያደርጋሉ::


የደሴ ሕዝብ ከመለስ ፋውንዴሽን ጋር በተያያዘ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈለግበታል::

 ከደሴ የሚደርሱኝ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በሕወሓት አዛዥነት በብኣዴን ሰብሳቢነት የመለስ ዜናዊን አመራር አካዳሚ ሕንጻን ለመገንባት የመለስ ፋውንዴሽን ከህዝቡ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚጠበቅበት እና ለግንባታው የግዴታ አስታውጾ እንዲያደርግ እያስገደዱት መሆኑን እና ሕዝቡም ከኑሮ ውድነት ጎን ለጎን ከአፉ ላይ ሊጎርሰውን ያዘጋጀውን በጉልበተኞች እየተነጠቀ መሆኑን በማማረር አቤቱታውን ማሰማቱን የደሴ የለውጥ ሃዋርያ ወጣቶች አንድነት ለምንሊክ ሳልሳዊ በላከው መረጃ ገልጽዋል::

መረጃዎቹ እንደጠቆሙት የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት በሁሉም ክፍለከተሞች ባሉ የወያኔ ካቢኔዎች ሲሆን እያንዳንዱ የካቢኔ አባል በግል እንዲሰበስብ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ የተሰጠው ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ለሰበሰበ ሽልማት ስለሚሰጠው የሚል ቅል ስለተገባላቸው የስልታን እና የደሞዝ እድገት ለማግኘት እና ታማኝነታቸውን ለማረጋገጥ በሽፍን ድጋፍ ሕዝቡን በግዳጅ እና በማስፈራራት በዛቻ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያደረጉት ሲሆን ይህንን በተመለከተ ሕዝቡ በቤቱ አሊያም በስብሰባ ካልተገኘ በቅጣት ሁሉ መልክ ተጨማሪ እንዲከፍል ይደረጋል የሉት የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ሕዝቡ በሚሄድበት መስሪያቤት አሊያም ስብሰባ ቀደም ብሎ የከፈለ ሰው ደረሰኙን ካልያዘ ጉዳዩን ለማስፈጸም በድጋሚ እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን እረስቸዋለሁ ሄጄ ላምጣ የሚል ነገር ተቀባይነት የለውም::

Sunday, March 2, 2014

ጥፋተኛ ጥፋቱን በይቅርታ እንጂ በዉሸትና በዕብሪት መሸፈን አይችልም


በቅርቡ አንድም የወያኔ ጌቶቹን ለማስደሰት ደግሞም ከህወሃት ካድሬዎች ስድብና ግልምጫ የማያድን ጎደሎ ስልጣን ለማግኘት ሲል ተወልዶ ያደገበትንና እመራዋለሁ የሚለዉን የአማራን ህዝብ ክብርና ታሪክ ያጎደፈዉና ያዋረደዉ የአለምነዉ መኮንን አስጸያፊ ንግግር በአለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንን ያስቆጣና ያነሳሳ ጉዳይ ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል። ይህ የአማራን ህዝብ ማንነትና ይህ ጀግና ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ያለዉን አኩሪ ቦታ ያላገናዘበና ባልተሞረደ አንደበት የተነገረ አስጸያፊ ንግግር ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተዉን የአማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩትን በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን አስቆጥቷል። አይናቸዉ ከገንዘብና ከሥልጣን ዉጭ ሌላ ምንም ነገር የማይመለከት ለሆዳቸዉ ብቻ ያደሩ ሰዎች የተከፈተ ሆዳቸዉንና ማለቂያ የሌለዉ የሥልጣን ጥማታቸዉን ለማርካት ሲሉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ ወያኔ በሥልጣን ላይ የቆየባቸዉ ያለፉት ሃያ ሦስት አመታት በግልጽ አሳይተዉናል። ሆኖም ግን አይናቸዉ የታወረና ጭንቅላታቸዉ ባዶ የሆነ ሰዎች በነገሱበት በወያኔ ስርዐት ዉስጥም ቢሆን የሚጠሉትን፤ የሚንቁትንና የገዛ ወገኖቹን የገቡበት ቦታ ሁሉ እየተከተሉ ወደ አገራችሁ ግቡ እያሉ የሚያፈናቅሉ ዘረኞችን ለማስደስት ሲል ስቃይ የበዛበትን የራሱን ህዝብ ያዋረደ ከሀዲና ሂሊና ቢስ ሰዉ ያየነዉ አንድ አለምነዉ መኮንንን ብቻ ነዉ። አለምነዉ የተናገራቸዉን አጥንት የሚሰብሩ የንቀት ቃላት ይሀንን ከንቱ ሰዉ ባወገዝን ቁጥር እየደጋገምን ብንጠቅስ በአንድ በኩል የወያኔን ዘረኞች አላማ ያራምዳል ብለን ስለምናምን በሌላ በኩል ደግሞ እንደዚህ አይነቱን ጸያፍ ንግግር መደጋገም ሂሊናችን ስለማይፈቅድንና የጠፈፈ ቁስል መቆስቆስ ይሆናል ብለን ስለምንሰጋም ንግግሩን አንደግመዉም።
አሜሪካንን በመሳሰሉና በዕድገት ወደፊት በገፉ አገሮች ዉስጥ ዉሻ የሚታወቀዉ የሰዉ ልጅ ታማኝ ወዳጅ በመባል ነዉ። ዉሻ ባለቤቱን ለማስደስት ጭራዉን ከመቁላት ባሻገር የባለቤቱን እግር ይልሳል፤ ይንበረከካል፤ እግር ስር ይተኛል፤ ደግሞም አምጣ ብለዉ የወረወሩለትን ነገር እየሮጠ ሄዶ ያመጣል። የሚገርመዉ እንስሳዉ ዉሻ እንኳን እነዚህን ነገሮች ሁሉ የሚያደርገዉ ለባለቤቱና ለለመደዉ ወዳጁ እንጂ ለሌላ ለማንም ሰዉ አያደርግም። ዉሻ ባለቤቱንና ወዳጁን በተለይ ደግሞ የሱንና የባለቤቱን ጠላቶች ለይቶ ያዉቃል፤ ስለዚህም ዉሻን ባለቤትህን ንከስ ብለን ያንን የሚወደዉን ስጋ ያሻንን ያክል ብናሸክመዉ እኛዉ ላይ መልሶ ይጮህብን እንደሆነ ነዉ እንጁ ዉሻ ባለቤቱን በፍጹም አይነክሰም።

በኖርዌይ የሚኖሩትን ኢትዮጵያን ስደተኞችን የአኖኖር ሁኔታ በሚመለከት ህዝባዊ ውይይት እና የኢሳት ምሽት ፕሮግራም በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ተካሄደ (በገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ)

በኖርዌይ ከተማ ኦስሎ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች በኖርዌይ የሚኖሩትን ኢትዮጵያን  ስደተኞችን የአኖኖር ሁኔታ በሚመለከት   ሐሙስ የካቲት20,2006 ዓ ም  በአንድ ላይ በመሰብሰብ ውይይት እና ምክክር አድርገዋል :: ስብሰባው በኖርዌይ የስደተተኛ ማህበር የተዘጋጀ ሲሆን በስብሰባው  ላይ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ እና በኦስሎ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የተሳተፉ ሲሆን የኢሳት ጋዜጠኛ የሆኑት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ጋር በመሆን በኖርዌይ ያሉ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ እንዲሁም ለስደት ያበቋቸውን ምክንያቶች በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፥፥

   በስብሰባውም ኢትዮጵያኖች በሀገራቸው እንዳይኖሩ የወያኔ መንግስት በሚያደርስባቸው ጫና እና በደል ሀገራቸውን ጥለው ቢሰደዱም ነገር ግን ኖርዌይ ከገቡ በኋላም የኖርዌይ መንግስት የኢትዮጵያኖችን የፓለቲካ ጥገኝነት በሚገባ እንደማያየው እና እንደማይቀበለው በየጊዜው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተለያየ ጫና እንደሚያደርስባቸው በሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን  በስብሰባው ላይ ከነበሩት ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች እና የየእራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ እና ኖርዌይ ከገቡ ጀምሮ በሕይወታቸው ያለፈውን እና እየኖሩ ያለው ኑሮ ምን እንደሚመስል እንዲሁም ለስደት ያበቋቸውን ምክንያቶች በተመለከተ ውይይት አድርገዋል  ::

 አንዳንድ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከሀገር እየወጡ  ኖርዌይ ገብተው የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ወረቀት ካገኙ በኋላ ወይም ፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ መስለው ትንሽ ጊዜ በመቆየት ካዛም በገዛ ፍቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ እና  በኢትዮጵያ መንግስትም ምንም አይነት በደል እንዳልደረሰባቸው የኖርዌይ መንግስት እንደሚያውቅ ከዚህም የተነሳ ሌሎች ኢትዮጵያን ስደተኞ ላይ ወደ የፓለቲካ ጥገኝነት እንደማይቀበል ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱም የኖርዌይ መንግስት የተለያየ ጫና እንደሚያደርስባቸው በስብሰባው ከነበሩ ተሳታፊዎች የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን  እንደነዚህ አይነት ሰዎች በመጀመሪያ ወደ ኖርዌይ የሚመጡበት ምክንያት እንዳላቸው እና ምክንያታቸውም  በኖርዌይ የሚኖሩትን እውነተኛ የወያኔ ተቃዋሚዎ ችን ለመሰለል እና ለማደን ሲሆን  እንደነዚህ አይነት ሰዎችን እንዳሉ እና እንደሚያውቆቸው ነገር ግን ኢትዮጵያውን እነዚህ የወያኔ ሰላዮች መፍራት እንደሌለባቸው ይህንንም ለኖርዌይ የስደተኞችን ጉዳይ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት utlendingsnemnda (UNE) በተለያየ ጊዜ መሳወቃቸውን በስብሰባው ላይ ተገልጾል ::

በስብሰባው ላይ በመገኛት በኖርዌይ ያሉ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ ምን እንደሚመስል ጥያቄ ሲጠይቁት የነበሩት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ኖርዌይ በሚኖሩት ኢትዮጵያኖች በሚያደርጉት ትግል ወይም እንቅስቃሴ በጣም እንደሚደሰቱ እና እንደሚደነቁ በመናገር ማንኛውንም ማድረግ ያለባቸውን እና ማድረግ የሚችሉትን  ነገሮች በማድረግ ከጎናቸው በመቆም አብራቸው እንደሚሰሩ ቃል ገብተውላቸዋል::

Friday, February 28, 2014

በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቹ መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጠረ

Image

“ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል።” ጄኔራል ሳሞራ የኑስ
ከሳምንታት በፊት ራሱን የአማራ ክልል ብሎ በሚጠራው የክልል አምባገነን ጁንታ አስተዳዳሪ ነኝ የሚለው የብኣዴን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አለምነህ መኮንን በድርጅቱ የውይይት መድረክ ላይ የአማራውን ህዝብ ለሃጫም እና ልጋጋም እንዲሁም መርዝ ብሎ መሳደቡን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ የውጪ እና የውስጥ ተቃውሞ በየአቅጣጫው እየተነሱ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል::
ሰሞኑን በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቻቸው መካከል ግለሰቡን የተመለከተ አለመግባባት መከሰቱን እና ጥያቄዎች ከአባላቱ በስፋት እየመጡ መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ጠቅሰው የአዲስ አበባ እና አከባቢው የድርጅቱ ካድሬዎች ግለሰቡ እና ሁኔታው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል እስከማለት ደርሰዋል:: ይህንን ለመናገር የፈለገው ለምንድን ነው ተልእኮውስ ምንድነው? በሌላው ብሄር ላይ ይህ ነገር ቢነገር የድርጅታችን እርምጃ ምን ይሆን ነበር? ግለሰቡ በህግ ሊጠየቅ ይገባል::የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተጠየቁ ቢሆንም አመራሮቹ እስካሁን መልስ ከመስጠት ይልቅ ኢዲሞክራሲይዊ በሆነ መንገድ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ በማስፋት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ጸረ-… እያሉ ጠያቄዎችን በመወንጀል እና ዋናውን ክትትላቸው ያደረጉት ድምጹን ቀድቶ ማን አውጣው የሚለውን የማይመለስ ጥያቄ ይዘው አደና ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ከድርጅቱ አንዳንድ ካድሬዎች እንደሚሰማው የድምጹን ቅጂ ያወጡት የሕወሓት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ እና ሕወሓትን በጥርጣሬ የሚይስቡ እንዲሁም ግንቦት ሰባት ናችሁ ብለው እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚፈልጉትን የብኣዴን ካድሬዎች ለመዋጥ የተደረገ ሴራ ነው::በድርጅታችን ውስጥ የማይበጁትን አንጠባጥቦ የራሱን ለመሰግሰግ ያሰረው ሕወሓት መንገድ አገኘ ቢሉም በለላ ወገን ደግሞ በድርጅቱ የተማረሩ እና የለውጥ ፍላጎት ያላቸው የብአደን አመራሮች አሹልከው ያወጡት እንደሆነ ይነገራል።ካድሬዎቹ ክፉና ደጉን እንድንለይ ላደረገን ኢሳት ቴሌቭዥን ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተደምጠዋል:: በአመራሮቹ እና በካድሬዎቹ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በዚሁ ከቀጠለ አቶ አለምነህ የድርጅት ስራ ብቻ እንዲሰሩ ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት እና በክልሉ ላይ የተሰጣቸውን ስልጣን ለስም ብቻ እንዲቀመጥ የሚደረግ እንደሚሆን እና ቀስ በቀስ ከድርጅቱ ገፍቶ በማስወጣት አምባሳደር አድርጎ መሾም የሚሉ አስተያየቶች ከድርጅቱ አከባቢ ተደምጠዋል::
=============================================
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የብሄር ተዋፅኦን እና የመኮንኖች ቅነሳን በተመለከተ ከፍተኛ የሆነ ክርክር መነሳቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ ከሆነ በዚህ ሰሞን በተካሄዱ ተከታታይ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ በአንድ ብሄር በተሰበሰቡ ጄኔራሎች የተሞላ ነው: የመኮንኖች ቅነሳ ለምን አስፈለገ? ለምንስ አማራው እና ኦሮሞው ላይ አተኮረ ?ሰራዊቱ እና ቤተሰቡ በኑሮ ውድነት እየዋተተ ነው ከፍተኛ መኮንኖች በሙስና ተዘፍቀዋል ህገመንግስቱ አልተተገበረም የሚሉ የህዝብ አቤቱታዎች ተበራክተዋል … የሚሉ በሰራዊቱ ውስጥ ተጠንቷል ተብለው በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ ክርክር እና ውይይት የተደረጉ ቢሆንም በሕወሓት ጄኔራሎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንዲሁም ሞራልም ያልጠበቁ ስድቦች ካለውጤት እንደተበተኑ ምንጭኦቹ ገልጸዋል::
የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው ያሉት ጄኔራል ሳሞራ ጥያቄውን የፓርቲ ስብሰባ እስኪመስል ድረስ ጮኽውበታል::በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል::
የሰራዊቱ መኮንኖችን ቅነሳ በተመለከተ የማይታጠፍ እቅድ ስለሆነ ተግብርዊ ይሆናል ያሉት ሳሞራ ብሄር ለይተን ያደረግነው ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና የመከላከያ ሰራዊቱ ተጠንቶ የሚወሰድ ኢርምጃ ነው ብለዋል::ለሰራዊቱ የምናደርገው ድጎማ የለም::ያልተመቸው ካለ ሰራዊቱን መሰናበት ይሽላል ሲሉ በቁጣ የመለሱ ሲሆን ሙስና የሚባለው ማስረጃ ያለው ሄዶ ሊከስ ይሽላል ከዚህ ውጭእ ስም ማጥፋት ነው ሲሉ ተደምጠዋል :;ህገመንግስቱን እና መንግስታዊ ስርኣትን በተመለከተ መልካም አስተዳደር እና ልማት ስለሰፈነ ቢዚህ ልይ ምተኮር ስፈላጊ አይደለም ብለዋል:: ከሰራዊቱ አባልት መሃል ገብተን ያስጠናነው ጥያቄ ነው እየተወይየንበት ያሉትን ሰነድ በተመለከተ ማንም የጦር መኮንን አስተያየት ያልሰጠበት እና ያልጠየቀ ሲሆን ሁሉም በዝምታ በማዳመጥ ሳይወያይ መስማማት አለመስማማቱን ሳይገልጽ የተነገረውን እንደ መመሪያ ተቀብሎት መውጣቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::



አቡጊዳ – የአድዋ በዓል እንዳይከበር ኢሕአዴግ መሰናክል እየፈጠረ ነው

አንድነት/መኢአድ እና ትብብር፣ በጋራ የአድዋ ድልን ለማክበር ከአንድነት ጽ/ቤት ጀመሮ እስከ ጊዮርጊስ የእግር ጉዞ እንደሚያደርጉ፣ በሚኒሊክ ሃዉልት ሥርም አበባ እንደሚያስቀምጡ በመግለጽ ፣ በሕጉ መሰረት ፖሊስ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ቢያሳዉቁም፣ ኢሕአዴግ በሚቆጣጠረዉ የአዲስ አበበ አስተዳደር አማካኝነት «በዓሉ በብሄራዊ ደረጃ ስለሚከበር ማስተናገድ አንችልም» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

addis_council
ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ በብሄራዊ ደረጃ የአድዋ በዓል፣ በኢሕአዴግ ዘመን፣ ከዚህ በፊት የተከበረበት ሁኔታ ብዙ እንዳለነበረ ይታወቃል። አገዛዙም አሁን በምን መልኩ በዓሉን ለማክበር እንዳቀደ ያሳወቀው አንዳች ነገር የሌለ ሲሆን፣ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ሌሎች ሲዘጋጁ፣ አብሮ ተቀላቅሎ ማክበር እንጂ ፣ መሰናክል መሆን እንዳልነበረበት ብዙዎች ይናገራሉ።
«አድዋን ለማክበር ስለፈለገ አይደለም። አገዝዙ መሰናክል እየፈጠረ ያለው» ያሉን በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ፣ በአዲስ አበባ ሰልፍ መደረጉ ስለሚያስፈራው እንደሆነ ይናገራሉ። «የአንድነት ፓርቲ በሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች መዋቅር አለው። በተጨማሪ መኢአድ እንዲሁም የአሥር ድርጅቶች ስብስብ የሆነው ትብብር አብረዉት አሉ። ስለዚህ አንድነት በሚጠራቸዉ ስልፎችና ስብሰባዎች ብዙዎች እንደሚገኙ የታወቀ ነዉ » ያሉት እኝህ ተንታኝ «ቢሆንም እስከአሁን በአንድነት በየቦታዉ የተደረጉ ሰልፎች ሁሉ ሰላማዊ ነበሩ። አንዲት ጠጠር አልተወረወር፣ የጠፋ ሕይወት፣ የወደመ ንብረት የለም። ሰልፈኛው በሰላም ወጥጦ ነው በሰላም የተመለሰው» ሲሉ የሕዝቡ ሰላማዊነት በማስረዳት አገዛዙ መፍራት እንደሌለበት የናገራሉ።
የአንድነት ፓርቲ ከዚህ በኋላ ምን አይነት ምላሽ እንደሚሰጥ የሚገልጽ መረጃ እስከአሁን አልደረሰንም።

Thursday, February 27, 2014

Ethiopian Airlines Co-pilot case: Interview with Attorney Shakespear Fey...


በአሜሪካ ሲያትል የሚገኝ እሳት የላሰ ኢትዮጰያዊ ጠበቃ አለ። ሼክስፒር ፈይሳ ይባላል። የረዳት አብራሪ
ሃይለመድን አበራ ጉዳይ ከህግ አንጻር ምን ይመስላል የሚለውን የኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ ውየም
ከረንት አፌርስ አሁንም ውይም ኢካድኤፎች አነጋግረውት ነበር። 
ረዳት አብራሪው ጠለፋ አድርጓል ማለት አይቻልም…
ሃይለመድን ነገሩን ያደረገው ጤናው ታውኮ ከሆነ አየር መንገዱ ተጠያቂ ነው…
አበራሪው ለደህንነቴ ሰጋሁ ብሎ ያደረገውን ማድረጉ ወንጀል አይደለም፤ ሰዎች ደህንነታችውን መጠበቅ መብታቸው ብቻ ሳይሆን ህጋዊ ግዴታም አለባቸው…
ሃይለመድን ቅጣት የሚያከብድበት ሰው ላይ ጉዳት አድርሶ ቢሆን ነበር…
እና ሌሎችንም ሃሳቦችን ያነሳል። ያነጋገረው እንደልቡ ነው። በዚህ ቃል ምልልስ ጠበቃ ሼክስፒር ለአብራሪ ሃይለመድን
አበራ የህግ ድጋፍ ለመስጥት ተነሳሽነትም አሳይቷል (የሀገር ልጅ የማር እጅ ብለን እያሞካሻን!) ከኢካድ ኤፎች ዩቲብ የጠለፍናትን ቃል ምልልስ እንሆ በድረ ገጻችን፤



በአዲስ አበባ ራሱን ያጠፋው የ24 ዓመቱ የጥበቃ ሠራተኛ ከኪሱ ደብዳቤ ተገኘ

bole

ባለፈው የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም በቦሌ አካባቢ አንድ የጥበቃ ሠራተኛ 3 ጊዜ ጥይት ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን እንዳጠፋ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ዘግበን፤ ለምን ራሱን ሊያጠፋ እንደቻለ የሚገልጽ መረጃ አለመገኘቱን ዘግበን ነበር። በአዲስ አበባ ከተማ ታትሞ የሚወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ እንደገለጸው ሟች በሱፈቃድ በጋሻው ራሱን ለማጥፋት የወሰነበት ደብዳቤ በኪሱ ተገኝቷል፤ ሲል ዘግቧል። ሟች ጊዜውን ባይጠቅሰውም በተወለደበት አካባቢ ነዳጅ የጫነ ተሳቢ ፍሬን ተበጥሶ ከሞት ማምለጡን፣ መሞት ካለበት ደግሞ ራሱን በራሱ ማጥፋት እንዳለበት መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፎ በኪሱ መገኘቱ ተዘግቧል።

የሪፖርተር ዘገባ እንደወረደ፦

በአዲስ አበባ ራሱን ያጠፋው የ24 ዓመቱ የጥበቃ ሠራተኛ ከኪሱ ደብዳቤ ተገኘ

በባንኩ አሠራር አንድ የጥበቃ አባል 24 ሰዓት ሠርቶ 24 ሰዓታት የሚያርፍ በመሆኑ፣ ሟች በሱፈቃድም የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት አዳሪ ጓደኛውን ከቀየረ በኋላ፣ ባንኩን ለመጠበቅ የቻለው ለ24 ሰዓታት ሳይሆን ለሰባት ሰዓታት ብቻ ነው፡፡ ወጣቱ ‹‹ኑሮ መሮኛል›› በማለት እያማረረ እያለ በመሀል የያዘውን ጠመንጃ ቃታ በመሳብ አንድ ጊዜ ወደ ላይ ሲተኩስ፣ አብረውት የነበሩ ሴት ፈታሽና ሌሎች የባንኩ ተጠቃሚዎች በመደናገጥ ወደ ውስጥና ወደ ውጭ ሽሽት ይጀምራሉ፡፡ ሁለተኛውን ጥይት በመተኮስ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ በኩል በፍጥነት መራመድ መቀጠሉን በሥፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

Sunday, February 23, 2014

የባህር ዳር ህዝብ ሆ ብሎ ወጣ!! ህዝቡ “ከባዶ ጭንቅላት… ባዶ እግር ይሻላል፡፡” አለ

የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ የብአዴኑ ምክትል ሊቀመንበር አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ በመናቅ እና በመሳደብ የተናገሩት ቃል ነው:: አማራውን… “በባዶ እግሩ እየሄደ ሌላውን ይንቃል” ካሉ በኋላ ለአማራው የሚቆረቆሩትን ደግሞ “ለሃጫቸውን…” እና የመሳሰሉትን እዚህ ላይ ለመጻፍ የምንጸየፋቸውን ቃላቶች ጭምር በመጠቀም አሽሙር አይሉት ስድብ ሰንዝረዋል:: ነገሩ ከአንድ የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ወይም እመራለሁ ከሚል ሰው የሚጠበቅ ባለመሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፣ አናዷልም::

በመሆኑም የአንድነት እና የመኢአድ ፓርቲዎች በጥምረት ሆነው በባህር ዳር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ወሰኑ:: ምክትሉ ሊቀመንበሩ ከሰልፉ በፊት እንደበፊቱ በት እቢት ተወጥረው ሳይሆን ረጋ ብለው ምን ለማለት እንደፈለጉ ቢያስረዱም ህዝቡ ግን ተቃውሞውን ቀጠለበት:: ለነገሩ በዚህ አጋጣሚ ሌሎች የሚነሱ የህዝብ ብሶቶች እንዳይነሱ በመስጋት የክልሉ አስተዳዳሪዎች አንዳንድ እንቅፋቶችን ለመፍጠር መሞከራቸው አልቀረም:: እርግጥ ነው… ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የተቃውሞ ሰልፉን ለማድረግ ሲዘጋጁ ብዙ እክል ገጥሟቸው ነበር:: ከተማ ውስጥ በራሪ ወረቀት መስጠት እና ቅስቀሳ ማድረግ ጭምር ተክልክለዋል:: ሆኖም ህዝቡ ራሱ ከልካዮቹን በመቃወሙ የፖሊሶቹ እገታ እና ጫና በረድ አለ:: ተቃዋሚዎቹ በባዶ እግር መሄድ ማለት ምንም ማለት እንዳልሆነ ለማሳየት ቅስቀሳ ሲያደርጉም ሆነ ዛሬ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ… ጫማቸውን አውልቀው በባዶ እግራቸው ነበር የታዩት::
bahrdar demo13 2232014
ዛሬ እሁድ… እ.ኢ.አ የካቲት 16, 2006 ባህር ዳር ቀበሌ 12፣ ግሽ አባይ በሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ ሰልፉ ሲጀመር የተለያዩ መፈክሮች እየተደመጡ ነው፡፡ በሰልፉ የፊት ረድፍ ላይ የፓርቲው ሊቀ መንበር ኢንጂነር ግዛቸው፣ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ እና ሌሎችም አመራሮች ከህዝቡ ጋር ሆነው ታይተዋል:: ከግሽ አባይ የተነሳው ሰልፈኛ ጉዞውን በባህር ዳር ጎዳናዎች ላይ ማድረግ ሲጀምር ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ የከተማው ነዋሪዎች ሰልፈኛውን ተቀላቅለዋል:: የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የያዙ ወጣቶች ከፊት ሆነው መፈክር በማሰማት ከተማዋን ከጠዋት እንቅልፏ አባነኗት:: የባህር ዳሩን የተቃውሞ ሰልፍ የአንድነት ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ፣ የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከፊት በመምራት ላይ ይገኙ ነበር:: bahrdar demo7 2232014
ከባህር ዳር በደረሰን ዘገባ መሰረት… ህጻናት ልጆቻቸውን በጀርባቸው ያዘሉ፣ በዊልቼይር የሚሄዱ፣ አዛውንቶች፣ ወጣቶች በአንድነት ሆነው በባህርዳር ከተማ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ bahrdar demo9 2232014 ሰልፉ ከመጠናቀቁ በፊት ቁጥራቸው 15 ሺህ ያህል ሰዎች እንደነበሩ ነው ከስፍራው የተዘገበው:: በወቅቱ ከተያዙት መፈክሮች የተወሰኑት… “የመሬት ቅርምቱ ያብቃ!” “ህዝብን ከርስቱ ማፈናቀል ይቁም” “ገበሬው በገዛ መሬቱ ስደተኛ አይሆንም” “የህዝብን ክብር የደፈሩት አቶ አለምነው ለፍርድ ይቅረቡ” “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” “ህዝብን እየሰደቡ መግዛት አይቻልም” “ድል የህዝብ ነው” “አቶ አለምነው የሰደቡት የአማራን ህዝብ ብቻ አይደለም” “ብአዴን /ኢህአዴግ የአማራን ህዝብ የመምራት የሞራል ልእልና የለውም”
ከስፍራው ሁኔታውን እየተከታተለ በቀጥታ ሲዘግብ የነበረው ነብዩ ሃይሉ እንደገለጸው ከሆነ… በሰልፉ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር ለሰልፈኛው ተለቆ ህዝቡ ንግግሩን በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን እያሰማ ነው፡፡ “ክብራችንን የደፈሩት የብአዴን አባላት ለፍርድ ይቅረቡ” “ነፃነታችን በእጃችን ነው” “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል፡፡” “ብአዴን የአማራን ህዝብ ለመምራት የሞራል ልዕልና የለውም” “መተማ የኛ ነው፣ ቋራ የኛ ነው” በሰልፉ ላይ ከተስተጋቡ መፈክሮች መሀከል ይገኝበታል፡፡ ሰልፉ በህዝብ እንደታጀበ ቀጥሏል፡፡

Saturday, February 22, 2014

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ጠረፍ ግጭት ተቀሰቀሰ! 71 ኢትዮጵያውያን ሞቱ! “ድረሱልን” እያሉ ነው!


ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ሲሉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ገለጹ::
ከመተማ ቀጥላ በምትገኘዉ ባሶንዳ በምትባለዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማና አካባቢ በኢትዮጵያዉን ሽፍቶችና በሱዳን ሽፍቶች መካከል የተነሳዉን ግጭት ተከትሎ አራት ሱዳናዉያን በመሞታቸዉ ሳብያ ለብቀላ የተነሱት ሱዳናዉያን ታጣቂ ሐይላት ኢትዮጵያዉይንን በጅምላ እየገደሉ ነዉ አገር ወገን ይድረስልን ሲሉ ወደ ሱዳን በመተማ በኩል የገቡ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተጣሩ ነዉ።
አራት ሱዳናዉያን ስለሞቱ በመቶ ኢትዮጵያዊ ነዉ የምንበቀለዉ ያሉት ሱዳናዉያን እስከ አሁን 77 ኢትዮጵያዉይንን መገደላቸዉን በኩራት ይናገራሉ ያሉት ኢትዮጵያዉያን የአብዛኛዎቹ ሟቾች መቃብር የማታወቅ መሆኑንም ይናገራሉ። በየጫካዉ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን አስክሬናቸዉ ለዱር አራዊት መወርወሩን የሚገልጹት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሌላ 42 ኢትዮጵያዉያን የተቀበሩበት መቃበር መኖሩንም ይጠቁማሉ፤ ይህ መቃብር ግን ከሞቱት 77 ሰዎች ጋር የሚያገናኘዉ ነገር ይኑር አይኑር የሚያዉቁት ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ ።
በህዳር 24/2006 የሱዳኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አህመድ አልቀርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሱዳንና ኢትዮጵያ ያላቸዉን የድንበር ልዩነት አስወግደዉ መስማማታቸዉን ይፋ አድርገዋል። ይህንንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ለስራ ጉብኝት አቅንተዋል። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኡመር ሐሰን አልበሽር ሁለቱ አገራት በጥበቃ፣በደህንንነት፣ ህገወጥ የሰዉና የ አደንዛዥ እጽ ዝዉዉርን ለመግታት መስማማታቸዉን ገልጸዋል። በሱዳኗ ባሶንዳ የኢትዮጵያዉያን በጅምላ መገደል ከዚሁ የደህንነት ስጋት ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ባይታወቅም ሱዳናን ኢትዮጵያ ግድያዉን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት እንዳላደረጉ ከጥቃቱ የተረፉ ኢትዮጵያዉያን ያስረዳሉ ።
በየካቲት 11/2006 ህወሃት የተመሰረተበትን 39ኛ አመት ለማክበር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ልዩ የክብር እንግዳ ሆነዉ መቐሌ ድረስ መምጣታቸዉ ታዉቋል። የሁለቱ አገራት መሪዎች ስለ ቀድሞ ስማእታት ቢናገሩም ወደ ሱዳን በኢኮኖሚ ሳቢያ ተሰደዉ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያዉያን ምንም ያሉት ነገር አልነበረም። በባሶንዳ ሱዳን ኢትዮጵያዉያን ነጥሎ የማጥቃቱ ዘመቻ እንደቀጠለ ነዉ! ኢትዮጵያዉያን ወገን ይድረስልን ሲሉም ይጣራሉ።

ሰበር ዜና!! አንድነት ለትግል በወጣበት የመድረክ አባል ፓርቲዎች አገዱት


የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ማገዳቸውን ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው የመድረኩ 9ኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ አሳውቀዋል፡፡ በጉባኤው አንድነትን ወክለው የተሳተፉት መካከል የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ሆኑት አቶ ተክሌ በቀለ ለፍኖተ ነጻነት እንዳስታወቁት የመድረክ አባል ፓርቲ የሆኑት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና በፕ/ር በየነ የሚመራው የኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ አንድነት ከመድረክ እንዲባረር ቢጠይቁም አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ አንድነት ላልተወሰነ እንዲታገድ የሚል ሞሽን አቅርቦ በጉባኤው ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
አቶ ተክሌ በቀለ የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑባቸው ምክንያዎች አስገራሚ መሆናቸውን ጠቅሰው “የመድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነትን ለማገድ የወሰኑት በቅርቡ በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አንድነት መድረክ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ጋር ውህደት እንዲፈፀም መወሰኑን፣ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮችም ውህደት እንደሚያስፈልግ በተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸውን፣ የአንድነት ፓርቲ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ድጋፍ ሰጪዎች በመድረክ ስም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ ትብብር አያደርጉም በሚልና ከመድረክ ዕውቅና ውጪ መስከረም 19(ሰላማዊ ሰልፉ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ የማጠቃለያ መርሀ ግብር ነው፡፡) በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡” የሚሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ አክለውም አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ አቶ ተክሌ መድረክ የራሱን ዕቅድ አውጥቶ በቁርጠኝነት የማይሰራ በመሆኑ አንድነት በተናጠልና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተለያዩ ስራዎችን መስራቱን ጠቅሰው “በተደጋጋሚ ለመድረክ በዕቅድ የተደገፉ እንቅስቃሴዎችን በማቅረብ በጋራ እንዲሰራ ቢጠይቅም ቀና ምላሽ አግኝቶ አያውቅም፡፡ ይልቁኑም የራሱን ጥፋት በአንድነት ላይ ለማላከክ ይሞክራል ” ብለዋል፡፡

በተጠለፈው አውሮፕላን ውስጥ የነበረው ኢትዮጵያዊ እማኝነት



“የተሳፋሪው ፍላጎት የሆነ መሬት ላይ ማረፍ ብቻ  ነበር”

በሃዋሳ ከተማ በተለምዶ ኬሮ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተወልዶ ያደገው ወጣት ምህረቱ ገብሬ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቀድሞው ሀዋሳ ኮምቦኒ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ነው የተከታተለው። የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና የመሰናዶ ትምህርቱንም በቅዱስ ዳንኤል ኮምቦኒ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ት/ቤት አጠናቋል። ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2001 ዓ.ም በሲቪል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ካገኘ በኋላም፤ እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ በመቀጠልም ነጻ የትምህርት ዕድል በማግኘት፣ ወደ ጣሊያን አምርቶ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡

በቅርቡ ለእረፍት ወደ አገሩ የመጣውና በሃዋሳ ቆይቶ ወደ ጣሊያን ለመመለስ አውሮፕላን የተሳፈረው ምህረቱ፣ ባለፈው ሰኞ በረዳት አብራሪው ተጠልፎ ጄኔቭ እንዲያርፍ በተደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት 200 ገደማ ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት በጣሊያን የሚገኘው ምህረቱ፣ የጠለፋውን አጋጣሚ በተመለከተ ጋዜጠኛ አንተነህ  ይግዛው በኢ-ሜይል ለላከለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሽ  እንደሚከተለው አጠናቅረን አቅርበነዋል፡፡ 

Thursday, February 20, 2014

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን


አቶ አልምነው

አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤
እኚያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ውጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤
አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???
ሁለትኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!
ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤  ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!

ወያኔን የሚጠላ ብቻ እየተመረጠ የሚያብድባት ሀገር



በአንድ ወቅት የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፈን ወደ አንድ የአእምሮ ህመምተኞች ሆስፒታል ለመጎብኝት ያመራሉ:: በመጀመሪያ ያገኛቸው የአእምሮ ህመምተኛ አቀባበል ያደረገላቸው እንዲህ በሚል ነበር
“የባለቤትዎን የ22 ዓመት የስራ ውጤት ለመጎብኘት እንኳን ደህና መጡ::” መራር እውነት ያለው ቀልድ::
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወያኔ የተባለው የስብስብ ቡድን በአመራሩ ተማረው ከህዝብ ወግነው ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር ብለውጥያቄና ተቃውሞ የሚያነሱ የህዝብ ወገኖችን በተለያዩ መንገድአሳንሶ ለማየት የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች እየተጋለጡና እያሳጡት ከመጡ ሰነባበቱ:: የቅርብ ጊዜውን እንኳን ብናስታውስ የመምህር የኔሰው ገብሬን ሰላማዊ የተቃውሞ መስዋዕትነት አጣጥሎና አሳንሶ ለማየት በአእምሮ ህመምተኝነት በተለያዩ እፅች ተጠቃሚነት መወንጀሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ያለውን የአፈናና የጭቆና ስርዓት በሞያው መስዋእትነት ከፍሎ ለአለም ያሳወቀውን ጀግና ረዳት ካፒቴን ሀይለመድህን አበራ የጤንነት ችግር እንዳለበት ተደርጎ እህቱ ነኝ በምትል ግለሰብ በተለያዩ ድረ ገፆች የሀሰት አሉባልታዎች ማናፈስ ጀምረዋል::
እኔ ለእነዚህ ፈጣን የአሉባልታ አናፋሽ ባለሞያዎችና ቤተሰብነን ባዮች 3 ጥያቄዎችን ማንሳት እወዳለሁ::
ጥያቄ 1:- እንደዚህ በፍጥነት የረዳት አብራሪውን የጤንነት ችግር ለማሳወቅ የፈጠናችሁትና የጣራችሁትን ያህል ምነው ስለ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አሟሟትና የህመም አይነት ለመናገር ጊዜ ወሰደባችሁ? ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቆርቋሪ ቤተሰብና አጣሪ ባለሞያ የላቸውም?

በሱዳን በጎረምሶች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት በድንጋይ ተወግራ ልትገደል ትችላለች ተባለ



የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋርድያን እንደዘገበው የ18 አመቷ ወጣትና ነፍሰጡሩዋ ኢትዮጵያዊት በዝሙት ተግባር በመከሰሷ በድንጋይ ተወግራ ልትገደል እንደምትችል የምስራቅ አፍሪካ የሴቶች ስትራቴጂክ ኔትወርክ ወይም ሲሃ የተባለውን ድርጅት በመጥቀስ ዘግቧል። የ9 ወር ነፍሰ ጡሩዋ ወጣት በእስር ቤት ውስጥ ያለምንም ምንጣፍ በባዶ ኮንክሪት ላይ እንደምትተኛ ጋዜጣው ዘግቧል።

ኢሳት ከወር በፊት ዜናውን ይፋ ባደረገበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ኢምባሲ የዲያስፖራ ዘርፍ ሃላፊ ሆኑት አቶ….ወጣቱዋ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ገልጸው ነበር።
ይሁን እንጅ ጋርዲያን እንደሚለው ፣ ወጣቱ የ3 ወር ነፍሰጡር እያለች በ7 ጎረምሶች መደፈሩዋን ወዲያውኑ ለፖሊስ ብታመለክትም፣ ፖሊስ ግን የኢድ አል ፈጥርን በአል ሰበብ በማድረግ አቤቱታዋን ሳይቀበላት ቀርቷል።

ወጣቱዋ ዝሙት አለመፈጸሙዋንና ተገዳ መደፈሩዋን ብትናገርም ተሰሚነት አላገኘችም። የሱዳን ፍርድ ቤት የአገሪቱን ፖሊስ ገጽታ ለመጠበቅ ሲል እንዲሁም ጥፋተኞችም ለመታደግ ሲባል ንጹዋን ወንጀለኛ አድርጎ ማቅረቡ አሳሳቢ መሆኑን ሲሃ መግለጹን ዘጋርድያን ዘግቧል።

Wednesday, February 19, 2014

ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ? “ኢህአዴግ የተጭበረበረ ሪፖርት አቅርቦ” ነበር



ኢህአዴግ “አልመረመርም፣ አልበረበርም” በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡

ኢህአዴግ ምርመራውን በተቀነባበረ የፈጠራ ሪፖርት ለማምለጥ ሞክሮ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች “የመርማሪዎቹ ቡድን ሪፖርቱን አንቀበልም፣ የችግሩ ሰለባዎችና ክሱን የመሰረቱት ክፍሎች በሚኖሩበት ቦታ በመገኘት ነዋሪዎችን በተናጠል ለማነጋገር እንፈልጋለን” በማለት ኢህአዴግን እንደሞገቱት አስታውቀዋል። ኢህአዴግ በልማትና በህዝብ ስም የሚያገኘውን ከፍተኛ የዕርዳታ ገንዘብ የጦር ሃይሉን ለማደራጀት፣ የደህንነትና የፖሊስ ሃይሉን ለማስታጠቅና ርዳታ በሚለመንባቸው ዜጎች ላይ የተለያየ ወንጀል ፈጽሟል፣ አሁንም እየፈጸመ ነው በሚል መወንጀሉ ይታወሳል።

Sunday, February 16, 2014

ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል

2665272d78511e341383257989

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በራሳቸዉ እጅ የጻፉት ማኒፌስቶ በግልጽ እንደሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ጫካ ገብተዉ የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ያነሳሳቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸዉ ጥላቻና መሰረተ ቢስ ቂም በቀል ነዉ። ይህ ጥላቻቸዉ ደግሞ አማራዉን በመግደልና ግዛቱን ሲያሻቸዉ ከራሳቸዉ ክልል ጋር በመቀላቀል አለዚያም ለጎረቤት አገሮች በመሸለም ብቻ ሊቆም ወይም ሊገታ አልቻለም። እነሆ የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።
ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማዳከም፣ ለዘመናት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያገለግለኛል ብሎ ዘመቻ ከከፈተባቸው ብሄረሰቦች አንዱና ዋንኛው የሆነው የአማራ ህዝብ በራሱ ማንነት እንዲያፍርና ብሄራዊ ኩራቱ እንዲሟሽሽ ላለፉት 23 አመታት በግብር ከፋዩ ህዝባችን ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛዎች ሳይቀር ከፍተኛ የስነ ልቦና ዘመቻ ተካሂዶበታል። በአማራ ሥም አማራውን የወያኔ አገር የማፍረስ አጀንዳ አስፈጻሚ ለማድረግ የተሾሙበት ተላላኪዎች በህወሃት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አጋጣሚዎች አማራውን የሚያዋርድና የሚዘልፍ አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ ሰምተናል አይተናል። ይህ ተግባራቸው ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ፍቅር ያልነበረው ዘረኛው አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከዚህች አለም በሞት ከተሰናበተ ቦኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።