Wednesday, July 24, 2013

የፓርላማው ውይይት መታፈኑን በይፋ ያጋለጠው ጋዜጠኛ ከስራ ተሰናበተ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል።
ይህን ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ዘገባ ላይ ተመድቦ የሠራው የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ለዝግጅት ክፍላችን ምላሹን ሰጥቷል።
እነዚህ ዘገባዎች ከተስተናገዱ በኋላ፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ መረጃ እንደሰጠና ሚስጢር እንዳወጣ ተቆጥሮ የዲስፒሊን ክስ ቀርቦበታል። ኢ.ሬ.ቲ.ድ በዲስፒሊን ክሱ ላይ  አራት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በምስክርነት ዘርዝሮ አቅርቧል። የድርጅቱ የዲስፒሊን ኮሚቴ በከሳሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና በጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ መካከል የክስ ዝርዝር እና የመልስ መልስ ደብዳቤዎች ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም በቁጥር ቴ02.1/131-304/02/8/ በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ  ከግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ የሚያሰናብተውን ቅጣት አሳልፏል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለቤትነት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት፣ በሙስና ችግሮችና በመሳሰሉት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተካሄደ ሲሆን በዚህ ውይይት ላይ የኢፌዲሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ የእምባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አበባው ስጦታው እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጠራውና የአስፈፃሚ አካላትና የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናን በተመለከተ የተደረገው ውይይት፣ በዕለቱ በሥፍራው ባልነበረ ጋዜጠኛ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ተቆራርጦና ተዛብቶ ለሕዝብ መቅረቡ ትክክል እንዳልነበረ በይፋ በመግለፁ ምክንያት ከሥራ የተሰናበተው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻን ስለሁኔታው ፋኑኤል ክንፉ አነጋግሮታል።
ሰንደቅ፡- የዚህ ዜና መነሻ አንተን አድርገው ለመውሰድ ያስቻላቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህን ምላሽ መስጠት የሚችሉት እነሱ ናቸው። በሰጡኝ የክስ ዝርዝር ላይ ግን ሌላ ምክንያት ነው ያስቀመጡት። ወይም ደግሞ ላነሳኸው ጥያቄ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችለው የዚህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ብቻ ነው።
ሰንደቅ፡- እንዴት?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” ለሚለው ዜና መነሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በእኔ በኩል ያልኩትም አንዳች ነገር የለም። እንደማንም አንባቢ ይህ ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ነው የተመለከትኩት። ስለዚህም መረጃ ከእኔ አግኝታችሁ ከሆነ አግኝተናል፤ ካላገኛችሁ አላገኘንም ለሚለው ምላሽ መስጠት የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ይመስለኛል።
ሰንደቅ፡- በርግጥ የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ለዚህ ዜና መነሻ መረጃውን ያገኘው ከሌላ ሶስተኛ ወገን መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን። ሆኖም ግን ይህ ዜና በወጣ በሳምንቱ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም.  እርሶ ለሰንደቅ ጋዜጣ ማስተባበያ መስጠትዎ የሚታወስ ነው። በወቅቱ ከዜናው ጋር በተያያዘ ለምን ማስተባበል ፈለጉ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀውን ፕሮግራም የቀረጽኩት እኔ በመሆኔ ነበር። በሰንደቅ ጋዜጣም የተሰራው ዜና “የባለስልጣናት ድምጽ ታፈነ” የሚል በመሆኑም ጭምር ነው። ከዚህ አንፃር እንደአንድ ጋዜጠኛ ውይይቱን አፈነ ተብሎ መወንጀል በጣም አደገኛ ነው። እንዲሁም ማንስ አፈነው? እንዴት ታፈነ? ለሚሉት ጥያቄዎችም ምላሽ የሚፈልጉ መሆናቸው ግልፅ የሆነ ነገር ነው። በተለይ በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ኃላፊነት ታሳቢ ስታደርግ በእኔ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ድንጋጤ መገመት ከባድ አይደለም። የእነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት አንደበትን ለማፈን በእኔ በተራ ረዳት አዘጋጅ ቀርቶ በሌላው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር የሚሞከር ተግባር ተደርጎ የሚወስድ አካል ያለ አይመስለኝም።
ይህ ችግር ከተፈጠረ በኋላም ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ተወያይቻለሁ። እንዲሁም አንድ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ለማግኘት ጥረት ባደርግም አልተሳካልኝም። የሆኖ ሆኖ ከባልደረቦቼ ጋር ከመከርኩ በኋላ ፕሮግራሙ ታፍኗል ብሎ ለዘገበው ጋዜጣ ማስተባበያ በመስጠት እራሴን ከጉዳዩ ነፃ ማድረግ እንዳለብኝ ተማምነናል። የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቱም እኔ አለማድረጌን ሊገነዘቡ የሚችሉት ፕሮግራሙ ታፍኗል የሚለውን ዜና ባሰራጫው ሚዲያ መሆኑ አሻሚ አይደለም። ስለዚህም በዚህ ጉዳይ ላይ ንፁህ መሆኔን ለማረጋገጥ ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በጉዳዩ ላይ ያለኝን መረጃ ለመስጠት ተገድጃለሁ።
ሰንደቅ፡-እርሶ እንደዚህ ቢሉም፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ታህሳስ 01 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ የዲስፕሊን ኮሚቴው “አቶ አዲሱ መሸሻ በየነ በፕሮግራሙ ኢ.ሬ.ቴ.ድ የባለስልጣኖች ድምጽ አፍኗል። ፕሮግራሙ ቆራርጧል የሚል የተሳሳተና ከኃላፊነት የራቀ እና በሀሰት የተሞላ መግለጫ ለሰንደቅ ጋዜጣ” ሰጥቷል ሲል ይከሳል። በዚህ ላይ የእርሷ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የኢ.ሬ.ቴ.ድ “የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” ያለው ሰንደቅ ጋዜጣ እንጂ እኔ አዲሱ አይደለሁም። በወቅቱም በሰጠሁት ማስተባበያ ተቋሙን በተመለከተ ያልኩት አንዳች ነገር የለም። የማፈን ነገር ተፈጽሟል ከተባለም ግለሰቡ እንጂ ተቋሙ ሊሆን አይገባም በማለት ነበር ተቋሙን የተከላከልኩት። በሌሎችም ተቋማት ግለሰቦች ከተቋሙ ዓላማ በመውጣት የሚፈጽሙት ስህተት በእኛም ተቋም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጽሟል። ይህ ማለት ግን ግለሰቦች ከተቋም በላይ ናቸው ማለት አይደለም። ስለዚህም ግለሰቦች በሰሩት ጥፋት በግል መጠየቅ አለባቸው እንጂ በተቋም ደረጃ ስህተቱ ሊታይ አይገባም። ስለዚህም አንድ ሰው በራሱ መነሻ በፈጸመው ተግባር የተቋም አድርጎ መውሰድ ከሕግም ከሞራልም አንፃር የሚያስኬድ አይመስለኝም።
ሰንደቅ፡- የተከሰስክበት የደብዳቤ ይዘት ሚስጥር በማውጣት የሚል ነው። የሰጠኸው ማስተባበያ ከሚስጥር መጠበቅ ጋር እንዴት ትገልፀዋለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ሚስጥር ማባከን ከመጥፎ ፍላጎት (intention) የሚመነጭ ነው። ሚስጥር የሚባክነው ተቋምን ወይም ግለሰብን ለማጥቃት ከመፈለግ የሚመጣ ክፉ መንፈስ ነው። ከዚህ አንፃር ስትወስደው፣ እኔ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የሰራሁትን ፕሮግራም የሚመለከት ዜና በመሰራቱ ብቻ ማስተባበያ ሰጠው እንጂ ምን አጠፈሁ። ከእኔ ጋር ተያያዥነት ያለው ዜና ባይወጣ እኔም ባልተናገርኩ፤ እነሱም ክስ ያሉት ክስ ባልመሰረቱብኝ ነበር። ስለዚህም የጋዜጠኝነት ሙያዬን (integrity) በሚያጠፉ “አፋኝ” ተብሎ በተሰየመ ሁኔታ ስሜ ጠፍቶ፣ ስሜን ለመመለስ መከላከሌ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ከሚስጥር ማባከን ከመጠበቅ ጋር ምን ያገናኘዋል?
ሁለተኛው፣ “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተካሄደው ውይይት ዋናው ዓላማው፣ ውይይቱ ለሕዝብ እንዲቀርብ ነበር። ተደራሽነቱም ለሕዝቡ ነው። ለሕዝቡም ግልፅ መረጃ ለማቅረብ የተዘጋጀ ውይይት ነበር። ከሁሉ በላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው የስብሰባ ይዘት፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ በዚህች ሀገር ውስጥ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ ለሕዝብ ማሳየት ነበር። ሕዝቡም አደጋውን በመረዳት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግንዛቤ ለማስጨበት ያለመ ስብሰባ ነበር። ይህ ታዲያ ምን ሚስጥር አለው? ሚስጥር ከሆነ መጀመሪያውኑ ሚዲያውን አይጋብዙም ነበር። በወቅቱም ፕሮግራሙ ሲቀረጽም ሚስጥር ነው ያለ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አልነበረም።
ሌላው በዚህ ተቋም ውስጥ በቆየሁበት የስራ ዘርፎች ሚስጥር ተብለው የሚቀረፁ ስራዎችን ጠንቅቄ አውቃለሁ። በሚስጥር ደረጃ የተቀረፁ ስራዎችንም ሰርቼ አውቃለሁ። በዚህ ደረጃ የሰራኋቸውን ስራዎች እንኳን ለሶስተኛ ወገን፣ በተቋሙ ውስጥ ማወቅ ከሚገባቸው ሰዎች ውጪ ዉይይት አድርጌም አላውቅም። አለቆቼም ይህን ጠንቅቀው ያውቁታል።
ሰንደቅ፡- የዲሲፕሊን ኮሚቴው እንደሚለው ከሆነ “በስሜት ያደረኩት ነው” ሲሉ አቶ አዲሱ በኢዲቶሪያል ስብሰባ ላይ ገልጸዋል ይላል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በነገራችን ላይ የነበረው ኢዲቶሪያል ስብሰባ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ብዙ ርቆ የሄደ ነው። ግልፅ የፖሊስ ምርመራ ነበር የተደረገብኝ። አስራ አራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባሉበት የተደረገ ስብሰባ ሲሆን አውጣ፣ አታውጣ የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ። እኔ ለማስፈራራት፣ ለማሸማቀቅ የተደረገ ኢዲቶሪያል ስብሰባ ነበር። የቀረበብኝ ውንጀላ እስከሀገር ክህደት የሚደርስ መሆኑ ነበር የተነገረኝ። የፖለቲካ ይዘት ፈጥረውለት እኔ አንገት ለማስደፋት በአደባባይ ውጣና ማስተባበያ ስጥ ብለውኛል። የሚገርመው እኔ ነኝ ፕሮግራሙን የቆረጥኩት ያለው አመራር በዚህ ስብሰባ ውስጥ አንዱ ወቃሽ ሆኖ የተገኘበት ነበር።
ሰንደቅ፡-በዚህ ስብሳባ ደረሰብኝ የሚሉት ጉዳት አለ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- አለ እንጂ። ከዚህ በፊት የኢዲቶሪያል ስብሳባ የምናደርገው አየር ላይ የዋሉ ፕሮግራሞችን ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን ለመገምገም ነው። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የተደረገው ኢዲቶሪያል ግን መንፈሱን የተለየ ነው። የአንድ ተቋም ኃላፊዎች ተሰብስበው የፖሊስን ስራ በመተካት ያን ሁሉ ወከባ ማስፈራራት ሲፈጥሩ መመልከት በጣም አሳዛኝ ተግባር ነው። በእኔ ውስጥ የፈጠረው ስሜት ለረጅም ጊዜ ውስጤን ጎድቶታል። በተለይ የኢ.ሬ.ቴ.ድ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ይታወቃል። የምክር ቤቱን ውይይት መቁረጡን በግልፅ መናገሩን ሳይፈራ፣ ለምን እኔን ውይይቱ ተቆርጧል ብልሃል ብሎ ከስራ ሊያሰናብተኝ እንደፈለገ አልገባኝም።
ሰንደቅ፡-በታህሳስ 01 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው ወጪ በሆነው ደብዳቤ ላይ “ፕሮግራሙን ያዘጋጁት ባልደረባችን አቶ አዲሱ መሸሻ” የሚል ሲሆን፣ በጥር 20 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው የወጣው ደብዳቤ በበኩሉ “ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ” ናቸው ይላል። ከዲሲፕሊን ኮሚቴው በዚህ መልኩ ደብዳቤዎቹ ሊዘጋጁ ቻሉ? ፕሮግራሙን የሰራው ማነው ሊባል ይችላል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ዲሲፕሊን ኮሚቴው ያወጣው ደብዳቤ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው። ለክሱ እንዲረዳቸው አንድ ደብዳቤ በእኔ አዘጋጁ። ለመከላከል እንዲረዳቸው ደግሞ ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ ናቸው የሚል ደብዳቤ አዘጋጅ። ይህ በራሱ የሚነግርህ ነገር አለ። በማኛውም ዋጋ እኔ መክሰስ እና ከስራ ማፈናቀል ለዲሲፕሊን ኮሚቴው የተሰጠው ተልዕኮ ነው። አቶ ሳሙኤል በወቅቱ ትምህርት ላይ ነበሩ። እንዴትም እንደመጡ አላውቅም።
እውነቱ ግን ጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅዳሜ ፕሮግራሙን ሰርቼ ሙሉ ዝግጅቱ እሁድ ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና በኋላ የሚቀርብ መሆኑ ነው። በዚህ ዕለት የሚተላለፍ መሆኑን የሚገልፅ ከውይይቱ የተወሰዱ አጫጭር ንግግሮች የሚያሳይ ማስታወቂውን /ስፖት/ የሰራሁትም እኔው እራሴ ነኝ።
ሰንደቅ፡- አሁን በዚህ መልስ በእርሶ ላይ የተወሰደው እርምጃ በሌላው ሰራተኛ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህ ጥያቄ ከነሳህልኝ በውይይቱ ላይ አንድ የተሰነዘረ ነጥብ ልንገርህ። በዚህ ውይይት ከተሳተፉት ተሳታፊዎች መካከል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዓሊ ሱሌማን አንዱ ናቸው። እሳቸው ከገጠማቸው አስቸጋሪ የፀረ-ሙስና ትግል ሲገልፁ፤ “የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚታገሉ እና የሙስና ተግባራትን የጠቆሙና ያጋለጡ ሰዎች በአለቆቻቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወሰዱባቸው ቤሰቦቻቸው ተበትነዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ግለሰቦች ምነው ይህን ባልተናገርኩ እያሉ አንገታቸውን ደፍተው ተሸማቀው እየሄዱ ነው። እነዚህ ሃይሎች ገነው ወጥተው ለፀረ-ሙስና ትግል የተሰለፉ ኃይሎች ግን አንገታቸውን ደፍተው ይገኛሉ” ነበር ያሉት።
ሰንደቅ፡- አሁን እርሶ ላይ የደረሰውን ነገር ከዚህ ከአቶ አሊ ሱሌይማን አባባል ጋር እንዴት ያስታርቁታል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የኮሚሽነሩን አስተያየት በእኔ ላይ መፈጸሙን ስመለከት በጣም አስገርሞኛል። ምክንያቱም በውይይቱ ላይ ተገኝቼ የቀረጽኩት ውይይቱን ለሕዝብ ለማቅረብ እንጂ፣ በዚህ የውይይት ፕሮግራም መቆራርጥ መነሻ እና በመልካም አስተዳደር ዕጦት ሰለባ ለመሆን አልነበረም። የሆነው ግን በእውነት አስገራሚ ነው። ከስራ ተፈናቅያለሁ። ልጆቼን ለጊዜው ለወላጆቼ ሰጥቻለሁ። ባለቤቴን ከፍዬ ነው፤ የማስተምረው። የፓርላማውን ውይይት በፈለጉት መንገድ የቆረጡት ግን ደረታቸውን ነፍተው ለእኔ የስንብት ደብዳቤ ፅፈው ሰጥተውኛል። ኮሚሽነሩም ያሉት ከላይ የዘረዘርኳቸውን ሂደቶች ነበር። ለእሳቸው አስተያየት ከእኔ በላይ ማረጋገጫ ማን ሊያቀርብ ይችላል?
እዚህ ላይ ማወቅ ያለብህ በጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ይህን እድል አግኝቼ ለመናገር ቻልኩ እንጂ ስንቶቹ የሆዳቸውን ይዘው የቢሮክራቶች ሰለባ ሆነው ቁጭ ማለታቸውን መዘንጋት የለብንም።
ሰንደቅ፡- ተጠሪነታችሁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። አሁን ደርሶብኛል የምትለውን የመልካም አስተዳደር ችግር በአካል ሄደህ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል፣ የቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያመለከትከው ነገር የለም?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ የወሰድኩት እርምጃ እራሴን ማረጋጋት ነበር። በዚህ ጉዳይ አንተ ሶስተኛ ወገን ስለሆንክ እንጂ የተፈጠረው ሁኔታ እጅግ ድፍረት የተሞላበት ነው። መዋሸት የማልፈልገው ከስራ ተሰናብተሃል የሚለውን ውሳኔ ስሰማ ደንግጫለሁ።
ሰንደቅ፡- ለምን?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠራው ስብሳባ ታማኝ ባለመሆኑ ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት ኢ.ቴ.ሬ.ድ ነው። ይህን የምለው የእኛ ተቋም አስፈፃሚ መስሪያቤት በመሆኑ ተጠሪ ለሆነበት ተቋም በሰራው ስህተት ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል የሚል እምነት ስለነበረኝ ነው። የሆነው ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት በአግባቡ አልተስተናገደም የሚል መከራከሪያ ባነሳሁት ግለሰብ ላይ፣ የስራ ስንብት ደብዳቤ ሲሰጥ ምን ሊሰማህ ይችላል። እንደዚህ ዓይነት ድፍረት የተሞላበት እርምጃ እንዴት ይወስዳሉ ብለህ ትገምታለህ። ስለዚህም ግራና ቀኙን ለመመልከትና የተፈጠረብኝን ጫና ለመርሳት ወደ ሆነ ቦታ ዞር ማለትን ነበር የመረጥኩት።
ሰንደቅ፡- ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ምን ትጠብቃለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ከእኔ ስራ መፈናቀል በላይ አጀንዳ ያለው ይመስለኛል። ምክንያቱም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ተቋም፣ በምን ምክንያት ውይይቱን ሊቆርጠው ይችላል? ውይይቱ መቆረጡንም ምክር ቤቱ ያውቃል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ምክር ቤቱ ውይይቱ እየተቆራረጠ መቅረቡን እንደሚያውቅ እየታወቀ፣ ለምን የሃሰት መረጃ እንዳቀረብኩ ተቆጥሮ ከስራ ገበታዬ እስናበታለሁ? የፓርላማው ውይይት በትክክል አለመዘገቡን በመቃወም ምላሽ መስጠቴ ዋጋው ከስራ መሰናበት ከሆነ፣ ከእኔ የስራ ዋስትና በላይ ፓርላማው ሊመለከተው የሚገባ ጉዳይ ነው። ይህን መሰል ብልሹ የመልካም አስተዳደር ከተለመደ ተቋሙም ወዴት እየሄደ እንደሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል።¾

Sunday, July 21, 2013

አባቱን አያውቅም አያቱን ይጠይቃል!! ለጆሀር

ስለ ጆሀር ብዙ ነገር ተጽፎ በማህበራዊ ድረ ገጾችና የጡመራ ደሮች ተጽፎ አንብቢያለው፡፡ አንድ ወዳጄ ፌስ ቡክ ላይ ‹‹ስለ ጆሀር ምን አስተያዬት አለህ!›› አለኝ፡፡ እኔም ቪዲዮውን እንዳላየሁትና አስተያየት መስጠት እንደሚከብደኝ ነገርኩት፡፡ ይህ ወዳጄ ቪዲዮውን ‹‹ሸር›› አድርጎልኝ ደጋግሜ አዳመጥኩት፡፡
እኔ በጆሀር ንግግርም ፌስ ቡክ ላይ አስተያዬት በሚሰጡ ሰዎችም እኩል አዝኛለሁ፡፡ ጆሀር ለክርስቲያኖችና ኦሮሞ ላልሆኑ ዘውጌ ማህበረሰባት ያለውን ጥላቻ እኩል ገልጧል፡፡ ‹‹እኔ ባደግኩበት አካባቢ 99 በመቶ ሙስሊም በመሆኑ ማንም ሰው ደፍሮ አይነናገርም! በፌንጫ አንገቱን ነው የምንለው›› ይላል ለሌላ እምነት ተከታዮች ያለውን የበቀል ስሜት ሲገልጽ፡፡ ጎንደር ላይ ያለው ሙስሊም እንደሱ ‹‹በፌንጫ›› አለማለቱ ሁሉ ያናደደው ይመስላል፡፡
ወጣቱ ፖለቲከኛ ጆሀር ‹‹ኦሮሞና እስልምና ሀይማኖት›› አንድ ነው፡፡ የኦሮምን ህዝብ ትግል መደገፍ የእስልምናን ትግል መደገፍ አንድ አይነት ነው ብሎም ለመደምደም ይሞክራል፡፡ እስልምና በአቢሲኒያ ‹‹እንደ መጤ›› ይቆጠር ነበር፡፡ የአቢሲኒያ ነገስታት ለኦሮሞም ለእስልምናም የነበራቸውን አመለካከት ጥሩ አለመሆኑን በስፋት ለመዳሰስ ሞክሯል፡፡ በተለይ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በመጣው በፖርተቹጋል ወታደሮች እስልምናን ለማስወጣት በነበረው እንቅስቃሴ የኦሮሞ የመከላከያ ሀይል እንዳሰቀረው አስረግጦ አብራርቷል፡፡
የጆሀር ንግግር ብዙ ህጸጾች እንዳሉበት ማንም ሰው የሚያምን ይመስለኛል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሀይማኖት ሙሉ በሙሉ እስልምና አለመሆኑን ጆሀር ይክደዋል ብዬ አላምንም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በክርስትና ፣ በእስልምና እና በአካባቢው ባለ የቆየ እምነት (ዋቃ) ያምናል፡፡ ምንም እንኳ በመቶኛ ስሌት መገለጽ አሁን ባልችልም ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ አይደለም ሁለት ሶስተኛው እንኳ ሙስሊም ያልሆነን ማህበረሰብ የብሄርና የሀይማትን ትግል አንድ አድርጎ መመልከት ጤነኛ ነው ብየ አላምንም፡፡ አይደለም በኦሮሚያ በሶማሌ እና በአፋር ክልሎች እንኳ ሀይማኖትንና የብሄር ጭቆናን አንድ አድርጎ ለማየት መሞከር ‹‹ኋላ ቀር›› አስተሳሰብ የሚለው የሚለው ሀረግ የሚገልጸው አይደለም፡፡
ኦቦ ጆሀርን ተቀብሎ መድረኩን የተቆጣጠረው ስሙን የማለውቀው ሰው ከሰማንያው ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ 50 ሚሊዮኑ ሙስሊም አድርገው ሲናገሩ ‹‹ዳታው›› ከየት እንደተገኘ ባለውቅም እኔ ስለማውቃት ኢትዮጵያ እየተናገሩ እንደሆኑ አልገባህ ብሎኝ ነበር፡፡
ያም ሆነ ይህ በዚያ ቤት ላይ የነበረው ስብሰባ በጥላቻ የተሞላ እንደነበር ቪዲዮውን ያዬ ሁሉ ለመገንዘብ ጊዜ አይወስድበትም፡፡
ካንድ ወር በፊት አንዳንድ ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት በካይሮ የኢትዮጵያን ግድብ ግንባታ ተቃውመው ሰልፍ ሲወጡ አቤ ቶክቾው ‹‹ጉድ በል ሰላሌ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ተባልክ›› የሚል ጽሁፍ በድረ ገጹ አስነብቦ ነበር፡፡ እናም የነጆሀር ንግግር ሰላማዊ ሰልፍ ከወጡት ሰዎች አስተሳሰብ የተለየ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
እኔ ኦሮሞነትና እስልምና ይለያያሉ፣ አማርነትና ክርስትና ይለያያሉ፣ ትግሬነትና ክርስትና ይለያያሉ፣ አፋርነትና እስልምና ይለያያሉ፣ የትኛውንም ዘውግ ከየትኛው ከሀይማት ጋር ማመሳሰል አይቻልም፣ ይህ ማንም ምንም ቢል ሊያሳምነኝ የሚችል ሰው የለም፡፡
በተቃራኒው በግብጽ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን እና በጆሀርን ንግግር የሚቃወሙ አንዳንድ ጨዋት የጎደለው አስተያዬት የሚሰጡ ሰዎችንም ጽሁፍ ማንበብ ከኦቦው ንግግር እኩል ‹‹አፍራሽ›› አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ሰዎች ቀላል አለመሆናቸውን ለማየት አስችሎኛል፡፡ ጆሀር አንድ ግለሰብ ነው፡፡ በምንም መልኩ የኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታዮችና የኦሮሞ ማህበረሰባትን ሊወክል ፈጽሞ አይችልም፡፡ አይደለም ጆሀር ሁሉም የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ‹‹ኦሮሞን››፣ በተቃራኒው ሁሉም የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ‹‹እስልምናን›› መወከል አይችሉም፡፡
ስለዚህ በምን ስሌት እንደሆነ አላውቅም ከሌላ ዘውጌ ብሄረሰባት አካባቢ ያሉ ሰዎች በኦሮሞነትና በእስልምና ላይ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት የሚሰጡት፡፡ በርግጥ በሳል አስተያዬት የሚሰጡ የሉም ለማለት አይደለም፡፡ ግን ብዙዎቹ ጽንፍ ይዘው የተጻፉ መሆናቸው አሳዛኝ ነው፡፡
ወደ ርዕሴ ስመለስ ኦቦ ጆሀርን በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን አንኳር የታሪክ ፍሰት እንዲህ ላስታውሰው ፈለግኩ፡፡ ጆሀርን ብቻ አይደለም በጆሀር ፍልስፍና የተጠመቁ አጃቢዎቹን ጭምር እንጅ፡፡ በሀይማኖት እና በዘውግ የነበረውን የታሪክ ፍሰት ተጣጥሎ መመልከቱ አስፈላጊ መስሎ ስለታዬኝ ለየቅል እናየዋለን፡፡
1. ኢትዮጵያና ሀይማኖት
በኢትዮጵያ ታሪክ ከጥንት እስከ አለንት ዘመን ድረስ የነበሩ ገዢዎች ከጥቂቶች በቀር ክርስቲያኖች መሆናቸው እውነት ነው፡፡ ይህ ታሪክ በመሆኑ እንጆሀርን ለማስደሰት ሲባል ከፊሉቹ ‹‹የእስልምና እምነት ተከታዮች ነበሩ›› አሊያም ‹‹እኩል በእኩል የኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት ነበሩ›› ብሎ ማስተካከል ከቶ የትኛው የታሪክ ምሁር ይቻለዋል!! የሚቻል ቢሆን ኖሮ ‹‹ለፍትሀዊነት›› ሲባል ማድረጉ ባልከፋ ነበር፡፡ በማይቻል ነገር ላይ ጊዜ ማጥፋቱ አስፈላጊ ባለመሆኑ ወደ ሌላው ጉዳይ ልለፍ፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስትናን ካስተማራቸው ሰዎች አንዱ የኢትዮጵያዊቷን ንግስት ጃንደረባ ፊሊጶስ የተባለው ሀዋርያ አጠመቀና ወደ ሃገሩ ላከው (ሐዋ 8፡-)፡፡ ምንም እንኳ ይህ የሆነው በ34 ዓ.ም. እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ብሄራዊ ሀይማኖት የመሆን እድል አላገኘም ነበር፡፡
ኢትዮጵያ (የኢትዮጵያ ነገስታት) በ4ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ወይንም በ340 ዓ.ም. አካባቢ ክርስትናን ብሄራዊ ሀይማኖት አድርጋ ከተቀበለች በኋላ ብዙዎቹ ነገስታቶቿ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነበሩ፡፡ አልፎ አልፎ ከኦርዶክስ ክርስትና እምነት ውጭ የነገሱ ወይም ወደ ሌላ ሀይማኖት የተቀየሩ ቢኖሩም በታሪክ በጥሩ መልኩ የሚወሱ አይደሉም (በጥሩ ላለመነሳታቸው ብዙ ምክንያት ሊኖር ይችላል፡፡ የታሪክ ጸሀፊዎቹ ክርስቲያን ስለሆኑ የሚያዩት ከራሳቸው ጥቅም አንጻር መሆኑ፣ በርግጥም ጥፋተኛ ስለሆኑ፣ … ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ችግር ማጥናት እና እውነተኛን ነገር ማሳወቅ/ ማወቅ የአንድ ጨዋ ሰው ግብሩ ነው)፡፡
በሰባተኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ነጃሽ የሚባል የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ እንደነገሰ ቢወራም ይህን የሚያጠናክር ከወሬ የዘለለ የታሪክ ድርሳን ማግኘት አልቻልኩም፡፡ እርግጥ ነው በ622 ዓ.ም. አካባቢ መሀመድ እስልምናን ለአካባቢው ቋሪሾች ሲሰብክ ‹‹አይንህን ላፈር›› ሲሉት በዘመኑ ለነበረው ኢትዮጵያዊ ንጉስ ቤተሰቦቹን አደራ ሰጠው፡፡ ንጉሱንም እንግዳዎቹን ተቀብሎ አስገድዶ አላስጠመቃቸውም፡፡ ነጻነት ሰጣቸው፡፡ ምንም እንኳ ለስርወ መንግስቱ መዳከምና ጨርሶ መፈራረስ ብሎም የግዘቶቹ ስፋት ማነስ አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም፡፡ የአክሱም ስርዎ መንግስት ማክተሚያ ላይ በአስረኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በ980ቹ አካባቢ የነገሰችው የአይሁድ እምነት አራማጇ ዮዲት ስሟ በጥሩ ተነስቶ አያውቅም፡፡ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላለች፣ የታሪክ መዛግብትን አውድማለች፣ የብዙ ሰው ህይዎት ቀጥፋለች፤…. ብዙ ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሰርታ ከማለፏ የተነሳ ‹‹ዮዲት ጉዲት›› ተባለች (በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ ጽንፈኛ አይሁዳዊ እምነት አራማጅ ሊህቅ አለመኖሩ ነው እንጅ ‹የአይሁዳዊነትን› ትግል ደግፉ ብሎ የሚነሳ ሰው ባልጠፋ ነበር)፡፡
በ16ኛው ክፍለ ዘመን የመባቻ አካባቢ አንድ ሃያል ጡንቻማ ሰው ከወደ ምስራቅ በኩል ብቅ አለ፡፡ የአዳሉ ንጉስ ሙሉ ስሙ ግራኝ አህመድ እብን ኢብራሂም አልጋዚ በአጭሩ ደግሞ ግራኝ አህመድ ይባላል፡፡ ከ1522-1540 ዓ.ም. ድረስ አጼውን እያሳደደ ከቆየ በኋላ ገደለው፡፡ ንጉሱም ባለቤታቸውን ‹‹ቀዳማዊት እመቤት›› ሰብለወንጌልን ጋለሞታ፣ ልጃቸውን ገላውዲዮስን ደግሞ እጓለማውታ አድረገው ወደማይቀረው አለም ሄዱ፡፡ አንበሳየም ከዮዲት ጉዲት በላይ ከአገር አገር እየዞረ አብያተ ክርስቲያናትን፣ የታሪክ መጽሀፍትን፣ ቅርሶችን… ወዘተ ከሚገበው በላይ አወደመ፡፡ ብዙ ክርስቲያኖችን አሰለመ፤ አንሰልምም፣ ብለው የተቃወሙት ደግሞ ገድላቸው ያልተጻፉ ሰመዕታት ሆነው አለፉ፡፡ እልፍ አዕላፋት ነፍሳት አለቁ፡፡ (ከዚህ ላይ ጆሀር ከፖርቱጋል የመጡ ወታደሮች በእስልምና ላይ ከአገር ለማስዎጣት ያደረጉትን ጠቅሷል፡፡ ከኦቶማን ቱርክ የመጡትን ወታደሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱትን ጉዳት ግን መግለጽ አልፈለገም፡፡) በ1543 ዓ.ም. አካባቢ ባይሞት ኖሮ ከዚህም የከፋ እልቂት ሊኖር ይቸል ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ግራኝ አህመድ ቅንጣት ታክል በጎ ምግባር ነበረው ያለ የታሪክ ጸሀፊ የለም:: ወይም ተጽፎ ቢሆንም በክርስቲያኖቹ ነገስታት እንዲጠፋ ተደርጎ ሊሆን ይችላል (የግራኝ አህመድ አስገድዶ ማስለም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ብዙዎቹ ነገስታት አስገድደው ክርስቲያን ያደርጉ ነበርና፡፡ ስለሆነም እሱ ያደረገው ብዙዎቹ ስልጣን ላይ ፊጥ ሲሉ የሚያደርጉትን በመሆኑና በዘመኑ በነበረው አስተሳሰብ መኮነን አለበት አልልም)፡፡
ታሪክ መልኩን እየቀያየረ ይደጋገማል፡፡ በ17ኛ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ከ1608 – 1632 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው ንጉስ አጼ ሱስንዮስ ይባላል፡፡
የንጉሱ ዜና መዋልዕ እንደሚያስረዳው ንጉሱ ብዞ ጊዜያቸውን ያሳለፉት ከኦሮሞች ጋር በመሆኑ ከብሀረሰቡ በርካታ መልካም ሥብዕናንና ጦረኝነትን ተምረዋል፡፡ ንጉሱ በመጨረሻ የንግስና ዘመናቸው ካቶሊክን አምነው ተቀበሉ፡፡ ምን ይኸ ብቻ፤ ብሄራዊ ሀይማኖት እንዲሆን አወጁ፡፡ አይሆንም ያሉ መኳንንቶች ተቀሉ፤ ተሰየፉ፡፡ ህዝብ እርስ በእርሱ ተጨፋጨፈ፡፡ ኢትዮጵያችን እንደለመደችው በልጆቿ ደም ታጠበች፡፡ እማ ሙዝ/ ፍቅርተ ክርስቶስ የተባለች ጻድቅ ሰማዕት የሆነችው በዚህ ዘመን ነበር፡፡ /ገድለ ፍቅርተ ክርስቶስ መመልከት ይቻላል፡፡/ በመጨረሻ የንጉሱ ምላስ አርባ ክንድ ወደ ውጭ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ የንጉሱ ልጅ አቤቶ ፋሲል እንዲህ የሚል አዋጅ አወጀ፡፡
‹‹የሮም ሀይማት ይርከስ፣ የእስክንድር ሀይማኖት ትመለስ፣
ሱስንዮስ ይፍለስ፣ ፋሲል ይንገስ፡፡››
ይቀጥላል…፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ እምየ ምኒልክ ይታመማሉ፡፡ በ1908 ዓ.ም አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ የሚተካ ወንድ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ የሸዋ መኳንንት ተጠበቡ፡፡ ከሞታቸው በኋላ የራስ ሚካኤልን ልጅ ወይም የቀድሞ የወሎውን ራስ አሊ ልጅ ልጅ ኢያሱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡ ልጅ ኢያሱ በአንድ በኩል ገና ሩጦ ያልጨረሰ ልጅ በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ በሀይማኖትና በብረሰባት ላይ ያለው አመለካከት ከሸዋ መኳንንት ፍላጎት ጋ ሊገጥም አልቻለም፡፡ ልጅ ኢያሱ ከክርስቲያኑም ከእስላሙም፣ ከአማራውም፣ ከኦሮሞውም፣ ከሶማሌውም ‹‹የሴት ወዳጅ›› እየያዘ በጋብቻ መልክ አንድነትን ለመፍጠር ያቀደው ሳይሳካ በነገሰ በሶስተኛ አመቱ በሌለበት ከዙፋኑ ተነሳ፡፡
2. ኢትዮጵያዊ ብሄረሰቦች
ኢትዮጵያችን ብዙ ቋንቋ ተናጋሪና ብዙ ባህል ያላቸውን ህዝቦች የያዘች አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ለልማቷም ለኋላ ቀርነቷም ሁሉም እኩል ሀላፊነት ይሸከማሉ ባይ ነኝ፡፡ አንዱ ሲያቀና ሌላው ሲያበላሽ፣ አሊያም ዝም ብሎ ሲመለከት፣ አንዱ አንዱን ሲያጠቃ የኖሩ ህዝቦችን የያዘች ሀገር ናት፡፡
አንዱ ብሄረሰብ ከየመን መጣ ሌላው ከደቡብ ምስራቅ አፍሪካ ጫፍ መጣ፣ አንዱ ቀድሞ ገባ ሌላው ዘግይቶ መጣ ለኢትዮጵያ ሁላችንም ልጆች ነን፡፡ ጆሀር እንደሚለው አንዱ ‹‹ማንነቱን›› በግዴታ የተቀበለው አሊያም ሌላው ደግሞ ‹‹ሰጪ እና ነሽ›› ሰዎች አይደለንም፡፡ መጋጨቱ፣ መፋቀሩ እና መናናቁ የታሪካችን አካል ሆኖ አልፏል፡፡ ግን አሁን ተማርን ያልን ሰዎች የበፊት ክፍተቶችን አርመን ወደ ፊት መጓዝ መቻል አለብን፡፡
ለምሳሌ በታሪክ የነበሩ እንዲህ አይነት ችግሮች አንኳር አንኳር የምንላቸውን ማየት እንችላለን፡፡ በሰለሞናዊውና በአገው ስርወ መንግስታት በነበረው ሽኩቻ ሰለሞናዊውን ስርዎ መንግስት አንኮታኩተው አገዎች የራሳቸውን መንግስት በ11/12ኛው ክፍለ ዘመን ዛግዌ ስርዎ መንግስት መሰረቱ እና ስልጣናቸውን በ1270 አካባቢ ፈጽመው እስኪያጡት ድረስ ተጠቀሙበት፡፡ በጣም ድንቅ የተባለው ‹‹የላሊበላ ኪነ ህንጻ ጥበብ›› የታየውም በዚሁ ዘመን ነበር፡፡ ምን አልባትም ንግስና ወደ አገዎች ባይመጣ ኖሮ ይህን የኪነ ህንጻ ጥበብ ላናውቅ እንችል ሁሉ ይሆን ነበር፡፡
በ15 /16ኛው ክፍለ ዘመን በነበረ የኦሮሞዎች የመስፋፍት እንቅስቃሴ ከሴሞቹ ጋር በነበረ ግጭት ብዙ ነገር እንደወደመ ግልጽ ነው፡፡ አማራዎቹ ይዘውት የነበረውን ለም መሬት በኦሮሞች በመነጠቅ ተራራ ላይ ብቻ እንዲወሰኑ ተገደዱ፡፡ በዚህ በኩል ከየትኛውም ብሄረሰብ የተሸለ ኦሮሞዎች ግዛታቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ እስከ ቀይ ባህር ድረስ ለመስፋፋት ቻሉ፡፡ ለዚህም ምስክር የሚሆኑ ብዙዎቹ ቦታዎች ቀድሞ የነበራቸውን ስያሜ በመተው ኦሮምኛ ስም ኖራቸው (ልክ አሁን ብዙዎቹ ከተሞች አማርኛ ስም አላቸው ተብሎ ወደ ኦሮምኛነት እንደተቀየሩት ሁሉ)፡፡ በተለይ ከአጼ ልብነ ድንግል እስከ አጼ ሱስንዮስ ድረስ በነበረው ጊዜ በነበረው የግዛት መስፋፋት ኦሮሞዎች እደለኞች ነበሩ፡፡ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ትግራይ ድረስ ገብተው ጥቃት ይፈጽሙ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ምንም እንኳ ድል አንዴ ላንዱ ሌላ ጊዜ ለሌላው ቢሆንም የነበረው የእርስ በእርስ ትርምስ ቀላል አልነበረም፡፡
ከዘመነ መሳፍንት በኋላ በሰሜን በኩል ያሉ ነገስታት ቀድመው መንቃታቸው ምን አልባትም በሌላው ኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ጠቅሟቸዋል፡፡ በአጼ ቴዎድሮስ የተጀመረው ሀገር የማቅናት ዘመቻ በአጼ ሚኒሊክ እስኪደመደም ድረስ የደረሰ ችግር አልነበረም ማለት አይቻልም፡፡ ግን ቀደም ብሎ ከነበረው ችግር የባሰ አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እርስ በእርስ ቢናቆሩም በአገር አንድነት ላይ ያላቸው አቋም ግን የሚያስደንቅ ሆኖ ለረጅም ዘመናት ዘልቋል፡፡ የውጭ ሀይል አገር በወረረ ጊዜ ሁሉም እኩል ይፋለማሉ፡፡ በቅርቭ ጊዜ ያነበብኩት ‹‹የሀበሻ ጀብዱ›› የሚል በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የታተመና ከአውሮፓዊ ጸሀፊ የተተረጎመ መጽሀፍ ‹‹ኦሮሞዎቹንና አማራዎቹን›› አገር ወዳድ አርበኞች አድርጎ ስሏቸዋል፡፡ በተለይ አንድ ‹‹አቢቹ›› የተባለን ብላቴና ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ወኔ በመደነቅ ነበር የገለጸው፡፡ ጆሀር የዚህን ልጅ ኢትዮጵያዊነት በምን መልኩ ሊያጣፋው እንደፈለገ አልገባኝም፡፡ አቤ ቶኪቻው ‹‹ጉድ በል ሰላሌ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ተባልክ›› ያለው ወዶ አይደለም፡፡
ጆሀር ሞሀመድ እንበልና ሀሳቡ ቢሳካ እሱ አቢሲኒያ እያለ የሚጠራቸው ‹‹አማራዎች››ም ከሌላው ብሄረሰብ የበለጠ አይጎዱም፡፡ አብረው በመሆናቸውም የበለጠ አይጠቀሙም፡፡ ክርስቲያኖቹም በተመሳሳይ፡፡
እንደያው በመጨረሻ ግን ኦቦ ጆሀር በክርስቲያንና ኦርሞ ባልሆኑ ህዝቦች ላያ ያለው ጥላቻ ፈር የለቀቀ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ጥላቻቸው ከመጠን የዘለለ ሲሆን ወደ በቀል ይገባሉ፡፡ በቀሉ ደግሞ መደበቅ አይችልም፡፡ ኦቦ ጆሀር በ1984 ዓ.ም. በደኖ ላይ በነሌንጮ ለታ እና በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር የተገደሉ፣ በ1992/93 ወለጋ ጊዳ ኪላሞ ላይ ወደ እሳት የተጣሉትን ህጻናትን፣ በ1999 በጅማ በሻሻ የተሰ ክርስቲያኖችን፣ በቅርቡ ደግሞ በቢኒሻንጉል የተፈናቀሉ አማራዎችን አስብና አንድም የበቀል ስሜትህን አርከሰው አሊያም አንተ እንደፈለግከው፡፡
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር፡፡

የፀረ ሙስና ትግሉን ለመቀልበስ ያደፈጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መኖራቸው ሥጋት ፈጥሯል፡፡

አዲስ አበባ ላይ የተንሰራፋው ሙስና ለብዙዎች አሳሳቢ ሆኗል

መንግሥት ሙስናን እየተዋጋ የሚያስመስሉ ምልክቶች ቢስተዋሉም፣ የፀረ ሙስና ትግሉን ለመቀልበስ ያደፈጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መኖራቸው ሥጋት ፈጥሯል፡፡
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙሰኞችን በተመለከተ ሲናገሩ፣ ‹‹ወይ እነሱ ያሸንፋሉ ወይ እኛ እናሸንፋለን፤›› ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን መንግሥት ሙስናን ለመታገል ደፋ ቀና የሚለውን ያህል በመንግሥት ጉያ ሥር ተሸጉጠው የሙስና ትግሉን በመቀልበስና የሚገኘውን አይስክሬም ለመላስ የቆረጡ እንዳሉ እየታየ መሆኑን የሚገልጹ አሉ፡፡
በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ሽኩቻ ወይም ትግል በማን አሸናፊነት እንደሚቋጭ ባይታወቅም አሸናፊና ተሸናፊ የግድ እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት እየጨሰ ከሚገኘው የፀረ ሙስና ትግል ባሻገር፣ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ጉዳዮችን ጥቂት ዓመታት ወደኋላ መለስ ተብሎ ቢመረመርና አሁን ካለበት ደረጃ ጋር ቢመዘን የጉዳዩን አሳሳቢነት መረዳት ያስችላል በማለት የሚገልጹ አሉ፡፡
የቀድሞወ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ አስተዳደር ሥልጣኑን ከእሳት አጥፊው ባለአደራ አስተዳደር ሲረከቡ ወደ ከተማው ይዘው ከመጧቸው ቁም ነገሮች መካከል መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ሙስናን መታገልና መሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ተግባራዊ ማድረግ ይገኙበታል፡፡
በተለይ ከገቢ አሰባሰብና ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ በርካታ የሙስና ተግባሮች እንደነበሩ በመታመኑ፣ በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ጠንከር ያለ ግምገማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በእነዚህ ግምገማዎች በርካታ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በሙስና መዘፈቃቸውና በርካታ ገንዘብ መመዝበሩ በተካሄደው ድርጅታዊና መንግሥታዊ ግምገማ ተረጋግጧል፡፡
የግምገማው ውጤት ለፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተመራ ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ በደረሰው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ምርመራ በጀመረበት ወቅት ግን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፀረ ሙስና ኮሚሽን በጻፈው ደብደቤ የተፈጠረው ችግር የከተማው ነው በሚል ምክንያት ኮሚሽኑ ምርመራውን እንዲያቆም ጠይቋል፡፡
ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የአስተዳደሩና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለሙያዎች ሁኔታውን አሳፋሪ ሲሉ ይገልጹታል፡፡ ምክንያቱም ያጠፋ መጠየቅ አለበት፡፡ የተመዘበረ የመንግሥት ገንዘብም ሊመለስ ይገባዋል ሲሉ እነዚህ ባለሙያዎች ምክንያታቸውን ገልጸው፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከእንግዲህ ደብዳቤ መጻፍ እንደሌለበትና ፀረ ሙስና ኮሚሽንም ምርመራውን ሊያቆም እንደማይገባ አስረግጠው መከራከሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡
በግምገማ ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠባቸውና ማጥፋታቸውን በግልጽ ያመኑ የሙስና ተጠርጣሪዎች  ግን ክስ አልተመሠረተባቸውም፡፡ ተመዝብሯል የተባለውም የመንግሥት ሀብት ተመላሽ አልተደረገም፡፡ በዚህ ምክንያት የተበደሉ ነዋሪዎችም እንዲካሱ አለመደረጉ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
ብዙዎችን የሚያስገርመውና እያስገረመ የሚገኘው እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ተጠያቂ አለመሆናቸው ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁኑም በአዳዲስ ሹመቶች መንበሽበሻቸው ነው፡፡
ከአሥሩም ክፍላተ ከተሞች በሙስና ተግባር ውስጥ ተሰማርተዋል ተብሎ ነጥብ የተያዘባቸው ሹማምንት ከነበሩበት ክፍለ ከተማው ወደሌላ ክፍለ ከተማ ተቀይረው ተሹመዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ በክፍላተ ከተሞች በሚገኙ የገቢ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ‹‹ሙሰኞች›› እንዳሉ ይነገራል፡፡
እነዚህ ‹‹ሙሰኞች›› ከነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ፍሬ ግብር በመቀነስ ሊከፈል የሚገባውን የመንግሥት ግብር የሚያሳንሱ፣ ማሳነስ ብቻም ሳይሆን ጭራሹኑ ሊገባ ይገባው የነበረ ገንዘብ ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት እንዳይገባ ዘብ የቆሙ እንደሆኑ ይነገራል፡፡
እነዚህን ያጋለጡ ሠራተኞች ግን በየጊዜው ተፅዕኖ እየተደረገባቸው ጭራሹኑ በፍርኃት ካባ ተሸፍነው እንዲኖሩ እየተደረገ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ ይህንን ሕገወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት ባላቸው ጠንካራ ኔትወርክ ምክንያት ለአዳዲስ ሹመቶች ሲታጩና ሲሾሙ ይስተዋላል፡፡
በሌላ በኩልም ከአንድ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማዕከል ደረጃ በተካሄደው ግምገማ ከአሥር በላይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሙስናና በኔትወርክ ተገምግመው ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ሐሳብ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ከዛሬ ነገ ዕርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ ባለሥልጣናቱ ባሉበት ፀንተዋል፤ ወይም አዲስ ሹመት አግኝተዋል፡፡ በወቅቱ እነዚህ ባለሥልጣናት ሲገመገሙ በሙስና መዘፈቃቸውና በቡድንተኝነት (ኔትወርክ) ያልተገቡ ተግባራትን ይፈጽማሉ በሚል ምክንያት እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል፡፡
አስገራሚው ጉዳይ በአዲስ አበባ አዲስ ምርጫ ተካሄዶ አዲሱ ካቢኔ ሥልጣኑን ይይዛል ቢባልም፣ ወደከተማው የመጡት ከንቲባው ብቻ ናቸው፡፡ አዲሱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ነባሩን ካቢኔ ይዘው ማዝገማቸውን ቀጥለዋል፡፡
የቀድሞው የከተማው አስተዳደር በሚፈለገው ስፋትና ጥልቀት ባይሆንም የልማት ሥራዎችን መሥራቱ እርግጥ መሆኑን ብዙዎችን ያስማማል፡፡ በመጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ በቤቶች ልማት፣ በመንገድ ልማት ዘርፎች የሚጨበጥ ሥራ ሠርቷል፡፡ ነገር ግን መልካም አስተዳደርን በማስፈንና ሙስናን በመዋጋት አገልጋይ ሲቪል ሰርቪስ ከመፍጠር አኳያ ብዙ እንደሚቀረው ብዙዎች ያምናሉ፡፡
የቀድሞው አስተዳደር መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና አገልጋይ ሲቪል ሰርቪስ በመፍጠር በኩል ፍላጎቱ ነበረው ቢባልም በአቅም ውሱንነት ባያሳካውም፣ ሙስናን በመታገል በኩል ግን የተነሳሽነት ችግር እንዳለበት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአስተዳደሩ ነባር ሠራተኞች ይናገራሉ፡፡
ኅብረተሰቡ ይህንን ችግር በመፍታት በኩል ኢሕአዴግ ቆራጥ መሆኑን በተደጋጋሚ በመግለጹ ምክንያት በአዲሱ አስተዳደር ላይ ተስፋ ቢጥሉም፣ አዲሱ አስተዳደር ከከንቲባው በስተቀር ነባሩን ካቢኔ ይዞ መቀጠሉ በተጣለው ተስፋ ላይ ደመና አጥልቷል፡፡ ምክንያቱም የሠራተኞችና የነዋሪዎች እንቀፋት የሆኑ ባለሥልጣናት ላይ ዕርምጃ ተወስዶ ሥርዓት የሰፈነበት ቢሮክራሲ ይኖራል የሚል እምነት ተጥሎ የነበረ በመሆኑ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ሁሉም ነገር ተዳፍኖ ምንም እንዳልተፈጠረ ተደርጎ ጉዞ ቢቀጥልም፣ ጉዳዩ ብዙዎችን ያስከፋ በመሆኑ መንግሥት የጽሞና ጊዜ ወስዶ ራሱን ሊፈትሽ እንደሚገባ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ያስጠነቅቃሉ፡፡

ደመና ሁሉ ዝናብ እንደማይሆነው ከዳሁ ያለ ሁሉም ወዳጅ አይባልም

ለአየር ትንበያ የንፋስ አቅጣጫ፣ የአየሩ ሙቀትና እርጥበት፣ የደመናው አይነትና ፍጥነት ሁሉ እገዛ ያደርጋሉ። ለፖለቲካም እንዲሁ ለትንበያ የሚመቹ በፖለቲካው ትኩሳት፣ በውስጥ ሽኩቻ ብዛትና በተቃዋሚው ጥንካሬና ብቃት መነሻነት ወደ ሌላኛው ጎራ ሲቀላቀሉ የሚታዩ መጪውን ለመተንበይ የሚያስችሉ አመላካች ሰዎች አሉ። የአየር ትንበያ ሰራተኞች እንደ መሳርያዎቻቸው ዘመናዊነት፣ እንደመረጃ ማሰባሰቢያ ነጥቦችና በእውቀት የተካኑ ባለሙያዎች ብዛት ወደ እውነት የተጠጋ ትንበያን ማቀበል ይችላሉ። ፖለቲካም እንዲሁ ነው። የውስጥ አዋቂ መረጃ፣ የውጪው ዓለም የሀይል አሰላለፍ፣ የህዝብ መነሳሳትና፣ የገዢዎችን የፖለቲካ ትኩሳት በማገናዘብ መጪውን የፖለቲካ አቅጣጫ ማመላከት ይቻላል።
Birhanu Damte Aba mela
ለፖለቲካው ትንበያ የሚያግዙ አጥር ሰብረው የሚመጡ የነበሩበት ትክክል እንዳልነበር እየተናገሩ ሌላኛውን ጎራ ልንቀላቀል መጥተናል ተቀበሉን እያሉ የምሬትና የእሮሮ እንጉርጉሮ ይዘው መድረኮች ላይ ብቅ ብቅ የሚሉ ሲኖሩም ለፖለቲካ አቅጣጫ ትንበያ እገዛ ያደርጋሉ። ያደረሱትን በደል በማሰብ ከመጨነቅ ሊያጠፉ ከሚችሉት በመቆጠባቸውና የጠላትን ጎራ የማዳከማቸው ዋጋ የበለጠ ነውና እንዳመጣጣቸው መቀበል ሌላኛውን ጎራ ለማዳከም ይረዳል። አመጣጣቸው በቀናም ይሁን በተለየ ተልዕኮ መጡልን ብሎ ከራስ በላይ ማድረግ ግን ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ያመጣል። የሚበላ ሲጎድል፣ በራሳቸው ኩርፊያና ሽኩቻ ወይም ሌላ መሰረታዊ ባልሆነ ልዩነት የሚመጡትን ከፍ ከፍ ማድረጉ ደግሞ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው። እንዲህ አይነቶቹ ይሉኝታቢሶች ለመታመን ሲባል የማያደርጉት የለምና ሀቀኞችንና ለዓላማ የቆሙትን ለስልጣን ጥመኞች የጥቃት ሰለባ ያደርጋሉ።
ይህንን ምልልስ በዘመናችን ተመልክተናል። ከድተን መጣን ብለው የተበላ መረጃ ሰጥተው የተሻለ መረጃ ይዘው ያፈተለኩና መልሰው የወጉ ብዙ ነበሩና ከተሞክሮ እንጂ እንደ አዲስ የምንማረው አይደለም። የሀገራችን የመከላከያ ሰራዊት ከገንጣይ ሀይሎች ጋር ግብ ግብ ገጥሞ በነበረበት ሰዐት መጡልን ተብለው የታቀፉ የተገንጣይ ወንበዴዎቹ ሰላዮችና አብዮቱን ተቀላቀልን ብለው የካድሬ ህጋዊነት ተሰጥቷቸው ጓደኞቻቸውን ያረዱ፣ ለዚህች ሀገር በሀቀኛነት ያገለገሉትን በየጉድባው እየገደሉና እያስገደሉ አሁን ወደምንገኝበት እንደርስ ዘንድ አስተዋጽኦ ያደረጉ በርካቶች መኖራቸውን ብዙዎች የምናውቀው እውነት ነው። ደርግ ሲዳከም ደግሞ ወዲህኛው ጎራ ተቀላቅለው ተገርፈን፣ ተሰደን፣ መከራ በልተን ተገደን እያሉ ሌላኛ ዙር ጥፋታቸውን ሲያከናውኑ የኖሩቱ አሁን ደግሞ ማርሽ ቀይረው ሌላ መዝሙር ሲዘምሩ እየተመለከትን ነው። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች በዚህ ከፍተኛ ልምዱ አላቸውና አኪያሄዳቸውን ሲቀይሩ ያኛው ቤት የተበላ እቁብ እንደሆነባቸው በመገመት የወያኔ ነገር ላይጠገን እየተሰበረ መምጣቱን መገንዘብ ይቻላል። ተቃዋሚ መስለው ክብርና ስም ይዘው የስለላ ስራቸውን የሚያጧጡፉ ወይም በተቃዋሚው ጎራ ያለውን እርስበርሱ እያናከሱ ጉርሻቸውን የሚቀበሉ እንዳሉም እናውቃለን። ወሬ የፈታው እንዲሉ እርስበርስ በማላተም፣ ጥርጣሬ እንዲፈጠርና መተማመን እንዲጠፋ በማድረግ ስራ የተጠመዱም በርካቶች መሆናቸው ይታወቃል።
ለዚህም ነው እነዚህ ዐይንአውጣዎች ጀንበር ሳለች እሩጥ አይነት ዘዴ የበሉበትን ወጪት ሰብረው ወደሚበላበት ለመጠጋት ቁና ወሬ ይዘው ሲመጡ ዊንድቬን ለንፋስ እንዳልነው ለፖለቲካ አቅጣጫ ትንበያም እነርሱ ያገለግላሉ ማለት የምሻው። እንደዚህ ያሉ ባለ ዘርፈብዙ አንደበቶችን የፖለቲካ ‘ዊንድቬን’ ብንላቸው የሚመጥን ስም ነው። ዊንድቬን ነፋስ በነፈሰበት አቅጣጫ የመሽከርከሩን ያህል እንዲህ አይነት ሞቅ ያለበት አለን የሚሉ ሰዎችን እንደ አሽከርካሪው ንፋስ የመቁጠር አዝማሚያ ሊወገዝ የሚገባው ነው። አቅማቸው ንፋስ የመግፋትና ሞገድ መፍጠር ሳይሆን በነፈሰበት የሚሽከረከሩ ክንፋሱ በላይ ጫጫታ የሚፈጥሩ ናቸውና በዚህ ጫጫታቸው የፖለቲካውን አየር እንዲበክሉ መፍቀድ የሞኝ መንገድ ነው።
ልክ የአየር ትንበያው ላይ እንደተጠቀሰው እነዚህ አመላካች ሰዎች በሚያደርጉት መገለባበጥ የወዲያኛው ቤት ላይጠገን መፍረሱን መገንዘቡ ግን ሊያበረታታ ይገባል። ይሁን እንጂ እንዲህ አይነት ሰዎችን እንደነቢይ መቁጠርና የማይገባቸውን ሽቅብ መቆለል ሁዋላ በአስቸጋሪውና ከፍተኛ መስዋዕትነት በሚከፈልበት ጊዜ ሰው ሆነው በተገኙት ላይ ተረማምደው እንዲሄዱ ማመቻቸት መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ዓላማቸውና ግባቸው ሆዳቸው ብቻ ነውና ሲቃወሙም ሚዛን የሚደፋ ምክንያት የላቸውም፤ ሲደግፉም የእውቀት ገለባነታቸው ከፕሮፓጋንዳ ጠቀሜታ በላይ አይሆንምና ነው።
ሀገራችን ከታገለው አርበኛ ይልቅ የከዳው ነውጠኛ የሚከበርበት፣ ከታገለው ጀግና ይልቅ የሰለለው ባንዳ የሚሾምባት ሀገር ነበረች አሁንም እንደዚያው ነች። እና ዛሬም ይህንኑ መንገድ ተከትለው የሚያምታቱና አንቱ በሉኝ የሚሉ አሉ። ለነዚህ ደግሞ ከበሮ የምንመታና እልል የምንል ራሳችንን የታክቲክና ስትራቴጂ መሀንዲሶች አድርገን የምንመለከት የእውቀትና የልምድ ረሀብተኞች አለን። ይህንን በማስተዋልና ዘወር ብሎ የትናንቱን በማየት ብልህነት ሊታረም የሚገባው ነው እላለሁ።
በእውቀታቸው አነስ ያሉ በልምዳቸው ያልጠነከሩ ግን ሰው በሚፈለግበት ጊዜ ሰው ሆነው የተገኙ፣ ሌሎች የራሳቸውን ህይወት ለማመቻቸት ስራና ትምህርታቸውን ሲማሩ እነርሱ ግን እንኳን ሥራና ትምህርት ሕይወትም ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለው በቃላቸው የተገኙት እየተገፉና እየተወነጀሉ፤ በምትካቸው የጀርባ አጥንት የሌላቸው ልፍሰፈሶች ሲንደላቀቁ መመልከት አዲስ አይደለም። ሌላው ቢቀር ይህ ደካማውና አንገት አስደፊው አሰራራችንን አጥብቀን ልነኮንነው ይገባል። ለዚህም ፖለቲካ ስድብ፣ እርግማንና አሽሙር የሚመስላቸው ሰዎችን አይዞአችሁ ማለቱን ማቆሙ እገዛ ያደርጋል።
በኢትዮጵያ በቻ ሳይሆን በበርካቶች ለነጻነት በተደረጉ ትግሎቸ ላይ የዓላማ ጽናት ያላቸው ለሕዝቡ ነጻነት፣ ሰላምና የሕግ የበላይነት የታገሉ አርበኞች መመታትና መባረር የሚጀምሩት ከነፃነት ማግስት ነው። ከነፃነት በሁዋላ የሚያስፈልጉት የዓላማ ጽናት ያላቸው፣ ቆራጦቹና ጀግኖቹ ሳይሆኑ ለስልጣን አስጊ ያልሆኑት ሰግዶ አደሮችና ወኔ አልባዎቹ ናቸው። እነዚህ አዳኝ ግዳይ እስኪጥል ወይም ተፈጥሮአዊ ሞት ቀለብ አስኪሰፍርላቸው አሰፍስፈው እንደሚጠብቁቱ ጆፌ አሞራዎች ይመሰላሉ። ለገዢው ሰግደው ለእውነት የቆሙትንና መስዋዕትነት የከፈሉትን አንገት የማስደፋት ተግባር ላይ ብርቱዎች በመሆናቸው ለአምባገነኖች መጠናከር ምክንያቶችም ናቸው። ለዚህ ነው ደመናዎች ሁሉ ዝናብ ያዘሉ ያለመሆናቸውን ያህል የትግሉን ጎራ ልንቀላቀል መጣን ያሉ ሁሉ የትግሉ አጋር ናቸው ማለት አስቸጋሪ የሚሆነው።
ይህ ጽሁፍ የነበሩበትን ጎራ ስህተት በሚገባ ተረድተው መንገዱ መንገዴ አይደለም ብለው ስለ እውነት፣ ስለሕዝብና ሀገር ተቆርቋሪ ለመሆን በንጹህ ልብ የሚመጡትን ሳይሆን የፖለቲካ ‘ዊንድቬን’ የሆኑ ጥቅም እስካገኙ ድረስ ከማንም ወግነው ማንንም ለማጥቃት የማይመለሱትን ወዳጅ አድርጎ ማቀፉ ያለውን አደጋ ለማመላከት ነው።
የነጻነት ቀን የመቅረቡን ያህል ጀግኖቻችንና ድላችን ላለማስነጠቅ ተግተን እንሥራ!

Saturday, July 20, 2013

የፊልም አዘጋጇ ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ክስ ቀረበባት

የፊልም አዘጋጇ ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ክስ ቀረበባት

ደራሲዋና አከፋፋዩ ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል
“ፔላማ” የተሰኘው ፊልም በጥንቆላና በመፍትሄው ዙሪያ የሚያጠነጥን እንደሆነ የፊልሙ ደራሲና አዘጋጅ ሜሊ ተስፋዬ የገለፀች ሲሆን፣ ፊልሙ እምነታችንን የሚካ ነው በሚል ቅሬታ አንድ የእምነት ተቋም ለፖሊስ አቤቱታ አቀረበ፡፡ ሜሊ ተስፋዬና የፊልሙ አከፋፋይ ወደ ማዕከላዊ ምርመራ ተጠርተው ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ የፊልሙ በርካታ ተዋናዮችም ቃላቸውን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ ፊልሙ ሃይማኖተን ይነካል የሚል ክስ ያቀረበው “ባፋ አባዩ ገዳ አንድነት የእምነት ተከታዮች ተቋም” መንፈሶቻችን ተነክተዋል፣ የሃይማኖት ተከታዮቻችን ተሰድበዋል ሲል ለፖሊስ አመልክቷል፡፡ ለእምነት የምንገለገልባቸውን ቁሳቁሶች ባካተተው ፊልም፤ ስማችን ጠፍቷል የሚለው ይሄው ተቋም፣ የእምነቱን ተከታዮች የሚያስጨንቅና የሚያሳቅቅ የድፍረት ስራ ተሰርቷል የሚል ክስ እንደቀረበባት ሜሊ ተስፋዬ ተናግራለች፡፡
“እኛ በፊልሙ ላይ የተጠቀሱትን መናፍስት የሚጠቀም የሃይማኖት ተቋም መኖሩን አናውቅም ነበር” የምትለው ሜሊ፤ ፊልሙ ከሁለት አመት በፊት በብሔራዊ ቲያትር ከተመረቀ በኋላ በተለያዩ የአገራችን ሲኒማ ቤቶች ከአገር ውጭም በዱባይ፣ በአቡዳቢ እና በሌሎች የአረብ ሀገራት እንዲሁም በጀርመን፣ በሆላንድ፣ በቤልጅየም፣ በፈረንሳይና በጣሊያን ከተሞች ፊልሙ ለእይታ መቅረቡንም ተናግራለች፡፡
በፖሊስ ፕሮግራም የተላለፉ የታምራት ገለታ ታሪኮች እንዲሁም “የአዳል ሞቴ” መንፈስ አለብኝ እያለ ብዙዎችን ያስጨነቀ የአንድ ጠንቋይ ታሪክ ለፊልሙ መነሻ እንደሆኑላት ትገልፃለች – ደራሲዋ፡፡ በዚህ መነሻ ጥናት አካሂዳ ፊልሙ እንደተሰራ ያወሳችው ሜሊ፤ ዋናው ገፀ ባህሪ በሀገራችን የሚታወቁትና አዳልሞቴ፣ ጠቋር፣ ወሰንጋላ የሚባሉ መናፍስትን እየጠራ ሰዎችን ሲያታልል፣ ገንዘባቸውን ሲበዘብዝና ለሞት ሲያበቃቸው ይታያል ብላለች፡፡ የፊልም ሙያዬን በመጠቀም ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስራ ለማቅረብ እንጂ የማንንም መብት ለመንካት አስቤ አልሰራሁም የምትለው ሜሊ፤ ለፖሊስ ቃሏን ከሰጠች በኋላ በዋስ እንደተለቀቀች ተናግራለች፡፡

ነፃነት የማያውቅ ነፃ አውጭ፦ ህወሀት

ነፃነት የማያውቅ ነፃ አውጭ፦ ህወሀት

የህወሀት መስራቾች “መግለጫ” በሚል ርዕስ በ1968 ካሰራጩት በባለ 28 ገፁ በእጅ የተፃፈው ማኒፌስቷቸው መቅድም ላይ እንዲህ ይላል “ይህ መፅሔት የትግራይ ሕዝብ ሀቀኛ ወኪል የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት (ተ.ኀ.ህ.ት)መግለጫና የትግሉ መመሪያ ነው።ልብ በሉ ህወሀት ገና በምስረታው ትግል ሳይጀምርና በትግራይ ሕዝብ ሳይወከል ራሱን ግን የምስኪኑና ጭቁኑ ሕዝብ ወኪል አድርጎ እንዲያውም ከወኪሎች ሁሉ አልቆ “ሀቀኛ ወኪልነትን” ለራሱ ሸልሟል።ህወሀት ከ1968 ዓ.ም በኋላ ለትግራይ ሕዝብ የምታገለው እኔ ብቻ ነኝ ከኛ ከህወሀቶች ውጭ በትግራይ ውስጥ ማንንም ማየት አልፈልግም አለ።ይህንንም አስታኮ ተነሳሁበት ያለውን አላማ ወደጎን አድርጎ ትግራይ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች ላይ ዘመቻ ጀመረ የመጀመሪያው ሰለባ በዮሀንስ ተክለሀይማኖት የሚመራው እንደ ህወሀት ትግራይን ለመገንጠል የሚታገለው የትግራይ ነፃነት ግንባር ሆነ ህወሀት በዚህ አላበቃም በራስ መንገሻ የሚመራው ኢዲዩም ከደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ ከትግራይ እንዲሸሽ ተደረገ።ከሁሉ የባሰውን ወንጀል ህወሀት የሰራው ግን የኢህአፓ አባል በሆኑ የትግራይ ተወላጆችና በኢህአፓ የጦር ክንፍ ኢህአሰ ላይ ነበር።በመጀመሪያ ኢህአሰ ከትግራይ የጦር ሰፈሩ ከአሲንባ ለቆ እንዲወጣ የፈለጉት የህወሀት አመራሮች ትግራይ ውስጥ በኢህአፓ ስር በትግራይ ተወላጅ አባሎቹ የተዘረጋውን መዋቅር ለደርግ አሳልፋ በመስጠት እንዲሁም ደርግን ሰርጎ በመግባት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የኢህአፓ አባሎች ብቻ ሳይሆኑ ከህወሀት ጋር አልቆም ያሉ በርካታ የትግራይ ተወላጆች የቀይሽብር ሰለባ እንዲሆኑ አድርገዋል።የኢህአፓ የጦር ክንፍ የሆነውን ኢህአሰን ደግሞ ሰርጎ በመግባት እና እንቅስቃሴውን ለደርግ አሳልፎ በመስጠት እንዲሁም በተደጋጋሚ ጊዜ ጦርነት በመግጠም ከሁለት ሀይል ጋር ከደርግም ከህወሀትም ጋር ጦርነት የገባው የኢህአሰ ጦር ከፓርቲውና ከጦሩ አማራር ችግር ጋር ተዳምሮ ኢህአሰ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ ሆኗል።
የጫካ ባህሪው ያልለቀቀው ህወሀት አራት ኪሎ ቤተመንግስት ሲከትም ከነጫካ ባህሪው ነበር አይደለም በትግራይ በመላው ኢትዮጵያ ከኔ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ አልይ አለ ይኸው ባህሪው ለ22 ዓመታት በኢትዮጵያችን ተንሰራፍቶ የኋላ ታሪክ እየጠቀሰ ቁልፍ የመንግስት ስልጣኖችን ፣ ፖሊስ መከላከያ ሰራዊትንና ደህንነትን ፣ የሀገሪቱን ኢኮነሚ ፣ ሚዲያውን ምን የቀረ አለ ከስትንፋሳችን ውጭ ያለውን ነገር በሙሉ ተቆጣጥሮ የሰቆቃ ህይወትን እንድንገፋ ተገደናል በሁኑ ከእንግዲህ ዘርና ብሔርን መሰረት ባደረጉ ነፃነት የማያውቁ ነፃ አውጭዎች ስር ለመተዳደር መሻት ይኖርብናል!?

Friday, July 19, 2013

‹‹ሲመቸኝ ዝም ብል፣ ዝም ያልኩ መስሎታል፣ ሲታሰብ ነው እንጂ ዝም ማለት የታል፡፡›› Temesgen Desalegn

‹‹ሲመቸኝ ዝም ብል፣ ዝም ያልኩ መስሎታል፣
ሲታሰብ ነው እንጂ ዝም ማለት የታል፡፡››
እነሆም ይህ የዮፍታሔ ንጉሴ ስንኝ ‹‹የት ጠፋህ?›› ብለው ለተጨነቁልኝ ወዳጅ ዘመድ መላሽ ይሆን ዘንድ ወደድኩ፤
የነገው ቅዳሜ ‹‹ፋክት›› በተሰኘ መፅሄት ይዋጃልና አንባቢያኖቻችን ሆይ ደስታችን ደስታችው ይሁን! ይህ መፅሄት ባለፈው ዓመት ለሶስት ጊዜ ያህል ከታተመ በኋላ በኪሳራ የተዘጋ ነበር፤ አሁን ትንሳኤው ሆኖለት የሚከተሉትን አምደኞች አሰባስቦ ተመልሷል፡፡
1.ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፡-ሀ/ የመንግስትን ስም ማጥፋት፤ ክቡርነታቸው ናቸው መንግስት?
ለ/ ምንም ይሁን ምን፣ የትም ይሁን የት አበሻ መናገር ይወዳል
(ሁለት የተለያየ ፅሁፍ)
2.ተመስገን ደሳለኝ፡- ሀ/ ብርቱው ሰው! /The Iron Man/
ለ/ ኢህአፓና የገሀነም ቅፅሩ!
(ሁለት የተለያየ ፅሁፍ)
3.ሙሉነህ አያሌው፡- ለውጥ አለ ወይንስ…?
4.ሐይለመስቀል በሸዋምየለ፡- በብሄርተኛ ልሂቃን የምትታመስ አገር
5.ዳዊት ታደሰ፡- ኡጃማ፡ የብርቱካን መንገድ
6.አቤ ቶኪቻው፡- ሀገራችንን ኢህአዴግ አክራሪነት እንደሚያሰጋት ተሰጋ!
7.ደ/ር በድሉ ወቅጅራ፡- ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል አራት)
8.ብርሃኑ ደቦጭ፡- የመለስ ውርሶችና ለሀልዮት የማይመቸው የኢህአዴግ ተፈጥሮ
9.እንዳለጌታ ከበደ፡- ቆራሌው፡- ነባር ልሂቃንን ፍለጋ
10.ቴውድሮስ ተ/አረጋይ፡- ለጌኛዎቹ ሳር ስጧቸው
እና የተለያዩ ፀሀፊያን ተሳትፈውበታል፡፡ ከዚህ በኋላም ዘውትር ቅዳሜ በየሳምንቱ አንባቢያን እጅ ትደርሳለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ማስታወሻ ለሪፖርተር ጋዜጣ
ሐምሌ አስር ረቡዕ በወጣው ህትመት ላይ ‹‹‹የነፃነት ዋጋ ስንት ነው?› ዥንጉርጉርነት›› በሚል ርዕስ በተለይ ደግሞ ‹‹ያላነበቡ ገምጋሚዎች›› በምትለው ግልገል ርዕስ ስር የተካተተው ሃሳብ ቅንነት የጎደላው ብቻ ሳይሆን ፍፁም በሬ ወለደ መሆኑን ስገልፅ ከጥልቅ ሀዘን ጋር ነው፡፡ በዕለቱ አቶ ግርማ ሰይፉ ‹‹የነፃነት ዋጋ ስንት ነው?›› በሚል ርዕስ ያሳተመው መፅሀፍ የምረቃ ፕሮግራም በውሃ ልማት አዳራሽ መካሄዱ እውነት ቢሆንም እኔ የተገኘሁት የመፅሀፉ ገምጋሚ ተደርጌ እንደሆነ የተገለፀው ግን ውሸት ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ድርሻ ከመፅሀፉ ውጪ ያለውን የግርማን ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መናገር ብቻ መሆኑን አስቀድሜ ከአዘጋጆቹ ጋር ስምምነት ላይ ደርሼአለሁ፡፡ የመድረክ መሪውም መፅሀፉ ትላንት ማታ እንደደረሰኝና እንዳላነበብኩት ተናግሮ ነው ወደ መነጋገሪያው የጋበዘኝ፤ እኔም መፃሀፉ ትላንት ምሽት እንደደረሰኝና ለማንበብ እንዳልቻልኩ ከተናገርኩ በኋላ፤ ምንም እንኳ ከመፅሀፉ ውጪ ባሉ ጉዳዮች ላይ ተናጋሪ ሆኜ ብጋበዝም፣ በቂ ምክንያት ቢኖረኝም ሳለናበው በመምጣቴ እናንተን ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ሆኖ ስላገኘሁት ‹‹ይቅርታ እጠይቃለሁ›› በሚል መግቢያነው ንግግሬን የጀመርኩት፡፡
ታዲያ ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ ሪፖርተር ጋዜጣ ከየት አምጥቶት ይሆን ‹‹ይህንን መፅሀፍ የገመገሙት ዶ/ር ኃይሉ አርዓያና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ናቸው›› ያለው? ስለቀጣዩ ምርጫ ዋጋ ቢስነትም የተናገርኩት መፅሀፉን ጠቅሼ ሳይሆን ከስርዓቱ ጉልበተኝነት ተነስቼ መሆኑንም ሪፖርተር እንዴት ሊሳተው እንደቻለ ግራ አጋቢ ነው፡፡ ‹‹ተቃዋሚዎች ለመሞት እንጂ ለመግደል አልተዘጋጁም›› የሚል ቃል እንዳልወጣኝም በአዳራሹ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ የሚያውቀው ነው፤ (በነገራችን ላይ ይህንን የምለው ከፍርሃት አይደለም፤ ውሸት ስለሆነ ብቻ ነው) እኔ በዕለቱ የተናገርኩት ‹‹ለስርዓት ለውጥ ምርጫን የግድ ጠብቁ የሚል ህግ የለም፤ አገዛዙ ካልተመቸን አደባባይ ወጥተን ቤተ-መንግስቱን ነቅንቀን ለውጥ ማምጣት አለብን፤ ይህ ማንም የማይሰጥን፣ ማንም የማይነሳን መብታችን ነው፤ መልካምነቱ ደግሞ በሰላማዊ ትግል ውስጥ መሞት እንጂ መግደል የለም፤ መታሰር እንጂ ማሰር የለም፤ አካል መጉደል እንጂ አካል ማጉደል የለም፤ መዘረፍ እንጂ መዝረፍ የለም…›› ነው ያልኩት፡፡ ከሁሉም የሚገርመው የጋዜጣው ነጭ ውሸት ‹‹‹በ2006 ዓ.ም ተቃዋሚዎችን ከውጪ ሆነን ከማየት ወጥተን ትግሉን እናፋፍመው› የሚለው ንግግሩ በከፍተኛ ጭብጨባ የታጀበ ነበር፡፡ በማጠናቀቂያ አስተያየቱም ‹መፅሀፉን ባላነበውም ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ እንደነገሩን…› ሲል ሲያጨበጭቡለት የነበሩትን ታዳሚዎች ያሳዘነ ነበር፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎችም ይህንን ቅሬታ ነው የገለፁት›› የሚለው ነው፤ መቼም እነዚህ ሰዎች ኢቲቪ ‹‹አንዳንድ ነዋሪዎች…›› እያለ የሚጠቅሳቸው ስም፣ ፆታ፣ አድራሻ፣ ዜግነት ያሌላቸው፣ እነዛ የማይጨበጡት፣ የማይዳሰሱት፣ የማይናገሩት… ሰዎች ካልሆኑ በቀረ ዕድምተኞቹ የተናገርኩትን በሚገባ ሰምተዋል፡፡
በመጨረሻም ስለማይመቸኝ መከራከሪያ፡-
ሪፖርተር በወቅቱ ያነጋገራቸው ሰዎች ‹‹ተቃዋሚ ነው ወይስ ጋዜጠኛ?›› የሚል ግርምት የሚያጭር ጥያቄ እንዳቀረቡለት ገለጿል፡፡ ይህ ግን ምን ማለት ነው? ጋዜጠኛ ሀገር የለውም፣ የፖለቲካ አቋም የለውም ያለውስ ማን ነው? እሺ! ሌላው ይቅር ይህ ሁሉ የመንግስት እና ‹‹ቅምጥ›› ጋዜጠኛ ‹‹ኢህአዴግ ጌታ ነው›› ሲል መዋሉን ስለምን ሪፖርተርን አላሳሰበውም? ወይስ ጋዜጠኛ የስርዓቱ ደጋፊ ብቻ ነው መሆን የሚችለው የሚል አመክንዮ አለ?
የሆነ ሆኖ አዎ! እኔ ጋዜጠኛ ነኝ፤ አዎ! የስርዓት ለውጥ የሚፈልግ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ነኝ-ሀገሬን እየገዳለት ነውና፤ አዎ! አደባባይ መውጣት ከምርጫም ይሁን ከሌላ በላይ ቅድሚያ እንደሚሰጠው ደጋግሜ እናገራለሁ፤ በ2007 ዓ.ም ለሚደረገው ምርጫም (ምን አልባት ኢህአዴግ በእኛ ድክመት እስካዛ ድርስ ከቆየ ማለቴ ነው) ፕ/ር መርጋ በቃና የሚመራውን ምርጫ ቦርድ ተማምኜ በፍፁም የምርጫ ካርድ አልወስድም፡፡ ምክንያቱም አደባባይ በመውጣት መሬት አርድ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሮ ለውጥ ለማምጣት እንጂ ለመምረጥና ለመጭበርበር አልተዘጋጀውምና፤ በአናቱም እውነት እውነት እላቸኋላሁ ከዚህ በኋላ ታሪክ ለመቀየር ብዙ እንጠብቅም፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

“ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የምናደርገው ትግል በስም ማጥፋትና በፍረጃ አይገታም!” ሰማያዊ ፓርቲ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ በሃገራችን የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የአስተዳደር ብልሹነት እንዲስተካከል የመንግሥት አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ነገርግን እነዚህ ጥያቄዎቻችን በመንግሥት በኩል ምላሽ ስለተነፈጋቸው ጥያቄዎቹ ከፍ ባለደረጃ ትኩረት እንዲያገኙ ሆነው መቅረብ እንዳለባቸው ተገንዝበናል፡፡ በዚህም መሰረት ጥያቄዎቹን በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቅ እንዳለበት ወስኖ ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሔደው ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ በተጨማሪም ጥያቄዎቻችን ከመንግሥት በኩል በሦስት ወር ጊዜ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ ሌላ የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ባለ ደረጃ የሚጠራ ስለመሆኑ ፓርቲው አቋሙን በሰልፉ ዕለት አሳውቋል፡፡Statement from Semayawi party of Ethiopia, regarding Nile issue.
ይሁንእንጂ ሰልፉ ከተጠናቀቀበት ዕለት ጀምሮ በገዥው ፓርቲና በመንግሥት ተወካዮች የተሠጡ መግለጫዎች ያስገነዘቡን መፍትሔ እንዲሠጣቸው ለቀረቡ ጥያቄዎች መንግስት ተገቢውን መልስ ለመስጠት ምንም ዓይነት ፍላጐት እንደሌለው ነው፡፡ ከዚህም አልፎ መንግስት ጥያቄዎቹ የቀረቡበትን መንፈስ እንኳ በቀናነት ለመቀበል ያልፈለገ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፓርቲያችንን ለመጫንና ስሙን ለማጉደፍ በፕሮግራሙም ሆነ በሥራ እንቅስቃሴው የሌለበትን በአክራሪነትና በአሸባሪነት ለመወንጀል ተደጋጋሚ ጥረት እያደረገ መሆኑን ከሚሠጣቸው መግለጫዎች ተረድተናል፡፡

እህአዴግዬ የምር ታሳዝነኝ ጀመር…!

601337_493630697377051_1548754887_n

እህአዴግዬ የምር ታሳዝነኝ ጀመር…!
ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በሙሉ በአንድ ላ እየተረባረቡባት ነውኮ! ይሄው ሀምሌ 14 አረና ትግራይ በመቐለ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በህዝባዊ ስብሰባው ላይ “ሜድ ኢን ኢህአዴግ” በሆኑ ችግሮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አንድ በሉልኝ፤
አንድነት ከሃምሌ 21 እስከ መስከረም 5 ድረስ ተለያዩ ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ሰላማዊ ሰልፎችን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለማድረግ አቅዷል፡፡
ሁለት አትሉም…
ሰማያዊ ፓርቲ ነሀሴ 26 በአዲሳባ “ያንን ነገር ምንው ዝም አልሽው” ብሎ ባለፈው ሰላማዊ ሰልፍ የጠየቀውን ጥያቄ መልሶ ኢህአዴግዬን ሊጠይቃት ቀጠሮ ይዟል፡፡
ይሄ ሶስተኛው መሆኑ ነው…
ይሄው የሙስሊም ወንድሞቻችን የእምነት ነፃነት ጥያቄ በዚህ በፆም ወቅት ደግሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
አራት…
የምር ኢህአዴግዬ ታሳዝነኝ ጀመር፡፡ ተቃዋሚዎቹ በሙሉ በዚህም በዚያም ወጥረው ያዟትኮ…! እኔ እርሷን ብሆን ኖሮ…  የሚነሱትን ጥያቄዎች በሙሉ ለእልህ ብዬ መልሼ መልሼ ተቃዋሚዎችን ጉድ አደርጋቸው ነበር… ኢህአዴግ ግን ሁልግዜ እንደሚፎርፍ ተማሪ አንድ ጥያቄ እንኳ መመለስ ተስኗት… ሳያት ከምር አሳዘነችኝ…
አሁን ሁሉም ተቃዋሚዎች ሙዳቸው መጥቷል፡፡ እናም በየፊናው ህዝቡን እያስተባበሩ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ማስተባበር ብቻ ሳይሆን መተባበር ከጨመሩበትማ…
“ኢህአዴግዬ ሲለምኗት ቀርታ ሲጎትቷት…” የሚለው ተረት ሊተረትባት ነው…
ምስኪን እንዳልልሽ ትዕቢተኛ ነሽ
እርኩስ እንዳልልሽ ያገሬ ሰው ነሽ
ይሄ አልሰማ ማለት ሰዎች ሲነግሩሽ
አኔንም አይበጀኝ አንቺም አይጠቅምሽ
ባክሽ
ባክሽ
ባክሽ
ባክሽ
(ምነው ቤት መምቻው ላይ “ሽ” በዛሳ…. ብሎ የሚያሽሟጥጥ ካለ ከ”ሽ” በላይ ቤት መምታት… ማምታታት…ብለን አልሸነፍ እንላለን!)
እውነቱን ለመናገር ግን ኢህአዴግዬ ምሳሩ በዛባትና የምር እያሳዘነችኝ መጣች!

Wednesday, July 17, 2013

የፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን ዘጋ

e520593e773260ae27abfdea1303b67a_L

- ‹‹ኮሌጁን የመዝጋት መብት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ነው›› የመንፈሳዊ ኮሌጁ ተማሪዎች
ከመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎቹ በሚያነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎች፣ የመማር ማስተማር ሒደት ሲስተጓጎል በመቆየቱና ባለፈው ሳምንት ደግሞ የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት አጠቃላይ ፈተና እንዳይሰጥ ተስተጓጉሏል በሚል ምክንያት፣ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቀን ተማሪዎች ትምህርት ተቋርጦ እንዲዘጋ አደረገ፡፡
በመንበር ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ኮሌጁ ከሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም. እስከ መስከረም አጋማሽ 2006 ዓ.ም. ድረስ ተዘግቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ሲሰጥ የነበረውን የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት አጠቃላይ ፈተና ተማሪዎቹ እንዳይሰጥ በማድረጋቸው ነው፡፡ ተማሪዎቹ ፈተናው ይሰጣል በተባለበት ዕለት የኮሌጁን ቢሮዎች በመዝጋትና ሊፈተኑ የመጡ መምህራንን በመከልከላቸው መሆኑን ደብዳቤው ያስረዳል፡፡ እንዲዘጋ በጽሕፈት ቤቱ ውሳኔ የተላለፈበት የቀኑ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሲሆን፣ ተማሪዎቹም ለሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም. በሰላማዊ መንገድ የኮሌጁን ግቢ ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
‹‹ኮሌጁን የመዝጋት መብት ያለው የከፈተው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ነው፤›› በማለት ተማሪዎቹ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጻፉትን ደብዳቤ በመቃወም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ተማሪዎቹ እንደገለጹት፣ ቀደም ብሎ በኮሌጁና በአስተዳዳሪዎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት ትምህርት መቋረጡ እውነት ነው፡፡ በመሆኑም የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት የትምህርት ጊዜ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡ ፈተና ይሰጣል የተባለበት ተመራቂ ተማሪዎች በመመረቂያ ጽሑፋቸው ላይ ‹‹ዲፌንስ›› የሚያደርጉበት ቀን በመሆኑ መጨናነቅ እንዳይፈጠርና የፈተና ጊዜያቸው እንዲራዘምላቸው የኮሌጁ የበላይ ኃላፊን አቡነ ጢሞቲዎስን ለማነጋገር ሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. በቢሯቸው መገኘታቸውን አስረድተዋል፡፡
ኃላፊውን ለማግኘት በቢሯቸው በራፍ ላይ በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ ‹‹ችግር ሊፈጥሩብዎት እየጠበቁዎት ነው›› የሚል የተሳሳተ መረጃ ስለደረሳቸው አቡነ ጢሞቲዎስ ሳይገኙ በመቅረታቸው፣ ተማሪዎቹ ‹‹አንማርም፣ ፈተና አንፈተንም›› ብለዋል የሚል ክስ ወይም ከእውነት የራቀ አቤቱታ እንደቀረበባቸው ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ልዩ ጽሕፈት ቤቱ የኮሌጁ ኃላፊዎችንና ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት ሲችል በሌለው ሥልጣን እንዲሁም ቀደም ብሎ በተማሪዎቹና በኮሌጁ ኃላፊዎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት ተማሪዎቹ ክስ ሲመሠርቱ፣ በክሱ ውስጥ ባካተቷቸው ብፁዕ አቡነ ገሪማ ፊርማ ኮሌጁ መዘጋቱ እንዳስገረማቸው ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎቹ ለቅዱስ ሲኖዶስ በጻፉት ደብዳቤ የጠየቁት ኮሌጁ እንዲዘጋ የተጻፈው ደብዳቤ ሕጋዊ ባለመሆኑ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲታይላቸው፣ ቦርዱ እንዲያጣራ የተሰጠውን ኃላፊነት ለስድስት ወራት ዝም ብሎ ከርሞ ከተጠያቂነት ለመሸሽ በመሆኑ በሕግ እንዲታይላቸው፣ ቦርዱ የመንግሥትና የኮሌጁን ጊዜ በማጥፋቱ ዕርምጃ እንዲወሰድበት ነው፡፡
በኮሌጁ አስተዳደርና በተማሪዎቹ መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ቢታወቅም ቅዱስ ፓትርያርኩን ሊያነጋግሯቸው እየለመኑ መሆኑን የሚገልጹት ተማሪዎቹ፣ ኮሌጁ እንዲዘጋ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የተጻፈው ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ግልባጭ አለመደረጉ፣ ኮሌጁ የተከፈተው ለመደበኛ ተማሪዎች ሆኖ ሳለ ‹‹የንግድ ማዕከል አደረጉት›› በማለት በመጮኻቸው የቀን ተማሪዎች ብቻ እንዲባረሩ መደረጉ ተገቢና ቤተ ክርስቲያንም እንደማትፈቅድ ተናግረዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም በቃለ በሕጉ መሠረት በምልዓተ ጉባዔው የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ አድርጎ እነሱንና ኮሌጁን ከአደጋ እንዲታደግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ይድረስ ለተገፋው ወገኔ !. . . "ህገ መንግስት ተጥሷል!" ካልክ ድምጽህን በሰላማዊ ተቃውሞ አሰማ !


letter


ይድረስ ትናንተም ሆነ ዛሬ ግፍ በነገሰባት ምድር ኑሮን በመከራ ለምትገፋው ወገኔ ! ይድረስ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ በደል ለተጫነብህ ፣ ፍትህ ርትዕ ተዛብቶ የአስተዳደር ሚዛኑ ኑሮህን ላጨለመው ወገኔ ! ይድረስ ከዲስኩር  ባላለፈ  ”የእድገት ስልጣኔ መንገድ እየተጓዝክ ነው ” ለሚሉህ ፣ ይድረስ ግልጽነት በጎደለው “መልካም አስተዳደር” ለምትረገጠው ታጋሽ ወገን፣ ይድረስ ትናንትም ሆነ ዛሬ ከአብራክህ ወጥተው አንተን ያልሆኑ ፣ ህመምህ የማያማቸው፣ በደልህ በማይገባቸው የመንግስት ምስለኔ ልጆችህ እየተሰቃየህ ላለህው ! ይድረስ የግፍ በደል ቀንበር ከትከሻህ ላልወረደልህ፣ ስቃይ መከራው ላላባራልህ ይድረስ ለከልታማው ወገኔ! ይድረስ የአንድ ጎልማሳ እድሜን በጭቆና መግፋቱ እያመመህም ቢሆን ለቻለከው፣ በቁጣ አመጻን ከመግለጽ ተገትተህ ጎስቋላ ኑሮን በዝምታ፣ በይሁንታ እየገፋህ ላለህው ወገኔ! በኮራህ በደላህበት፣ አክብረህ በተከበርክበት ቅየ ያ ክፉ ቀን አለፈ ስትል፣ ዛሬም ክፉው ቀን ተከትሎ  አበሳህን እያሳየህ ለምትገኘው ተገፊ ወገኔ!
ኑሮ ሳይደላህ አመጻን አለመምረጥህ እና በደልን በዝምታ ቁዘማ ማሳለፍን የመምረጥ ምክንያትህን ከቀየው የወጣሁ ነኝና አውቀዋለሁ ! ጎንደሬውም ሆንክ ወሎየው እንደቀረው ኢትዮጵያዊ በጨካኙ ወታደራዊ ጁንታ አገዛዝ ከአብራክህበወጡ ጨካኝ ልጆችህ የጋለ ብረት አለሎ ተቀጥቅጠሃል። ልጆችህ ታስረው ርህራሄ በሌላቸው የአገዛዙ አቀንቃኞች ቁም ስቅላቸውን እያዩ ተገርፈዋል። በግፍ የተገደሉ ልጆችህን አስከሬን በወጉ እንዳትቀብር ተደርገሃል። መሽቶ እስኪነጋ በጨካኞች አረመኔያዊ የቀይ ነጭ ሽብር ዘመቻ ባሩድ የተረሸኑ ልጆችህ ደም ጉራንጉሩን፣አውራ ጎዳናዎችና አደባባዩን አጨቅይቶት የከፋ የሽብር ጊዜ አሳልፈሃል፣ አይገፋ የለም ቁጣህን አምቀህ ክፉውን ቀን በሆደ ሰፊነት  ገፍተሃል! በዚያ ክፉ ዘመን የስጋ ክፋይ ወንድሞቸን ፣ “የት ይደርሳሉ!” የተባሉ የዘመድ አዝማድ ጎረቤት ትንታግ ወጣቶችን በግፈኛው አገዛዝ የተነጠቁ ወገኖች አካል ነኝ ። ስለዚያ ዘመን የወላድ መከራ የማውቀው ጥቂት ባይባልም፣ ሰለነበረው ስርአት አስከፊነት የታሪክ መዛግብት አገላብጫለሁ ፣ የአይን እማኞችን “አህ” ብየ አድምጫለሁ! ከሁሉም በላይ የልጆቻቸውን የሞት መርዶ ለመስማት ብርቅ ሆኖ ሳይሳካላቸው ከቀሩት እናቶች መካከል ልጅ ብሆንም ያኔ የእኔዋን እናት እንባ አልረሳውም! በድህነት ቤት ልጅ ወልደው ፣አሳድገው በሞት ሲነጠቁ ለመቅበር ሳይታደሉ የቀሩት እናቶችን ቤት ይቁጠረው። ማቅ ለብሰው ማቅ መስለው አመታትን የገፉ እናቶች አብራክ ውጤት ነኝና የዘመኑን ስርአት ክፋት ጭነት አውቀዋለሁ። በዚያ የግፍ ዘመን በቀሩት የሃገሪቱ ክፍል እንደሆነው ሁሉ በጎንደር በጎጃም እና በወሎ ዋና ከተሞች ያለተወሰነው የግፍ እርምጃ በገጠር የወረዳና የአውራጃ ከተሞች በወጣቱ ደም የጨቀዩበተት ዘመን ፍጹም አይረሳም ።
ወገኔ ሆይ ! እዚህ ባደረሰህ መንገድ ለጋ ወጣት ልጆችህን ገብረሃልና የዛሬው ዝምታህ አይደንቀኝም ። በግፍ ጭቆናው ዘመን የሌሊቱ ጥይት እሩምታ በረድ ሲል የማለዳው ደሮ ሲጮህ ሬሳ የመፈለጉ አሰቃቂ የታሪክ ሂደት እንደ ቀረው የኢትዮጵያ ወገንህ ምሬት ሃዘንክን ጠባሳ ጥሎብሃልና ዛሬ አንገት መድፋት መቆዘምህ አያስደንቀኝም። ዛሬም ዘመን ከፍቶህ ዳግም ትንታግ ልጆችህን አንዳታጣ ስጋት ሆኖብህ ዝም በማለትህ “ሃሞትህ ፈሰሰ!” እያልኩ ላሳብቅብህ የረከሰ  ሰብዕናን አውርሰህ አላሳደግከኝምና ፣ በቁዘማ ዝምታህ አልፈርድም ። በከተማ ባሩድ እና ባልጠቀመን የእርስ በርስ ጦርነት የአብራክህን ክፋይ ልጆችህን በጆፊ አሞራ የተነጠቅክ የህብረተሰብ ክፍል ነህና ህመምህ ህምሜ በመሆኑ ይገባኛል። እናም የዛሬ ህመም ስጋትክን አሳምሬ አውቀዋለሁ ! እናም ” ለምን ግፍ ሲጫኑህ  በዝምታ ትቆዝማለህ? “ለማለት አይዳዳኝም! ያኔ! ያ ክፉ የደርግ ስርአት ያከትም ዘንድ ሃዘንክን ሃዘን አድርገህ በአገዛዙ ላይ አኮረፍክ ፣ ዳሩ ግን ልክ እንደ ዛሬው በዝምታ ቁዘማ አንገትክን ደፍተህ ግን አልተቀመጥክም ። ለምስክር የተረፉ ልጆችህ ለመስዋዕት በማዘጋጀት መርቀህ ወደ መራራው ትግል መርቀህ ላክካቸው ፣ እኒያ አንበሶች ተራራ ቋጥኝ ቧጠው ፣ ሸንተረር ወንዙን ተጋፍተው ተሻግረው ብሩህ በመከባበር የተገነባች ኢትዮጵያን ይፈጥሩ ዘንድ ነበር ።
መራራው መስዋዕትነት በደም ተከፍሎ ያገኘህውን ውጤት ቢያሳዝንም ለሰላም ሲባል ይሁንታህን ሰጠህ ! ዲሞክራሲ ተሰብኮ እንለይ ያሉት ተለይተው፣ሃገሬው በቋንቋ ሲደለደል ሌላ መከራ ለመምጣቱ ምልክቶች ቢታዩም ይህንንም ይሁን አልክ! ለሰላም ለእድገት ሲባል! የሰቆጣ አላማጣው ፣ የሁመራና የወልቃይት ጠገዴውን ክፍፍልም ሳትመርጥ ፣ ሳትወድ የተጫነብህ ቢሆንም ይህንንም በዝምታ ቁጭት አለፍከው ! ያልቻልከውን ህመም የመጣብህ ፣ ከአመታት በፊት ከሱዳን የሚዋሰነው ድንግሉ የሃገርህ መሬት ከፍትህ ርትህ ውጭ ሃገሬው እየተፈናቀለ ለሱዳን እንዲሰጥ መደረጉ ነበር። ይህ አስቆጭቶ ቢያንገበግብህም ዝምታ ቁዘማህ ዛሬም ትዕግስት መሆኑን የሚረዱ ምስለኔዎችን አልታደልክም!
እናም የደም ክፋይ ነኝና ምክሬን ትሰማ እማጸንሃለሁ ! የተሰጠህን ዲሞክራሲያዊ መብት ተጠቀምበት ! ዝምታ ቁዘማውን ፣ ቁጭት ንዴት አቤቱታህን በሰላማዊ ተቃውሞዎች ሁሉ ተሰልፈህ ጥያቄዎችህን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጽህን ከፍ አድርገህ በማሰማት ዝምታህን ትሰብር ዘንድ እመክርሃለሁ!
ኑሮህ ከድጡ ወደ ማጡ የመሆኑን ግራ አጋቢ እንቆቅልሽ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያለ ፣ ድህነት እና ስራ አጥነት በሃገር ነግሰው ፣ ኢኮኖሚ የሚሉት “አደገ !” ይሉናል ። ለእድገቱ ዋቢ ደግሞ በኑሮውን ጣራ መንካት የተደቆስውን ያንተን  ጓዳ የማያውቁት የአለም ገንዘብ ድርጅት እና ከአመት አመት የሚሰጠው የእድገት ቁጥር ከፍ ማለት ብቻ ነው ። ምድር ላይ ያለውን እውነታ ግን ከሚባለው የተለየ ነው! የኢኮኖሚው ብቻውን ማደግ ከመንገድና ከፎቅ ግንባታ ያለፈ ላለመሆኑ ብዙ ማለት ይቻላል ። የኢኮኖሚው ማደግ በአንተ በዜጋው የለት ተለት ኑሮ ላይ የማይታይ የማይዳሰስ ለመሆኑ ለማንም የተደበቀ አይደለም ። በኑሮው ጣራ መንካት ፣ በድህነቱ፣ በመልካም አስተዳደር እጦትና በስራ አጥነት ምክንያት እኔ ወዳለሁበት አረብ ሃገር ብቻ ያለ ህጋዊ ማዕቀፍ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ እድሜያቸው ለአቅመ አዳም ያለደረሱት ዜጎች በህጋዊ ኮንትራት ስም ተሰደዋል። እኒህ አብዛኛው ከገጠሩ የሃገራችን ክፍሎች በደላላ ተግዘው የመጡት አብዛኛው ሴት እህቶች እድሜያቸውን ቆልለው ሲሰደዱ እንኳ ከልካይ የለም። ይህ ብቻ አይደለም ። ለስራ ወደ ስለሚሔዱበት ሃገርም ሆነ ሰለሚሰሩት ስራ በቂ መረጃ አይሰጣቸውም! ችግር ቢገጥማቸው ለማን አቤት አንደሚሉና ወዴት እንደ ሚሄዱ አያውቁም! የመልካም አስተዳደሩ እና የመንግስት ተቀቋማት ግልጽነት ብሎም ተጠያቂነት አለመኖር ድህነት እንዳሸሸው ዜጋ ድንበር ለመሻገሩ ብዙ አመላካች መረጃዎችን ማቅረብ እችላለሁ ! በዋናነት የሚነሳው ዜጎች ከሃገር በስራ ኮንትራት ከመላካቸው አስቀድሞ በሃገሮች መካከል ግልጽ ስምምነት አለመደረጉ ነው። በዚህ ሁኔታ የተሰደዱትም ቢሆን የመብት ጥሰት ሲገጥማቸው አቤት ብለው ወደ ፍትህ የሚያቀርባቸው የተዳራጁ ሚስዮኖች አሉ ከማለት የሉም ማለት ይቀላል !
ወገኔ ሆይ! የዜጎች የከፋ ስደትና የመብት ጥበቃ ጉድለት መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ለመንግስት ያለመታከት ተናግሬ ፣ መክሬ ፣ ዘክሬ የሰማኝ የለም! እናም ይህ በአብራክህ ክፋዮች ላይ እየደረሰ ላለው በደል በማናቸውም ስብሰባም ሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ተሳትፎ በማድረግ ድምጽህን እንድታሰማ እመክርሃለሁ! አማጸንሃለሁ!  የህዝብን ድምጽ የሚሰማ መንግስት ይስጠን!

Monday, July 15, 2013

ጃዋር መሃመድ የአረቦች ኢትዮዽያን የማፍረስ ሴራ ተቀላቀለ እንዴ ?



ሰበር ዜና ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ታገቱ

Hanna Metasebia

ሰበር ዜና
————–
ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ታገቱ
——————————
————————————————–
በጎንደርና በደሴ በደረሰበት ፖለቲካዊ ኪሳራ የተበሳጨው ኢህአዴግ ዛሬ ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላትን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች አግቷል፡፡ የታጋቾቹን ስም ዝርዝርና የታሰሩባቸውን አከባቢዎች ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ እናደርጋለን፡፡

ሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰለፍ ያወጣዋል

1069387_203643919793903_873502461_nሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰለፍ ያወጣዋል
ባለፈው ጊዜ አዲስ አበባ በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይም ለገዢው ግንባር ኢህአዴግ ተነግሮታል፡፡ የምጠራጠረው መስማቱን ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ሟች ጠቅላ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲናገሩ እንደሰማነው አንዲት እንስሳ አለች ትልልቅ አይን አላት ግን አታይም ትልልቅ ጆሮ አላት ግን በቅጡ አትሰማም… ብለውን ነበር፡፡ ይቺን የሰማቻቸው ጊዜ የአብዬን ወደ እምዬ ብላቸው ነበር አሉ… እስንስሳዋን ብዙዎቻችን እናውቃታለን… ለደህንነቷ ስንል ስሟን እንዝለለው…
ኢህአዴግዬ ትልልቅ መስሚያ ጆሮዎች ትልልቅ መመልከቻ ኤኖች አሏት ብዙ ጊዜ ግን በቅጡ ስታይ በቅጡ ስትሰማ አላየናትም፡፡ (የኔ እናት… እግዜር ቀላሉን ያደርግልሽ ብዬ ተቆርቋሪነቴን እገልፃለሁ)
ለማንኛውም እንዲህ የመስማት እና የማየት ችግር ያላለበት ሰው እንዲሰማን እና እንዲያየን ደመቅ ብሎ መታየት እና ጮክ ብሎ መጮህ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡
ትላንት በደሴ እና በጎንደር ህዝቡ ደምቆ ታይቷል ጮክ ብሎም ተናግሯል፡፡ አሁንም ኢህአዴግዬ መስማቷን አንጃ… ስለዚህ ዳግም ድምፃችንን ከፍ ማድረግ አለብን ማለት ነው፡፡
አንድነቶች እንደነገሩን በቀጣይም፤ በሃያ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰልፎች ይደረጋሉ፡፡
የሀገሬ ሰው፤ ሆድ ያባውን ሰላማዊ ሰልፍ ያወጣዋል! ኢህአዴግ እስክትሰማን ድረስ ደጋግመን የሆዳችንን ልንነግራት ይገባል ያለ ይመስላል፡፡
ኢህአዴግ ሆይ ስሚ…

Sunday, July 14, 2013

የአፍሪቃ ኅብረት፣ መፈንቅለ መንግሥትና ፈታኙ አቋም

አንድ ቢሊዮን ገደማ ህዝብ ባለው ክፍለ ዓለም 54 አባል ሃገራትን ያቀፈውና ዘንድሮ 50 ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የአፍሪቃ ኅብረት በየጊዜው በሚከሠቱ የአህጉሩ ችግሮች መፈተኑ አልቀረም ። የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ወይዘሮ እንኮሳዛና ድላማኒ
ዙማ ፣ በቅርቡ በግብጹ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ከሥልጣን ገለል እንዲሉ የተደረገበትን እርምጃ መነሻ በማድረግ ፤ኅብረቱ ከግብፅ ህዝብ ጎን እንደሚቆም ፤ሆኖም አገሪቱ ለጊዜው ከአባልነት እንደምትታገድ መጠቆማቸው የሚታወስ ነው ። ይህ ጊዜያዊ ወይስ ዘለቄታ ያለው የኅብረቱ መርኅ ነው? «የአፍሪቃ ኅብረት፣ መፈንቅለ መንግሥትና ፈታኙ አቋም ፣»የዛሬው የእንወያይ ዝግጅት ትኩረት ነው በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር 3 እንግዶችን ጋብዘናል ። እነርሱም
1.የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር፣እንዲሁም የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ ሊቀመንበር ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና
2.የፀጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ ዶክተር ሰሎሞን አየለ ደርሶ እንዲሁም
3. የቀድሞ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ባልደረባና ጋዜጠኛ አቶ ንጉሤ ደስታ ናቸው

የኢህአዴግ የፖለቲካ ዥዋዥዌ

እንቆቅልሽ እየሆነ የሚያስቸግረን የኢህአዴግ የፖለቲካ ዥዋዥዌ፤ በአብዛኛው ጊዜያዊ ጨዋታ ሳይሆን፤ ከራሱ ከኢህአዴግ ተፈጥሮ የሚመነጭ ነባር ባህርይ ነው። ኢህአዴግ በተፈጥሮው፤ “አንድም፤ ሁለትም ነው” ማለት ይቻላል። አንድም “አብዮታዊ” ልሁን ይላል፤ ሁለትም “ዲሞክራሲያዊ” ልሁን ይላል። አንደኛውንና ገናናውን “አብዮታዊ ኢህአዴግ”፤ ሌላኛውንና አናሳውን “ዲሞክራሲያዊ ኢህአዴግ” ብለን ልንሰይማቸው እንችላለን። ይህንን መንታ ማንነት፤ በሁሉም የኢህአዴግ አስተሳሰቦች ውስጥ ታገኙታላችሁ።
ለምሳሌ የኢኮኖሚ አስተሳሰቦቹን ተመልከቱ። አንድም፤ “ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል” እያለ የሚሰብክ ሶሻሊስት ነው። ሁለትም፤ “ያፀደቅኩት ህገመንግስት ነጭ ካፒታሊዝምን ያሰፍናል” እያለ የሚናገር ነው። በፓለቲካውስ? አንድም፤ “የቡድን መብት፤ የብሄር ብሄረሰብ መብት፤ የብዙሃን መብት” እያለ ህዝባዊነትን (ሶሻሊዝምን) ይደሰኩራል። ሁለትም፤ “የግለሰብ መብት የህገመንግስታዊ ስርአታችን አንድ ምሶሶ ነው” በማለት ይናገራል።
አንዳንዴ “ኢህአዴግ” ይነሳበታል፤ እናም ወደ ግራ አቅጣጫ ይንደረደራል። ሌላ ጊዜ ደግሞ፤ ሰከን ብሎ “ዲሞክራሲያዊው ኢህአዴግ” ይባንናል፤ ያኔ ወደ ቀኝ አቅጣጫ ይንፏቀቃል። በእርግጥ እንዲህ በተቃርኖ ተወጥሮ እስከ ወዲያኛው መዝለቅ አይችልም። ፈጠነም ዘገየም፤ ወደ አንዱ አቅጣጫ እያመዘነ መሄዱ የማይቀር ነው (በተቃርኖ ተወጥሮ መፍረስ ወይም መፈንዳት ካልፈለገ በቀር)። ከሁለቱ ተቃራኒ አቅጣጫዎች (ከሁለቱ ተቃራኒ ማንነቶች) መካከል አንዱ እስኪያሸንፍ ድረስ ግን፤ ተቃራኒዎቹ ማንነቶች እየተፈራረቁ በዥዋዥዌ አገሪቱን ይዞ በአዙሪት መሾሩ ይቀጥላል።
ኢህአዴግና ዲሞክራሲያዊው ኢህአዴግ፤ ምን ያህል ተቃራኒ አቋሞችን እንደሚይዙ ለማየት፤ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮችን በማንሳት እንመልከት። በቢዝነስና በመንግስት ጣልቃ ገብነት ላይ፤ በኪራይ ሰብሳቢና በጥገኛ፤ በተቃዋሚ ፓርቲና በሚዲያ ክርክር ላይ፤ በህገመንግስትና በአገራዊ መግባባት ላይ፤ “ሁለቱ ኢህአዴጎች” በአቋም ይለያያሉ። ሌላው ይቅርና በዲሞክራሲና በአብዮት ላይ ያላቸው አቋምም ለየቅል ነው። አንዳንዶቹን ለመመልከት እንሞክር።
“ኢህአዴግ”፤ የኛ ዲሞክራሲና የፖለቲካ ምርጫ ከአሜሪካ ይበልጣል ይላል – የመራጮች ተሳትፎ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ። በአሜሪካ፤ መምረጥ ከሚችለው ህዝብ መካከል ከ60 በመቶ በታች ያህሉ በምርጫ ይሳተፋል። በኢትዮጵያ ግን ከ85 በመቶ በላይ ድምፅ በመስጠት ይሳተፋል በማለት ያብራራል  ኢህአዴግ። ኮሙኒስቶች የሚያዘወትሩት አባባል መሆኑን ልብ በሉ። የአንድ ፓርቲ አገዛዝና፤ እንደ ሳዳም ሁሴን የመሳሰሉ አምባገነኖች በነገሱባቸው አገራት ውስጥ፤ ከ90 በመቶ በላይ ህዝብ በምርጫ ይሳተፍ እንደነበረ ግን አይወራም።
በአሜሪካ እንደሚታየው፤ በቀጥታ የሚተላለፍ የፓርቲዎችና የፖለቲከኞች ክርክር አስፈላጊ እንዳልሆነ የሚገልፀው “ኢህአዴግ”፤ በቀጥታ ስርጭት የህዝብ ጥያቄች ጎልተው አይወጡም በማለት ያጣጥለዋል። የፖርቲዎች ክርክር በሚዲያ ከመሰራጨቱ በፊት “ኤዲት” ሲደረግ፤ የህዝብ ጥያቄዎች ጎልተው ይወጣሉ በማለትም ይከራከራል።
“ኢህአዴግ” በበኩሉ፤ የአሜሪካ ዲሞክራሲ እጅግ የዳበረ እንደሆነና ኢትዮጵያም ቀስ በቀስ ዲሞክራሲን በመገንባት እንደምታዳብር ይገልፃል። በቀጥታ የሚሰራጭ የፓርቲዎችና የፖለቲከኞች ክርክር፤ በአሜሪካ እንደሚታየው ከጠንካራ የዲሞክራሲ ባህል ጋር የተሳሰረ እንደሆነና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በአድናቆት ይናገራል ኢህአዴግ”። በኢትዮጵያ ግን የዲሞክራሲ ባህል ስላልዳበረ፤ በቀጥታ የሚሰራጭ የፓርቲዎች ክርክር፤ እንደ 97ቱ ምርጫ ስሜታዊነትንና ግጭትን ይፈጥራል የሚለው  ኢህአዴግ”፤ ቀስ በቀስ ዲሞክራሲያዊ ባህል ማዳበር አለብን ይላል።

የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል‬ የፖለቲካ ስልጠና ሰነድ

Tagay-Manual-Banner

ይህን አነስተኛ ሰነድ የተወሰደው ከ220 ገጾች በላይ ርዝማኔ ካለው ‪#‎የግንቦት7ህዝባዊሃይል‬የፖለቲካ ስልጠና ሰነድ ነው።
የፖለቲካ ስልጠና
ምእራፍ 1- እኔ
የፖለቲካ ሥልጠና ትምህርታችን የሚጀምረው እኔ በሚለው ርዕስ ነው። ለምን ይህ ርዕስ ከሁሉም ርዕሶች ቀደመ? በዚህ ርዕስ ሥር ምን ጉዳዮች እናነሳለን? በመጨረሻም የዚህን ርዕስ ወይይት ስንጨርስ ምን መጨበጥ ወይም ማግኘት ይቻላል ብለን እናምናለን? የሚቀጥለው
1. ለምን እኔ በሚለው ርዕስ ጀመርን?
መልሱ ቀላል ነው። ሁላችንም ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስንመጣ በግላችን ነው የመጣነው። ከሌሎች ጓደኞቻችን ጋር ብንመጣም ሕዝባዊ ኃይሉን እንቀላቀል የሚለውን ውሳኔ የወሰንነው እያንዳንዳችን በተናጠል ነው። ብዙዎቻችን ከዚህ በፊት አንተዋወቅም። የመጣነው እያንዳንዳችን ከሌላው ጋር ሆነን፣ ድርጅት ፈጥረን፣ ወያኔን ተዋግተን እናስወግዳለን ብለን አስበን ነው። ከተሰባሰብን በኋላ ከተናጠል ወደ ብዙሃን ተቀይረናል። ከእኔ እኛ ሆነናል። የእኛነታችን መሠረት ግን እኔ ነው። የእኛነታችን መነሻ እኔ ሆኖ መድረሻችን ደግሞ እኛ ሆኗል። መነሻውን የማያውቅ መድረሻውን አያውቅም ይባላል። እኔን ሳናውቅ እኛን ማወቅና እኛን መሆን አይቻልም። በመሆኑም እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ በሚ
ገባ ለራሴ መመለስ መቻል ይኖርብኛል። ከሌሎቹ ጓዶቼ የሚቀርብልኝ አንተ ማነህ የሚል ጥያቄ በሚገባ መመለስ የምችለው ስለራሴ ከሚኖረኝ ጥልቅ እውቀት በመነሳት ብቻ ነው። እውን ስንቶቻችን ነን እራሳችን በደንብ የምናውቅ? እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ የተሟላ መልስ ለመስጠት ትልቅ ድፍረትና ከራስ ጋር መፋጠጥን ይጠይቃል። ጀግንነትን ይጠይቃል። ከራስ ስሜት፣ ዝንባሌና ፍላጎት ጋር መሟገት ያስፈልጋል። የእኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ በሚገባ መልስ ስሰጥ ነው ነገ በጦር ሜዳ ጓዴን ጥዬ እንደማልሸሽ፣ ወንድሜን በሰላሳ ሽልንግ እንደማልሸጥ እርግጠኛ የምሆነው። ወያኔ እንዳደረገው ነፃ አወጣዋለሁ የምለውን ሕዝብ መልሼ ረጋጭ መሆን እንደማልችል የማውቀው። ዘራፊ፣ ገፋፊ፣ አስገድዶ
ደፋሪ እንደማልሆን እርግጠኛ መሆን የምችለው። ሰለ ሀገሬ ስለወገኔ መዋረድ የማነበንባቸውን ቃላት፣ ጉልበቱ እድሉ ስልጣኑ ሲኖረኝ ወደ በጎ ተግባራት እንደምቀይራቸው እርግጠኛ የምሆነው ራሴን በሚገባ ሳውቅ ነው። ጽናት ኖሮኝ የምዘልቅ፣ ምንም ፈተናና ችግር ወያኔን ከመደምሰስ ሊያስቆመኝ እንደማይችል እርግጠኛ የምሆነው እራሴን በሚገባ ሳውቅ ብቻ ነው:: ለጓዴ፣ ለድርጅቴ ለሃገሬ ሰዎችና ለሃገሬ የገባሁትን ቃል የማላጥፍ እንደሆነ እርግጠኛ የምሆነው እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ስሰጥ ነው።
እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ በሚገባ ለራሴ ስመልስ ከጓዶቼ የሚቀርብልኝን አንተ ማነህ የሚል ጥያቄ በቀላሉና በእርግጠኛነት መመለስ እችላለሁ። እኔ፣ የእኛ የግንቦት 7 ሕዝባዊ አባላት ስብስብና ድርጅት፣ ከዛም አልፎ የማኅበረሰባችንና የሀገራችን የመሠረት ድንጋይ ነው። የመሠረት ድንጋይ ብቻ አይደለም። ድርጅታችንን፣ ማኅበረሰባችንና ሀገራችንን የምንገነባበት እያንዳንዱ ጡብ እኔ ነው። እኔ በደንብ ካልተገነባ፣ እኔ በደንብ ካልታነጸ፣ እኔ ነካ ሲያደርጉት የሚፈርስ፣ እፍ ሲሉት ብን የሚል ከሆነ፣ እኔ የሚያዝ የሚጨበጥ የሌለው ሙልጭልጭ፣ እኔ መርህ- የለሽ ልክስክስ፣ አከርካሪ የለሽ ልምጥምጥ ከሆነ እኛም የለንም። ድርጅት አይኖርም። ማኅበረሰብ መማቀቁ፣ ሀገር መውደሙ አይቀርም።
እንደ ወያኔ ድርጅት በሚያጭበረብሩ መሪዎችና ተከታዮች የተገነባ ድርጅት በለስ ቀንቶት ወያኔን ቢያስወግድ የሚፈጥረው ሀገራዊና መንግሥታዊ ሥርዓት የአጭበርባሪዎች ይሆናል። አድሎን፣ የድርጅትን ንብረት እንደራስ አድርጎ አለማየትን፣ ራስ ማስቀደምን፣ መስገብገብን፣ ወታደራዊ ፖሊስ ወይ ጓዶቼ አያዩኝም በሚል በጋራ ያጸደቁትን ሕግ ሥርዓትና ደንብ የሚጥሱ፣ ለጓዶቻቸው ደህንነትና ጤንነት የማይጨነቁ፣ እርስ በርስ የማይፋቀሩ፣ የግል ድሎትንና ምቾትን ብቻ ማሰላሰልን ሥራዬ ብለው የያዙ አባላት የተሰባሰቡበት ድርጅት ታግሎ አታጋይ መሆን አይችልም። እንደ ድርጅትም መዝለቅ አይችልም። ነጻ ወጥቶ ሌላውን ነጻ ማውጣት አይችልም። በአንድ ተአምር ወያኔን ማስወገድ ቢሳካለት ከወያኔ በላይ
ሕዝብ አስመርሮ ወያኔ ማረኝ የሚል ዘመን እንዲመጣ ማድረጉ አይቀርም። በሀገራችን ታሪክ የሆነው ይህ ነው። ደርግን ያየ ሃይለስላሴ ማረኝ አለ። ወያኔን ያየ ደርግ ማረኝ አለ። እኛን ያየ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ሁኔታ ልንፈጥር አይደለም ትግል ውስጥ የገባነው። እኛ ትግል ውስጥ የገባነው መንግሥት ተቀይሮ መንግሥት በመጣ ቁጥር ካለፈው ሥርዓት አዲሱ እየባሰበት የሕዝብ ስቃይ የረዘመበትን የታሪክ ጉዞ ለመቅጨት ነው። እያንዳንዳችን ወደ ትግል የገባነው የሕዝብ እሮሮና ስቃይን ለአንዴና ለመጨረሻው እልባት ወይም መቋጫ ልናበጅለት ነው። ይህ ማድረግ የምንችለው በምንገነባው ድርጅት አማካይነት ነው። የምንገነባው ድርጅት የሚሰራው ከሲሚንቶና ከአሸዋ ወይም ከሌሎች ቁሳቁሶች አይደለም። በሰው ነው። በእኔ ነው። ሰው እንደሸክላ እንደ ብሎኬት ከአሸዋና ከሲሚንቶ የሚሰራ ወይም እንደ እንስሳ የምናራባው ፍጥረት አይደለም።ሰውን ሌላው ሰው አይሰራውም። ሰው ራሱን በራሱ ብቻ የሚሰራ ፍጥረት ነው። እኔ ፈቃደኛ ካልሆንኩ፣ ለመማር ዝግጁ ካልሆንኩ ሌላው ሰው ላስተምርህ፣ ልምከርህ ቢለኝ ዋጋ የለውም።ዛሬ እኔነታችንን ወደፊት ለማምጣት ለምንፈልገው ሀገራዊና ማኅበረሰባዊ ለውጥ እንዲመች አድርገን በሚገባ እዚሁ ካላነጽነው መጨረሻችን አሳፋሪ ውድቀት ነው። የሀገር እጣ፣ የ90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እጣ የሚወሰነው እዚህ እኛ መሃል እያንዳንዳችን በምንላበሰው ስብእና፣ በሚኖረን ሰብአዊ ሥነሥርዓትና ጥብቅነት፣ በምንገነባው የአብሮነትና የአንድነት ስሜት፣ በምንሸምተው እውቀትና ክህሎት ላይ ተመስረቶ ነው። እባብ ከሆነን የርግብ እንቁላል አንጥልም። የእባብ ፍልፈሎች እንጂ። ለዚህ ነው ከማናቸውም ጉዳዮች በላይ በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ እኔ ማነኝ ለሚለው ጥያቄ ቅድሚያ የሰጠነው። እኔ ማነኝ ወይም አንተ ማነህ ለሚለው ጥያቄ በጣም ቀላል ከሆኑ ነገሮች ተነስተን መልስ መስጠት እንችላለን። የእኔ ማነኝ ጥያቄ ምላሽ ግን እንደምናስበው ቀላል እንዳልሆነ ቀጥለን እንመለከታለን።
2. እኔ ማነኝ
“አንተ ማነህ?
“እኔ?”
“አወን፣ አንተ”
“እኔማ ከበደ አበበ ነኝ፣ እንደ ሰው በማልቆጠርበት ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር የምኖር ሰው ነኝ”
“ሰው መሆንክን አውቃለሁ። እሱ ምን ችግር አለው። ስምም የሁላችንም ነው። ሃገርም እንደዛው። ከዚህ ውጭ ሌላ ነገር ስለራስህ ንገረኝ።”
“እንደምታየኝ ወጣት ኢትዮጵያዊ ነኝ። እድሜዬ 30 አመት ነው። የተወለድኩት ጎንደር፣ አዲስ ዘመን ነው። እስከ 12ኝ ክፍል ተምሬአለሁ። በውትድርና ሙያ ሰርቻለሁ። 3 ወንድሞች 2 እህቶች አሉኝ። እኔ የመጨረሻው ልጅ ነኝ። የመጀመሪያው ወንድሜ ታላቃችን አዲስ አበባ ውስጥ በምርጫ 97 ወቅት በወያኔ ተገድሏል። ሁለቱ እህቶቼ በሃገራቸው ስራ አጥተው አረብ ሀገር ሥራ ብለው ሄደዋል። እናቴ በውንድሜ ሞት ሃዘን የተነሳ ብዙም ሳትቆይ አርፋላች። አባቴ ነጋዴ ነው። በሕይወት አለ። ወያኔ ከምርጫ 97 በኋላ ተቃዋሚ ትደግፋለህ ብሎ አሰረኝ። ከዛም ከሠራዊቱ ተባረሃል ብሎ ፈታኝ። መጀመሪያውኑ የወያኔ ወታደር መሆን አልነበረብኝም። በሠራዊቱ ውስጥ ያየሁት የዘር አድሎና መጠቃቀም ቆሽቴን ያበግነው ነበር። የከፍተኛ መኮንኖቹ እጅግ የሚገርም በዘር ላይ የተመሰረተ የዘረፋና የቅንጦት ህይወትና የተራው ወታደር ሬት ሬት የሚል ህይወት አንገሽግሾኝ ነበር። መባረሩን በደስታ ነው የተቀበልኩት። ችግሩ ሌላ ሥራ ማግኘት አልቻኩም። በመንግሥት መስሪያ ቤት እንዳልቀጠር በጸረ_መንግሥትነት የሚፈርጅ ደብዳቤ ሰጥተው ነው ከሰራዊቱ ያባረሩኝ። ያንን ደብዳቤ እያየ ማንም የሚቀጥረኝ ጠፋ። በግል ሥራ እዛም እዚህም ሁሉን ነገር ሞከርኩት። ነገር ግን የኑሮ ውድነቱ፣ መተንፈሻ የነሳኝ የሰላዩ ብዛትና አፈናው፣ የወንድሜና የናቴ ደም መና ሆኖ መቅረቱ፣ በአረብ ሃገር በእህቶቼ ላይ የሚደርሰው ውርደትና ስቃይ፣ ወያኔዎች ሲፋፉ እኔ እንደ ስልክ እንጨት መድረቄ ሌላውም ተደራርቦ ወያኔን መታገል
አለብኝ ወደሚል መደምደሚያ አደረሰኝ። የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል መቋቋሙን ሰማሁ። መጣሁ። ተቀላቀልኩ።የግንቦት 7ሕዝባዊ ኃይል አባል ነኝ”
ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው እኔ ማነኝ ወይም አንተ ማነህ የሚለው ጥያቄ በዚህ መልኩ ሊመለስ ይችላል። ይህ ምላሽ ግን ሁላችንም በየግላችን እንደማንነታችን የምንመልሰው ምላሽ ነው። ይህን አይነት ምላሽ ለመስጠት ሁላችንም ብዙ አይቸግረንም። ሁላችንም በየግላችን ስለራሳችን ታሪክ በቀላሉ የምናየው ጭብጥ ነው። ስማችን፣ የተወለድንበት ቦታ፣ እድሜያችን ወዘተ አይቀየርም። ስለወያኔም ሥርዓት የምንናገረው ጭብጥ እንዲሁ ለሁላችንም አንድ ነው። በወያኔ የደረሰብን በደል ይለያይ እንጂ ሁላችንም በደል ደርሶብናል። የምሬታችን ደረጃ ይለያይ እንጂ ሁላችንም መሮናል። ይህ ምሬት ሁላችንንም ወያኔን እንድንታገለው ገፍቶን በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውስጥ አሰባስቦናል። ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስንመጣ ደረቅ ስማችን፣ የግልና የቤተሰብ ታሪካችንን፣ የግል ብሶታችንን ብቻ ግን ይዘን አልመጣንም። ቀጥለን እንደምንመለከተው ብዙ ነገር ይዘን መጥተናል።
እኔ ማነኝ?
ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ስመጣ ምን ይዤ መጣሁ? ስሜን ብቻ ነውን? በወያኔ ላይ ያለኝ ምሬትና ጥላቻ ብቻ ነውን? በደል የወለደው ምሬትንና መንገፍገፍ ብቻ ነውን? መንገፍገፍ የወለደው እልህና ቁጭት ብቻ ነውን? እነዚህ ብቻ አይደሉም። ሌሎችም ነገሮች ይዤ መጥቻለሁ።እያንዳንዳችን የተለያዩ ሙያዎቻችንን ይዘን መጥተናል። የወታደራዊ፣ የሂሳብ ሠራተኛነት፣ የጋዜጠኛነት፣ የሃኪምነት፣ የግንበኛነት፣ የገበሬነትና የአስተማሪነት ወዘተ የመሳሰሉትን ሙያዎች ይዘን መጥተናል። ግን እነዚህን ብቻ ነውን ይዘን የመጣነው? የለበስኩትን ልብስ ብቻ ነው ወይስ መቀየሪያ ጭምር፣ ገንዘብ፣ መሣሪያ፣ ሞባይል፣ መጽሃፍ ይዤ መጥቻለሁን? በሽታ፣ ህመምና ቁስል ይዤ መጥቻለሁን? የሲጋራ፣ የመጠጥ፣ የጫት ሱስ ይዜ መጥቻለሁን? ሌላም ጥያቄ ማንሳት ይቻላል።ከዚህ በላይ የተጠቀሱት እኔ ወደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ይዣቸው የመጣኋቸው ወይም ላመጣቸው የሚችሉ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች የተለያዩ ጥቅምና ጉዳት አላቸው። ስሜ ታሪኬ ማንም አይጎዳም። ሙያዬ ይዤ የመጣሁት ንብረት ገንዘብ ወዘተ የኃይሉን አባላትና ድርጅታችንን ይጠቅማል። በሽታ፣ ህመም ቁስል ይዤ ከመጣሁ ቆራጥነቱና ጽናቱ እስካለኝ ድረስ ጤናዬንና አቅሜን የሚመጥን ተግባር እያከናወንኩ ለትግሉ የድርሻየን አበረክታለሁ። ከነህመሜ የጓዶቼ መመኪያ መሆን እችላለሁ። ይዤ የመጣሁት ሱስ ካለ ግን ምንም ጠቀሜታ የለውም። በዚህ ሱስ የተነሳ እራሴን እጎዳለሁ። ጓዶቼን እጎዳለሁ። የሱስ ምርኮኛ መሆን ሱስ ለማርካት ሲባል የማያመጣብኝ ፈተና አይኖርም።ሱስ አላስፈላጊ የደህንነት አደጋ ያለበት ሁኔታ ውስጥ ይጨምረኛል። ሱስ ልመናን ውርደት ያስከትላል። ሱስ የድርጅትን የአደራን ገንዘብና ንብረት ማባከንንና ሌባ መባልን ያስከትላል። ሱሱ ምሱን ካላገኘ ማንቀላፋት፣ መንገላጀጅ፣ ትእግስት የሌለን፣ የምንነጫነጭ፣ የምንቀዠቀዠ ወይንም የምንደበት ያደርገናል። ሱስ ሰው እራሱ ጥሮ ግሮ ወይም ሌሎች ጓዶቹ ጥረው ግረው ላባቸውን አንቆርቁረው ያሰባሰቡትን ሃብት በከንቱ እንዲባክን የሚያስደርግ ነው። እንኳን ለትልቅ ዓላማ አባላት በተሰባሰቡበት ድርጅት ውስጥ ቀርቶ የግል ሕይወት በሚኖርበት ሁኔታ ይህ ብክነት አሳዛኝ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የተጠቀሱት ሱሶች በተለያየ ደረጃ በጤንነታችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው። ሲጋር በቀጥታ ከሳምባናከልብ ጋር፣ መጠጥ ከልብ፣ ከጉበት፣ ከኩላሊት ወዘተ ጋር፣ ጫት ከሆድ ከአእምሮ ጋር የተያዙ የጤንነት ጉዳት አላቸው። ይህ ጉዳት እያንዳንዱ ሱስ ያለበትን ሰው በተለየ የሚጎዳ ቢሆንም የርሱ መጎዳት በሌሎች ላይ ጉዳት ያስከትላል። ጤና የሌለው፣ የአእምሮና የአካል ብቃት የሌለው ታጋይ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በእኩልነት መንቀሳቀስ አይችልም። በጉዞ መድከም፣ መፍዘዝ ይመጣል። እነዚህ ሱሶች የየግለሰቡ ናቸው ብለን የማንተዋቸው ለዚህ ነው። ሌሎችንም ጉዳት ላይ የሚጥሉ መዘዞች አላቸው። እኔ ማነኝ ስንል እነዚህ አይነት ሱሶች ካሉን እነዚህ ሱሶች ያ
ሉኝ ግለሰብ ነኝ የሚል ተጨማሪ ምላሽ ይኖረዋል። እኔ ማነኝ የሚለው ጥያቄ ግን በነዚህ ስለራሴ ባቀርብኳቸው ጭብጦች ብቻ የሚጠቃለል አይደለም። የተሟላ ምላሽ ለማግኘት ብዙ የሚቀረው ነጥቦች አሉ።
እኔ ማነኝ?
እኔ ማለት ስሜ፣ ንብረቴ፣ ሱሶቼ፣ እድሜ፣ የትውልድ ቦታዬ፣ ጎሳዬ ዘሬ፣ ሃይማኖቴ ብቻ ናቸው ወይ? ወይንስ ሌሎች ጓዶቼ በቀላሉ ሊደርሱባቸው የማይቹላቸውና የማያዩዋቸው እኔ ግን ለብቻዬ የማውቃቸው ነገሮችም ይዤ መጥቻለሁ። እነዚህ ጓዶቼ በቀላሉ ለማየት የማይችሏቸው ነገሮች ግን እኔ የማውቃቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ድፍረት፣ ጀግንነት፣ ቆራጥነት፣ ታማኝነት፣ ፍቅርን፣ ትእግስትን፣ ጽናትን ወዘተ ይዤ መጥቻለሁ? ሌሎችስ የነዚህ ተቃራኒ የሆኑ። ፈሪነትን መሠሪነትን፣ ክፋትን፣ ተንኮልን፣ መዋሸትን፣ ወላዋይነትን፣ ተራ ቅናትን፣ አሉባልተኛነትን ወሬኛነትን፣ አጭበርባሪነትን፣ ተላታሚነትን፣ ጠብ ጫሪነትን፣ መለገምን፣ መስገብገብንስ፣ ቱግ ማለትን ግብዝነትን ይዤ መጥቻለሁ? እየዋልን እያደርን መተዋወቅ ስንጀምር ለነዚህ ጥያቄዎች አንዳችን ስለ አንዳችን የምንለው ነገር ይኖረን ይሆናል። ገና ሕዝባዊ ኃይሉን ስንቀላቀል ግን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ስለእኔ ከኔ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ሰው አይኖርም። ፈሪ ልሁን ደፋር፣ ሃቀኛ ልሁን አጭበርባሪ የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ። ደፋር፣ ሃቀኛ፣ ጀግና፣ ታማኝ፣ ጓዱን አፍቃሪ የሆኑ ባህሪዎቼ ለጎዶቼና ለድርጅቴ ጥንካሬዎች ናቸው። ሌሎች ባህሪዎቼ፣ ለምሳሌ መዋሸት፣ መወላወል፣ ተላታሚነት፣ አምባገነንነት፣ ሌብነት፣ ስግብግብነት ግለሰበኛነት፣ ወዘተ የሕዝባዊ አባላቱንና ድርጅቱን የሚጎዱ አደጋ ላይ የሚጥሉ መጥፎ ባህሪዎች ናቸው። ቀደም ብለን ከጠቀስናቸው ከሱስ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ችግሮች እጅግ የከፉ ናቸው። ለምን ብለን እንጠይቅ።አሉባልተኛ ሰው ድርጅት ያምሳል። በአሉባልታው የተነሳ ግለሰቦችና ቡድኖች እርስበርሳቸው ሊጋጩ፣ በመሃከላቸው መተማመን ሊጠፋ ይችላል። ብሎም ድርጅት እስከማፍረስ ሊደርስ ይችላል። የሲጋራ ሱስ ወይም የመጠጥ ሱስ ያለበት ሰው ራሱን በቅድሚያ ይጎዳል። ድርጅቱንም ይጎዳል ግን ድርጊቱ ድርጅት የሚያፈርስ አይሆንም። ሲጋራ የሚያጨስ ሰው በጀግንነት ሊዋጋ ይችላል። ወላዋይ ሰው ግን ጓዶቹን በጦር ሜዳ ጥሎ ሊፈረጥጥ ይችላል። ሌሎችም ጎጂ የሆኑ ባህርይዎቻችንና ባህሎቻችን እያንዳንዳንችን ቤተስብ፣ ሃብት፣ ቤትና ንብረት በትነን እዚህ የተሰባሰብንለትን ዓላማ እንዳናሳካ የሚያደርግ አቅም አላቸው። ዋናውን ጠላት ወያኔን ትተን እርስ በርስ እንድንባላ፣ ወያኔ እስካሁን ካደረሰብን በደል በላይ የከፋ በደል እንዲያደርስብን የሚያደርጉ ናቸው። ይህ የከፋ በደልና ጥቃት ምን ሊመስል እንደሚችል ሁላችንም በቀላሉ ልንገምተው
የምንችለው ነው።ይህ በመሆኑም እያንዳንዳችን ወደ ሕዝባዊ ኃይሉ ስንመጣ ይዘናቸው የመጣናቸውን ጎጂ ባህሎችና ባህርይዎች ያለምንም መወላወል መጋፈጥና ከሁላችንም ውስጥ አጥበን ማውጣት ይኖርብናል።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል እነዚህን አይነት ጎጂ ባህሎች እንታገል ሲል የመጀመሪያው ድርጅት አይደለም። በሀገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ከተፈጠሩ ጀምሮ እነዚህ ጎጂ ባህሎች በየፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ተነግሮ የማያልቅ ውድመት አስከትለዋል። እየዋለ እያደረ በበርካታ የሀገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የእነዚህን ጎጂ ባህሎች አውዳሚነት እየታወቀ መጥቷል። ሆኖም ግን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እነዚህ ባህሎች በየድርጅቱ ውስጥ እንዳይሳፋፉና ሥር እንዳይሰዱ ማድረግ የቻለ ድርጅት እስካሁን የለም። በየመድረኩ የተለያዩ ድርጅቶች መሪዎች እነዚህን ጎጂ ባህሎችና ባህሪዎች እንታገላላን በማለት ቃል ቢገቡም እስካሁን ግን አንድም የተሳካለት ድርጅት አልተገኘም። ይህ ትግል ቀላል ስላልሆነ
ብዙዎቹ ድርጅቶች በገዛ አባሎቻቸው የውስጥ ሽኩቻ፣ የርስበርስ መጠላለፍ፣ ሲወድሙ ሲሰነጣጠቁ ሥራ የማይሰሩ በድኖች ሆነው ሲቀሩ አይተናል።ከ1966ቱ አብዮት ጋር ብቅ ካሉት ድርጅቶች ጀምረን ታሪካቸውን መቃኘት እንችላለን። ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ መኢሶን፣ ኢሰፓ፣ ኦነግ ወዘተ በራሳቸው ድርጅትና ከሌሎች ድርጅቶችጋር የገቡበት ሽኩቻና መጠላለፍ ነው ያወደማቸው ወይም ከሞት አፋፍ ላይ ያስቀመጣቸው። የወያኔ አይነት ድርጅት ዘረኛነትን መሰባሰቢያ በማድረጉና የሰዎችን ግንኙነት በዘር ሙጫ ለማጣበቅ በመቻሉ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሲወዳደር ብዙም የውስጥ መጠላለፍ አልታየበትም። በሌሎችም ላይ የበላይነት ያገኘው ዘረኛ በሆነ ዓላማ ዙሪያ የተሰባሰቡት ከፍተኛ መሪዎች ለዘር አጀንዳቸው ቅድሚያ ሰጥተው አንድ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ በማስቻሉ ነው። ይህም ሆኖም ወያኔም ቢሆን የድርጅት ውስጥ ሽኩቻና ሴራ መጠላለፍ ያልነበረበትድርጅት አይደለም። አሁንም ቢሆን መጠላለፉ የሌለበት ድርጅት ነው ማለት አይደለም። በቅረቡ እየታየ ያለው የወያኔ መዳከም በተቃዋሚ ጥንካሬ የመጣ አይደለም። የድርጅቱ ውስጣዊ መበስበስ፣ የቡድኖችና የግለሰቦች የሥልጣን፣ የጥቅም፣ የከንቱ ክብርና ዝና ሸኩቻ ነው።በወቅቱ በሚገኙት የተቃዋሚ ድርጅቶች ጎራ ያለውን ጉድ ሁላችንም እናውቀዋለን። ዛሬ ትብብር፣ ቅንጅትና ኅብረት ፈጥሮ ነገ መበታተን የተለመደ ነው። በየቀኑ ድርጅት መፈልፈል ነው። ዛሬ ተመሥርተው፣ በማግስቱ መሰነጣጠቅ መፍረስ እጣቸው የሆነው የሀገራችን ድርጅቶች ይህን መራራ ጽዋ በመጎንጨት ላይ ያሉት በወያኔ የስለላ ችሎታና ሌላም ክህሎት አይደለም። የየድርጅቶቹ መሪዎችና አባላት ደካማና ጎጂየሆኑ ባህሎቻቸውንና ባህሪዎቻቸውን በደንብ መገንዘብና ማስወገድ ስላልቻሉ ነው። ሃገርና ወገን የመሳሰሉ እጅግ ክቡር የሆኑ ነገሮችን ከተራ የግል ስም፣ ክብር ጥቅምና ፍላጎት በታች አድርጎ ለማየት የማይፈልጉ አባላት ድርጅቶች በማቀፋቸው እነዚህ አሳፋሪና አሳዛኝ የመሰነጣጠቅ ችግሮች ሲከሰቱ አይተናል። እኛስ? እነዚህን ከየአንዳንዳችን ማንነት የሚፈልቁትን ጎጂ ባህሎች አስወግደን የጓዶቻችን የወገናችን የሕዝባችን ተስፋመሆን እንችላለን? የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ትልቁ ፈተና ይህ ነው።አናሳ ቁጥራችንን በሂደት ማብዛት እንችላለን። ወታደራዊ ሙያ የሌላቸውን ጓዶቻችንን ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ማድረግ እንችላለን። የታሪክ፣ የፖለቲካና የሥነ መራር እውቀት የሌላቸውን እውቀቱን በቀላሉ እንዲላበሱ ማድረግ እንችላለን። የቀለም ትምህርት ለሌላቸው እዚሁ በረሃ ውስጥ ከየትኛውም የሀገራችን ት/ቤት ወይም ኮሌጅ በላይ ጥራቱ የጠበቀ ትምህርት መስጠት እንችላለን። ይህን ሁሉ ማድረግ መ
ቻላችን ግን ጎጂ ባህሎቻችን ከሚያስከትሉብን ውድቀት አያተርፉንም። ብዙ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት የነበራቸው፣ ወታደራዊ መሪዎች የያዘ መንግሥት አነስተኛ ወታደራዊ እውቀትና ልምድ ባላቸው ግለሰቦችና መሃይሞች በሚመራ ጦር ሲፈታ አይተናል። በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ሊቃውንት ሊባሉና እንዲሁም በእድሜና በተመክሮ በከበዱ ምሁራን የታጨቁ ድርጅቶች ወያኔን የመሰለ የሀገር ተምች አስቀምጠው እንደ ባለጌ ኮማሪት በአደባባይ ሲዘላላፉ፣ ሲዘራጠጡ፣ ራሳቸውን አዋርደው የኛ ናቸው ያላቸውን ሕዝብ ሲያዋርዱ አይተናል።ለድርጅቶች መዳከም ወይም መውደም ምክንያቶቹ ክህደት፣ ጭቅጭቅ፣ መጠላለፍ የመሳሰሉት በሰዎች መሃከል መልካም ግንኙነት እንዳይኖር እንቅፋት የሆኑ ባህሪዎች ብቻ አይደሉም ። አድርባይነት፣ አጎብዳጅነት፣ ዝርክርክነት፣ ተጨንቆና ተጠቦ አለማቀድ፣ የግብር ይውጣ አሰራር ፣ጀብደኛነትና ወዘተ የመሳሰሉት ባህሎቻችን ለድርጅቶች መዳከም መውደም የራሳቸው አስተዋጸኦ አድርገዋል።እኛስ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አባላት እስካሁን በሀገራችን ውስጥ ከበቀሉት ድርጅቶች የተሻለ እጣና ታሪክ እንዲኖረን ምን ማድረግ አለብን? መልሱ በሌሎች ጥያቄዎችና ምለሾች የሚገኝ ነው። በቅድሚያ ራሳችንን መጠየቅ የሚገባን፣ ቀደም ብለን የጠቀስናቸውና ሌሎችም ጎጂ እና አፍራሽ ባህርያት በተለያየ ደረጃም ቢሆን በውስጣችን እንዳሉ እንገነዘባለን ወይ? ለዚህ ጥያቄ የሉም የሚል ምላሽ መስጠት አንችልም። ምንም ያህል ብጹእና የበቃን ብንሆንም ህጸጽና ድክመት አያጡንም። የሰው መሆን አንዱ ትርጉሙ የሚሳሳት የሚያጠፋ የሚል ነውና። እነዚህ ጎጂ የምንላቸው የግለሰቦች የቡድኖች ባህርያትና ልምዶች ምንድን ናቸው? እውን በደንብ እናውቃቸዋለን? ለምንድነው እነዚህ ባህርያት ልምዶች በማኅበራችንና በሀገራችን ውስጥ ከሌላው ማኅበረሰብና ሀገር ውስጥ ከሚታየው በላይ ሥር ሰደውና ደንድነው የሚገኙት? የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ከዚህ የባህልና የባህርይ ነቀርሳ ለማምለጥ ምን ማድረግ አለበት? ለመሆኑ እነዚህን ጎጂ የምንላቸውን ባህርያትና ልምዶች በደንብ እናውቃቸዋለን?