Tuesday, July 9, 2013

አዲሶቹ የኢህዴግ ሹማምንት ለመመረጫ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ፡

..ከጎን እደር ህወአት ዘ አዲስ አባባ፤ አዲሶቹ የኢህዴግ ሹማምንት ለመመረጫ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ፡አዲሱ ሹመትና ሽግሽግ

አቶ ሬድዋን ሁሴን ቃል አቀባይ ተረቆ በአቶ ሽፈራሁ ሽጉጤ ከትምህርት ሚ/ር ተቀርፆ አቶ በረከትና አቶ ኩማ ኮምኩመው የላኳት..ጀት ሳትሆን ከወረቀት የተሠራች ሮኬት እንበላት የጽሁፏን ብዛት ሳይሆን የሰከፈችውን እንይ ይህንንማ አቶ መልስ አሌት ነው ካላችሁ ታገይ አይሞትም!ራእይና ለጋሲ…ፋውንዴሽን ማለት አንዱ የተፋውን ሌላው ልሶ ደግሞ ሲተፋው ማለት ነው።
በቀጥታ ወደ ገደለው>>>
“የኢትዮጵያ ህዝብ የአምስት ዓመት ኮንትራት ሰጥቶናል…በማስጠንቀቂያ !ውላችን በአመፅ አይፈርስም ሕዝዩ ይታገሰናል። ግን ስለመረጣችሁን እናመሰግናለን እጅ እንነሳለን!”
ዘ-እጎን እደር በራሱ ሲቀይረው
፩) *“በሕዝብ የተመረጠ መሪ አጉራ ዘለል ሆኖ ተገኘ ከተባለ በመጣበት መንገድ ለመሸኘት ድጋሚ ምርጫ ማድረግ ነው የሚገባው ወይስ የአደባባይ ግርግርን መሰረት አድርጎ መዘርጠጥ?” ኢህአዴግ ፺.፮ በሕዝብ ምርጫ እያንጫጫችሁ ነውና እናንተም ከግብፅ አይታችሁ ድንገት ከገልብጣችሁ ጉድ እንዳትሠሩን አደራ! (ተማፅኖ- ፩)
፪) “ይህን ያህል ሃይል ያለው የግብፅ ጦር ለምን ሕዝብ ድምፁን በስነ ስርዓት የሚያሰማበትን ወይም በሕጋዊና ‘ ስነ ስርዓት የሚካሄድበትን መንገድ አላመቻቸም?”
ዘ-እጉን እደር.. ዓይኑን ክዶ ጆሮውን የሚያምን የኢህአዴግ አድርባይ በቀቀን በለው! የሙርሲ ደጋፊዎችም ገና ከመጀመሪያው አንስቶ አደባባዮች ላይ ነበሩ። በቢቢሲ መስኮት ያልታየ ሕዝብ “ሕዝብ” አይባል ይሆን? ብየም ልጠይቅ። የሙርሲ ሲታው የተቃዋሚው
ታህሪር አደባባይ የወጣው ህዝብ የጎጃምና ጎንደር ወይም የኢትዮጳያ ተገንጣይ የብሔር አባላትና የግንቦት ፯ ደጋፊዎች ናቸው ተብሎ ህወአት ቢሮ ተወራ ዘ-ጎን እደር ናቸው ብሎ ያምናል?ጥያቄው የግብፅ ጦር ኅይል የለውም ለማለት ነው? ለመሆኑ ለሠላምና ማረጋጋት የዕለቱ ዕለት ምርጫ ይደረጋል? ሠራዊቱ የሽግግር መንግስት እስኪመረጥ ሀገር የማስተዳዳር ሥልጣንና ኅላፊነት የለውም? የእኛ ሠራዊት በዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት’ ባለው የድምፅ አሰጣጥ ተክኗልና የተቃውሞ ሠልፍ አድርጋችሁ ከምንገላችሁ አሁኑኑ ሠራዊታችንን ፍሩ አክብሩ(ተማፅኖ- ፪)
ዘ-እጎን እደር ጎንድር ፈርስት ማለቱ ይሆን ?
አቶ በረከት ስምኦን ጎበዝ ነበሩ አሁን ቦታቸውን ሲለቁ ችግር አለ ብለን ኤርትራንና ጎንደርን እንድናደንቅ ከሆነ እሰየው! ግለሰቡ የካድሬነት ሥራውን በአግባቡ አልሠራም…ብዙ ተፈራገጠ በለው! ከዕርዳታ ሰጪ ግለሰቦችና ድርጅት በቀጥታ ወደ አሜሪካ መሪዎች፤.. ከአሜሪካ መሪዎች ወደ ሚዲያ ተቋማቸው፤ አልፎም ስለ እንግሊዝ ነገስታት እርግዝና ኢኮኖሚና ማስታወቂያ ነፋው። “ኢህአዴግ አሥር ቦታ ጥዳ ዘጠኙ አረረባት” ያለው ማን ነበር? “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ፡ይሰፋል አሉ ይቺ እንግዲህ ለአቤ ቶክቻው የተሰያመች አዲስ የኤምባሲ ካድሬ ናት!እነሱ ናቸው ስለሚዲያ ነፃነት የሚቆሽሹ ብዬ ነው።
፫) ዘ-እጎን እደር ኢትዮጵያ…ማስታወቂያ ሠራ…አቤንም መከረው(አባበለው)
“ለአቤ መረጃ አቀባይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማለት ቢቢሲ እና መሰሎቹ ብቻ ይሆኑን? ብዙ ድረ ገፆችና ነፃ ሚዲያዎች እንደ ልብ በሞሉበት በዚህ ዘመን… ምነው… ምነው… ?
**አይጋ ፎረም፣ኢቲቪ፣ፋና ኤፍ ኤም ፣ኢትዮጵያ ፈርስት፣አውራእንባ፣ኢትዮ ሲቪክ፣ዛሚ፣ታዲያስ አዲስ፣የቅዳሜ ማስታወሻ፣ሀገርፍቅር፣ድሬ ቲዩብ፣ኢቢ ኤስ፣አዳ፣ቲዳ ፣ኦዳ ብቻ እውነተኛ መረጃ ምንጭ ናቸው ሲል ሰበከው (ተማፅኖ-፫)
ዘ-ጎንእደር ” ተወደድኩኝ ብለሽ አትበይ ደንበር ገተር…ወዳጁን ይበላል የኢህዲግ ነገር!”
ለአንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ‘ምርጫ ተጭበርብሯል እየተባለ የአውሮፓ መንግስታትም ሆኑ የአውሮፓ ህብረት ለምን ጠንካራ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጠቡ?’ ሲል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። ለዚህ መልስ ነው ብለው የፓርላማ አባሉ ብዙ ነገር ነው የተናገሩት። ዋና ዋና ነጥቦች ለመጥቀስ ያህል “… የአካባቢው (የአፍሪካ ቀንድ) ወታደራዊ ሚዛን ሊዛባና ክልሉ ሊበጣበጥ ብሎም የሽብር መነሃሪያ ሊሆን ይችላል…
***አሃ !ታዛቢው ምርጫ መጭበርበሩን ለጋዜጠኛው ተናግረዋል ግን ብጥብጥ እንዳይነሳ ተፈርቶ እንጂ ኢህዴግ አላሸነፈም ሲሉ ከአውሮፓ ፓርላማ አባል ሠምተሃል። አዎን፤ አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ባዶ ይቀራል አሉ። ይህንን ግለሰብ ኢህዴግ ቢያገኘው በላው !
“What happens in the Palace Remains in The Palace” አብዮታዊ ዴሞክራሲን ለእኛ በእኛ ተወወው እንበላለን እናባላለን ከነቁብን እንገላለን !።ልታይ እንጂ ልትናገር አይፈቀድልህም በአማርንእኛ ሲተረጎም ነው። በለው!
*** ዘ እጎንደር ኢትዮጵያ “አበበ ገላው በዋሽንግተኑ የሬገን አዳራሽ ተቃውሞ….አንድ ተማሪ ኢራን የግብረ ሰዶማውያንን መብት አታከበርም ብሎ…ቪኦኤ ነገሩን የዘገበው ከአድማጮች ብዙ ኡኡታና ተቃውሞ ከገጠመው በኋላ ነው፡፤ እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ?
የአሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች ለምንድን ነው የሙርሲን ደጋፊዎች ‘ኢስላሚስቶች’ የሚሏቸው?”
፬) **አበበ ቶላ ፈይሳ በተደጋጋሚ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ነኝ ሲል አንብቤአለሁ፡ የሙርሲ ሀገር ሠው ነኝ ደጋፊውም ነኝ ሲል አልሠማሁም!!። አቤ የማንንም ሃኢማኖት ቋንቋ ሲዘልፍም ሲአናንቅም አልሰማሁም!ጥሩ ኢትጵያዊ ኦሮሞ ነው።ማንም ሚዲያ ድርጅት የመወከልም ይሁን…ተመሳስሎ መልስ መስጠት አይጠበቅበትም በለው!
“ቪኦኤ የአማርኛና የትግርኛ ክፍለ ጊዜ ‘እስላማዊው’ ሲሉ ቪኦኤ ኦሮምኛ ደግሞ ‘ኢስላሙማ’ ሲል ይሰማል። የቸችኒያ፣ የሶርያ፣ እየኮሰመኑ የመጡት የኢራን መጂሃዲኖችና የመሳሰሉት የአሜሪካ ጠላት የሆኑ መንግስታትን ያጠቃሉ የሚባሉ ተዋጊዎች ሙስሊሞችና የእስልምናን መመሪያ አንግበው የሚዋጉ ቢሆንም ‘እስላማዊ’ ሲባሉ አይሰሙም። በአውሮፓና በአሜሪካ ለእስልምና ጥላቻን ማራመድ እየተስፋፋ ነው። ***ለባለቤቶቹ በግንባርህ ሄደህም ሆነ ጽፈህ ድምፅህን አሰማ!! ቱልቱላ ምን ይቀባጥራል?
በመጨረሻም…አቶ ሙርሲ “ኢትዮጵያውንን እርስ በርስ እናበጣብጣታቸው ብለው ሲዶልቱ” ያልከው የኢትዮጵያን ተቀዋዋሚዎች በመርዳት የኢትዮጵያን መንግስት እናዳክመው ያሉትን ነው?ግብፅና ሱማሌ ኢትዮጵያን እያዳከመ ጦርነት በማካሄድ አንድነትን ሉዓላዊነትን ቋንቃን ባሕልን ማፍረስ እንዳለበት ሲያስበው። ሻዕቢያንና ወያኔን ማገዝ ጀመረ፣ አስታጠቀ፣ ፓስፖርት ሰጥቶ በፈለጉበት እየተንቀሳቀሱ የውጭ ሃይሎችን ድጋፍ እንዲያገኙና ደጋፊዎዎቻቸውን ማደራጀት ይችሉ ዘንድ ሀኔታዎችን አመቻቹ አብረው ድልድይ መስበር፣ ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ማፍረስን፣ ተያያዙት አብረውም ህገመንግስት አርቅቀው በፈለጉት ሰዓት ሊበትኑን በአመቺው ሁኔታ ሁሉ አውስጥ ገብተው እንደሚያናቁሩን አጥንተው ጨርሰዋል። በአጭር ቃል የአንድ ጥርብ ድንጋይ ናቸው።ኢትዮጵያችን በእጅጉ እንደተጎዳች እያየን ነው። ይህ ጉዳት ይሽር ይሆን?በጭረሽ ! “የጠላቴ ጠላት…” ሲባል ምን ማለት ነው?ኢትዮጵያን የሚያጠፋን አትንኩ ማለት አፍን ከፍቶ መበላት ነው በለው!! በቸር ይግጠመን ኢትዮጵያው ከሀገረ ካናዳ >>>>>>>>>>>>>>>>>>

No comments:

Post a Comment