Saturday, July 13, 2013

በኢትዮዽያ መጠየቅ ሲያስቀጣ፡-

-

በደ/ብ/ብ/ ክልላዊ መንግሥት ጋሞ ጎፋ ዞን ቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት በሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ መልኩ፤ በሥርዓት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የብሔር ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት ለእስራትና ለድብደባ ከደረጉት ውስጥ ጥቂቶቹ፡-
በ28/10/2005 ፖሊስ ያሰራቸው፤
1. አቶ ደፋሩ ዶሬ
2. አቶ ሻምበል ሻዋ
3. አቶ አማኑኤል ጎቶሮ
4. አቶ ባንትይርጉ ሄባና
5. መ/ር መሸሻ ዜማ
6. ባሻ ፋንታሁን ታደሰ
7. መ/ር ዶለቦ ቦንጃ
8. አቶ ቲንኮ አሻንጎ
9. አቶ አበራ ገ/መስቀል
10. አቶ ጴጥሮስ ሀላላ
ከላይ የተጠቀሱት እላይ በተጠቀሰው ቀን የተያዙ ሲሆን ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከ29/10/2005 ዓ.ም – 01/11/2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከታፈሱት ውስጥ ጥቅቶቹ፡-
11. አቶ ሀብታሙ አብራሃም
12. አቶ ኃይሉ ንጉሤ
13. አቶ ሕዝቅኤል ቶማ
14. አቶ ሌቃ ለምሶ
15. አቶ መስፍን ዱሎ
16. አቶ መንግሥቱ ማናዬ
17. አቶ ማርቆስ ማዶ
18. አቶ ማቴዎስ ሚልኪያስ፤
19. አቶ ሣህሉ ለማ
20. አቶ ሣሙኤል ቡናሮ
21. አቶ ሳዳ ባሣ
22. አቶ ሳዶ ቡታ
23. አቶ ስለሽ ሲሳይ
24. አቶ ሥላስ ሶፓ
25. አቶ ሻምአ ሾሎ
26. አቶ ቡላቻ ሻጋ
27. አቶ ባንተይርጉ ሙንዱሮ
28. አቶ ብርቁ አንበሴ
29. አቶ ብርቁ ዶሌቦ
30. አቶ ተመስጌን ጋዳና
31. አቶ ተስፋሁን ገድሎ
32. አቶ ተስፋዬ ታና
33. አቶ ተክለ ሚኮላ
34. አቶ ታመነ ታንጋ
35. አቶ ታመነ ታንጋ
36. አቶ ታምራት ባንተሮ
37. አቶ አማሮ አንጁሎ
38. አቶ አማኑኤል አማኖ
39. አቶ አማኑኤል አማኖ
40. አቶ አስፋው ኤና
41. አቶ አበራ ኡንካሴ
42. አቶ አብራሃም አንጃ
43. አቶ አብራሃም ዓለሙ
44. አቶ በለጠ ባሣ
45. አቶ አቻዮ ያዕቆብ
46. አቶ አንዱ ደረሰ
47. አቶ አንዴ ዳርጋሶ
48. አቶ አዝመራ ብርሃኑ
49. አቶ አየለ አሻንጎ
50. አቶ አዳነ ዓሳ
51. አቶ አድማሱ አርባ
52. አቶ ኡባራ ደአ
53. አቶ ኡንዱሬ ኡባሌ
54. አቶ ኤልሳዕ ፎላ
55. አቶ እስካቸው ያዕቆብ
56. አቶ እሸቱ እስራኤል
57. አቶ ክፍሌ ክንዴ
58. አቶ ዘካሪያስ ጎንዳሎ
59. አቶ ያዕቆብ ያያ
60. አቶ ይስሐቅ ታንጋ
61. አቶ ዮሐንስ ማለቾ
62. አቶ ዮሴፍ ባሣ
63. አቶ ዮናስ ሙሴ
64. አቶ ዮናስ ጩምአ
65. አቶ ጋንታ ጋኔቦ፤
66. አቶ ጋጋ ጋደቦ
67. አቶ ጌዛኸኝ ጋኔቦ
68. አቶ ጫፋ ጫራ
69. አቶ ጳውሎስ ኩሉላ
70. አቶ ፈለቀ ፈረንጃ
71. አቶ ፍልሞን ባልቻ
72. አቶ ፍቅሩ ኃ/ግዮርጊስ
73. ወ/ሮ ግስታኔ ፋላሃ፤
74. አቶ ሚስጥር ብርሃኑ
75. አቶ ወርቁ ባረዶ
76. አቶ ኢዮብ ጦና
• እስካሁን ባለኝ መረጃ የታሳሪዎች ቁጥር ከ470-ሊያሻቅብ እንደሚችል እየተነገረ ያለ ቢሆንም ግን ለጊዜው ስም ዝርዝራቸው የደረሰን ከላይ የተጠቀሱት ናቸው፡፡
• ለእኔ ባለኝ መረጃ መሠረት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆነው ግን በተለያዬ ክፍል በመታሰራቸው ምክንያት ዝርዝራቸው ያልደረሰንን ትተን፤ ከላይ በስም የተጠቀሱትን ፕሮፓይላቸውን ሲናይ አብዘኞቹ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው ሲሆኑ፤ በሙያቸው ረዥም ዓመታትን ያገለገሉ ናቸው፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ከዲግሪ በታች (የዲፕሎማና ሠርቴፍኬት ያላቸው) የሆኑና ግን በተለያየ ሙያ ዘርፍ ልዩ ልዩ ሥልጠና ያገኙና ብዙ ያገለገሉ፡፡ በቁጥር ከ22-የማያንሱ የኢህአዴግ አመራር አባላት የነበሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ ሥራ አጦች፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ሌክቼሬሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፤ የከተማ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ የታሳሪዎችን የዕድሜ ክልል ሲናይ ከወጣትነት እስከ አዛውንትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ የገቡ ወንዶችና ሰቶች ናቸው፡፡
• የኢህአዴግ አመራር አባላትና አባላት በቁጫ ብቻም ሳይሆን በሌሎች አከባቢዮችም ከድርጅቱና ከአበላይ አመራሩ ጋር በግጭት ውስጥ መሆናቸው ግልጽ፡፡ ይህ ማለት ሥርዓቱን ለረጅም ጊዜ በውስጣቸው እየከዱ ኖረው ዛሬ መሸከም ሲያቅታቸው… በመጠየቃቸው ምን ልመጣ እንደሚችል በቂጡ ቢረዱትም ግን ጥያቄያቸውን ይዘው ሕዝብን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡ ከሕዝቡ ጋር አብሮ በመሆን በዕኩል መከራውን፣ እስራቱንና ድብደባውን ለመቀበል፤ አልን የሚሉትንም ጥያቄዎቻቸውን ከሕዝቡ ጋር አብሮ ለማቅረብ/ለመጠየቅ የበቁ ሲሆን በተለይም አሁን አሁን በኢሕአዴግ ላይ በግልጽ፣ በድፍረትና ማስረጃ አስደግፈው እየተነሱ ይገኛሉ ለማለት ነው፡፡ ተቀዋሟቸውን እያንፀባረቁ ነው፡፡ የፍትህ፤ የዴሞክራሲ ወ.ዘ.ተ ጥያቄያቸውን አንግበው ሕዝብን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ለማለት ያህል ነው፡፡
ለሚጠይቅ ማስረዳት ነው እንጂ ዱላ መፍትሄ አይሆን!!!
ለሕመማችን ፈዋሽ መዲኃኒትን ነው እንጂ ቁጣ በሽታውን ከማባባስ ውጭ ምንም ፋይዳ የለውም፡፡
በዳንኤል ሺበሺ፤

No comments:

Post a Comment