እህአዴግዬ የምር ታሳዝነኝ ጀመር…!
ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በሙሉ በአንድ ላ እየተረባረቡባት ነውኮ! ይሄው ሀምሌ 14 አረና ትግራይ በመቐለ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በህዝባዊ ስብሰባው ላይ “ሜድ ኢን ኢህአዴግ” በሆኑ ችግሮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አንድ በሉልኝ፤
አንድነት ከሃምሌ 21 እስከ መስከረም 5 ድረስ ተለያዩ ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ሰላማዊ ሰልፎችን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለማድረግ አቅዷል፡፡
ሁለት አትሉም…
ሰማያዊ ፓርቲ ነሀሴ 26 በአዲሳባ “ያንን ነገር ምንው ዝም አልሽው” ብሎ ባለፈው ሰላማዊ ሰልፍ የጠየቀውን ጥያቄ መልሶ ኢህአዴግዬን ሊጠይቃት ቀጠሮ ይዟል፡፡
ይሄ ሶስተኛው መሆኑ ነው…
ይሄው የሙስሊም ወንድሞቻችን የእምነት ነፃነት ጥያቄ በዚህ በፆም ወቅት ደግሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
አራት…
የምር ኢህአዴግዬ ታሳዝነኝ ጀመር፡፡ ተቃዋሚዎቹ በሙሉ በዚህም በዚያም ወጥረው ያዟትኮ…! እኔ እርሷን ብሆን ኖሮ… የሚነሱትን ጥያቄዎች በሙሉ ለእልህ ብዬ መልሼ መልሼ ተቃዋሚዎችን ጉድ አደርጋቸው ነበር… ኢህአዴግ ግን ሁልግዜ እንደሚፎርፍ ተማሪ አንድ ጥያቄ እንኳ መመለስ ተስኗት… ሳያት ከምር አሳዘነችኝ…
አሁን ሁሉም ተቃዋሚዎች ሙዳቸው መጥቷል፡፡ እናም በየፊናው ህዝቡን እያስተባበሩ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ማስተባበር ብቻ ሳይሆን መተባበር ከጨመሩበትማ…
“ኢህአዴግዬ ሲለምኗት ቀርታ ሲጎትቷት…” የሚለው ተረት ሊተረትባት ነው…
ምስኪን እንዳልልሽ ትዕቢተኛ ነሽ
እርኩስ እንዳልልሽ ያገሬ ሰው ነሽ
ይሄ አልሰማ ማለት ሰዎች ሲነግሩሽ
አኔንም አይበጀኝ አንቺም አይጠቅምሽ
ባክሽ
ባክሽ
ባክሽ
ባክሽ
(ምነው ቤት መምቻው ላይ “ሽ” በዛሳ…. ብሎ የሚያሽሟጥጥ ካለ ከ”ሽ” በላይ ቤት መምታት… ማምታታት…ብለን አልሸነፍ እንላለን!)
እውነቱን ለመናገር ግን ኢህአዴግዬ ምሳሩ በዛባትና የምር እያሳዘነችኝ መጣች!
No comments:
Post a Comment