Saturday, March 15, 2014

መልካም ዜና የአንድነትና የመኢአድ ውህደት ወደሚታይ ምዕራፍ ተሸጋገረ


መልካም ዜና
የአንድነትና የመኢአድ ውህደት ወደሚታይ ምዕራፍ ተሸጋገረ
የአንድነትና የመኢአድ ብሄራዊ ምክር ቤቶች በውህደት ዙሪያ የፊታችን እሁድ ሊወያዩ ነው፡፡ፓርቲዎቹ እንዲዋሃዱ ይሁንታን የሰጡት የፓርቲዎቹ ብሄራዊ ምክር ቤቶች የውህደቱን ሂደት ሲመሩ በቆዩት ሽማግሌዎች አማካኝነት የፊታችን እሁድ ውይይት እንደሚያደርጉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ሰንደቅ ጋዜጣ መኢአድ አንድነትን በውህደት መዘግየት እንደከሰሰ በመጥቀስ ባሳለፍነው ረቡዕ ዘግቦ የነበረ ቢሆንም ፓርቲዎቹ ለመዋሃድ በጀመሩት ሂደት በመቀጠል በጣም በቅርቡ ትግላቸውን በአንድ ፓርቲ ጥላ ስር በማድረግ ህዝብን እንደሚያደራጁ ብሄራዊ ምክር ቤቶቹ ለውይይት ለመቀመጥ ቀጠሮ መያዛቸውን እንደ መነሻነት በመጥቀስ መተንበይ ይቻላል ፡፡

1 comment: