Wednesday, March 12, 2014

በካፋ ውስጥ እድሜያቸው ለአቅሜ አዳም ባልደረሱ ሴት ልጆቻችን ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጣ::








በካፋ ውስጥ  እድሜያቸው ለአቅሜ አዳም ባልደረሱ ሴት ልጆቻችን ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ በማህበረሰቡ ውስጥ ስጋትን ፈጥሮዋል:: ስለሆነም መንግስት በጉዳዩ ላይ ምንም አየነት ትኩረት እየሰጠ ስላልሆነ በተቻለ መጠን የካፋ ተዎላጅ የሆናቹ ሁሉ ይሄን ችግር ለመከላከል እንረባረብ:: እባካችሁ የከፋ ተወላጅ የሆናችሁ እና ኢትዮጵያዊ የሆናችሁ በከፋ ዞን በየ ወረዳ እና ቀበሌ እየተበራከተ የመጣውን  የሴት ልጅ ጠለፋን ለማስቀረት ( ለመቀነስ ) ተነሳሱ። ምንም በማታውቅ ሴት ህፃን ልጅ ትምህርቷን አቋረጣ በገንዘብ እና በደላላ ተደልላ ምንም በማታውቀው ተዳር ለዝያውም ያለ ዕድሜ (ያለ አቻ ጋብቻ ) ስደርስባቸው እንመለከታለን። የሚመለከታቸው አካላት በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ወረዳዎች ይህንን ጉዳይ ከመከላከል ምንም ከማያውቀው ማይም ገበሬ ጉቦ በመቀበል ወዴ ሀገር ሽማግለ በመመለስ የታዳጊ ህፃናት ላይ እየነገደ እንደሚገኝ ሁሉም የአከባቢ ህ/ሰብ የሚያውቀው ጉዳይ ሲሆን ይህንን ለመታገል እባካችሁ በያላችሁበት ሆናችሁ በመወያየት ህፃናትን እንታደጋቸው!::

No comments:

Post a Comment